ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ!!!!
ከትናንት እስከ ዛሬ "ኦነግ ፈጸማቸው" የሚባልልን ክፉ ተግባራትን ከመነሻው ጀምሮ ጥናት ካደረግንባቸው ዋና ዋናዎቹን ለማየት እንሞክር (ትናንትም ሆነ ዛሬ ጥላቻቸው ኦነግን ከመሰለን ተሳስተናል። እነዚህ ሰዎች አሁንም ጀዋር ይገደልልን ሲሉ በቀጥታ ጣታቸውን እየቀሰሩ ያሉት መላው ኦሮሞ ላይ እንጂ አንዱ ጀዋር ላይ አይደለም)
ከመነሻው በሰማንያዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ይህን ሲያራግቡ ከነበሩት አንዱ በእስክንድር ነጋ ይመራ የነበረው መጽሄት እና ጋዜጣ ሲሆን ተግባሩንም ኦነግ ፈጸመ ማለትን ከመግለጽ ይልቅ“ኦሮሞ ጨካኝ ነው” የሚል እድምታ ለመፍጠር የታለመ ነበር፡፡እነዚያ በኦሮሞ ላይ የተለየ ተልእኮ የነበራቸው ድርጅቱ የፈጸመውን ማውራት ይተውና ድርጅቱ ያልፈጸመውን
ወንጀል ይነግሩን ነበር! ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ማለት ይህ ነው፡፡
.
እነዚህ ሰዎች የኦነግን ስም ከሳጥናኤል እሪያዎች በማስተካከል ተቧድነው እንዳሻቸው ክርፋታቸውን ሲያቀረሹ እንደነበሩት ዛሬ ላይ ፈጽሞ እልፍታ አንሰጣቸውም በውሸት የተገነባው ግንባቸውን በራሳቸው ቋንቋ በሀቅ የሚያደባይ ትውልድ ገንብተናል(እድሜ በኦሮሙማ ኮትኩቶ ላሳደጉን አባቶቻችን)
፡
እስከዛሬም ድረስ "ኦነግ አማራን ጨፈጨፈ" በማለት የሀሰት ድሪቷ ቋጥረው የሀሰት ክስን ከሚወሻክቱባቸው ስፍራዎች ጥቂቶቹ በደኖ፣ አርባ ጉጉ፣ ወተር፣ አረካ፣ የመሳሰሉት ሲሆኑ እነዚህ አራቱን እንመልከት እንዲሁም በወቅቱ የመአህድ መስራች የሆኑት ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሀገሪቱን ለሚመራው መንግስት በራሳቸው ፊርማ የቀረበው ባለ 5 ገጽ ደብዳቤ ጭምር በክሱ አንዱም ላይ የኦነግ ስም እንደሌለበት ማረጋገጥ ይቻላል
በቅድሚያ ብዙ ስለ ተባለላት አረካ እንመልከት...
አረካ..
ወገኖቼ ይህች ከተማ የት ነው ያለችው? ኦሮሚያ ውስጥ ነው? ወይስ ሌላ ቦታ?አረካ ማለት እኮ በደቡብ ክልል በወላይታ አውራጃ ከሶዶ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ያለች ከተማ ናት፡፡ ኦነግ እዚያ ድረስ ሄዶ ሀገር አላስተዳደረም፡፡ “አረካ የኦሮሚያ ግዛት ናት” ብሎም አያውቅምኮ፡፡ እናም ጂኦግራፊን በትክክል የሚያውቅ ጋዜጠኛ የአረካውን ግጭትና ጭፍጨፋ ለኦነግ አይሰጥም ነበር፡፡ በተጨማሪም የአረካው
ግጭት አስቂኙ ጉዳይ ኦነግ የሽግግር መንግሥቱን ለቆ ከወጣና በእጁ የነበሩት መሬቶች በሙሉ በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ከወደቁ በኋላ ነው፡፡
.
