Translate

Friday, March 26, 2021

#የወሎ የዘር ሀረግ/እልማን ባሬንቱ

®የ ወሎ የዘር ሀረግ☜
አዘጋጅ ፤miky sultan/wollo oromo.**********
የካም ልጆች ኩሽ ፣ፋጥነ ከነዓን ናቸዉ፣ ከነዚህ መሃል የወሎ የዘር ሀረግ ከኩሽ ይመዘዛል  ኦሮሞ የ ኩሽ ዘር ነው።
ወሎን ያቀኑት ስምንት ትልልቅ የ ኦሮሞ አባቶች ናቸዉ ፦ ወይም  የ ባሬንቶ ልጆች  ነበሩ ፤እነሱም ፦
1. ወረ ባቦ
2. ወረ ኢሉ
3. ወረ ሂመኖ
4. ወረ ቃሉ
5. ወረ ቆቦ 
6. ወረ ራያ 
7. ወረ ዋዩ
8. ወረ የጁ በመባል ይታወቃሉ።
እነዚህ ስምንት ወንድማማቾች ግዛታቸዉ ከሸዋ ሮቢት አንስቶ እስከ ዋጀራት ያለዉን ቦታ ያጠቃልላል።
ታሪክ አይዋሽም ሲናገር ይኖራል፤ራያ ማለት ስርወ- ቃሉ ኦሮሚፋ ነው፤ ራያ ማለት ሰረዊት ማለት ነው በ ኦሮሚፋ፦ራያ ራያ ነው ማንም አይሽረውም።የራያ አገሮች  ስም ጥቅቶች፣
ዋራባየ 
ኣጋምቴ 
ኩኩፍቶ 
ቃልኣዳም 
ጋበቴ 
ትልወ 
ዳንሳ 
ትልዎ  
ጋርጃለ  
ኮባን   
ባሶ  
ጎድኣደ 
 በርተኽላይ 
ሞኾኒ 
ዳዮ 
ትኦ 
ዳርዐይታ 
ጨርጨር  
ሓስታባ 
ዓዲደርጊ  
ዓዲሃንጥያ  
ሓሸንገ    
ዓድሻወ  
ቃልቃላ 
ዓዲጅሎ  
ዓዲቦረ 
ሃላማጣ  
አጅራ 
ማጨው 
መኻን 
ዓይባ 
ሽምጣ 
ሐሸንገ 
ኦፍላ 
ኣለማጣ 
ቆቦ 
ራያ አዘቦ 
ባሌ 
ኢረሻ 
ዋራ ባይቶ 
ላጤ 
ጋማ ዳድኤ 
ሀርወረሻ 
ኩቤ ጃብለ 
ጋንዳ ኣባቶላ 
ይቀጥላል .....
ዞቡል ዋና ከተማ ቦራን
ጩሉቄ
ጋትራ
ሶሎቃ
ኡላጋ
ዶዶታ
ፎቅሳ
ኣልያምባ
እኛ ራያዎች ንፁህ የኦሮሞ ዘር እንዳሆንን ከስማችን ማረጋገጥ ይቻላ 
ምሳሌ በራያ ቆቦ የሴቶች ስሞች ብናይ
ሃታቶ
ደይማ
ቃናኔ
ኮርቶ
ሻንታሞ
ኣረይሮ
ጃኖ
እርጎ
ዳሞ
ዳድኢው
ወዘት
የወንዶች ስም በራያ ቆቦም በራያ ኣዘቦም
ሃብጦ
ኩቤ
ጃርሶ
ባሮንቶ
ባድኣሰ
ኣራርሰ
ልበን
ሙሄ
ኣባየ
ሓለፎም
ጩፋ
ዳድኤ
ጋልሞ
ባሌማ
ጃለ
ዋዩ
ራያዎች አፄዎችን በመፈለም ወደር የለሽ ናቸው ራያዎች ጀግኖች ናቸው በራያ ፈሪ ቦታ የለውም ።የራያና የወሎ ህዝብ ከአንድ የዘር ግንድ የተገኘ አንድ ህዝብ ነዉ።የራያ ህዝብ ከወሎ ህዝብ ጋር ያለዉ ዝምድና የደምና የአጥንት ነዉ የምንለዉ ለዚህ ነዉ (Blood is thicker than water)።ማንም ኢትዮጵያዊ ሂዶ የራያ አዘቦን፣የራያ ቆቦን፣የኦፍላን፣የአላማጣና የእንዳ መሆኒን ትልልቅ አባቶች ቢጠይቃቸዉ ከጥንት ዘመን ጀምሮ ያለውን ታሪካቸውንና የ ኦሮሞ የዘር ሀረጋቸዉን ወደ ኋላ ቆጥረዉ ማንነታቸዉን አብጠርጥረዉ ይነግሩታል።
