Translate

Saturday, February 12, 2022

#Abay-#አባይ(አባያ) በ #ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድሕን ሮበሌ ቀዌሳ

~~~~~አበያ (አባይ)በሎሬት ፀጋዬ ሮበሌ ቀዌሳ~~~~~ አባይ የማን ነበር? አሁንስ የማነው? ኦሮሞ(የኩሽ ታላቅ ልጅ) እና አባይ የነበራቸው ቁርኝት ምን ይመስል እንደነበር ሎሬት ፀጋዬ ሮበሌ ቀዌሳ በሚገርም መልኩ በብዕሩ ከትቦልን አልፏዋል። 🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 አባይ የምድር አለም ሲሳይ የቅድመ-ጠቢባን አዋይ አባይ የጥቁር ዘር ብስራት የኢትዮጵያ ደም የኩሽ እናት የዓለም ስልጣኔ ምስማክ ከጣና በር እስከ ካርናክ በጡትሽ እቅፍ እንዲላክ ለራህ ለፀሐዩ ግማድ ፥ ለጣህ ለክዋክብት አምላክ ከጥንተ-ፍጡራን ጮራ ፥ የመነጨሽ ከኩሽ አብራክ። አባይ የምድረ-ኩሽ መኩሪያ በቅደመ-ታሪክሽ ጥርጊያ ከደም-ቢያ እስከ ኑ-ቢያ ከሜምፊስ እስከ ሜሮኤ በስልጣኔሽ ትንሳኤ ከዴልታሽ እስከ ዴር-ሡልጣን ከኡመ-ራህ እስከ ኡመ-ዱርማን፤ አባይ የአቴስ የጡቶች ግት ለዓለም የስልጣኔ እምብርት፤ ጥቁር አባይ የጥቁር ምንጭ የካም የስልጣኔ ምንጭ፤ አንቺ የምድረ ዓለም ሲሳይ በረሃውን ጥለሽ ግዳይ ሰሃራን እንዳክርማ ተልም ሰንጥቀሽው በወዝሽ ደም ፥ በጥበብሽ ስርወ-ፋና አንቅተሽ በአንቀልባሽ አዝለሽ ፥ የቅድመ ታሪክን ዝና የራምሴስን አበ-ሲምቦል፥ የመነስን ልዕልና በአልፋ የአልሙጋን ሐውልት፥ የቢያ-ሃንኬን ፍልስፍና በኮማምቦ የሶባቃን፥ በናፖታም የኤዛና ፊላኤ የአቴሰን ምኩራብ፥ በልቅጾር የአሞንን ዜና፤ አባይ ታላቅ ቅድመ-ተስፋ የኪነት ጉባኤ አልፋ፥ ረቂቅ አባይ ያንቺ መገን ምጥቀትሽ አይተንተን፥ የእጅ ማስነሻሽ በረከት ግብርሽ ከአድማሳት ሲክትት መንጣለያሽ ከዕለት ዕለት መሻገሪያሽ ካመት-አመት በመስዋዕት ሲወድቅልሽ በዝማሜ ሲፈስልሽ በመመለክ በመመስገን ጽላትሽ ከዘመን ዘመን በአዝርእት አበቅቴሽ ሲታጠን አቤት አባይ ላንቺ መገን አባይ ረቂቅ የጠቢብ ዘንግ የጨረቃን ጉዞ ፈለግ አስቀምረሽ በጠቢብ ዘንድ በፍሳሽሽ ውጣ ውረድ በሙላት ሚዛን ረገድ የሰማይን ጥርጊያ መንገድ ፥ የጊዜ መለኪያ ሰዓት ፥ ዜኒት ባንቺ ተቀምራ ከቴቤስ እስከ ዳንዳራ ብስራትሽን እንደደመራ ሥልጣኔሽ አንዳበራ፥ የመጽሐፈ-ሙታን ዜና አድርጎሽ ቅድመ-ገናና ዛሬ ወራቱ ራቀና ምድረ-ዓለም ያንቺን አድናቆት ፈለጉን መሻት ተስኖት እንዲህ ባንቺ መንከራተት ታሪክ ወሮታሽ ጠፍቶበት ትላንት በባዕድ ጩኸት ዛሬም ባላዋቂ ሁከት ቋንቋ ለቋንቋ ቢራራቅ የቅድሚያሽ ንድፍ ላይፋቅ እዚህ ደሜም እዚያ ተማም መባልሽ ብቻ ባይበቃም