የወሎ ኦሮሞ ሁለት ኃያላንና ተፎካካሪ ብርቱ ጀግና አይደፈሬ ጠንካሬ ንግስቶች ወርቂትና መስታውት ታሪክ በነጋሽ ቅማንት የተፃፈ
×××××××××××××||||||||||||××××××××××××××××
የሊበን አመዴ ዋና ከተማ መቅደላ ፣ የወርቂት ዋና ከተማ አምባሰል ነበር : ወርቂት የባላቸው አሊ ሊበን( አባ ቡላ) በ1842 ሰለሞቱ የልጃቸው አመዴ አሊ ሞግዚት ሆነው ያስተዳድሩ ነበር። ሙሉ ስሟ ንግስት ወርቂቱ ወዳጆ ይመር ቦሩ ትባላለች።
የመስታውት ልጅ እንደ ወርቂቱ ልጅ አመዴ ይባላል። ወርቂትና መስታውት በሽር ሊበንና አሊ ሊበን የተባሉ የሁለት ወንድማማች ሚስቶች ነበሩ ። ስለዚህ ሁለቱ አመዴዎች ከስማቸው መመሳሰል ባሻገር የስጋ ዝምድና ነበራቸው ። ከሁለቱ ግን እስከ መጨረሻው አፄ ቴዎድሮስን ያስጨነቀው የመስታውት ልጅ አመዴ በሽር ነበር ። በወሎ ኦሮሞ የአፄ ቴዎድሮስ በትር የበረታውና በርካታ ግፎችን የፈፀመው አመዴ በሽርን አሸንፈው አለመያዛቸው ነበር ። አፄ ቴዎድሮስ 7 ጊዜ በወሎ ኦሮሞ ላይ ዘምተው አንዱንም ሳያሸንፊ አመዴ ሊበንን ለመማረክ አልቻሉም ነበር ።
~ የወርቂት ልጅ ግን አመዴ አሊ ወርቂት በተሸነፈች ጊዜ አመዴ አሊን ለንጉሱ ቴዎድሮስ ሰጥተው ክርስትና አስነስተውት ነበር ከዚያም ለጥቂት ጊዜ የአምባው ገዥ አድርገው ሹመውት ነበር ።ወዲያው ግን እናቱ ወርቂት ለምርኮኛው ምኒልክ ከመቅደላ ለማምለጥ እጇ አለበት ተባብራለች ተብሎ ልጇ አመዴ አሊ በሰንሰለት ታስሮ ሲማቅቅ ከቆዩ በኃላ በአሰቃቂ መልኩ በመቅደላ ገደል ተገድሏል። ንግስት ወርቂትም በአንድ ልጃቸው ሞት ከባድ መሪር ሃዘን ገቡ ። ወደ ሸዋ በመሄድም ለአንድ አመት ቆይተው በጉዲፈቻ አንድ ወንድ ልጅ ይዘው ወደ ወሎ ተመለሱ ።
የወርቂት ከፓለቲካ ውድድሩ በልጇ መሪር ሃዘን መውጣት ለመስታውት ጥሩ አጋጣሚ ፈጠረላት። ወይዘሮ መስታዉትም የልጃቸው አመዴ ሊበን ሞግዚት በመሆን ከድፍን ወሎ ኦሮሞ ሙሉ ድጋፍ ተቸራቸው። የመቅደላን አምባን በተደጋጋሚ መውጋት ጀመረች ። የእንግሊዝ ጦር ወደ መቅደላ ሲቀርብም ከወሎ ኦሮሞ ባላባቶች ወርቂትና መስታውት ጋር መደራደር ነበረበትና አስጠርቶ ሁለቱንም በሰራዊቱ ካምፕ ውስጥ አነጋግሯቸዋል ታሪካዊ ፎቶግራፎችም አንስተዋቸዋል። የወርቂት ይሁን የመስታውት ጦርም መቅደላን እያንዳንዱን መግቢያ መውጫ በር መሽሎኪያ ቀዳዳዎች ሁሉ እንዲዘጉ አፄ ቴዎድሮስና ሰራዊታቸው እንዳያመልጡ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። የሚያሳዝነው ግን ጀኔራል ሮቤርት ናፒየር ከመቅደላ ድል በኃላ ለመስታውት ይሁን ለወርቂት ምንም የጦር መሳሪያ እርዳታና ድጋፍ ሳያደርጉ ይባስ ብሎ የመቅደላ አምባን በርካታ ቦታዎችን ምሽጎችን እንዳይጠቀሙባቸው በፈንጅ አፈራርሰው ነበር የሄዱት ።
በመጨረሻም ይህ የወራሂመኑ መሐመዶች ስርኦ መንግስት ሃረግን ተከትለው ወሎን ሲያስተዳድሩ የቆዩት መሀመድ አሊ በአፄ ዩሃንስ ክርስትና ተነስተውና የክርስትና ስማቸው ሚካኤል ተብሎ የራስነት ማዕረግ ተሰጣቸው። በተመሳሳይ ሁኔታም የባላባቷ የወይዘሮ መስታውት ልጅ የሆኑትና እና በፈረስ ስማቸው አባዋጠው በመባል የሚታወቁት አመዴ ሊበን በንጉስ ሚካኤል የክርስትና አባትነት የክርስትና ስማቸው " ኃይለማርያም " ተብለው ተጠምቀው የደጃዝማችነት ማዕረግ ተሰጣቸው። ራስ ሚካኤልም የንጉስ ሚኒልክን ሴት ልጅ አግብተው ልጅ እያሱን ወለዱ ።
ልጅ እያሱም ኢትዮጵያን ከ1913-1916 በመፈንቅለ መንግስት እስኪወገዱ ድረስ አስተዳደሩ በርካታ ለውጥም አምጥተው ነበር ለምሳሌ ኃላቀር የፍርድ ስርዓትን የቁራኛ ስርዓትን ( ከሳሽና ተከሳሽ ታስረው የሚቆዩበት) አስቀሩ ፣ ሌባን የሚያውጣጡበትን ሌባ ሻይ የሚባለውን ስርዓት አስቀሩ ይህ ስርአት አንድን ህፃን ልጅ እጽ ወይም አደንዛዥ መጠጥ ይሰጠውና በርካታ ሰዎች ይሰበሰቡና ከእነዚህ ውስጥ ሌባውን ጠቁም ይባል ነበር፣ ልጅ እያሱ የመንግስት ኦዲት ያስጀመሩ ነበሩ ፣ የከተማ ውስጥ ደንብ አስከባሪ ፓሊስ ያስጀመሩ ነበሩ ።
ባላምባራስ ነጋሽ( ገሞራው ቅማንት)
No comments:
Post a Comment