Translate

Saturday, March 6, 2021

#Abba Seeruu Gwangul/ #አባ ሴሩ ጎንጉል

አባሴሩ ጓንጉል እና ዘመነ የጁ
ዘመነ የወሎ ከፍታ 
ክፍል አንድ፡
ብዙ የታሪክ ምሁራን ብልህነትንና ፖለቲካዊ ሴራ ጥንጠናን አጣምሮ የያዘ እንደነበር የሚያወሱትን የስሁል ሚካዔልን አገዛዝ በመገርሰስ ጎንደርን ከስሁል irony rule ነጃ ያወጣና አክሱም አካባቢ እንድመሽግ ያስገደደ ፥  የሰሎሞናዊያንን ገዢ መደብ ወደፑፔት ደረጃ  (Symbolic puppet)  በማውረድ የሿሚ ሻሪነትን 'የእንደራሴ ርዕሰ መኳንንት' (Regent Head of the Nobility) ማዕረግን የተቀዳጄ ገዢ መደብ ነበር የአባሴሩ ጓንጉል ቤተሰብ፡፡የውጭና የሀገራችን የታሪክ ምሁራን ስለአባሴሩ ጓንጉል ቤተሰብ ወደርየለሽ ጀግንነት ብዙ ከትበዋል፡፡የእቴጌ ጣይታ የዘር ሀረግ ከዚህ ስመገናና ወረሴህ ቤተሰብ በጉግሳ ክንፉ በኩል የሚመዘዝ እንደሆነ ይታወቃል፡፡እንደ አለቃ ታዬ ዘገባ "አባሴሩ ጓንጉል የመርሳ አባገትዬ አባት ሲሆኑ የአባገትዬ አባት ደግሞ ወሌ ይባላሉ፡፡ወሌ የአብዬ ልጅ ሲሆኑ የአብዬ አባት ደግሞ ወሌ ይባላሉ፡፡የወሌ አባት ደግሞ ሸይኽ ዑመር ይባላሉ፡፡"ከዚህም የየጁ ስርዎ መንግስት መሥራቾች ከሸይኽ ዑመር የዘር ሀረግ የሚመዘዝ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ፖል ሄንዝ ዘመነ የጁ ከኢያሱ ሁለተኛ (በንግስና ስሙ ብርሃን ሰገድ)  ከሞተበት ከ1755 ዓፄ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ተብለው እስከነገሱት 1855 ድረስ በአጠቃላይ ለአንድ መቶ ዓመት እንደቆዬ ዘግበዋል፡፡ የኋለኞቹ ሰሎሞናዊያን ዘመነ የጁ ወረሴህን ዘመነመሳፍንት ሲሉ የሰዬሙት በዘመኑ የጁ ወረሴኾች የሿሚ ሻሪ ርዕሰመኳንንትነትን የመጨረሻ የልቅና ማዕረግ  ተጎናፅፈው የሰሎሞናዊያንን ገዢ መደብ  ፑፔት አድርገዋቸው ስለነበር በዚህች አቂመው ነበር፡፡'ንጂማ ከነርሱ የቀደሙት ሰሎሞናዊያን የገዙትን ግዛት ወረሴኾችም ገዝተውታል እስከዓፄ ቴዎድሮስ ዘመን ድረስ ይላሉ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ዋሚ፡፡
በሌላ በኩልም ወረሴኾች ፣ ወረሒመኖ ሙሃመዶ እና የዋግሹም ባላባቶች የሥልጣን ተቀናቃኝ ስለነበሩ እርስበርስ መጎሻሹም እንደነበር ይታወቃል፡፡በዚህ ላይ ከራስ ዓሊ በፊት የነበሩት የወረሒመኖ ሙሃመዶ ቤተሰብ ገዢዎች በኢስላም ኃይማኖት ላይ ነበሩ፡፡የወረሴህ (ወራሼህ) ሁሉም ወደ ኦርቶዶክስ ኃይማኖት የገቡ ነበሩ፡፡ይህም ሀገርን በየራሳቸው አምሳል ለመመስረት በሚያደርጉት ግብግብ ቅራኔ የፈጠረበት አጋጣሚ እንደነበር ይታወቃል፡፡በመጨረሻ  የሴሩ ጓንጉል ቤተሰብ የበህር ልጅ አባሴሩ ጓንጉል የታወቀውን የላስታ ባላባት የራስ ፋሪሴን ልጅ ገለቡን በማግባቱ የግዛት ማስፋፋትና የሥልጣን ሸኩቻው ዕልባት አገኘ፡፡ ከሙሃመዶ ሥርዎ መንግስት ወራሾች ጋር የነበረውን የግዛት ማስፋፋት ጋር በተያያዘ ሲፈጠር የነበረን መለስተኛ ቅራኔ ዕልባት ለመስጠትም ከአባሴሩ ጓንጉል ቤተሰብ የሆነው የየጁው አሉላ ክንፉ ከወረሒመኖ ሙሃመዶ ቤተሰብ ከሆነው የሊበን አባጅሩ ልጅ ሐሊማ ሊበን የኋለኛዋ  ዕቴጌ መነን (Empress Menen )ጋር ጋብቻ ፈፀመ፡፡ከዚህ ጋብቻ  ነበር ራስ ዓሊ ትንሹ የተወለደው፡፡ የሥልጣንና የግዛት ማስፋፋት ሽኩቻውም በዚህ ዕልባት አገኘ፡፡ ከዚያ ጎንደር ቤተመንግስትን ተቆጣጥረው ሀገር ማስተዳደር ጀመሩ ራስ ዓሊ ንጉስ ዮሃንስ እናቱን እንዲያገባት አድርጎ  በንጉስነት አስቀመጠው፡፡እርሱ ግን በራስ ቢትወድድ ማዕረግ ማስተዳደር ወይም መግዛት ጀመረ፡፡
ደቡብ ወሎ ከሰሜን ወሎ ላስቴዎች ጋር በዝምድናና በባህል የተሳሰሩትና የተጋመዱት  ከጧቱ እንደነበር ልብ ማለት ይበጃል፡፡
ምንጭ፡
የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን አንድርዜይ ባርትኒስኪ ዮዓና ማንቴል ኒየችኮ ትርጉም በዓለማየሁ ዓበበ 
3/ የውገና ታሪኮችና የታሪክ እውነቶች
 በፕሮፌሰር ታቦር ዋሚ

2 comments:

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...