የቅርስሽ ጭብጥ ይዞታ ሆሄታሽ እስካልተፈታ፥ አባይ ፋናሽ የሕልም ርቅ ፈለግሽም ቢሆን ደቂቅ እንዴት እንዴት ነበር ብለን ካልደረስንበት ፈልፍለን፥ የጥንቷ አባይ እንዴት ትሆን አባይ-አቢይ አባይ-ግዮን ከምንጩ የጥበብ ሳሎን ግሪክ ፋርስና ባቢሎን ጭረው በቀዱበት ሸሞን፥ አባይ የአማልክት አንቀልባ የቤተ-ጥበባት አምባ ከኩሽ የቅድመ-አበው ብሁል ከተራራሽ አናት ቁልቁል የሰው ዘር የታሪክ-ፊደል ፥ ገና ከፅንሱ ሲረቀቅ ሲሳይም የእትብቱን ቆባ፥ ምጥቀቱን ለማንፀባረቅ ዘለዓለሙን ለማሳወቅ እስከሜዲትራኒያ፥ ጢሰ እሳትሽ ሲፍለቀለቅ፥ አባይ-አብይ ፥ አባይ ግዮን ለአማልክቶች አምላክ ለአሞን የኪነት ምንጩ እምትሆን፤ ለኦሩሰ ርቱእ አክናፋት ለነዳዮናይሶስ አባት ከእምብርትሽ የፀሐይ አምላክ ፥ ተቀስቶ በሰማያት ያረበበብሽ እንደ እሳት፤ ጥቁር አባይ ነጥቁር ምንጭ የካም የስልጣኔ ፍንጭ የቅድመ ታሪክሽ ጥርጊያ ከደም-ቢያ እስከ ኑ-ቢያ፥ የኢትዮጲስ ደም የኩሽ እናት አባይ የጥቁር ዘር ብስራት የዓለም ስልጣኔ ምስማክ ከጣና በር እስከ ካርናክ በጡትሽ እቅፍ እንዲላክ ለራህ ለፀሐዩ ግማድ፥ ለጣህ ለከዋክብት አምላክ፤ ከጥንተ-ፍጡራን ጮራ፥ የመነጨሽ ከኩሽ አብራክ፤ ሰሃራን እንደምሁር ተልም ያለመለመሽ በወዝሽ ደም የቅድመ-ጠቢባን አዋይ አባይ የምድር ዓለም ሲሳይ። ተነስ ንቃ አስመልስ ንገስ... ባላምባራስ ነጋሽ Negash Qemant~~~~~አበያ (አባይ)በሎሬት ፀጋዬ ሮበሌ ቀዌሳ~~~~~ አባይ የማን ነበር? አሁንስ የማነው? ኦሮሞ(የኩሽ ታላቅ ልጅ) እና አባይ የነበራቸው ቁርኝት ምን ይመስል እንደነበር ሎሬት ፀጋዬ ሮበሌ ቀዌሳ በሚገርም መልኩ በብዕሩ ከትቦልን አልፏዋል። 🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 አባይ የምድር አለም ሲሳይ የቅድመ-ጠቢባን አዋይ አባይ የጥቁር ዘር ብስራት የኢትዮጵያ ደም የኩሽ እናት የዓለም ስልጣኔ ምስማክ ከጣና በር እስከ ካርናክ በጡትሽ እቅፍ እንዲላክ ለራህ ለፀሐዩ ግማድ ፥ ለጣህ ለክዋክብት አምላክ ከጥንተ-ፍጡራን ጮራ ፥ የመነጨሽ ከኩሽ አብራክ። አባይ የምድረ-ኩሽ መኩሪያ በቅደመ-ታሪክሽ ጥርጊያ ከደም-ቢያ እስከ ኑ-ቢያ ከሜምፊስ እስከ ሜሮኤ በስልጣኔሽ ትንሳኤ ከዴልታሽ እስከ ዴር-ሡልጣን ከኡመ-ራህ እስከ ኡመ-ዱርማን፤ አባይ የአቴስ የጡቶች ግት ለዓለም የስልጣኔ እምብርት፤ ጥቁር አባይ የጥቁር ምንጭ የካም የስልጣኔ ምንጭ፤ አንቺ የምድረ ዓለም ሲሳይ በረሃውን ጥለሽ ግዳይ ሰሃራን እንዳክርማ ተልም ሰንጥቀሽው በወዝሽ ደም ፥ በጥበብሽ ስርወ-ፋና አንቅተሽ በአንቀልባሽ አዝለሽ ፥ የቅድመ ታሪክን ዝና የራምሴስን አበ-ሲምቦል፥ የመነስን ልዕልና በአልፋ የአልሙጋን ሐውልት፥ የቢያ-ሃንኬን ፍልስፍና በኮማምቦ የሶባቃን፥ በናፖታም የኤዛና ፊላኤ የአቴሰን ምኩራብ፥ በልቅጾር የአሞንን ዜና፤ አባይ ታላቅ ቅድመ-ተስፋ የኪነት ጉባኤ አልፋ፥ ረቂቅ አባይ ያንቺ መገን ምጥቀትሽ አይተንተን፥ የእጅ ማስነሻሽ በረከት ግብርሽ ከአድማሳት ሲክትት መንጣለያሽ ከዕለት ዕለት መሻገሪያሽ ካመት-አመት በመስዋዕት ሲወድቅልሽ በዝማሜ ሲፈስልሽ በመመለክ በመመስገን ጽላትሽ ከዘመን ዘመን በአዝርእት አበቅቴሽ ሲታጠን አቤት አባይ ላንቺ መገን አባይ ረቂቅ የጠቢብ ዘንግ የጨረቃን ጉዞ ፈለግ አስቀምረሽ በጠቢብ ዘንድ በፍሳሽሽ ውጣ ውረድ በሙላት ሚዛን ረገድ የሰማይን ጥርጊያ መንገድ ፥ የጊዜ መለኪያ ሰዓት ፥ ዜኒት ባንቺ ተቀምራ ከቴቤስ እስከ ዳንዳራ ብስራትሽን እንደደመራ ሥልጣኔሽ አንዳበራ፥ የመጽሐፈ-ሙታን ዜና አድርጎሽ ቅድመ-ገናና ዛሬ ወራቱ ራቀና ምድረ-ዓለም ያንቺን አድናቆት ፈለጉን መሻት ተስኖት እንዲህ ባንቺ መንከራተት ታሪክ ወሮታሽ ጠፍቶበት ትላንት በባዕድ ጩኸት ዛሬም ባላዋቂ ሁከት ቋንቋ ለቋንቋ ቢራራቅ የቅድሚያሽ ንድፍ ላይፋቅ እዚህ ደሜም እዚያ ተማም መባልሽ ብቻ ባይበቃም የቅርስሽ ጭብጥ ይዞታ ሆሄታሽ እስካልተፈታ፥ አባይ ፋናሽ የሕልም ርቅ ፈለግሽም ቢሆን ደቂቅ እንዴት እንዴት ነበር ብለን ካልደረስንበት ፈልፍለን፥ የጥንቷ አባይ እንዴት ትሆን አባይ-አቢይ አባይ-ግዮን ከምንጩ የጥበብ ሳሎን ግሪክ ፋርስና ባቢሎን ጭረው በቀዱበት ሸሞን፥ አባይ የአማልክት አንቀልባ የቤተ-ጥበባት አምባ ከኩሽ የቅድመ-አበው ብሁል ከተራራሽ አናት ቁልቁል የሰው ዘር የታሪክ-ፊደል ፥ ገና ከፅንሱ ሲረቀቅ ሲሳይም የእትብቱን ቆባ፥ ምጥቀቱን ለማንፀባረቅ ዘለዓለሙን ለማሳወቅ እስከሜዲትራኒያ፥ ጢሰ እሳትሽ ሲፍለቀለቅ፥ አባይ-አብይ ፥ አባይ ግዮን ለአማልክቶች አምላክ ለአሞን የኪነት ምንጩ እምትሆን፤ ለኦሩሰ ርቱእ አክናፋት ለነዳዮናይሶስ አባት ከእምብርትሽ የፀሐይ አምላክ ፥ ተቀስቶ በሰማያት ያረበበብሽ እንደ እሳት፤ ጥቁር አባይ ነጥቁር ምንጭ የካም የስልጣኔ ፍንጭ የቅድመ ታሪክሽ ጥርጊያ ከደም-ቢያ እስከ ኑ-ቢያ፥ የኢትዮጲስ ደም የኩሽ እናት አባይ የጥቁር ዘር ብስራት የዓለም ስልጣኔ ምስማክ ከጣና በር እስከ ካርናክ በጡትሽ እቅፍ እንዲላክ ለራህ ለፀሐዩ ግማድ፥ ለጣህ ለከዋክብት አምላክ፤ ከጥንተ-ፍጡራን ጮራ፥ የመነጨሽ ከኩሽ አብራክ፤ ሰሃራን እንደምሁር ተልም ያለመለመሽ በወዝሽ ደም የቅድመ-ጠቢባን አዋይ አባይ የምድር ዓለም ሲሳይ። ተነስ ንቃ አስመልስ ንገስ... ባላምባራስ ነጋሽ Negash Qemant

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...