Translate

Sunday, April 3, 2022

#ሼኽ ጀማሉዲን አንይ

ጀማሉዲን ሙሀመድ አኒ (አራርሶ ሮውብሶ) https://t.me/Oromo_geography * ــــــــــــــــــــــــــــــــــــ * ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የዒልም ኮኮብና የጅሀዱ ጀግኖችን አውጥታ በታሪኳ አሳይታናለች። ከነዚህ ዘመነኞች ሙስሊም ጀግኖች መካከል: ታላቁ አባታችን ጀማሉዲን ሙሀመድ አል-ዐኒ (ረሂመሁላህ) በግንባር ቀደምነት እናገኛቸዋለን። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና እስልምና ታሪክ ስናስብ አባዬ ለእያንዱ ትውልድ ተምሳሌትና ታላቅ ባለውለታ ናቸው። በተለየም በኢስላም መድረሳ ፍሬያማ-ፍሬዎቹን ኮትኩተው፡ በዲኑ ሥርዓታማ ዘዴዎች ላይ ተንከባክበው በሁሉም የጥበብ ዘርፍ የተካኑ ብቁዎችን ቀርጸው … ሙስሊሙ ዑማ የሚመሩ ፣ ኢስላምን የሚያስፋፉና ዘብ የሚቆሙ የቁርጥ ቀን ልጆችን በማብቀት እና እንዲሁም በየ ጉራንጉሩ በየ ኮሮብታው ከመሾም አንፃር እርሳቸውን የሚመስል የሀገሬ ታሪክ እንዳጣ በተከታዩ ጽሑፉ እናያለን። . . . #ጀማሉዲን_ሙሀመድ_አኒይ ------------------ እንደ ሒጅሪያ ዘመን አቆጣጠር 1211 ወይም በሀገራችን 1781 ዓ.ም በራያ ምድር፡ ወርሳ-ሜሳ መንደር ፡ በልዩ ስሟ ‹ገልገሎ› ተብላ ከምትታወቅ ስፍራ ፡ ከሮውብሶ ኦቦ እና ሃዋ አብዱልቃድር አብራክ ወንድ ልጅ ተገኘ። ስሙም ‹አራርሶ› ተባለ። - ጀማሉዲን ሙሀመድ አኒ የልደት ስማቸው «አራርሶ» ነው። የትምህርት ዕድሜ ላይ ሲደርሱ «ሙሀመድ» የሚለዉን አንጋፈው ስያሜ በመምህራቸው ተለገሱ። የሗላሗላ ለአያሌ ህዝቦች አባት ፣ ዓይንና ጆሮ ፣ ኃይልና ጉልበት ሆነው ትሩፋተ-አያልነታቸው ገዝፎ ሲታይ እጅግ በርካታ የክብር ስያሜ እንደጉድ ተዥጎደጎደላቸዋል። ተገቢ የሆኑና ባልተቤታቸውን ያገኙ ገላጭ ሞክሼ ስያሜዎች ነበሩ። ለአብነት ያህል ፣ እውቀት ተግባር ሁለተናቸው ኢስላማዊ ሆነው ሲገኙ «ጀማሉል-ዲን» የሚል እካያ ተቸረ። ነገረ ሁሏቸው መምህራቸውን ይመስሉ ነበረና ‹አንይ› የሚል ተጥሮተ-ስም ተደለበ። አባዬ ፣ የዲኑ-ችቦ ፣ የኢስላም-እንፅብራቅ ፣ ጸሐይ ፣ የፍቅር እርሾ ፣ የእዉነት-ጥራዝ ፣ የዕዉቀት ማማር ፣ የእውቀት ውበተ-ጉልላት ፣ የቡራኬ ልዕል እና . . . . . . ወዘተ ሌሎች የተለዩ ክብረ ስያሜዎችን ወዳጅ ገበር ሁሉ ባፈቀረ ቀልቡ አንዳሻው ስያሜም ይጠራቸዋል። እኛም በዚህ አብዣኛው ዘንድ በሚታወቁት ፣ ጀማሉዲን ሙሀመድ አኒይ እና አራርሶ እንዲሁም አባዬ የሚሉ መጠርያዎችን ተጠቅመናል። #አራርሶ_ሮውብሶ (ጀማሉዲን አኒይ) ------------------------- ጀማሉል-አኒይ አባታቸዉ ሮውብሶ (ቃዲ-ኢብራሒም) ፣ ባቦ ፣ ቦሩ ፣ ዱዮ ፣ በረንቶ ፣ ሃሞ ፣ ሸኽ ሀሰን #ሐሰኒይ (ከነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ የዘር ሀረግ የተመዘዙ) ናቸው። ከኦሮሞ ከታወቁ ጎሳ ሆርሶ-ሴሮ የተገኙ ናቸው። እናተቸው ደግሞ ሃዋ ሸኽ አብዱል-ቃድር ሸኽ ሙስጠፋ ሸኽ ኡመር ሸህ አይፈራ ሸህ ሙሀመድ ሰኢድ ትባላለች። ቤተሰቦቿ መግሪብ (ሞሮኮዊ) አረቦች ናቸው ይባላል። የዘር ሀረጓ ከፈቂህ ሙሳ አልጀበርቲ ዘር የተመዘዘ #አዴ_ከቤሬ ከተባሉት ከነቢዩ ሙሀመድ (ሶለላሁ አለይ ወዓሊሂ ሰለም) ዘር #አህለልቤይት ናት። ለኢማሙ የጀማሉዲን-አኒይ ስኬት ትልቁ አስተዋጽኦ፡ የእናታቸው ጥረትና ትግል ዋነኛው ነበር። እርሷም ለሁሉም ሙስሊም ምርጥ ተምሳሌት ናት። የልጇ ታላቅነት የርሷ ጥረት ዉጤት በመሆኑ ለኢትዮጵያ እስልምና ባለዉለታ ነች። የጀማሉዲን አኒይ እናት ሃዋ ሸኽ አብዱል-ቃድር (የአላህ እዝነትና ቱሩፋት በእርሳቸዉ ላይ ይጉረፍና) ልጇም የትምህርት እድሜ ላይ ሲደርስ፡ ከትውልድ መንደሯ ወደ ዕዉቁ ዓሊም ሸኽ ሰይድ አል-ፈቂህ ዙበይር አስቃሬ ዘንድ ለዚያራ (ጉብኝት) እና ልጇም ከቡራኬያቸው እንዲሳለምና ዱዓ ያደርጉለት ዘንድ መጡ። ከዚያም እናታቸውም እንዲህ አለች፦ «ለዚህ ለልጄ ጸልዩለት። አላህ በእስልምና መንገድ እንዲቀርፀው። የሱ አያቶቹና አጎቶቹ የጦር ሰዎች ስለነበሩ የሞቱትም በጦርነት ነው። ስለዚህ ይህ ልጄም የቤተሰቡ አይነት እጣ እንዳይገጥመው ስጋት ይዞኛል » አለቻቸው። ሸይኽ አስቃሬም ዱዓ አደረጉላቸውና እንዲህ አሉ፦ «ይህ ልጅ ላይ ስጋት የሆነብሽ ፍርሃት መድሃኒቱ ይህ ቁርዓን። የዚህ እውቀት ነው ፈውሱ። እኔ አስተምረዋለሁ» አሏት። ከዚያም የልጃን መጠርያ ስሙን ጠየቋት። እርሷም፡ « ስሙ አራርሶ ሮውብሶ ባቦ ነው። (አራርሶ የኦሮምኛ ቃል ሲሆን ፣ አስታራቂ ማለት ነው።) ስሙን አራርሶ ያልኩት ይህን በሁለቱ ጎሳ መካከል ያለው ጦርነት በስሙ በርከት ሰላም ይለግሰን ዘንድ በመሻት ነው» አለቻቸው። ሸኽ አስቃሬም « እኔ ሙሀመድ ብዬ ሰይመዋለሁ» አሏት። እሷም በዚህ ተስማማች። ( እንዴትስ አትስማማ ? የማን ስም ሆኖ ? ) ልጃንም ለሸኩ አስረክባ ተመለሰች። ቁርዓንም በእረሳቸው ላይ አከተሙ (ጨረሱ)። ቁርዓን ያስቀሯቸው እናተው ናት። እንዲሁም አክስታቸው ናትም ይባላል። ሸኽ አስቃሬ ፣ ተማሪያቸውን ጀማሉል-አኒ የቁርዓንን ንባብ ተምረው እንደጨረሱ ፣ የፊቂህ ትምህርት ሊቅ ወደሆኑት ሸኽ ፈቂህ ገንደ-አውልዮ (የአውልዮ መንደር ሸኽ) ዘንድ ላኳቸው። በእርሳቸዉም ላይ የመጀመርያ ደረጃ የፊቂህ ትምህርት (ከሻፊዒይ መዝሃብ) ሚንሃጁ-አጧሊቢን ድረስ ተማሩ። በዚህም የመማር ልክፍት ፣ የምሁርነት ጥማት ፣ የኢልም ፍቅር በረታባቸው። ይሁን እንጂ መምህራቸው በወቅታዊ ሙስሊሞች ሁኔታ ከሀገር ሀገር ይቀያይሩ ነበር። ትምህርት