Seenaa ilma nuuh "Ham " Abbaa afrikaa qaroomina kush & kana'an የኖህ ልጅ ታሪክ ሃም የአፍሪካ አባት የኩሽ እና ከነዓናዊ ስልጣኔ! For those who want to learn more about the history, culture, way of life, and civilization of the Cushites, visit our website.https://mikysultan.blogspot.com
Translate
Sunday, February 13, 2022
#ዋለልኝ መኮንን ካሳ ኩራሽ ጅማ ማነው?
ዋለልኝ መኮንን ካሳ ኩራሽ ጅማ ማነው?
1. ትውልድና እድገቱ በከፊል
ዋለልኝ መኮንን የተወለደው መጋቢት 11 ቀን 1938 ዓ.ም ደቡብ ወሎ ቦረና ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሲሆን የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደሴ ከተማ በሚገኙት ስመ ጥሮቹ ንጉስ ሚካኤልና ወይዘሮ ስህን ትምህርት ቤት ተከታትሏል። የ12ኛ ክፍል ትምህርቱንም ያጠናቀቀው በ 1958 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ስር ይተዳደር በነበርው በልዑል በዕደማርያም ቅድመ ዝግጅት ትምህርት ቤት (Preparatory School) ውስጥ ነበር። በዚህ ትምህርት ቤት ቆይታው በሥነ ፅሁፍ ዝግጅት የላቀ ሚና ተጫውቷል። የክርክር ክበብ ምክትልና ዋና ፕሬዝዳንትም በመሆን አገልግሏል። በዚሁ ክበብ አማካኝነት በተለይም የሥነ አመክኗዊ ውይይት አካሄድን ልቅም አድርጐ እንደተማረ ይነገርለታል። ትምህርት ቤቱ ዋለልኝን ተከራካሪ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ፀሃፊም እንዲሆን ረድቶታል። በሁለት ዓመት ቆይታው የትምህርት ቤቱ የጋዜጣ ረዳት አዘጋጅ በመሆንም አገልግሏል።
ዋለልኝ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በ Political Science የትምህርት ክፍል ትምህርቱን ቀጥሏል። ከዚያም በኋላ በ ሕዳር 18, 1961 ዓመተ ምሕረት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በተደረገው የሥነ ጽሁፍ ውድድር ኢትዮጵያውያን ከጣሊያን ወታደር ጋር ያደረጉትን ተጋድሎ፣ መስዋዕትነት፣ ጀግንነት፣ ለአገር ታማኝነትና ፍቅርን የሚያሳይ ሰነ ጽሁፍ ጽፎ ከተወዳዳሪዎቹ ውስጥ የአንደኝነት ማዕረግ በመጐናጽፉ ሽልማት አግኝቷል። በየዓመቱ በሚከበረው የዩኒቨርሲቲው ቀን ላይም በመወዳደር ካሸነፉት ስመጥር ገጣሚዎችና ባለቅኔዎች አንዱ ነበር።
.ዋለልኝ መኮንን ካሳ ኩራሽ ጅማ ማነው?
ውሎ የከረዩ ልጅ ነው፡፡ የባሬንቱ የልጅ ልጅ፡፡ ከከረዩ ልጆች መካከል ባሶና ዱለቻም ይገኙበታል፡፡ ዱለቻ ውስጥ እነ ሊበን አሉ፡፡ ሰባት ቤት ወሎ፡- ወረ ኢሉ፣ ወረ ሂማኑ፣ ወረ ባቦ፣ ወረ ቃሉ፣ለገ ሂdhaa፣ ለገ ጎራ እና ለገ አምቦ ናቸው፡፡ ከከረዩ ልጆች ወሎን አልፈው ጎንደር ድረስ የሄዱት ሊበኖች ናቸው፡፡ ሊቦ ከመከምን ፡፡ ከመ ከም “Warra Akkam akkam jedhu” “እንዴት እንዴት ነው? የሚሉት” ፡፡ የጃዊ ሽመል የሚባሉትን ሎጋዎችም፡፡ ጎጃም ባሶ ሊበን ወረዳ አለ፡፡ በተሻለ ጥበቡ መጽሀፍ የጎጃም አዛውንቶች “Gojam ጋ* ነው” ይላሉ ሲል ደምድሟል፡፡ ወሎ ያለው ሜታ በደራ በኩል የተሻገረው ቡድን ነው፡፡ ደራ ደግሞ ዋጂቱ ነው፡፡ የበቾ ዋጂቱ ኦሮሞ፡፡ ደራ “አደሬ ዋጂቱ” የሚባል ገበያ አለ፡፡
“አደሬ” ማለት ገበያ ማለት ነው፡፡ ትንሽዬ ገበያ፡፡ እነሱ "ሚዳ ኦረሞ" በማለት የሚጠሩት ዋጂቱዎች ናቸው፡፡ )
.