የራያ ህዝብ በትግራይ መጠቃለል ወይ መካለል የጀመረው ከአፄ ዮሃንስ አራተኛ ጀምሮ ነዉ።ከአጼ ዮሀንስ አራተኛ ስልጣን መያዝ ተከትሎ የትግራይ ሰዎች(ሴሜቲኮች) ወደ ራያ በመምጣት ማለትም ወደ ኦፍላ፣አላማጣ፣አላጄ፣ማይጨው፣እን­­­ዳመሆኒ፣ራያ አዘቦና ራያ ቆቦ አካባቢ መጥተው እንዲሰፍሩ ተደርጓል። 
አገውና ወሎ የተቀራረቡ ህዝቦች ናቸው ሁለቱም የኩሽ ልጆች ናቸዉ፡፡የዋግና የላስታ ሕዝቦች (Ze-Agaw ) ከመላዉ የወሎ ህዝብ ጋር ለዘመናት አብረዉ የኖሩ፣የተዋለዱ፣በባህል፣በቋንቋ፣­­­በሀይማኖት የተዛመዱ ሕዝቦች ናቸው።አገዉና ወሎ በረጅሙ የኢትዮጵያ የታሪክ ሂደት ዉስጥ እንደ ደምና ስጋ አንድ ላይ የተዋሃዱ ህዝቦች ናቸዉ።
የወሎ ግዛት ቀይ ባህር ድረስ ነዉ።ከጅቡቲ ድንበር እስከ መርሳ ፋጢማ ያለዉ አሰብን የሚጨምረዉ የወሎ (የኦሮሞ) ግዛት ነዉ። 
በደቡብ ወሎ በረሀማው ስፍራ 
ከደራ እስከ ዳር ኦሮምኛ ይነገረሉ
ባቲ
ከሚሴ
ቦረነ
ሀርቡ
ኮምቦልቻ 
ጨፋ ሮቢት
አጣዬ
አገዩ 
ሚናስ 
ባከት 
ቀያማሬ
ከረሞች 
አገዩ 
ስቀሲምቢራ
ቆቦ
ለገቀርሳ 
ወርቄ
ደርቢቶ 
ቡልቡል 
ጀገንፎ
ማሳ
ዋርጃ ሽነት
እስከ ገረዋ እና ወጊድ ለሚ 
የኦሮምኛ ቋንቋ ይነገራሉ::
የ ወሎ ኦሮሞ
ሸበላዎች በ“ሚጊራ ጉራ” (አክርማና ስንደዶ መልቀም ማለት ነው) እና በእንጨት ለቀማ ወቅት ተገናኝተው የውስጣቸውን በዜማ ሲተነፍሱ ፍንጭትነትን ሳያደንቁት አያልፉም፡፡

   እሷ፡ “ና ካሮዬ ካሮዬ ካሮዬ”
  እርሱ፡ “ነይ ካሮዬ ካሮዬ ካሮዬ”
    
እንዲህ ነው የሚባባሉት፡፡ “ፍንጭቴ! የኔዋ ፍንጭት! ፍንጭቷ” እያሉ ነው የሚሞጋገሱት፡፡ ዛሬም ጥርሰ ፍንጭት መሆን በወሎ ምድር ያስከብራል፡፡ የቁንጅና ምልክት ነው፡፡ 
ታዲያ ወሎየዎቹ የሚሞጋገሱበት “ካሮ” ስርወ-ቃሉ ኦሮሚፋ ነው፡፡ 
#ወሎ የዑለማ ሀገር ናት፡፡ የኢትዮጵያ አዝሀር የተባለላት የዒልም ሀድራ! ወሎ “አዝሀር” የመሆኗ ክብር ቢነጠቅባት እንኳ የኢትዮጵያ “መዲና ዩኒቨርሲቲ” የመባልን ያህል ትከበራለች፡፡ እስቲ ተመልከቱ እርሷ ያፈራችውን ዑለማ!… ከኢፋት ምድር ጀምሮ እስከ ራያ ድረስ በተንጣለለው ክልል ውስጥ ያለው ጎራና መንደር ሁሉ የየራሱን አንድ ቱባ “ዓሊም” አበርክቷል፡፡ ሼኽ ጠልሃ ጃዕፈር (ኢፋት)፣ ሙፍቲ ሲራጅ (ራያ)፣ ሼኽ ዳኒይ (ዳና)፣ ሐጂ ከቢር (ከሚሴ አውራጃ)፣ ሼኽ ዑመር ቡሽራ (ቃሉ አውራጃ)፣ የጀማው ሼኽ (ደሴ ዙሪያ አውራጃ)፣ የዶርቃው ሼኽ…..ሼህ ሰይድ ጫሊ (ወራ ባቦ ባቲ)።።።።። እያልን መዘርዘር እንችላለን፡፡ ቅዱስ ቁርኣንን በአማርኛ የተረጎሙት ሁለቱም ዓሊሞች ወሎዎች ናቸው- ሼኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ፡፡ 
የቀድሞ የ ወሎ ጀግኖች