የአረካው ግጭት በሽግግሩ ዘመን ለነበረው የተወካዮች ምክር ቤት የውይይት አጀንዳ ሆኖ እንደቀረበ ይታወሳል፡፡ በከተማዋ ያለቁት የ31 ሰዎች
ግድያ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተፈጸመ መንግሥቱ በይፋ አምኗል፡፡ መንግሥት ያቀረበው ምክንያት "ሰልፈኞቹ የተገደሉት ቦንብ በመወርወራቸው ሳቢያ
የመከላከያ ሰራዊቱ ራሱን ለመከላከል በወሰደው እርምጃ ነው” የሚል ነው፡፡
በነገራችን ላይ በአረካ የሞቱት የቀድሞ መንግሥት ወታደሮች ነበሩ፡፡ እነዚያ ወታደሮች “የጡረታ መብታችን ይከበርልን” በማለት የተቃውሞ ሰልፍ በማድረጋቸው ነው ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር የተጋጩት እነዚህ ከኦሮሞ አናት የማይወርዱት ጋዜጠኞች ኦነግ ፈጸመው በማለት ከ45 በላይ መጽሀፎች እና ብዛት ባላቸው ሰነዶች ለአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሰጥተዋል፡፡
ቀጠልኩ ሁለተኛዋ "ወተር" ናት
.
ወተር...
ኦነግ አማራን ጨፈጨፈ በማለት የተከሰሰበት አንዱ በሚያዚያ ወር 1984 በወተር ከተማ የተደረገውን ኩነት ነው፡፡
ወተር ላይ በተካሄደ ጭፍጨፋ የሞቱትም በተመሳሳይ መልኩ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተገደሉ የሽግግር መንግሥቱ በወቅቱ አምኗል፡፡
፡
ወገኖቼ በወተር የተገደሉት 230 ሰዎች በሙሉ ኦሮሞዎች እንጂ አንድም አማራ አልነበረበትም፡፡ እነዚያ ሰዎች የተገደሉት የኦነግ ተዋጊ ሀይል በኢህአዴግ
ተገፍቶ ከከተማው በመውጣቱ ኢህአዴግ ከከተማቸው ወጥቶ ኦነግ ወደ ከተማዋ እንዲመለስ በመጠየቃቸው ነው (ወተር ለአንድ ዓመት ያህል በኦነግ ቁጥጥር ስር ነበረች፤ ኦነግ ከከተማዋ ሲወጣ ኢህአዴግ ገብቶባታል፤ ነዋሪዎቹም “እንደ ቀድሞው ጊዜያችን ኦነግ ወደ ከተማዋ ይመለስ” በማለታቸው ነው ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር የተጋጩት)፡፡ ጋዜጦቹ ግን “ኦነግ አማራዎችን ጨፈጨፈ” እያሉ ነበር ሲዘግቡ የነበሩት፡፡
(ከዚህች እልፍ የሚል እውነታ ያለው በማስረጃ ወጣ ብሎ ያቅርብና እንፈርበት)
፡
ቀጠልኩ....
በደኖ
.
በወቅቱ በደኖ ላይ የነበረው ኦነግ ትጥቁን ፈትቶ የቀረውም አፈግፍጎ በነበረበት ሰአት ህወሀት ኦነግ በህዝብ እንዲጠላ የተፈጸመ እና ኦሮምኛ ተናጋሪ የነበረችው የኦህዴድ ትራጀዲ መሆኑን በወቅቱ ከጭፍጨፋው በህይወት የተረፉት ስላሉ አሁንም ምስክርነት እየሰጡ ይገኛሉ ፡፡ በነገራችን ላይ በዚህኛውም እልቂት ከሞቱት 53 ሰዎ መካከል ግማሽ ያህሉ ኦሮሞዎች ነበሩ፡፡
የሌሎቹም ይቀጥላል
(ከዚህች እልፍ የሚል እውነታ ያለው በማስረጃ ወጣ ብሎ ያቅርብና እንፈርበት)
No comments:
Post a Comment