የዋለልኝ አባት የሜታ ኦሮሞ ናቸው፡፡ መኮንን ካሳ ኩራሽ ጅማ፡፡ አስራ ሶስተኛ ትውልዱ “ጭላሎ” ነው፡፡ በእናቱም እንዲሁ “ኛአ”የሚል ስም አለ፡፡ደራሲ አለማየሁ ኀይሌ እስከ 13 ትውልዱ መዝግቧል፡፡
2. የተማሪዎች ንቅናቄ ላይ የነበረው ተሳትፎ
ዋለልኝ መኰንን በዩኒቨርስቲ ቆይታው የኢትዮጵያን አርሶ አደሮችና ላብ አደሮች ነፃ ለማውጣት በ1960ዎቹ ውስጥ በተደረገው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ውስጥ ዓብይ ሚና የተጫወተ ወጣት ነበር። ጥላሁን ግዛው የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ ከተመረጠ በኋላ ባደረገው ከፍተኛ የትግል ተሳትፎ ከባድ ክትትል ይደረግበት ነበር። አፍንጮ በር አካባቢ ታህሳስ 19, 1961 ዓ.ም ጥላሁን ግዛው በጥይት ይመታል። ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ሲፈጠር ዋለልኝ መኰንን አምስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ቤቱ ከጓደኞቹ ጋር ነበር። አንድ ወጣት ወደ ቤት ይመጣና ስለ ጥላሁን ግዛው በጥይት መመታት ይነግራቸዋል። እነሱም በድንጋጤ ተያይዘው ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ይሄዳሉ። ሐኪሞቹ ሕይወቱን ለማትረፍ ሞክረው እንዳልተሳካላቸው ይነግሯቸዋል።
በዚህ ወቅት ዋለልኝና ጓደኞቹ የጥላሁንን አስከሬን ከሆስፒታሉ በመውሰድ ዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ በስርዓት ያስቀምጡታል። ከዚያ በኋላ የተቃውሞ ትዕይንትና የቀብሩን ሥርዓት ዝግጅት ያደርጋሉ። ለኮሌጅና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ። የጥላሁን ሞት ትግላቸውን እንደማይገታው፣ ጥላሁን ቢሞት ሽህ ጥላሁኖች እንደሚፈጥሩ በመግለጽ ጽሁፎችን በሕዝብ መሃል ያሰራጫሉ። በዩኒቨርስቲው ውስጥ ያለውን የጥላሁንን አስከሬን ለመውሰድ ወታደሮች በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገባሉ። በዚህ አጋጣሚ ዋለልኝ ከፎቅ ላይ ሆኖ በድምፅ ማጉያ ጥላሁንን የሚቀብሩት የትግል ጓዶቹና ሕይወቱን የከፈለለት ሕዝብ እንጂ ገዳዮቹ መቅበር እንደማይችሉ ይናገራል። የክብር ዘበኛ ወታደሮች በተማሪዎቹ ላይ ተኩስ ከፍተው አበበ በርሔ፣ ስብሃቱ ውብነህ፣ ጀማል ያሲን የተባሉ ሶስት ተማሪዎችን ይገላሉ። በዚያ ሽብር ወቅት ዋለልኝ መኰንን ይተርፋል ያለ ሰው አልነበረም። ነገር ግን ዋለልኝና ጓደኞቹ ኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማሰልጠኛ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይታሰራሉ። ዋለልኝ ከአሁን በፊት በገደብ ስለተለቀቀ እንደገና ወደ ከርቸሌ እስር ቤት ይላካል። ዋለልኝ መኰንን ከእስር ቤት ከተለቀቀ በኋላ ወደ ትምህርቱ እንዳይመለስ ታገደ።
3. የዋለልኝ የብሔረሰቦች ጥያቄ በኢትዮጵያ ፅሁፍ (Walelign On the question of nationalities in Ethiopia)
ዋለልኝ መኮንን ይህንን አወዛጋቢና ዝነኛ የሆነ አጭር ፅሁፍ “ታገል” (Struggle) ተብሎ በሚታወቀው የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መፅሄት ላይ ሲያወጣ ገና የ 24 ዓመት ወጣትና በዩኒቨርስቲው ደግሞ የ4ኛ አመት የ (Political Science) ተማሪ ነበር። በዚው ፅሁፉ ውስጥ ዋለልኝ እልል ያለ ማርክሲስት (Marxist) እንደነበረና በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብሎ ያመነው “የብሄረሰቦች ጭቆና” በተባበረ የህዝብ አመፅና (Popular Armed Violence) በሶሻሊስት ፖለቲካዊ ርዮተ-አለም (Socialist Political Ideology) ብቻ ሊፈታ እንደሚችል በግልፅ አስቀምጧል። ብሄራዊ ጭቆናውን ለማስረዳት ኢትዮጵያዊ ማን ነው? የሚል የዜግነት ጉዳይና ኢትዮጵያ ከምን ከምን ነው የተሰራችው ? የሚሉ መሰረታዊ ጥያቄዎችን አንስቷል። "What are the Ethiopian peoples composed of? I stress on the word peoples because sociologically speaking, at this stage, Ethiopia is not really one nation. It is made up of a dozen nationalities with their own languages, ways of dressing, history, social organization and territorial entity. And what else is a nation? It is not made of a people with a particular tongue, particular ways of dressing, particular history, particular social and economic organization? Then, may I conclude that, in Ethiopia, there is the Oromo Nation, the Tigrai Nation, the Amhara Nation, the Gurage Nation, the Sidama Nation, the Wellamo [Wolayta] Nation, the Adere [Harari] Nation, and however much you may not like it, the Somali Nation.”
ከዚያም በመቀጠል የመፍትሄ ሃሳቦች ያላቸውን በወቅቱ ሲደረጉ ከነበሩት የፖለቲካ ትግሎች ጋር እያዛማደ ለማስረዳት ይሞክራል። ለምሳሌ ስለ መፈንቅለ መንግስት ያነሳና፤ መፈንቅለ መንግስት ቢካሄድ የታሰበውን ለውጥ እንደማያመጣ ይልቁንም ሃገሪቱን ወደ ባሰ ችግር ውስጥ ሊከታት እንደሚችል ይገልፃል። “Can we do it through military? No!! A military coup is nothing more but a change of personalities.” በመቀጠልም በወቅቱ ይደረጉ ስለነበሩት የጎጃምና የባሌ አመፆች ያነሳና አስፈላጊነታቸውን አምኖና ተቀብሎ ነገር ግን የመጨረሻ ግብ የላቸውም ብሎ ያልፋቸዋል። “Can the Eritrean Liberation Front and the Bale armed struggle achieve our goal? Not with their present aims and set-up. Both these movements are exclusive in character, led by the local Bourgeoisie in the first instance and the local feudal lords in the second.”
“. . . The same can be said for the Gojjam uprising.”
ሌላው ዋለልኝ በዚው ፅሁፉ ውስጥ ያነሳው፤ በአሁኑ ወቅት በኢፌዴሪ ሕገ-ማንግስት አንቀፅ 39 በግልፅ የተቀመጠዉን “የራስን እድል በራስ የመወሰን ብሎም እስገመገንጠል” የሚለውን ሀረግ ነው። ዋለልኝ ሲገልፀው እንዲህ ይላል፤ “There is nothing wrong with secessionism as such. For that matter secession is much better than nationally oppressive government. I quote Lenin, “…People resort to secession only when national oppression and national antagonisms make joint life absolutely intolerable and hinder any and all economic intercourse. In that case the interests of the freedom of the class struggle will be best served by Secession.”