የ በሬንቶ ልጆች ።፦
1.በላይ  ዘለቀ=ወሎ ቦረነ
2.አባ መርሴ= ራያ
3.መሀመድ መኪ= ራያ
4.ሀሰን ረሺዴ =ከሚሴ
5.ሀሰን አሜ=ከሚሴ
6.አባ ጋንጉል=የጁ
8.መሃመድ አሊ.የ ወሎ ንጉስ=ደሴ
9.ልጅ እያሱ= የ ንጉሱ ልጅ=ደሴ
ብዙዎች ነቻው የልጠቀስኳቸው

በ ዘመነ መሰፊንት ንጉስ የነበሩት ፣እና ራስ አሊ  ራስ ጉግሳ ወሌ የ በጌምድር ( ጎንደር) ንጉስ የነባሩት ኦሮሞ ነቻው ከዛ በሃለም የ ወሎ ነገስታት የ ነባሩት  ራስ ሙሀመድ አሊ ( ሚከኤል) ፣ ልጅ ኢያሱ የ ሙሀመድ አሊ ልጅ፣ኤቴጌmenen" ጣይቱ ብጡል፣ ተወበች፣ ከዚ በፊት የነበሩት ነገስተቶች ኦሮሞዎች ነባሩ ወሎን የ ሰየሙት የ ኦሮሞ ነገድ ወይም ጎሰዎች ነቻው፣ከ ጥንት ጀምሮ በገደ ስረአት የሚኖሩ ኦሮሞዎች ነባሩ ፣አፄዎች የ ታሪክ ሰረቂዎች ስለ ሆኑ ኦሮሞ ታሪክ እንደለለው አርጎ ጽፏወል፣ አፄዎች የ ሙስልም ጠላት የ ኦሮሞዎች ጠላት ነቻው ፣እሄ ግልፅ ነው ማንም መካድ አይችልም በ ወሎ አፄ ዩሀንስ  የ ወሎ ሙስልሞች ከ 30 ሺ በለይ የሚሆኑትን ገድሏል፣ አፄ ሚኒልክ  ኣኖሌ ለይ ንፁ የ ኦሮሞ አባቶች እና እናቶች ለይ እጃቸውን እና ጡተቸውን ቆርጧል እሄ እውነት ነው እስከ ቅርብ ግዜ እጀቻው የተቆረጡት በ ህዬት ነበሩ፣አፄዎች ጀግነ ሰይሆኑ የ ጀግኖች ታሪክ ሰረቅዎች ነቻው።
 ራያ ራዩማ ( Raya Rayumma)
የራያ ህዝብ እንደማንኛዉም ማህበረ ሰብ የራሱ የሆነ ቋንቋና ባህል ያለዉ ማህበረ ሰብ ነዉ። ከዝህ በታች ያለዉ ቃላቶች እና ፍቻቸው እንመልከት።ምናልባት የቃላት ግድፈቶች ካሉ ከወድሁ ይቅርታ እየጠየቁ ለመታረም ፍቃደኛ  ስለ ሆንኩ መልካሙን ትብብራቹህ አይለየን እላለሁ።   የራያ    ልጆች ቋንቋቹህ በመጽሃፍ ባይጻፍም ትርጉሙ እኖሆ ብያለሁ።መልካም ንባብ 

ራያኛ                     ኦሮምኛ                    አመ
ፋጀ                       ፋጅ                         አርማ
አራርሳ                  አራርሳ                     አስታራቅ
ቃናኔ                    ቀነን                         እንክብካቤ
ዱረይቲ              ዱረይቲ                    ባለጸጋ
ዳሙ                 ዳሙ                          ጣዝማ
ባድ አቱ               ባድ አቱ                    ሃብታም
ጉግሳ                ጉግሳ                       ፈረሰኛ
እብሳ                 እብሳ                                        መብራት
