Translate

Thursday, February 11, 2021

#ወሎ ደዌ ዶዶታ መስጂድ/masgiida doddota dawwee!

☾︎★የዶዶታ መስጂድ ☾︎★
★★★★★★★★★★
ይህ መስጂድ በኦሮሞ ብ/ዞን ደዌ  ሀረዋ ወረዳ በመዲኔ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን፣ ከከሚሴ በስተ ምስራቅ በኩል በ40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የገኛል። የዶዶታ መስጂድ ያረፈው በኮረብታማ ቦታ ላይ ሲሆን አካባቢው እንደ ግራር ባሉ የበረሀ ዛፎች የተከበበ ነው።
መስጂዱ በሂጂራ አቆጣጠር 1176 እንደተሰራ እና 360 አመት በላይ እድሜ እንደሆነው ይነገራል። መስጂዱን የሰሩት " አባ አሲያ"/ አባስያ/ ይባላሉ።   መስጂዱ ሰርተው ለማጠናቅ 18 አመት እንደ ፈጀባቸው  ይነገራል።   አሰራሩ በአራቱም መአዘን በሰው አቅም ተንቀሳቅሰው ተገጠሙ ለማለት በሚያስቸግሩ በትላልቅ ድንጋዮች የተሰራ ግምብ ነው። የመስጂዱ ግድግዳ ውፍረት 3 ሜትር ያህል በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል። ጣራያው በ27 ምሶሶዎች ላይ እንጨት ርብራብ የተሰራ ሆኖ ከላይ በኮረት ተደልድሏል ። በመስጂዱ ጣሪያ ላይ የጸሀይ ብርሀን ማስገቢያ ያለው በመሆኑ መስጂዱ ጨለማ እንዳይሆን ይረዳል። ★★★★★★★★★★★★★★★★★★
ይህ መስጂድ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ እንዲይዝ ካስቻለዉ አንኳር ጉዳይ መካከል:- 
• በአካባቢው የሸሪአ ስርአት እንዲተገበር ጥረት የተደረገበት:
• የሀይማኖት ትምርት በስፋት ሲሰጥ የነበረበት መሆኑ:
• አያሌ እድሜ ጠገብ በእጂ የተጻፉ  ሀይማኖታዊ መፀሀፎች በቅርስነት በውስጡ መያዙ በጥቂቱ የሚገለፁ ናቸው።
ይህ መስጂድ ጥንታዊ በመሆኑ በዉስጡ በርካታ መፀሀፍቶች ይገኛሉ። ለምሳሌ ያክል ከ200 አመት በላይ እድሜ ያለው በእጂ የተፃፈ ቁርአን ይገኛል። 
መስጂዱ የእስለምና ሀይማኖት በስፋት እንዲዳረስ የተደረገበት በመሆኑ ልዩ ቦታ እንዲሰጠው ያደርገዋል። ህረተሰቡ ቅርሱን በመጠበቅ የመንከባከብ ስራ መስራት ይጠበቅበታል።  ★★★★★★★★★★★★★★★★★★
ለቀጣይ ህብረተሰቡን በማስተባበር መሰረተ ልማት እንዲሟላ በማድረግ እና በዝርዝር እንዲጠና በማድረግ የማስተዋወቅ ስራ መሰራት አለበት።

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...