Translate

Saturday, February 6, 2021

#kuullee-#Kaarruu-ኮለምላማ

 ኮለምላማ፡- ኮለምላማ ማለት “አይነ ኩሌ” ሴት እንደማለት ሲሆን በራያ ቆቦ  አካባቢ በተለያዩ ክብረ በአላት ጊዜ በባህላዊ አለባበስ፣ አጊያጊያጥና የጸጉር አሰራር የተዋበች ሴትን ለማድነቅ የተዘፈነ ዘፈን ነው፡፡ ይህ ባህላዊ ዘፈን በራያ ቆቦ  ከድሮ ጀምሮ ሲዘፈን የነበረና ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣና አሁን ግን በአንጻሩ ዘፈኑ የተመናመነ ሲሆን የዘፈኑ ግጥሞች ግን ወደ ሌላ ግጥሞች እየተሸጋገሩ /እየተዋሀዱ/ ይገኛሉ፡፡ ይህ ዘፈን የሚዜመው በሚከተለው መልኩ ነዉ፡፡

አውጭ                                          ተቀባይ 

ኮለምላማ እንደው ኮለምላማ (2)                                   አሀ

    እንሶሱላ ሙቃ »

    ሎሚ ጨብጣለች »

  ያች የቆቦ ልጅ »

 እሷ ትሆናለች፡፡ »

ጋሪያ ለንጫ ሎሚ 

ጮቢበር እንኮይ አሀ

ያነን እየበላሽ 

ቆቦ አትገቢም ወይ፡፡ »

እሄድ እሄድና

 እላለው እረፉ »

የጥርሷ ውቅራት

 እየታየ ዘርፉ፡፡ »

የራያ ማሽላ 

ውስጣውስጡ መንገድ »

ማን አስለመደብኝ 

ከአንገት በላይ መውደድ፡፡ …እየተባለ በዜማ ይዜማል፡፡


By miky sultan

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...