Translate

Sunday, March 7, 2021

#Raayyaa Abbaa Maccaa# ራያ አባ መጫ


ራያ አባ መጫ

ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተዋጊ አዋጊነት እሰከ ሀይማኖት መምህርነት

ራያ አባመጫ አባ ግቤ አባ ሰንጊ.....

የተወለደው በአምስቱ ግቤዎች(ጅማ) ጎማ ጨዋዳ ለቾ በምትባል የገጠር መንደር 1965 ነው። አስር አመት እስኪሞላው በትውልድ መንደሩ በጨዋዳ ለቾ ከዚያም ወደ ጅማ በመሄድ ትምህርቱን ሄርማታ በተባለው የመንግስት ትምህርት ቤት እየተማረ ከንግድ ጋር ትስስር ካለው ቤተሰብ በመውጣቱ ገና በህጻንነት ንግዱንም ከቤተሰብ ጎን በመሆን ማሳለጥ ጀመረ።

1981 በአንድ ወንድሙ አመካይነት ወደ ፊንፍኔ በማምራት ሰንፍላወር ትምህርት ቤት እየተማረ ጎን ለጎን የወንድሙን የንግድ ስራ ያግዘዋል።

የህይወት ኡደት ፊንፍኔ የወሰደችው የ16 አልያ 17 አመቱ ራያ 1983 ላይ የሀገሪቱን ስርአት ብቻ ሳይሆን የእርሱንም ህይወት ልትቀይር ግድ ሆኖ ነበር። ገና ህጻን እያለ በአከባቢው ማህበረሰብ ዘንድ የሚወሳበት ባህሪው ዛሬም አልተለየውም።  ባመነበት ፍንክች የማይል ግና ደግሞ እጅግ አዛኝነቱ።

በወቅቱ መሳሪያ የያዙ እና አፋን ኦሮሞ የሚናገሩ ወታደሮችን ሲመለከት "ለካንስ ለመብቱ የሚታገል ኦሮሞ አለ" ማለት ጀመረ። እርሱም እነሱን መሆን ተመኘ። ግና በዙበት። ወደ የትኛው መሄድ እንዳለበት ማረጋገጥ ነበረበት።

አንዳች ፍርሀት የሚይታይበት ወጣት ለውጡን ወዳመጡት ድርጅቶች ቢሮ በቀጥታ በማምራት ጥያቄ መጠየቅ ጀመረተ
"እንዴት መጣቹ":"ከየት መጣቹ?" አላማቹ ምንድነው?" በማለት ካነጋገራቸው ቦሀላ ከእለታቶች በአንዱ "ሌላ ድርጅትምኮ አለ" ሲሉት የቀረውን የኦሮሞ ድርጅት ለማናገር ወደ ጉለሌ አመራ።
አጋጣሚ ሆኖ  ትንሹን ብስል ወጣት ያናገረው ሰው ለራያ ሞኝ ሆኖ ታየው። ሰውየው እንደተቀመጠ ትንሹን ራያ ጠየቀው
"ራያ ጢቃ (ትንሹ ራያ ማለቱ ነው) የሁለት እጆችህ ተመሳሳይ ጣቶች ቢቆስሉብህ የትኛውን ትታከመዋለህ?  ሲለው
ጩልሌው ራያ መልስ ሰጠ
"ለመታከም መጀመሪያ መቀመጥ ነው ያለብኝ። እኔ ያጣሁት መቀመጫ ነው። መታከምም ያለብኝ ማረፍ ስችል ነው" በማለት ጥሎት ወጣ። ተስፋ ቆርጦ ግቢውን ለቆ እየወጣ ባለበት አንድ dhaባ የተባለ የኢናንጎ ልጅ ተጠግቶት እያጽናናው ወደ አንድ ቢሮ ይዞት ገባ።
እድሜው በሰላሳዎቹ አጋማሽ የሚሆን አንድ ጠይም መልከመልካም ሰው ከሚያነበው መጽሀፍ ቀና በማለት አያቸው። ፊቱ በጺም የተሸፈነ ሲሆን አይኖቹ ውስጥን  የሚያነቡ ያህል ጥልቅ የሆኑ....
ሰውየው ፈገግ እንዳለ በኦሮምኛ
 "ጢቃ" ትንሹ ልጅ ምን ፈልገህ ነው?
 ጃል ነdhi ገመዳን ነበር ያገኘው።
ዛሬም ድረስ ያቺን እለት ሲዘክራት "ጃል ነdhi ማናገር ሳይሆን እራሴን ነበር የነገረኝ፣ በውስጤ ለራሴን ሳብሰለስለው የምለውን ነበር የዘረገፈልኝ። በዛች እለት እውነትን አገኘሁዋት። ለራሴም እንዲህ አልኩት
"ከዛሬ ጀምሮ ኦነግ ነህ" አልኩት።

