#የመረዋ_ልጆች
ክፍል አንድ
ከሁለቱ ትላልቅ የኦሮሞ ብሄር ግንዶች አንዱ በሬንቶ ነው። በሬንቶ አምስት የኦሮሞ ዘር ሀረግ ያቀፈ ነው። ከአምስቱ የበሬንቶ ኦሮሞ ልጆች አንዱ ሰፊው የመረዋ በሬንቶ የኦሮሞ ዘር ሀረግ ነው። አንዳንዶች መረዋ ብለው ሲጠሩ አንዳንዶች ደግሞ ሙረዋ በማለት ይጠራሉ። የአጠራር ጉዳይ ነው እንጂ ሁለትም የሚገልፁት ይህንኑ ንዑስ የበሬንቶ ኦሮሞ የዘር ሀረግን ነው። የፌስቡካችን ኢቱ ኦሮሞ ፖስት ገፅ የተለያዩ ቀደምት ጥናቶችንና የመረዋ ኦሮሞ ሙሁር ሽሜግሌዎችን እማኝ አድርገን ስለመረዋ ኦሮሞዎች እንደሚከተለው አስፍረናል።
መረዋ ከአምስቱ የበሬንት ኦሮሞ የዘር ሀረግ #ከጡሙጋ ቀጥሎ ሁለተኛ ልጅ ሲሆን #ከረዩ፣ #ሁምበና ና #ቀሎ በቅደም ተከተል ይከተሉታል። መረዋ አንድ ወለደ። እሱም #ኢቱ ነው። የመረዋ ኢቱ ኦሮሞዎች የሰፈሩበት መሬት #ኦነ_ኢቱ ወይም #ጨርጨር ተብሎ ይታወቃል። የመረዋ ኦሮሞ ዘሮች ከምዕራብ ሀረርጌ ጀምሮ ፈንታሌ መተሃራንና ደቡብ ምስራቅ ወሎን ጨምሮ እስከ ሰሜን ወሎ ራያ ድረስ ሰፍረው የሚገኙ ሰፊ የበሬንቱማ ኦሮሞ ግንድ ናቸው።
በጥንት ዘመን የኢቱ መረዋ ልጆች በሶስት ቤት (Man-Bultii) ይካፈላሉ። እነሱም #የወርሬ ፣ #የገላን ና #የኩረ በመባል ይታወቃሉ። ወርሬ ሰበት ፥ ገላን አምስት ፥ ኩረ አምስት ቤተ ጎሳን ያቀፉ እንደ ነበር የመረዋ ሽማግሌዎች ይናገራሉ። ነገር ግን በታሪካቸው ውስጥ ይህ ጊዜ ላይ ነው የሆነው ተብሎ ሊገለፅ ባልቻለ ወቅት ላይ አንድ ክስተት በሶስቱ የኢቱ መረዋ በተ ጎሳዎች መካከል ተከሰተ ይላሉ። እሱም መጠነኛ የእርስ በርስ አለመግባባት ግጭት ነበር። እናም በውቅቱ ከኢቱ መረዋ ልጆች ስርዓት፣ ባህል፣ ወግ እና ተለምዶ ውጪ የራሱን ቤተ ጎሳን ለማንገስ እንቅስቃሴ አድርገው ነበር ተብለው የሚወሱት #የወርሬ ኢቱ መረዋ ቤተ ጎሳ አባላት እና በተቀሩት የገላንና የኩረ ኢቱ መረዋዎች መካከል ነበር። ይህን ግጭት ለመፍታት የኢቱ መረዋ ልጆች ከሌላ ወገን ዳኝነትን አላሹም ይላሉ ሽማግሌዎቹ። ከኢቱ ልጆች በትውልድ ስድስተኛ የሆነውን #ቃሉን (ወረ ቃሉን) ከኩረ ቤተ ጎሳ ውስጥ በስምምነት ወጥቶ ገለልተኛ በመሆን, ከዋቃ የተሰጠውን ዋዩን ተጠቅሞ እንዲዳኝ በመወሰን ሁሉም ጉባዔ ቁጭ አሉ። እናም ከሰባቱ ቤተ ወርሬ ጎሳ አባላት መካከል ችግር መፍጠሩ ውስጥ እጅ ያሌላቸውን ከወርሬ ቤተ ጎሳ ወጥተው በጨርጨር ኦነ ጎሳ ተሰጥቷቸው ከሌላው ወንድሞቻቸው ጋር ተቀላቅለው እንዲ ኖሩ ተወሰነ። በዚህ መልኩ በቤተ ገላን ስር ተዘዋውሮ ራሳቸውን ችለው በመቆም የራስ ጎዛት (ኦነ) እንዲኖሯቸው የሆኑት #ጋዱላ ናቸው።
ችግር መፍጠሩ ውስጥ በከፊል የነበሩ ና በከፊል ያልነበሩትን የቤተ ወርሬ ጎሳ አባላትን ደግሞ በተሳትፎቸው መጠን በከፊል ችግሩ ውስጥ የነበሩትን ከኦነ ኢቱ ውጪ እንዲ ሄዱ፣ያው ጎሳ ሆነው ችግሩ ውስጥ ያልነበሩትን ደግሞ በሌላ የኢቱ ግሳ ስር እንዲ ጠቃለሉ ወይም ከጥፋተኞቹ ለብቻ ወጥተው ለብቻ ኦና እንዲ ሰጣቸው ሆነ ነበሩ። በዚህ መሰረት ሜታ ና አሮጂ ወርሬ ይጠቀሳሉ። ሙሉ በሙሉንኳን ባይሆን በመጠኑ ከችግር መፍጠሩ ነፃ የነበሩ የሜታ ወርሬ ጎሳ በአፉርገላን ስር ገብተው የኢቱ ማንነትን እንደያዙ እንዲቆዩ ተደረጉ። በችግር መፍጠሩ ውስጥ ድርሻ የነበራቸው የዛው የሜታ ወርሬ ጎሳ አባላት ደግሞ የኢቱ መረዋነት ተገፍፈው ለአፍረን ቀሎው ልጆች ወደ ወረ አላ ተሰድደው አላ ኦሮሞ ሆኑ። እንደዚያው ወደ ምስራቅ እንዲሰደዱ የተደረጉ ጥፋተኛ የአሮጂ ወርሬ ኢቱ ጎሳዎች ከአላ አፍረን ቀሎ ጋር ሲቀላቀሉ የተቀሩት ና ጥፋት ውስጥ አልተሳተፋም የተባሉ አሮጂዎች እዛው ጨርጨር የሰፈራ ግዞት መስርተው ራስን ችለው ከአስሩ የኢቱ መረዋ ጎሳዎች አንድ ሆነው እንዲ ቀጥሉ ተደረግ።
ችግሩን በመፍጠር ዋና ና ግንባር ቀደም የሆኑ የቤተ ወርሬ ጎሳ ከመረዋ ልጆች መሬት እንዲሰደዱ ና የኢቱ ሙረዋነቱን ማንነት በመግፈፍ ሌላ ወገን ፈልገው እንዲያፈሩ ና እንዲቀላቀሉ ተወሰነባቸው። በዚህ ረገድ ወደ ኦቦራ አፍረን ቀሎ ና ወደ ሶማሌ ተጠቃለሉ የሚባሉት #አኪቹ ወርሬ ና ወደ አርሲ ና ሶማሌ ተከፋፍለው ወጡ የሚባሉት #ከረረን ወርሬ ይጠቀሳሉ። ችግሩን በመፍጠር ውስጥም ሆነ ችግሩ እንዲፈታ በሚደረገው ሂደት ውስጥ ብዙም ተሳታፊ ያልሆኑ ና በመሃል ሰፋሪነት የተዋጡትን የቤተ ወርሬ አባል ጎሳን ደግሞ በራባ ዶሪ ውስጥ በሰራዊትነት እንዲያገለግሉ ና የሩቅ ጦርነት በሰፊው እንዲሳተፋ ነገር ግን የኢቱ መረዋነታቸው እንዲቆይላቸው ተደረጉ። በዚህ ረገድ ወደ ሰሚን ኦሮሚያ የዘመቱ ና እዛው የሰፈሩ ዶሪንቦጁ ወርሬ ኢቱ ና ገማ ገልቲ ተብለው በወሎ ውስጥ የሰፈሩ እንደ ሆኑ ሽማግሌዎቻችን ይናገራሉ።
