Translate

Saturday, February 6, 2021

#Jowar mohammed/ ጀዋር ሙሀመድ

 ነገረ–ጃዋር

ነፃነትን የማያውቀው ሓራ ህዝብ የመናገር፣ የመፃፍ፣ የማመን ነፃነትህን

ይገፈዋልና ትታፈናለህ የምታደንቀውን ሰው እንኳን በይፋ ለማድነቅ

ትቸገራለህ ማድነቃችን፣ ማመስገናችን ለመታፈናችን አሊያም ለመታሰራችን

መክንያት አይሆንም ብለን ተስፋ በማድረግ በዘመኔ እጅግ ተዐምር የሆነብኝ

ሰው ጀውሐር ሙሐመድ ነው።

ጀውሐርን በአካልም ሆነ በማንኛውም መንገድ አግኝቸው አላውቅም ግን

ከ2008 እስከታሰረበት ድረስ ያደረጋቸውን ኢንተርቪዎች፣ የፃፋቸውን ፅሁፎች

በተለይም በኦ ኤም ኤን ያስተላልፋቸው የነበሩ ፕሮግራሞቹን በከፊል

ለመመልከት እና ለማንበብ ችያለሁ።

ጀውሐር ሙሐመድ ከዮዲት (ጉዲት) እና ከ ኢማም አህመድ (ግራኝ) ቀጥሎ

ጭራቅ ተደርጎ የተሳለ፣ በእቅድ በጀት ተይዞለት ሰይጣን፣ ዲያቢሎስ ተደርጎ

እንዲሳል ዘመቻ የተደረገበት ሰው ነው።

ጃዋርን የሚከሱበትን፣ የሚወቅሱበትን፣ የሚጠሉበትን ሁሉ ለመመልከትና

ለመረዳት ሞከርኩ የጥላቻ ማሽኑ፣ የፕሮፓጋንዳው ቀያሽ ኃይል ጥላቻ

ርዕዮተዓለማዊ እንጅ ውሐ የሚቋጥር ክስ ሆኖ በፍፁም አላገኘሁትም ግላዊ

ባህሪውን፣ ወይም ስውር ተልእኮ ይኑረው አይኑረው ባላውቅም ጃዋርን

የሚመጥን፣ ፍፁም የበሰለ፣ ተዓምር የሆነ፣ በፖለቲካ ግንዛቤውና አቅሙ፣

በፖለቲከኛነት ተክለ ቁመናውና እልሁ፣ ለህዝባዊነት (በተለይ ለቆመለት

ህዝብ)፣ በቻይነት ትከሻው የደነደነ ፣ በአይዲዮሊጂካል ፍሬም ወርኩና

አንፕሪድክቴብል ባህሪው ያስደነቀኝ፣ ያሳመነኝ አንድም ፖለቲከኛ አላየሁም

ጀዋር የኦሮሞን ፖለቲካ የቀየሰበት መንገድ፣ ጃዋር ፌደራሊዝምን የተረዳበት

መንገድ፣ ጀዋር ለልዩነት ያለውን የፀና አቋም የተላበሰ አንድም ፖለቲከኛ

አላጋጠመኝም

የጀዋር ጥፋቶች

እኔም የማምንባቸው የፖለቲካ ጥፋቶቹ ብዙ ናቸው። ግና ጥፋቶቹን

ከርዕዮተዓለማዊ ቅርፅ ስመለከተው:–

ጃዋር የወጣበት ህዝብ ዋናው የጀዋር ህመም ነው። ጃዋር የወጣው ከኦሮሞ

ህዝብ ለዚያውም ከእስላሙማው ቀጠና ለዚያውም ለባለፉት ሃምሳ አመታት

በተፈጠረው የኦሮሞ ፖለቲካ ትርክትና ድባብ ውስጥ ነው። ይህ ጃዋር

በተፈጥሮ፣ ሳይፈልገው የተጋረጠበት አደጋ ነው። ጃዋርን የመሰለ ተዐምረኛ

