Translate

Friday, February 26, 2021

#AtseMinilik _Genocide

ሀገሪቱ በአሁኑ ሰአት ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ የአጼዎቹን ስርአት ዳግም ለመመለስ እየተፍገመገሙ ባሉት  ሀይሎች እጅ መግባቷን አንዳች ማስተባበል አይቻልም።

በ21ኛ ክ/ዘ ወደ ሁዋላ ተመልሰው ግዛተ አጼ የናፈቃቸው እና ቢቻላቸውን የአያቶቻቸውን ክፉ ምግባር ለመድገም እየተፍገመገሙ ያሉት ሀይሎች መላው ሀገሪቱን ተቆጣጥረው ያሻቸውን እየፈጸሙ ነው የሚገኙት።

 ምኒሊክን በሚያወድሱ የጠነባ ዲስኩሮች የተሞላውን የመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ስመለከት እኔም ይህ የምኒሊክ እውነተኛ ጎኑን መዘከር አሻኝ....
.
እስቲ ተከታታይ ከማቀርባቸው ውስጥ ትናንት የወላይታ ህዝብ ላይ ምን ፈጸመበት ለሚለው በጥቂቱ....
.
የምኒሊክ ጦር ወደወላይታ ሲዘምት አብሮ የዘመተው ቫንደርሄይም (Vanderheym) ያሰፈረውን የአይን እማኝነት እንመልከት።
.
"ጭፍጨፋው እጅግ ዘግናኝ ነበር። አንድ በብዙ ጦርነቶች ላይ የተሳተፉ ራስ እንደነገሩኝ እንዲ አይነት እልቂት ከዚ በፊት በተሳተፉበት ጦርነት አይተው አያውቁም። ንጉሱን (ምኒሊክን) የሟቾቹ ወላይታዎች ብዛት ስንት እንደሆነ ስጠይቃቸው መረጃውን የእርሳቸው seal holder እንዲነግረኝ አዘዙ። እሱም ከተለያዩ የጦር አለቆች መረጃውን አጠናክሮ የሞቱት እና የተያዙት ብዛት 96,000 እንደሆነ ነገረኝ። በእኔ ግምት ግን ትክክለኛው ቁጥር ወደ 20, 000 ይመስለኛል። "
.
"ሁለት የምኒሊክ ወታደሮች በተገናኙ ጊዜ አንዱ ሌላውን ምን ያህል (ወላይታ) ገደልክ ብሎ ይጠይቀዋል። መላሹም እጅግ የተጋነነ ቁጥር በጠራ ጊዜ ጠያቂው እስቲ ምኒሊክ ይሙት በል ብሎ በመሀላ እንዲያረጋግጥለት ጠየቀው። መላሹም ምኒሊክ ይሙት ብሎ በመማል ቁጥሩን አረጋገጠ"
.
"በደም የሰከሩ የምኒሊክ ወታደሮ የቆረጡዋቸውን የወላይታዎች ብልቶች በጠመንጃቸው ጫፍ ላይ እንደሰኩ ታዩ። እንዲህ እያሉም ይዘምሩ/ይጨፍሩ ነበር። የሰማይ አሞራዎች ሀሴትን አድርጉ ዛሬ የሰውን ስጋ ትበላላቹና"
.
"ሚስቶች እና ልጆች በግፍ የተገደሉ ባሎቻቸውን /አባቶቻቸውን ሬሳ እንዲያዩ ይደረጉ ነበር"
.
"በርካታ ሰዎች በባርነት በግዞት በሚወሰዱበት ሰአት ልጅ የታቀፉ ሴቶች ሰልፉን ሲያንቀራፍፉት ወታደሮቹ ልጁን ከእቅፋቸው ቀምተው ወደ ሜዳ ይጥሉት ነበር"
.
የጨፍጫፊው ምኒሊክ ልጆች ዛሬም " ምኒሊክ ቅዱስ ነው " ሲሉን የሚዳዳቸው ይህን መሰል ነውሩን መደበቅ የመቻል አቅም አይኖራችሁም።.
.

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...