Translate

Saturday, April 6, 2024

የወሎ ንግስት ወርቂቱ ወዳጆ

#ታላቋ #የወሎ #ሡልጣን#ወርቂት#ወዳጆ #ይመር
-----------------------------------------------------------------------------------
★ Miky Sultan Barento★
ገዥ ሳለች ወደርሷ የምትጮህ ተበዳይ ነፍስ አልነበረችም ፤ ለጊዜዉ በጨበጠችዉ መንበር ላይ የሚተፉ የሃሰት ዉንጀላዎችን በቁም ተቀባይ ኖላዊም አልሆነችም ፤ ርቱዕ አንደበቷ ከረር መረር ያለች ቢያደርጋትም በፍጥረቷ ወርቅና መሬት ናት - ታላቋ ሡልጣን ‹ወርቂት›

የዛ ዘመን ብሩክ መሣፍንቶች(ፓለቲሺያን) አይገቡ ገብተዉ እምነት ነክ ክዋኔዎችን ከመፈትፈት ዕቅብ መሆናቸዉ ፤ የሰብዕናቸዉን ለኬት ያስረገጠ  ቅዱስ ተግባር ነበር ፡፡ እናም ወርቂት ፤ አግቦዉንና አግባቡን እየቅል እየለየች ቃዲ/ዳኞችን ነሺም ለጋሽም ከመሆን ባለፈች ለሕብረተሰቡ በእምነቱ ጉዳይ የለችም ፡፡

ጠንካራ ጀግና የሙስልም መሪ የነበረች፣  ሚዛናዊ ሀቀኛ የወሎ ሡልጣን ነበረች።

ለአከባቢዉና ለሕብረተሰቡ የሚበጅ የሙስሊሞች  ተወካይን ፤ የመሾምና የመሻር ወይም የማስሾሙ ፈንታ የአንጋፋ ከዋክብታን ነበር ፡፡

ሙስሊሙ ህብረተሰብ በግ ሲያርድ ቆዳ አላግባብ ይወስዱ በነበሩት ዳኛዎ(ቃዲዎ)ች ያዘኑት ሼህ ጃዕፈር ፤ ሼህ/ቃዲ ያሲንን ከመንበሩ ለሕዝቡ ሲሉ አወረዱ ፡፡

በዚህ የተበሳጩት ሼህ ያሲን ፤ ለአከባቢዉ ገዥ ሄደዉ አቤት አሉ - እንዲያ መሄድ ሳይኖርባቸዉ በመሄዳቸዉ አንገታቸዉን ሰብረዉ ተመለሱ ፡፡ ዉስጠ-ጉድለታቸዉን ከሼህ ጃዕፈር ጋር ፈትተዉ ግን እልሞታቸዉን አገኙ ፡፡

‹‹ ዳኛ ቃዲ ያሲን 1861 ዓ.ም ያረፉ ፣  ከዛም ያዉ  ወደ ሡልጣን ‹ወርቂት› ሄዶ ‹በሙስሊሙ ላይ የዳኝነቴን ሹመት ነፈገኝ(አወረደኝ)› አላት ።

እርሷም አለች  ‹እንግዲህ  ሼህ ጃዕፈር ወሎ ገራዶ 1778 -1847 እርሱ  አትሆንም ብሎ ካወረደህ የምሰጥህ ሹመት አይኖርም› ብላ መለሰችዉ ፤ በዚኸዉ ሁኔታም ቆይ - ከአባቴ ጋር ነገሩን አስተካክሎ እስኪመለስ ድረስ ፡፡ ›› - ዋቢ 1877 ሚስኪል አዝፈር ገጽ-79 ፤ ሼህ ሙሃመድ ፈቂህ(1816-1814)

የሸዋ ጦርና የወሎ ጦር ግጥምያ
  70 የሸዋ  ጦርና የወሎዋ ንግስት  ወርቂቱ 7ት ጦር ግጥምያ…
የአጣዬ ዋርካ(ኦዳ) ታሪክና 7 ት የወርቅቱ ጦር 70  የመንዝ ጦር ግጥምያ።

  በኤፍራታና ግድም ወረዳ በበርግቢ ቀበሌ ከአጣዬ ከተማ በስተምዕራብ በኩል በ18 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ቱሉ ገበያ አካባቢ ይገኛሉ ፡፡
" ምኒሊክ ከመቅደላ እስር  በ ንግስት ወርቅቱ ድጋፍ  ሲመጣ በወቅቱ የመንዝ አስተዳዳሪ ከነበሩት ከአቶ በዛብህ ጋር የተዋጉት እዚህ ቦታ ላይ መሆኑን ሽማግሌዎች ነገሩን "ነገሩ እንዲህ ነዉ  ምኒሊክ በወሎዋ ባላባት ወ/ሮ ወርቂቱ ለአጃቢነት የሰጧቸዉን ሰባት (7ት) ወታደሮች ይዘዉ በዚህ ዋርካ ስር መሽገዉ እንደ ነበር ይናገራሉ ፡፡
በወቅቱ የአቶ በዛብህ የሸዋ ጦር ሰባ አካባቢ ስለ ነበር የንግስት ወርቂቱን ጦር በማቃለል የሚከተለዉን ስነ ቃል ተናግረዉ ነበር ይባላል፡-
       አንተን አድብኜህ አንተን አጭሼኅ ስላሴ ያዉቃል
       አይጥ ከድመት መች ተረፎ ያዉቃል
ብሎ መንዜው ሽለለውን ያዘ ምኒሊክን ለመያዝ።

የዚህን አጸፋ ለመመለስ የወሎዋ ወርቂቱ ወታደሮች በበኩላቸዉ የሚከተለዉን ብለዋል።
       ዋርካ ድንኳኑ ሸማ ገበታዉ
      የማታ ማታ እኛ ነን ጌታዉ
ብለዉ በመግጠም  ወደ ጦርነቱ እንደገቡና የወሎዋ ወርቂቱ ሰባቱ ጦር  ሰባውን የሸዋ ጦር  ድል እንዳደረጉም ይነገራል፡፡
በመጨረሻም የአቶ በዛብህ ጦር ድል ተደርጎ ወደ መንዝ አፍቀራ ቆላ እንደሸሸና  ድሉ የ ወርቅቱ ወዳጆ ሰባቱ ወታደሮች ከሆነ በኋላ የአካባቢው ህዝብ የወርቂቱን አሸናፊነት የበዛብህን ተሸናፊነት  በስነ ቃል እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል፡፡ 
               አረ እናንተ ሰዎች ሆዳችሁ አይባባ
               ይዋጋ የለም ወይ ሰባት እና ሰባ
በማለት አዚመዋል፡፡
ይህ ዋርካና የቁርቁራ ዛፍ ያለበት ቦታ በአሁኑ ሰአት የቅቤ፣የማር፣የሸንኮራ፣የሙዝ እና የቡና ተራ በመሆን ያገለግላል፡፡

የንግስት ወርቂትና አፄ ቴውድሮስ ውግያ

የወሎዋ ንግስት ወርቂት፣ ከ አፄ ቴውድሮስ ጋ መቅደላ  ላይ ተዋግታለች። አፄ ቴውድሮስ ጎንደር ያስተዳድር  በነበረ ግዜ ፣ንግስት ሡልጣን ወርቂት ደግሞ  ወሎን ታስተዳድር ነበር።

የወርቂት ልጅ  አመዴ አሊ  በአፄ  ቴዎድሮስ ተይዞ ስሰቃይ ነበረ ። እናቱ ወርቂት ለምርኮኛው ምኒልክ ከመቅደላ ለማምለጥ እጇ አለበት ተባብራለች ተብሎ ልጇ አመዴ አሊ በሰንሰለት ታስሮ ሲማቅቅ ከቆዩ በኃላ በአሰቃቂ መልኩ በመቅደላ ገደል  ተገድሏል።

ንግስት ወርቂትም በአንድ ልጃቸው ሞት ከባድ መሪር ሃዘን ገቡ። የወሎ ጦሯን ይዘ ፣ የአፄ ቴውድሮስን ጦር መቅደላ ላይ ተዋጋች፣ ተዋግታም  ድል ተጎናፅፈች።

ሼህ ሁሴን ጅብሪል እንዲህ ብሎ ገጥሞ ነበር። መቅደላ አፋፋ ላይ፣ ጩሃት በረከተ፣ የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ ብሎ  ነበር።

አፄ ቴውድሮስ የተገደለ በንግስት ወርቂት  ጦር ነበረ።
የታሪክ ፀሃፊዎች፣ በግዜው የነበሩት የደብተራ ፀሃፊዎች ስለነበሩ፣ ታሪኩን አውቆ በሴት ተገደለ እንዳይባል እራሱን አጠፋ ብሎ ፅፏል።

ወሎ ሴቱም ወንዱም ጀግና ነበር።

Website:-https://mikysultan.blogspot.com
t.me/Oromographya

#ወሎ #wallo #worseh #mammadoch #ኢትዮጵያ #ethiopia #wollo #worrahimnno



No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...