Translate

Thursday, February 25, 2021

# ADWA# አድዋ

አድዋ......

ለድሉ መገኘት ሕይወታቸውን የሰጡ ሙስሊሞች በእምነታቸው ብቻ  ቀባሪ ሲያጡ የጠላት የኢጣሊያ ወታደሮች ግን በክብር የተቀበሩበት ዘመቻ ነው። 

አድዋና ሙስሊም አርበኞች
 አድዋ ጥሪውን ተቀብለው የተሳትፉት ሁሉ ውጤት ነው ። በሃይማኖቱና በብሄሩ ተለይቶ የቀረ አልነበረም ።

አዎ እውነትን እውነት ማለት ግድ ይላል።
ለሀገሩ ነፃነትና ክብር ከሌሎች ክርስቲያን ወንድሞቹ ጋር ተደጋግፎ ፊት ለፊት የመጣን ጠላት የተፋለመ ሙስሊም ወገንን አስክሬን አንቀብርም(ክርስትያኑ በአንገቱ ማተብ ተለይቶ ሲቀበር) በሚል ለጅብና ለአሞራ መጣሉን ዛሬ ላይ ማመን ግድ ይላል። 

አንዳርጋቸው ፅጌ ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር በሚለው መፅሀፋ ገፅ 38 ሁኔታውን እንደሚከተለው ይገልፀዋል፦

    "     እስከ ዛሬ ስለ አድዋ ድል ሲነገር ደማቸውን አፍስሰው ፣አጥንታቸውን ከስክሰው ነፃነታችንን ለማስጠበቅ የወደቁ ሙስሊም ቀደምቶቻችን ፣በእምነታቸው የተነሳ ቀባሪ እንዳጡ አናውቅም ነበር ። በተለይ በአድዋ ተራሮች ላይ ሌላው ሁሉ ቀባሪ ሲመደብለት ፣ከጅብና ከጥንብ አንሳው የተረፈው የሙስሊም ጀግኖቻችን አጥንት በአድዋ ተራራ ላይ ተበትኖ ቀርቷል ። ."
የመጽሀፉ ምንጭ
 " Raymond Joans The battle of Adwa , Harvard Univerisity Press Massachussetes, 2011 በመጥቀስ ነው ።  መጽሐፉንም በገጽ 291 ላይ በዋቢነት አስቀምጧል ።

 ለድሉ መገኘት ሕይወታቸውን የሰጡ ሙስሊሞች በእምነታቸው ብቻ ቀባሪ ሲያጡ የጠላት የኢጣሊያ ወታደሮች ግን በክብር መቀበራቸውንም ያትታል ።
/Guma Qeerroo/

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...