እነዚሁ መሃል ሰፈሩ በመባል ወደ ራባዶሪ እንዲቀላቀሉ ከተደረጉት የተረፉት ደግሞ በሌላ የኢቱ መረዋ ጎሳዎች ስር ደቂቅ ቅርንጫፍ ሆነው (በልበላ ጎሳ) እንዲታቀፉ ወይም በራባዶሪ በተቆጣጠሩት አዲስ መሬት ላይ እንዲ ሰፍሩ ነገር ግን ማንነት ያልተነፈጋቸው ነበሩ። እነዚህ ሊበን። ግማሹ ሰሜን ሲገባ የተቀሩት ግማሾች ደግሞ አፋርገላን ስር ተጠቃለሉ። ኤጃ(ኤጁ) ና ቆቦ ወርሬ ደግሞ ግማሹ ከረዩ ና ሰሜን ሲገቡ የተቀሩት ደሞ በሌላው እንደነ____ና ባዬ ጎሳ ውስጥ ተጠቃለው የባዬ ና የ___(to be filled later) ኢቱ መረዋ ጎሳ ቅርንጫፍ በመሆን ቀሩ።
ከዚህ ወቅት በኋላ ነበር #በኦነ_ኢቱ (በጨርጨር) የሚኖሩ የመረዋ ልጆች በሁለቱ ቤተ ጎሳ ማለትም #በገላን ና #በኩረ ኮንፌዴሬሽን ተጠቃልለው በአስር ዋና ጎሳዎች ታቅፈው የቀሩ መሆኑን ከኢቱ መረዋ ሽማግሌዎች ያገኘነው ታሪካዊ መረጃ ያስረዳል። ከዛ ጊዜ በኋላ መረዋ የበሬንቶ ልጅ እንድ ኢቱን ወለደ። ኢቱም እስር ወለደ ይባላል። አምስቱ የገላን ና አምስቱ የኩረ ኢቱ ቤት ተብለው መጠራት የጀመሩት።
ለማንኛውም አስሩ የኢቱ መረዋ ግሳዎች ከበኩር እስከ ትንሹ በቅደም ተከተል እንደ ሚከተሉት ናቸው። የመጀመሪያዎቹ አምስቶች ሸነን ገላን ሲባሉ የሚቀጥሉት አምስቶች ደግሞ ሸነን ኩራ ይባላሉ።
#10_የኢቱ_መረዋ_ጎሳዎች።
1️⃣. ባቦ
2️⃣. ጋዱላ
3️⃣. አፉርገላን (4 ናቸው)
1)#ኤሌሌ. 2)#ወጫሌ. 3)#ሊበን. ና 4)#ሜታ.
4️⃣. #አልጋዮ [ሰዴን አልጋ] 3 ናቸው።
1)#አልገ. 2)#ሞመጂ. 3)#ጂሌ
5️⃣. ጋሞ
6️⃣. ቃሉ
7️⃣. አዳዮ
8️⃣. ዋዬ
9️⃣. አሮጂ
1️⃣0️⃣. ባዬ
............ #ይቀጥላል።
Ituu Oromoo Post የመረጃ ና የእውቀት ምንጭ ነው። Follow ና Share አድረጉ
No comments:
Post a Comment