ሻንታሞ              ሸንታማ                     50
ቆቦ                   ቆቦ                          ጉሎ
ቅልሻ                 ቅሌንሳ                   ንፋስ
ድማ                 ድማ                       ቀይ
ጉራቻ                ጉራቻ                     ጥቁር
አዴ                    አድ                         ነጭ
ኩሌ                 ኩሌ                        ጠይም/ፍልቅልቅ
እቱ                        እቱ                       የጎሳ ስም
ሃራ                    ሃራ                         ጥራግ/ጥረግ
ኦዳ                      ኦዳ                       ዋርካ
ቕልጣ               ቅልጦ                          ፨   
 ጃኖ                      ጃኖ                   ርባን/ ልብስ
ጫሌ                    ጫላ                   በለጠ
መጋል/ለ             መጋላ                 ጠይም
ሃንጥያ              ሃጥያ                     እላማ
ዳድእ/ኤ         ዳድእ/ኤ                 ካትካላ
ዳይማ             ዳእማ                     ህጻን
ሮብሰ/ሮባ         ሮብሰ/ሮባ            ዝናብ/ ዘነበ
ጃሪ                  ጀሪ                       ሰዎች
ገለታ                 ገለታ                 ምስጋና
ጅሎ               ጅሎ                የሰዉ/የቦታ ስም
ደዮ/ዳዩ         ደዮ/ዳዩ               የሰዉ/የቦታ ስም
በድ አሳ         በድ አሳ            ሃብታሙ
ቶላ               ቶላ                   ጡሩ
ከነ               ከን                       አምጣ                         
ወሆሎ             ዋህሎ                   ጓደኛ
ኩኩፍቶ            ጉጉፍቱ                  ኮረብታማ
ሆርማት               ሆርማታ             አርብ/አርብቶ አደር
ጎልና                   ጎለና                   ከትንሽ ግዜ ቡሃላ
