Translate

Wednesday, February 2, 2022

#አማራነትና ሰሎሞናዊነት ሲመዘኑ

አማራነትና ሰሎሞናዊነት ሲመዘኑ ~~~~~~~~~~~~~~~~~ አሁን ሀገራችን የተፈጠረው ምስቅልቅል ታሪካዊ ዳራው ከ13ኛው ክ/ዘ የሰሎሞናዊነት የፈጠራ አፈ-ታሪክና ተያይዞ ከተፈጠረው ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው። በወቅቱ ከአክሱም ዘመን ጀምሮ ክርስትናን ወደ ቤተ መንግሥት አስጠግቶ ያላመነውን ሕዝብ መረሸን፡ መመዝበር፡ ማፈናቀልና ልዩ ልዩ የስም ማጥፊያ ስሞችን መለጠፍ በጣም የተለመደ ነበር። በተለይም በኦሪትና ሕገልቡና ተከታይ ቅማንቶች ላይ የተፈጸመው ግፍ በቃል የሚገለፅ አለነበረም። በዚህ ግፍ የተመረሩት የኦሪት እምነት ተከታይ ቅማንቶች ዮዲት ጌዲዮንን አንግሠው የመልሶ ማጥቃት ርምጃ ወስደው አክሱም ላይ ተቀምጦ ሲበጠብጥ የነበረውን ሥርዎ መንግሥት ገርስሳውታል። በዚህም ምክንያት እስከ 13ኛው መቶ ክ/ዘመን ሠላማቸውን አግኝተው ሀገሪቱንም ሠላም አድርገዋታል። ዋና ጠባቸውም በክርስትና ሰበብ ሲገድላቸው ከነበረው ከአክሱሙ የቅማንት ገዢ መድብ ጋር እንጂ ከክርስትና ጋር እንዳልነበር ግልጽ ነው። ከክርስትና ጋር ጠብ ቢኖራቸው ኖሮ ከዛግዊ ሥርዎ መንግሥት ጋር ሲዋጉና ሲገዳደሉ እንደነበር እናይና እንሰማ ነበር። ~~~ የአክሱም ስርዎ መንግሥት ሲገረሰስ ቤተመንግሥቱን ከበው ሲደሰኩሩና ሲተነኩሉ የነበሩ መለካዊያን ካህናት ፈርጥጠው ወደ ሸዋ ቅማንት በመሔድ በጥገኝነት ተቀመጡ። በዚህ ቦታ በነበራቸው ረጅም ቆይታም የሸዋን ቅማንት በእነሱ እሳቤና አመለካከት ሥር እንዲሆንላቸው ትልቅ ሥራ ሰርተው ከጎናቸው አሰለፉት። ለረጅም ዘመናት ሥልጣንን እንዴት አድገው ወደ እጃቸው ማስገባት እንደሚችሉ መንገድ ሲፈልሁ ኖረዋል። በመጨረሻም የግብፅ ኮፕት ቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ቅኝ ገዢዎቻችን ጋር በመገናኘት አንድ ተንኮል ወጠኑ። በወቅቱ የዛግዌ ሥርዎ መንግሥት ነገሥታት "እኛ በራሳችን ጳጳስ ነው መመራትና መባረክ ያለብን፡ ከግብፅ ለሚመጡ ጳጳሳት ግብርና ሥጦታ አንከፍልም። ግብፆች ይሄን የማያደርጉ ከሆነ ደግሞ አባይን እንገድበዋለን" እያሉ ይከራከሩና ተግባራዊ ርምጃዎችን ይወስዱ ስለ ነበር፣ የግብፅ ሃይማኖታዊ ቅኝ ገዢ ደብተራዎች የዛግዌ ሥርዎ መንግሥትን ገልብጠው ለሌላ ተላላኪ ቡድን ማስረከብ ፈለጉ። በዚህ ጊዜ ከሸዋው ደብተራ ተክለሃይማኖት ጋር ይገናኛሉ። የዛግዌን ሥርዎ መንግሥት ገርስሰው መንግሥትን ወደ ሸዋው የደብተራ ቡድን