........................እምዘነገደ ኩሽ..........................
ኩሽ እንደ አንድ ህዝብ ፣ ኩሽ እንደ አንድ ቋንቋ ነገድ ፣ ኩሽ እንደ ሃገር አንድም ሶስትም ነው ። የታሪክ ባለቤት ለሆነ ሕዝብ የታሪክ ባለሙያው ፍጹም ባዕድ ሲሆን ታሪክ መወላገዱ አይቀርም ። ለዘመናት የኦሮሞ ታሪክ ነው እየተባለ፣ ሲንጋት የነበረው ነገር በፍጹም የኦሮሞን ሕዝብ አይወክልም። የኦሮሞ ሕዝብ የፈለቀው ከኩሽ ሕዝብ እንደመሆኑ መጠን ከ8000 አመታት በፊት ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ሰፍሮ የኖረ ስሆን በ3500 ዓ.ዓ. እና በ2000 ዓ.ዓ. መካከል ከምስራቅ ቅርንጫፍ ኩሽ ተለይቶ በቋንቋና በባህል እራሱን የቻለ ሕዝብ ሆኖ መውጣቱን የሥነ ልሳን ማስረጃዎች የሚያረጋግጡት ሃቅ ነው። ከዚህ አንፃር ኦሮሞ ከየት መጣ? መነሻው ምንጩ ከየት ነው? ብሎ መጠየቅ፣ ጥንታዊ ኩሽ ከየት መጣ? መነሻው ምንጩ ከየት ነው ብሎ እንደመጠየቅ ይቆጠራል። ኦሮሞ መነሻና ጥንተ መኖሪያ አገር የት ነው ብሎ መጠየቅ፣ ወፍ ይበራል ወይ፣ ዶሮ ላባ አላት ወይ ብሎ እንደ መጠየቅ ይቆጠራል። ምክንያቱም ኦሮሞ ከጥንታዊ ኩሽ የፈለቀ እንደመሆኑ የጥንታዊ ኩሽ መነሻና ጥንት መኖሪያ ተረጋገጠ ማለት፣ የኦሮሞ መነሻና ጥንት መኖሪያ ተረጋገጠ እንደማለት ስለሆነ።
ተረታችን ታሪካችንን ተጭኖት በዕውነት ሳይሆን በህልም መሰል መማለል ውስጥ የምንኖር ሕዝቦች ከሆን ቆይተናል ፣ ይሁን እንጂ አሁንም ወደ ንቃት ከማምራት ይልቅ የበለጠ እንዲጫጫነን በሚያደርጉ የተረት እሹሩሩዎች እየተባበልን እንገኛለን፡፡ ከታሪክ ሊቃውንት ይልቅ ..የተረት አባቶች.. የደብተራ ተረት.... ብሄርና ህዝብ የሚሰድቡ ድርሳናት የፀሎት መጽሃፎች በገነኑባት በዚች አገር መግባባታችን በአፈ ታሪክ ተወርሮ የኋላ ምስላችን እንደ ልጆች ትረካ ከሳይንሳዊው ዓለም የማይደባለቅ አስቂኝ ቀልድ ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ስም ላለፉት 150 አመታት በገዳማት፣ በአባተ ክርስቲያናት፣ በትምህርትቤት፣ በኮሌጅ በዩኒቪርስቲ በአውቅልሃለው በየተፃፈው ታሪክ በራሳቸው ፍላጎት የእናተ ታሪክ ይህ ነው ብለው ቆርጠው ቀጥለው መርጠው፣ አንተን መጤ ራሳቸውን ጥንታዊ ነዋሪ አድርገው፣ ማንነትህን አጠልሽተው ራሳቸውን ገዥ አንተን የበታችን ተገዥ ዜጋ አድርጎ ራሳቸው የጀግና ጀግና አድርገው አንተን ተራ አሽከር ደንገጡር ፈሪ ተሸማቃቂ አድርገው ጽፈው፤ ራሳቸውን የእግዚአብሔር የተመረጠ ምርጥ ዘር አድርገው አንተን እርጉም በእንጨት በዛፍ የምታመልክ የእንጨት ዘር አድርገው የፃፉትን ተረት እንዴት ታሪክህ ይህ ነው ተብሎ ትውልድ ይማርበታል። እውነተኛ የማንነት ታሪካችን ባህላችን እሴታችን በራሳችን ልጆች እውነተኛ ምርምር ጥናት ታሪክ ሆኖ ተጽፎ ለትውልድ ይተላለፋል እንጅ በተረት አባቶች እንደድሮው በአውቅልሃለው በደላላ ታሪካችን አይጻፍም።