መካንሳ                 መካንሳ                  ብሳና
ገንዳ ጢራቻ                ጢረቻ               ጠጠር
ጥጣ                    ጥጣ                   ፉጭት
ካራጉቱ                 ካራጉቱ                ሙሉ በር
ጢሳ ባልማ            ጪሳ ባልማ            የባሃልማ ማረፍያ
መርሳ                  መርሳ                    ዙር
በደኖ/ቁርቁራ/አጎብድ      በደኖ/ቁርቁራ/አጎብድ

   "የጁ ኦሮሞ 
በ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ኦሮሞ  አንዱ የ የጁ ኦሮሞ ነው።
በ 14ኛው ክፍለ ዘመን በፊት በተፃፈው ታሪክ  ይመሰክራል ፡
እንደ ታሪክ ፃፈው የየጁ ኦሮሞ  ከ ቦቆጂ ከምባሉ ጎሳዎች እንደሆነ ያመለክታል። የጁ ኦሮሞ የ ሙስሊሞች  የሼሆቹ ( የወረ ሼህ) ዘር ነው።በመጀመሪያ ከ ቦቆጂ ጎሳዎች  የመጀመሪያዎቹ ,ቁንቢ,መርሶ,ሸካ,አባ ድምበር መልዬ, ገመዳና እልማን ኦሮሞ ተብሎ መጣራተቸውን ይነገራል።ቁንቢ መቻሬ በምትባል አሁን በስተ ምስራቅ  ወልደያ የምትገኝ  ይኖሩ ነበር ። አባ ድምበር  መሊዬ ደግሞ ጉባላፍቶ ላይ ይኖሩ ነበር ።የ የጁ ኦሮሞ የዘር ሀረገቸው ወደ ኀለ ሥቆጥሩ "ገመ ገሊ"(Gamaa gali) ወደ ምባል የሰገባሉ።የጁ በአራት ጎሳዎች ይከፈላል እነሱም :-ወራ ዶረን ቦጁ, ወራ ሩፎ ሮባ,ወራ ካሎ,ወራ ኡጊ በመባል ይጠራሉ ።

የጁ ኦሮሞ የመሻኢኽ አገር 
ሸህ ዳኒዩል አወል ሸህ አህመድ አደም ጉራቻ 
ሸህ ዳኒዩ ሳኒ  ሸህ ሙሀመድ ያሲን ዳለቻ 
ሸህ ሙሀመድ ሚአዋ መርሳ 
ሸህ ሲሪጁ ዲን ጓጉር 
ሸህ አሊ መንታ አባ ሰርባ 
ሸህ ከረም ( ሸህ አብዱ ረሂም ወረ ገራ ) 
የሌሎችም ስማቸውን ያልጠቀስኳቸው መሻኢኽ አገር ናት ከሌላው ለየት የሚያረጋት ዳኒዩል አወል ና ዳኒዩ ሳኒ እንደ ሽሀቸው ጀማሉል አኒይ ኦሮምኛን በአረብኛ ፊደል  የፃፋ የሸህ አገር መሆኗ ነው

በላይ ዘለቀ
በላይ ዘለቀ ላቀዉ ቂልጡ አያኖ ገልገሊ የወሎ ክፍለ ሃገር ተወላጅ ሲሆን እድገቱና ጅብዱ ደግሞ በጎጃም ክፍለ ሃገር ሲሆን በጎጃም ቤተሰብ መስርተዋል ።ጀግናው በላይ ዘለቀ ከአባታቸው ከዘለቀ ላቀው እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጣይቱ አስኔ በወሎ ክፍለ ሐገር በቦረና ሳይንት አውራጃ በጫቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጅሩ ጉጣ ከተባለው ቀበሌ በ1904 ዓ.ም ተወለዱ።