ማስተማሩን አቁመው ከአገራቸው ርቀው ወደ ተለያዩ አከባቢ እየተንቀሳቀሱ የዑማውን ሁኔታ ጥናት ያደርጉ ስለነበረ፡ ጀማሉዲን ሙሀመድ አኒን የማወቅ ጉጉት እና የመማር ጥማት አላረካም። በየእለቱ የመማር እድልን ይናፍቁ ነበርና በዚህም ቅር ይሰኛሉ። ሆኖም ወደ ኃይሉ አላህ (ሱ·ወ) ብቁ የሆነ ቋሚ መምህር እንዲገጥማቸው ይጸልዩ ነበር። በዚሁ መካከል ወደዚች መንደር ብዙ ተጓዥ መንገደኛ ጭፍሮች ይመጣሉ። ለሐጅ (ወደ ቅድስቷ ከተማ መካ) ተጓዥ መንገደኛ ሓጃጆች ሲሆኑ። እንግዶቹም ወደዚህ ከመምጣታቸው አስቀድመው ወደ #ሙፍቲል_አናም ሐጂ ዳዉድ አቡበከር ዘንድ በመሄድ፡ ዱዓ እንዲያደርጉላቸው ዚያራ አድረገው ነበር። ሐጂ ሙፍቲ ዳውድ (ረሂመሁላህ)ም « … ከራያ አውራጃ ውስጥ ስትደርሱ ባልደረባዬን ሸህ ሐጂ ጧሂርን ፈልጋችሁት ዘይሩት። ሰላምታዬን አድርሱልኝ። ለናንተም ከሱ ዱዓ ፈልጉ።» ብለዋች ስለነበረ ፣ ከራያ ግዛት እንደደረሱ ስለተጠቆሙት ሰው ማጠያየቅ ያዙ። ሐጂ ጧሂር ከሰዎች ተጠልለው ጧትማታ አላህን በማውሳት ላይ የተጠመዱ ስለሆኑ እምብዛም አያውቃቸውም ነበርና እያፈላለጉ ቀናቶችን ካሳለፉ በሃላ፡ #ገንደ_ሶቶላ ከተባለች መንደር ውስጥ አገኙዋቸው። ሐጅ ተጓዥ እንግዶቹም ጎብኝተዋቸው ከተመለሱ በሃላ ፣ ሰዉ ሁሉ ስለ ሐጂ ጧሂር ማንነት መወራት ይጀምራል። ይህን ስም ተማሪው ሙሀመድ ሮብሶ (ጀማሉል አኒ) ሰማ። ሐጂ ጧሂርም ዘንድ በመሄድ ቂርዓት ጀመረ። መምህሩንም በሁሉም ሸሪዓዊ የጥበብ ዘርፍ እና እነዲሁም በአረበኛ የቋንቋ ጥናት በጠንቃቄና በጥልቀት መርምሮ የፈተሸ እና ለጥቃቅን ነገር ሁሉ የሚጨነቅ ጥንቁቅ ምሁር ሊቅ ሆነው አገኘው። ያጣውንና በናፍቆት ሲፈልግ የነበረው ገጠመው። አስራ ሁለት (12) አመት ከርሳቸው ላይ ተማረ። ከነብዩ (ሶ·ዐ·ወ) ሀዲስ በስተቀረ በሁሉንም የጥበብ ዘርፎች ተካነ። እናማ ይህን ሁሉ ኢልም በመሰብስ ሙጅተሂድ ደረጃ የደረሰው ከሀገሩ ራያ ምደር ሳይርቅ ነበር። የጀማሉዲን ሙሀመድ አኒ የደለበ ወፍራም እጣ ጅመማሮ ከዚህ ይጀምራል። ጥልቅ ከሆነው የህይወት ታሪካቸው መርፌ ባህር ውስጥ ነክሮ የማውጣት ያህል ተሞክሯል። በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል። #ይህ ጽሁፍ የተወሰደው 1· በወሌኔ ሸይኽ (ረሂመሁላሁ) የተዘጋጀ፣ «ታላላቅ የሐበሻ ኡለማወች ታሪክ (ጥሮኖ) መጽሐፍ። 2· የኢማም ጀማሉል አኒ «ሪሳለቱል መይሙን» ለተባለው ኪታባቸው ሙቀዲማ/መቅደም መግቢያ ከተዘጋለት። መሰረት አድርጌ የተወሰዱ ናቸው። በመጨረሻም ምዕራፍ ግርጌ ማን ምን አለ ? የሚለውን ለማመልከት እሞክራለሁ። በይበልጥ ሊንኩን ጠቅ ያድርጉት። https://t.me/Oromo_geography

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...