የኢትዮጵያ ታሪክ ተረት የሚመስል ታሪክ እንጂ ትክክለኛ የሆነ ታሪክ አይደለም። በኢትዮጵያ የታሪክ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ ታሪክ ፀሀፊዎች ከነገስታቱ እና ከወቅቱ ሹማምንት ጋር ጥብቅ ቁርኝነት የነበራቸው በመሆኑ ታሪክን የፃፉት ከተቆራኙበት አካል ፍላጎት አንፃር እንጂ ከታሪክ ጥናት አንፃር ነበር የሚል እምነት የለኝም። በዚህ የተነሳ እነዚ የሹማምንት አጎብዳጆች የፃፉትን ተረት እንጂ ታሪክ እንደሆነ ለመቀበል ያስቸግራል። ቀዳማዊ ምኒልክና ጓደኞቹ የእሥራኤል ወጣቶች ከኢየሩሳሌም ታቦት ሰርቀው አክሱም ከተማ ቤተ መቅደስ አኖሩት በሚባልበት ጊዜ አክሱም አልተቆረቆረችም፡አክሱም ከተማና የታሪክ ዘመን የሚጀምረው የቀዳማዊ ምኒልክ አባት ነው ከሚባለው ከንጉሥ ሰለሞን 800 ዓመታት ያህል ቆይቶ ነው፡፡ የአይሁዶችም ሃይማኖት በዚያን ጊዜ ተመሥርቶ፣ ንጉሡ፣ ተከታዮቹና ሕዝቡ ሁሉ ቋንቋ ወደ ግዕዝ ተተርጉሞ ነበር የሚባለውም እንዲያው የሃይማኖት ነው እንጂ የታሪክ መሠረት የለውም፡፡ ሕዝቡ ሳይቀር ከጥንት እስራኤል አገር የመጣ ነው እያሉ ይተርታሉ፡፡ የንግሥት ሳባና ቀዳማዊ ምኒልክ [ታሪክ] ይህንን ነው የሚያስተምረው፡፡ ካህናቱ እንደ እውነት አድርጎ ተቀብለውታል፡፡ በየመድረኩም ይሰብኩታል፡፡
በካህናት አንደበት የሚነገር ደግሞ እንደ ሃይማኖት አጥብቆ ስለሚያዝ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ትውፊትና አፈ ታሪክ ውስጥ በጣም ዘልቆ ገብቷል፡፡ ነገሥታቱ፣ መኳንንቱ፣ ካህናቱና ተራው ህዝብ እንኳ ሳይቀር፣ ዘር ሲቆጥር ወይም ከንግሥት ሳባና ከልጇ ከቀዳማዊ ምኒልክ ወይም ከምኒልክ ጋር የእስራኤል ታቦት ሰርቀው መጡ ከሚባሉት ከአሥራ ሁለቱ ነገደ እሥራኤል ካንደኛው ነው የሚጀምሩት፡፡ ሰለሞናዊ የሚባለው ሥርወ መንግሥት መነሻው ከዚሁ ተረት ነው፡፡ የፈላሻ ሕዝብም እንደዚሁ፡፡ እስከማውቀው ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ራሱን ችሎ ገለልተኛ በሆነ መንገድ ታሪክን የፃፈ ግለሰብ ወይም ተቋም ነበረ ማለት አይቻልም። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የታሪክ ጥናት በራሱ ያልተለመደ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ታሪክ ፀሀፊዎች ራሳቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የውጪ አገር የታሪክ ፀሀፊዎችን እንደ መረጃ በስፋት ሲጠቀሙ ታዝቢያለሁ። ስለዚህ ይህ የሚያሳየው አሁን የምናውቀው የኢትዮጵያ ታሪክ የታማኝነት ችግር ውስጥ ያለፈ በመሆኑ ትክክለኛ ታሪክ እንደሆነ ለመቀበል ያስቸግራል።
ኢትዮጵያ ለውሸትም፣ በውሸትም የሚኖሩ፣ ለውሸትም በውሸትም የሚሞቱ ቡዙ ውሸታሞች፣ ተወልደውባት እንጂ የኦሮሞ ሕዝብ ቀደምት የአገሪቱ ነዋሪ መሆኑን ታሪክ ይመሰክራል። ዳሩ ምን ያደርጋል ዛሬም ድረስ ይሄንን ሀቅ ላለመቀበል ሲሉ አባቶቻቸው የጀመሩትን የውሸት ትርክት በልጆቻቸው እና በልጅ ልጆቻቸው ከመቶ ዓመት በኋላም ሲደገም ስታይ ለካስ ውሸትም ይወረሳል እንዴ? ከማለት ውጭ ምን ይበላል ኦገኖቸ ?
ከኑማ ✊
No comments:
Post a Comment