በተወለዱ በአራት ዓመታቸው አባታቸው ባሻ ዘለቀ ላቀው የልጅ እያሱ ባለሟል ሆነው የአንድ ክፍለ ጦር ኃላፊ ስለነበሩ ልጅ እያሱ በተያዙ ጊዜ ከዚያ አምልጠው በቦረና ሳይንት አውራጃ በጨቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጣቀት መድሉ ከተባለው ቀበሌ ተቀምጠው እንዳሉ ከአንድ ሰው ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው በፀብ መካከል የሰው ህይወት ያልፍባቸዋል።በዚህ ምክንያት ወሎን ለቀው ወደ ጎጃም ሄዱ።ወሎ የአገዉና የኦሮሞ ስብጥር ነዉ።የኦሮሞ ህዝብ የኩሽ ዝርያ ነው፡፡ይህ የኩሽ ነገድ ህዝብ ከደቡባዊ ግብፅ ጀምሮ በዛሬይቷ ሱዳንና በአፍሪካ ቀንድ ለብዙ ሺህ ዓመታት በመኖሩ ይህ አካባቢ ለኩሾች ጥንት መኖሪያቸው ነው፡፡ስለወሎ ህዝብና አካባቢው ታሪክ ሲወሳ ከኦሮሞዎች ታሪክ ጋር በእጅጉ ተቆራኝቶ እናገኘዋለን ለዚህም አሁን ላይ ያሉትን የቦታዎች ስያሜ እና የነዋሪዎችን ስም እንድሁም የመሬቱን አቅኝዎች የኋላ ታሪክ በመመልከት ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡የኦሮሞ ህዝብ ቦረና እና ባሬንቱማ በሚባሉ ሁለት ትላልቅ አብይ ጎሳዎች ይከፈላል።የወሎ ኦሮሞ ከባሬንቱማ ይመደባል።የወሎ አብይ ጎሳ ስምንት ንዑስ ጎሳዎች አሉት።እነሱም ወረ ባቦ፣ወረ ኢሉ፣ወረ ሂመኖ፣ወረ ቃሉ፣ወረ ቆቦ፣ወረ ራያ፣ወረ ዋዩና ወረ የጁ በመባል ይታወቃሉ።የወሎን ህዝብ አኗኗርና ባህል በጥልቀት ለመረመረ ሰዉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከላስታና ከዋግ አዉራጃ ዉጭ ኦሮሞዎች በትግል ያቀኑት መሆኑን ይገነዘባል።

.ጀማሉል አንያ(ሞሀመድ ሮብሶ)
አባታቸዉ ከኦሮሞ ከታወቁ ጎሳዎች፤  ሮብሶ-ባቦ እና ሀዋ-አብዱልቃድር ፡፡ ከሁለቱ አብራክ ፤ ራያ አከባቢ ልዩ ስሟ ‹ገልገሎ› ተብላ ከምትታወቅ ስፍራ በ1781 ዓ.ም ወንድል-ልጅ ተገኘ ስሙም ‹ሙሓመድ› ተባለ ፤ በኑረቱ ትሩፋተ-አያል ሁኖ ታየና ‹ጀማሉል አኒይ የሚል እካያ ተቸረ ፡፡ ዕዉቀቱን ጨምሮ ቅርፀ - ፊቱም መምህሩን ይመስል ነበረና ‹አንይ› ሲባል ሌላ ተጥሮተ-ስም ተደበለለት ፡፡ የሗላ ሗላ ለአያሌ ነዋሪዎችና ተማሪዎች ዓይንና ጆሮ ፤ ጉልበትና ጨዉ በመሆን አንቱታ - ገዴ ሆኑ ፤ የዕዉቀት ጸሐይ - የፍቅር እርሾ - የእዉነት ጥራዝ እና ሌሎች የክብር ስሞች እየተዥጎደጎደላቸዉ ሀገር ፤ ህዝብንና እምነታቸዉን ሳያስደፍሩ አስታፍረዉና አስከብረዉ በጥበብ ሲመሩ ኖሩ - ጀማለዲን-አንይ(1781-1870 ዓ.ም) ፡ወቢ ከ ከድር ታጁ ጽሁፍ 
