Translate

Sunday, February 7, 2021

# አፄ ቴውድሮስ# ጎንደር ኃውልት

ጎንደር ያለው የአፄ #ቴዎድሮስ ኃውልት ይገርመኛል! አፄው ጎንደር ላይ ከፈጸሙት ጭካኔ አንፃር ከተማዋ ለምን እንደምታገናቸው አይገባኝም! በጎንደር ካደረሱት ጭፍጨፋ የተነሣ ውሾች እንኳ የሰው ሥጋ መብላት ለምደው እንደነበር ተጽፏል። 😱
.
#ፌክኢትዮጵያኒስቱ የሚያንቆላጵሳቸው #ቴዎድሮስ ደም የተጠናወታቸው አረመኔ ገዢ እንደነበሩ ሊያሳይ ከቻለ  እስቲ «ኪነት ያገነነው አፄ» ከተሰኘው መጽሐፍ ካገኘሁት ሁለቱን ልጥቀስ... አፄው ጎንደርን እንዲህ ነበር ያደረጓት👇
.
.
«ክረምቱ ሁሉ ወታደሩ በመከራ ከረመ፤ የሚቃጠልም ሲያቃጥሉ፣ የሚደበደብም ሲደበደብ ከረመ። በዚያው ጊዜ ውሾች ሰው አላሳልፍም እያሉ እንደዱር አውሬ ሁነው ነበር፤ የሰው ሥጋና የከብት ሥጋ ለምደው።» 
.
ሉዊጂ ፉሲላ | ያጤ ቴዎድሮስ ታሪክ | ገጽ 40
.
.
«የጎንደር ሲራራ ነጋዴዎች የሚስቶቻቸውን እና በእጃቸው የሚገኘውን ወርቅ እንዲሰጧቸው አዘዙ። ወርቁን ካሰረከቡ በኋላ እጅና እግራቸውን ታስረው በአንድ ቤት ውስጥ ታጉረው በእሳት እንዲቃጠሉ አደረጉ። በአጠቃላይ ጎንደር ከተማን በእሳት አወደሟት። አፄ ቴዎድሮስን በደማቅ ሁኔታ ለመቀበል ወጥተው የተሠለፉት እንኳን አልቀሩም። ሁሉም ቤቱ እየተዘጋበት በእሳት እንዲቃጠል አድርገው ከተማይቱን አወደሙ። በእሳት በጋየችው ከተማ ፍርስራሽ አመድ ላይ የነገሠው የሙት መንፈስ ብቻ ነበር።» 
.
ፊሊፒ ማርሲዲን፤ ገጽ 313
.
የአካባቢው ኤሊት «ያጎነበሰው ነፍጥ ዘቅዛቂ ሽማግሌ ስድብ ነው» ብሎ ያስነሣ መሆኑን ስታስታውስ ነው የቴዎድሮስ ፍቅር  እና ኃውልት ግራ የሚገባህ! #Ironic ይላል ፈረንጅ ☺️

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...