ጥቅምት 10, 1909 እለተ ጁምዓ
ሐረር
የባለግዜው መንግስት ቀሚስ ስር ፍርፋሪ እየለቀሙ ያሉ አስመሳዩች ሐረርን የሚመለከት ፅሁፎችን በለቅሶ መልክ እና ፌደራሊዝምን አስታከው ሲቀበጣጥሩ እያየን ነው ። የዚህ ሁሉ መንስኤ የአባታቸው ተፈሪ መኮንን እና የአያታቸው ራስ መኮንን ሐውልቶች መፈራረስ አንጀታቸውን ስለበላቸው ነው ።
▫️
የፖለቲካው መስመር አጉልቶ ስላላሳየው እንጂ ተፈሪ መኮንን የሐረር ህዝብ ላይ የሰራው አባቱ ጨለንቆና ሐረር ላይ ከሰራው ቢብስ እንጂ የሚያንስ አልነበረም ።
▫️
ጉዳዩ እንዲህ ነው …
▫️
የሸዋ ክርስትያኖች በእንግሊዞች አጋዥነት በተቀናበረ የፎቶ ፖለቲካ ምክንያት ልጅ እያሱን ከሐዲ አድርገው ከዙፋኑ ባወረዱበት ወቅት ሐረር ላይ ሙስሊሙ ልጅ እያሱ ጎን ሲቆም እስከ አፍጢሙ ታጥቆ የሰፈረው የሸዋ ክርስትያን (ሁሉም ወታደር እና የወታደር ቤተሰብ ነበር) ከተፈሪ መኮንን ጋር በማበር አንድ ግፍ ፈፅሟል ።
▫️
በግዕዝ አቆጣጠር ጥቅምት 10, 1909 እለተ ጁምዓ ላይ ሙስሊም ኦሮሞ ፣ ሶማሌ ፣ ሐረሪ ፣ አርጎባ እና የመኖች ላይ ቤት ለቤት ሳይቀር በተካሄደ ፍጅት የጁምዓ ሰላት ከመድረሱ በፊት ከቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ ብቻ ከ500 በላይ ሙስሊሞች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ። ይህ ሲደረግ ሁሉም የጀጎል መግቢያና መውጫ በሮች ተዘግተው ነው ። ፍጅቱን እንዲቆም ያደረገው የእንግሊዝ ቆንስላ ባስተላለፈው ትዕዛዝ ነው ( ከሴራው ጀርባ ዋነኛ አጋዦችም ስለነበሩ) ። ይህ ትዕዛዝ ባይመጠላቸው ኖሮ ግባቸው ምን ይሆን ነበር የሚለውን ወደፊት የምናየው ይሆናል ።
▫️
የራስ መኮንን እና የልጁ ተፈሪ መኮንን አይደለም ሐውልታቸው ስማቸው በዚህች ከተማ የመነሳት እድል ሊያገኝ አይገባውም ።
▫️
👉 ማስታወሻ
▫️
No comments:
Post a Comment