የሼህ ሙ.ታጁ(ዑላሙል-አግቢያዕ 1974)ን ፣ የሙሐመድ ፈቂህ(ሚስኩል-አዝፈር 1884)ን ፣ የሼህ አህመድ ዲማ(መጥለዑ አል-ረዉይ-ፊ- መናቂቢ-አል አንይ)ን ፣ የሼህ አህመድ ደራ (ነሽሩል-አንበር 190*) እና የልጃቸዉን(ሃጅ ሙሐመድ-ወሌ) እንዲሁም የሌሎች ለታሪኩ ቅርብ የሆኑ የአባቶችን የድምፅ መቅርጽና ድርሰቶችን ተንተርሰን ፤ ጀማሉል አንይ እንደ ኢትዮ. አቆጣጠር 1870 ዓ.ም ላይ ማረፋቸዉን ግን መደምደም እንችላለን ፡፡ ልዩ መጠሪያዋ ‹ኮረም› ገፍራ አከባቢ ፤ የጁ-(ወሎ) ዙሪያም አካለ-አጽማቸዉ ተቀብሯል ፡፡

asirraa kaasi
ጉዞ ወደ የጁ ምድር 
ከ ባቲ ተንስተን ኮምቦልቻ  ገባን  ከዛም  ወደ ደሴ ከ ዛም ወደ መርሳ አሁንም መርሳ ሳን ደርስ ጊረነ መሄድ ፈላግን ግን ጉዟችን ወደ ወልደያ ነበረና ወልደያ አደርን ከዛም ጉዟችንን ወደ ሀረከተማ ሀረ ትንሽ ቡና ብለ ወደ ሀሮ ወደ ዳነ ቀጠልን ሀሮበጣም  ደስ የምትል ከተማ ናት ደስ የምል የተከመቸ ውሃ ሀሮዬ አላት  ሰዎቹም ፍቅር ናቸው እዛ ቡናና ሻይ  እያልን አንድ የየጂ ሽማግሌ  አገኛን ከዛም አባት ቡና አርሂቡ አልነቸው መቼም  ወሎ ፍቅር ነው አብሮ መብላት  መጠጣት  ይወዳል  ደግ ኣሉን ቡና አብረን  መጠጣት  ጀመርን ከዛም ስለ የጁ ወሬ ጀመርን  አባት የጁ እንዴት ናት ብለን ጠየቅናቸው  የጁማ የፍቅር  አገር የ አባ ጌትዬ አገር የሼኮቹ አገር ናት ብሎ ጀመሩልን ከዛም አባት ወሎ ምድር  ድሮ የ ኦሮሞ  ነበረች ይለሉ እንዴት  ነው ስለሱ የምታቁት ነገር አለችሁን ኣልናቸው ኤሬ በጣም  የጁ ምድር  ውስጥ ብትሄድ  የየጁ ምድር  በሙሉ ራሱ የኦሮሞ መሬት መሆኑን ይመሰክራል ኣሉን እንዴት አልነቸው?አሁን ሀሮ (haroo)ራሷ አፋን ኦሮሞ  ነው ሀሮ ማለት  በ አፋን  ኦሮሞ ነው በ አማረኛ  የ ተ ከመቼ ውሃ ወይም  ሀይቅ  ማለት  ነው ከ ሀሮ ለጥቃ የምትገኝ ደግሞ  ሀረ ነው ከ ሀረ ለጥቆ የምትገኝ  ዴሬ ሮቃ ይባላል  ድሬ ሮቃ ማለት  አፋን ኦሮሞ  ነው ድሬ ማለት  ሜዳ  ማለት ስሆን ሮቃ ማለት የ እንጨት  ስም ነው ሮቃ እንጨት የምገኝ ቦታ ማለት  ነው ከ ድሬ ላጥቆ የላው ጃራ ነው ጃራ ማለት  አፋን ኦሮሞ  ነው ጃራ ማለት  አመታት  ማለት ነው በ ጃራ በኩል ያሉት ተራሮች ስም በጣም  ደስ ይላሉ  አንዱ  ትልቁ ተራራው አኬካቺሳ ነው ይህ ተራራ ከ የጁ ሶዶመ ተንስቶ  እስከ ወራ ባቦ ድረስ  ይረዝማል  በጣም ትልቅ  ተራራ ነው አኬካቺሳ ማለት  አፋን ኦሮሞ  ነው አኬካችሳ ማለት ማስጠንቀቂያ ወይም  ማመልከቻ  ማለት ነው፣ደግሞ አንደኛው ዘምዘም  ተራራ ነው ዘምዘም  ተራራ ላይ የምኖሩ ህዝቦች   በጣም ፍቅር ናቸው ሰዎቹም በ ኦሮሞነተቸው ኩሩ ናቸው መሬቱን የምየቅ ሰው