ፖለቲካ አንድም ለፕሮፓጋንዳ ተሰላቢነት መሰረት ሁለትም የማህበራዊ

መሰረቱን ስሜት ለማስታገስ ሲል ከመሰረታዊው እሳቤው ያፈነገጠ ክስተት

ውስጥ እንዲገኝ ወይም ድርጊት እንዲያደርግ ሲያስገድደው ተመልክቻለሁ።

ለምሳሌ ጃዋር የኦሮሞ ህዝብ አይከን ሆኖ በሀጫሉ የቀብር ስነ–ስርዓት ላይ

አለመገኘት ይችል ነበር ወይ? "ፊንፊኔ ኬኛ " በሚል አቋሙ የሚታወቀው እና

ሌላኛው የኦሮሞ አይከን የሆነው ሀጫሉን ከአዲስአበባ ውጭ ይቀበር የሚል

አቋም ማራመድና ከመንግሥት ጋር ተመሳሳይ አቋም እንዲያራምድ የተገኘበት

ህዝብ ይፈቅድለት ነበር ወይ? አዲስአበባ ለዚያውም ሥላሴ ቤተክርስቲያን ቤተ

መንግሥት ጎን ሃጫሉ ይቀበር ሲባል ሊፈጠር የሚችለውን ክስተት ጃዋር

መገመትና መመልከት ይሳነዋል ወይ? የሚፈጠረውን ያውቀዋልና ከመሰረታዊው

ማንነቱና ብስለቱ እንዲሁም መሻቱ አንፃር "ሃጫሉ አምቦ መቀበር አለበት "

የሚል አቋም ቢያራምድ ህዝቡ በተለይም በመንጋ እያሰበ የነበረው ቄሮ

ይፈቅድለት ነበር ወይ?

እናማ የጀዋር አለመታደል የወጣበት ህዝብ የፖለቲካ ንቃት፣ ተፈራጅነት፣

ተሰጊነትና ፖለቲካዊ ተክለ ቁመና ነው።

የጀዋር ሌላው አለመታደል የኢትዮጵያ ስሪት፣ ታሪክና ዐምድ እንደ ጃዋር ዓይነቱን

ተዐምር የሆነ ወጣት ፖለቲከኛ ለመጠቀምና እውቅና ለመስጠት ፈፅሞ

አለመፍቀዱ ነው። የኢትዮጵያ ስሪት፣ ታሪክና ዐምድ እስላም ለዚያውም ኦሮሞ

የሆነን ሰብእ፣ ሃሳብ፣ ራዕይ፣ ማንነት በስጋትነት፣ በነውርነት፣ በጉድለት እንጅ

በሃብትነት፣ በጌጥነት፣ በሙሉነት ወስዶ አያውቅም

እናማ ጀዋር በማንነቱ ብቻ የኢትዮጵያ ስሪት፣ ታሪክና ዐምድ አገሪቱ ጉድለቱንና

ልጅነቱን እየሞላች፣ እያረቀችና እያረመች እንድትጠቀምበት ሳይሆን ሙላቱን

እየሸራረፈች፣ በመግፋት፣ በማግለል፣ ዲሞናይዝ አድርጋ በማጥላላት እያጎደለች

… እየሸረፈች ድራሹን እንዲታጠፋ ብቻ ስሪቷ እንደሚፈቅድላት ጃዋር መዘንጋቱ

ሌላው ስህተቱ ነው

ሌላኛው ስህተቱ የኃይሌ ፊዳን ስህተት መድገሙ ነው። 1966/67 ስንቱ በተስፋ

ወደ አገሩ መጣ በአንድና በሁለት ዓመታት ውስጥ ሁሉም በጅምላ መቀበሩን

ዘንግቶት ነበር።እናም የጃዋር ምፅዓትና የፓርቲ ጉዞ ታሪካዊ ስህተቱ ነበሩ።

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...