በመጨረሻም ዋለልኝ ፅሁፉን ወደ ማጠቃለሉ ሲመጣ How can we form a genuine egalitarian national-state? a genuine Nationalist Socialist State? ሲል ጥያቄ ያቀርባል። ለጥያቄውም መልስ ሲሰጥ “It is clear that we can achieve this goal only through violence, through revolutionary armed struggle.” ብሎ ይደመድማል።
4. የዋለልኝ ያልተሳካው ያውሮፕላን ጠለፋ
ዋለልኝ መኰንን፤ የጥላሁን ግዛውን መገደል ተከትሎ በተነሳው አመፅ ዋና ተሳታፊ ስለነበር ታስሮ ከርሟል። ከዛም በተጨማሪ “የአዋጁ አዋጅ” የሚል አፄ ሀይለስላሴ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ አስመልክቶ የተቃወሙብትን ንግግር የሚያጣጥል ፅሁፍ በመፃፉ ምክንያት የከፍተኛው ፍርድ ቤት አምስት አመት ፈርዶበት ነገር ግን አፄው በሴራ ለማስገደል ባደረጉለት ይቅርታ ከሶስት ወር እስራት በኋላ ከእስር ሊፈታ ችሏል። ዋለልኝ ከእስር ቤት ከተለቀቀ በኋላ የተማሪዎቹ ልሳን የነበረው ታገል መጽሄት ታገደ እሱም እንደዚሁ ከትምህርት ቤቱ ታገደ። ከዚያ በኋላ፤ በወቅቱ የመንገድ ማመላለሻ አስተዳደር ተብሎ ይጠራ በነበረው መንግሥታዊ ድርጅት ሥራ መስራት ጀመረ። በዚሁ ድርጅት ሥራ እየሰራ እያለ ብርሃነ መስቀል ረዳና (የኢሃፓ መስራችና ካዛ አስቀድሞ አውሮፕላን ጠልፎ ከሃገር የወጣ) ሌሎች የትግል ጓዶቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ድርጅት መሥራች ጉባዔ ስብስባ በርሊን ላይ በመጥራታችው ፤ ዋለልኝም በዚህ ስብስባ ላይ ለመገኘት ወሰነ። ወደ ስብሰባው ለመቀላቀል አውሮፕላን ከመጥለፍ ሌላ አማራጭ አልነበረውም።
ሕዳር 29, 1965 ዓመተ ምሕረት ከጥዋቱ አንድ ስዓት ተኩል ላይ ከአዲስ አበባ ተነስቶ (በአሥመራ በኩል ወደ አቴንስ ሮም ፓሪስ) ለመሄድ የተነሳውን የበረራ ቁጥር 708 ቦይንግ ጄት አውሮፕላን፣ ዋለልኝ መኰንን፣ ማርታ መብራቱ (በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ተማሪ የነበረች)፣ታደለች ኪዳነ ማርያም (በማስታወቂያ ድርጅቶች ትሰራ የነበረች)፣ አማኑኤል ዮሐንስ (የዩንቨርሲቲ ተማሪ የነበረ)፣ ጌታቸው ሀብቴ (የዩንቨርስቲ ተማሪ የነበረና ከውጭ ሃገር ጋዜጠኞች ጋር ይሰራ የነበረ)፣ ፣ ዮሐንስ ፈቃዱና (የዩንቨርስቲው 4ኛ አመት ተማሪ የነበረ) ተስፉ ቢረጋ (በመድሐኒያለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ያስተምር የነበረ) ሊያስገድዱት ሞክረው ባለመሳካቱ ታደለች ኪዳነ ማርያም ስትተርፍ ዋለልኝ መኰንን እና ሌሎቹ በአውሮፕላን ውስጥ በጸጥታ አስከባሪዎች በተተኮሰ ጥይት አየር ላይ ሕይዎታቸው አለፈ።
በመጨረሻም የዋለልኝ መኮንን ቤተሰቦች አባቱን ጨምሮ አስክሬኑን ከምኒልክ ሆስፒታል ተቀብለው ከአዲስ አበባ አገሩ ወሎ ተወስዶ በደሴ ከተማ መድሃኒዓለም ቤተክርስትያን ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት በተወለደ በ27 ዓመቱ በክብር ተቀብሯል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
mootittii saba'a Queen of sheba
"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...
-
#Hiika Maqaa #Gosaa ★******************-****************★ #Baareentuu=Jiraattoota warra bahaa kara aduun bariituun jiraatan jechuudha. #Wal...
-
#Horte # ituu #murawwaa Harargeef Walloof Raayyaa ~ ★Miky Sultan Wallo★ Gosa oromoo keessaa ituu n damee ilmaan bareentumaa yeroo tah...
-
Walloof Hararghee (Kutaa 1ffaa) Jaarraa 16ffaa dura lafa amma Walloo jechuun beekamturra ummanni Oromoo bal’inaan akka jiraachaa ture seenaa...
No comments:
Post a Comment