ይዘን ጉዟችን ወደ እነሱ አደረግን ሶስት  የየጁ ልጆች እኛጋ ነበሩ ምንገድ ላይ ከዛም  አንድት ድመት መኪና  ምንገድ ላይ ነበረች ከዛ ለ ሹፌሩ  እንድህ ይለዋል እችን አዱሬ እንዳት መታት ይለወል ፣ ኦኦ በጣም  ደስ አለኝና ወንድም አልኩት ምነው  ኦሮምኛ ትችላላችሁ እንዴ አልኩት ምነው አለኝ አይ አዱሬ ስትል ሰምቻችሁ ነው አልኩት ፣ ነው አለኘ አንደኛው ምነው ምንም  ኦሮሞኛ ቋንቋ  ያልቀራ መስለችሁ ነበር  ወይ አለን አያቴ ኦሮምኛ የወሩ ነበር  ይነግሩንም ነበር  አለን ከዛም ዘምዘም  ተራራ ላይ ደራስን ጃራን ሀሮን ሀረን እንደ ፈለግን የጁ ሶዶመ መዬት ጀመርን ከዛም  እዛ ተራራ ላይ ወደ ስድስት መንደር  አገኛን እዛ የሉት ስማቸውን ትነግሩናለችሁ አልነቸው አዎን አሉን ያ እዛች ያለችው መንደር ሬቡ ትባላለች የቺ ደግሞ  ኢሌቲ  ከዛም  አጆ ወይም  አርጆ ናት አሉን እዛ ወድያ ያላው ደግሞ ወራ ሞመጂ ይበለሉ አሉን ያንኛው ተራራ ደግሞ ጋረ ዲማ ይባላል  አሉን ሁሉም መሬቱ የላው በ ኦሮምኛ ቋንቋ  ነው እኛ ኦሮምኛ ባንችልም መሬቱ እየነገረን ነው  ኦሮሞ  እንደሆን እናውቃለን  ይነገሩን ነበር  አየቶቻችን አሉን ።የ የጁ ሽማግሌዎች  ዱዓ ስጀምሩ ነጊ ነገያ ብሎ ይጀምረሉ   አንድ ሽማግሌ ጋ አገላልንና አብሮ መጨዋወት ጀመርን  ቤት አስገቡን  ምሳ አቀረቡልንና በ ዱዓ እንጀምር  አሉ  ደግ አልን ዱዓ አረጉ በጣም  ደስ የምል ነገር ዱዓ ስጀምሩ ነጊ ነገያ ብሎ ነው
ግን  ከሚገርም ወደ ባቲ ስንመጠ ደግሞ፣ ነጊ ነገየ ሰግለነረ ወጨሌ አፍረን ባቦ ቶርበን ባሬንቶ እየሉ ዱዓ ያደርገሉ በጣም ደስ በምል ዱዓ ነው የምጀምሩት ዱዓቸው ነጊ ነገያ ማለት አፋን ኦሮሞ  ነው ነጊ ነገያ ማለት ሰላም በ ሰላም  ላይ ይስፈን  ማለት  ነው ከዛም  እንዴት ነው ነጊ ነገያ ማለት ታቀለችሁ እንዴ አልነቸው አዎን  አሉን ምን ማለት  ነው ብለን ጠየቅናቸው  ነጊ ነገያ ማለት አባ ጌቲዬ ዱዓ የምጀምሩባት የሰላም  መክፈቻ ሰላም  በሰላም  ላይ ይስፈን  ማለት ነው አሉን
ስረው ቃሉ ኦሮምኛ  እንደሆነ እናውቃለን  ግን ምን እናርግ በ ጨቆነ ቋንቋችን ጠፍቷል አሉን ፣በጣም ሆደ ተረበሻ እንባ መጣኝ አልቻልኩም  ለ አፄዎች  መቼም  ይቅርታ  አለረግላቸውም ብዬ ቃል ገባሁ ።
 የጁ!!!!!!!!!

   ወሌ ወሌ ቢሏችሁ ፤
   ያነ ቆለኛ ፤
   ከብት ጠባቂው እንዳይመስላችሁ ፤
  የእሳቱ ጉማጅ ፤
  የእሳቱ አለሎ ፤ 
   የጁ ምድር ላይ ፤መርጦ አለላችሁ! !!!ግጥም መንግሥቱ ዘገዬ።.

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...