በቁቤ ለመጻፍ ከአንድ ቀን በላይ አልፈጀበትም።የካድሬ ትምህርት ቤት ገብቶ በመመረቅ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሰራዊት አዛዦች መካከል ስመጥር ከሆኑት አንዱ እና ጥቅምላይ26/1986 ላይ በጠላት ሲከበብ እጁን ላለመስጠት ቦንቡን በራሱ ላይ አፈንድቶ የተሰዋው አበዬ (ጉቱ ጫሊ) ጋር በመሆን ወደ መንዲ አመራ። ከመንዲ መልስ ሀረርጌ ላይ እያለ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ወደ ቻርተር ገባ።
ትንሹ ራያ ለመጀመሪያ ግዜ " እነግ ወደ ቻርተሩ መግባት የለበትም" በማለት አመጸ። አዎ ዛሬ ታጥቋል።
መታጠቅ ብቻም አይደለም በእርሱ ስር ጥይት የጎረሰ መሳሪያ ያነገቱ 136 ወጣቶች አሉ።

ራያ አባመጫ አባ ግቤ አመጸ።
የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች በአጭር ግዜ ውስጥ የራያን ባህሪይ የተረዱ ይመስላሉ። ከአቋሙ ፍንክች እንደማይል ስለተገነዘቡ ራያ አባመጫን ለማለዘብ ሌንጮ ለታ በሂልኮፕተር ወደ ሀረርጌ አመራ።

ከቀናቶች ውይይቶች ቦሀላ ራያ አባመጫ ከሚመራው ሰራዊት ተነጥል እንዲወጣ ከተደረገ ቦሀላ በሀረርጌ የምርጫ አስፈጻሚ እዲሆን መመደቡ ተነገረው። ይህን የተገነዘቡ  አንድ ኦቦ ገመቹ የተባሉ የኦነግ አመራር ትንሹ ራያን አቅፈውት "ወደዛ የምርጫ ጣጣ ወዳለበት ቦታ ፈጽሞ መሄድ የለብህም። አንተ የተፈጠርከው ለአርት ነው። ሰለዚህ ወደ በዴሳ ሂደህ የኦዳ ቡልቱምን ባንድ (ወታደራዊ ኪነት ቡድን) አዛዥ ሆነህ ስራ" የሚል ትእዛዝ ተሰጠው።

ራያ አባመጫ የኦዳ ቡልቱምን ኪነትቡድን በመምራት ላይ እያለ ነበር ኦነግ ከምርጫው ተገፍቶ የወጣው።

በኤርትራ ጊዜያዊ መንግስት እና የአሜሪካ አምባሳደር አሸማጋይነት በሰኔ14 ለሚደረገው ምርጫ በሚል ማዘናግያ የኦነግ ጦር የያዛቸውን ከተሞች በመልቀቅ ወደተዘጋጀላቸው ስምንት ካምፖች እስከ ሰኔ 12 ድረስ ሙሉ በሙሉ እንዲገቡ ተደረገ።
ቀጥሎ የተፈጸመው ዛሬም ድረስ ያልተነገረለት ግፍ ነበር። ባዶ እጁን ወደ ካምፕ በገባው የኦነግ ሀይል ላይ
በእኩለ ለሊት እሳት ነገፈደደባቸው። ምክንያቱን መጠየቂያ አፍታም አልተሰጣቸውም። ለሰላም ባሉ መልሱ በጥይት ላንቃ እንዲሆን....
ወራጅ ወንዝ ቀለሙን ቀይሮ እስኪፈስ ድረስ ተጨፈጨፉበት።
ከዚህ ጭፍጨፋ ከተረፉት መካከል ወደ ካምፕ ያልገቡት የኦዳ ባንድን የሚመሩት ጪብሳ(የወለጋ ተወላጅ) እና ራያ አባ መጫ ሰራዊታቸውን ይዘው ወደ ውግያ ገቡ።
.
ይቀጥላል....
.
በክፍል ሁለት

ጊርኖፍ የተባለውን መትረየስ ዛፍ ላይ ሰቅሎ ሲታኮስ የነበረው እና ራያ አባ መጫን ወደ ሀኪም ቤት ተሸክሞ ሲያመላልስ ስለ ነበረው የጉደሩ ጎበና አመንሲሳ፣
 "በድሬዳዋ እስር ቤት ለስልሳ ሶስት ቀን ጭለማ ውስጥ ለብቻው የታሰረው ራያ አባመጫ ለፍርድ ቤቱ "እባካቹ ቢያንስ የሚያናግረኝ እብድም ቢሆን አብሬው ልታሰር ብቻየን ላብድ ነው" ብሎ በጠየቀ ማግስት መለመላውን የሆነ እና በሰውነቱ ላይ አንዳች ልብስ ያላደረገ  እብድን አምጥተው ከርሱ ጋር የታሰረበትን ታሪክ እንቃኛለን።
በ ጉመ ቄሮ

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...