Translate

Sunday, March 7, 2021

#ጀነራል _መርዳሳ _ሌሊሳ

የጅባትና ሜጫ አውራጃ ጀግና 
*****************************
ሜጀር ጀነራል መርዳሳ ሌሊሳ በያኔው ጅባትና ሜጫ አውራጃ በአሁኑ ግዜ ሚዳ ቀኚ በመባል በሚታወቀው ጎሮ ኘመር የተባለ ቆላ ቀበሌ ነሀሴ 23 ቀን 1933 ዓ.ም ተወለዱ። አባታቸው አባ ገዳም ነበሩ። ወደ ትምህርቱ አለም ሲዘልቁ ቄስ ትምህርት ቤት ነው የገቡት። ቀጥለውም ዘመናዊውን ትምህርት አምቦ ከተማ ተከታትለው ሲጨርሱ የወጣቱ መርዳሳ ፍላጎት ሀገርን በውትድርና ማገልገል ሆነ። ወጣቱ መርዳሳ ሌሊሳ የተሰጠውን ፈተና አልፈው በ1953 ዓ.ም የ21ኛውን ኮርስ እጩ መኮንን (ካዴት) በመሆን ሆለታ ጦር ትምህርት ቤት ገቡ። ኮርሱ ታህሳስ 1 ቀን 1953 ዓ.ም ስልጠና ጀምሮ የካቲት 1 ቀን 1954 ዓ.ም በምክትል መቶ አለቃ ማእረግ ተመረቁ። የያኔው ም/መ/አለቃ መርዳሳ ሌሊሳ በ1954 ዓ.ም አየር ወለድ ኮማንዶ ስልጠና ገቡ። የፓራሹት ዝላይና የልዩ ኮማንዶ ስልጠናውን አጠናቀቁ። ታንከኛና ሜካናይዝድ ልዩ ኮማንዶ በእስራኤሎች ሰልጥነዋል። በምስራቅ ጦር ግንባር 14 ዓመታት በሰሜኑ ጦርነት ሶስት ግዜ እየተመደቡ እየተቀየሩ በመጨረሻም የጀግናውና በውጊያ ብቃት ስም ያተረፈው የ18ኛው ተራራ ክፍለ ጦር አዛዥ ሆነው ለረዥም ግዜ ሰርተዋል።18ኛውን ተራራ ክፍለ ጦርና የጀነራል መርዳሳን ስም መለየት አይሞከርም።

ሜጀር ጀነራል መርደሳ ሌሊሳ በሰሜኑ ጦርነት እጅግ ስመጥር ከነበሩት የጦር ጀነራሎች ውስጥ አንዱ ናቸው። ሜጀር ጀነራል መርዳሳ የሌተና ኮሎኔልነትና የብርጋድየር ጀነራልነት ማእረግ ያገኙት በጦር ሜዳ ውስጥ በፈጣን የማእረግ እድገት ሹመት ነው። በውጊያ አመራር ባሳዩትና ባስመሰከሩት ብቃትና ጥበብ የሚመሩት 18ኛው ተራራ ክፍለ ጦር የላቀ የጦር ሜዳ ጀብዱ አርማና ኒሻን ተሸልመዋል። ሜጀር ጀነራሉ በላቀ አመራር ብቃት የየካቲት 66 ኒሻን ተሸላሚ ሆነዋል።

ሜጀር ጀነራል መርዳሳ ብዙ ግዜ በጦር ሜዳ ቆስለዋል። እንደገናም ከሞት ተርፈው የመስራት እድል አግኝተዋል። የኢትዮጵያዊነቴ ትውስታ የሚል የውትድርናን ሕይወት ፈተናና መከራ እንዲሁም ቁርጠኝነት የነበረውንም ችግር አጉልቶ የሚያሳይ መጽሀፍም ደራሲ ናቸው። ዛሬ የሀገር ባለውለታው በጡረታ ላይ ይገኛሉ::

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...