በሚያሸጋግሩበት ሁናቴ ተወያይተው ተስማሙ። ~~~ የግብፅ ሃይማኖታዊ ቅኝ ገዢዎች ክብረ ነገሥት የሚባል የድራማና ተውኔት መፅሃፍ እንዲያዘጋጁ እነ ተክለሃይማኖትና ሞአ እየሱስ ይህን አፈታሪክ በሃይማኖት ስብከት አሥመስለው በህዝቡ ዘንድ ለማስረጽ ተስማሙ። የአፈ ታሪኩ ዋናው ጭብጥ "በኢትዮጵያ መንገሥ ያለበት ትክክለኛው ዘር የሸዋው ዘር ነው። ምንያቱም በፈጣሪ ከተቀባው ከእስራኤላዊው ንጉሥ ሰሎሞን ዘር የሚመዘዘው ይህ የሸዋው የንግሥት ማክዳ ልጅ የቀዳማዊ ምኒልክ ዘር ስለሆነ ነው። የዛግዌ ሥርዎ መንግሥት ከንግሥት ማክዳ ገረድ የተውለዱት አገዎች የመሠረቱት ስለሆነ እግዚአብሔር አልተቀበለውም።" የሚል ነበር። መጽሐፉን ግብፃዊያን በአረብኛ ጽፈው ለነተክለሃይማኖት ሰጧቸው እነ ተክለሃይማኖትም ወደ ግዕዝ አስመልሰው ይህን የፖለቲካ ድስኩር ሃይማኖት አስመስለው በመላው ሃገሪቱ ሰበኩት። እንዲያውም "ጋኔን መሀሮሙ ልሣኖሙ ለሰብአ አገው እስም ሰብአ አገው እኩያን እሙንቱ።" እያሉ አገዎችን ከዲቃላነት ፕሮፓጋንዳ በተጨማሪ "ጋኔኖች ናቸው፡ ቋንቋቸውም የጋኔን ነው" እያሉ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳና መርዝ ረጩ። ለምንድነው የአገው ቋንቋን ጋኔን አስተማረው ያሉት? ምክንያቱም በዛ ጊዜ አዲሱ የወታደሩና የወዲላው ቡድን ቋንቋ አማርኛ ገና ዳዴ እያለ የነበረ ስለሆነና ሕዝቡም ይህን የወዲላ ቋንቋ መናገር ስለማይፈልግ አሸማቀው አማርኛ እንዲናገር ለማድረግ ነው። ቋንቋውን ሲጥልላቸው በቀላሉ የአገውና ቅማንት ማንነቱን አስጥለው "ሰሎሞናዊ ነህ" ይሉታል ማለት ነው። ሕዝቡም ከጋኔንነት ወደ "ጋኔን አሳሪው" ሰሎሞንነት በቀላሉ ይመለሳል ማለት ነው። በዛ ጊዜ የወሎ ህዝብ ቅማንትኛና አገውኛ ተናጋሪ ሕዝብ ነበር። የሸዋው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ቅማንትኛ ተናጋሪ ነበር። የጎንደር ሕዝብ ቅማንትኛ ተናጋሪ ነበር። ጎጃም የዳሞት ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝብ ነበር። ዳሞትኛ ከአሁኑ የአዊኛ ቋንቋ ጋር ተመሳሳይ ነበር። እናም ለአዲሱ ሥርዎ መንግሥት ምሥረታ ያገለግላል ተብሎ የታሰበው ከዛግዌ ወታደሮች መካከል የተገኘው አማርኛ ቋንቋ ነበር። ይሄን በደንብ ለመረዳት የንቡረ እድ ኤርሚያስ ከበደን መጽሐፍ ማንበብ ይጠቅማል። ስለዚህ አማርኛ ለማስፋፋትና አገውኛና ቅማንትኛን በማጥፋት ሕዝቡን ሰሎሞናዊ ለማድረግ "አገው ጋኔን ነው፡ ቋንቋውም የጋኔን ነው" ማለት ነበረባቸው። ~~~ በዚህም ተክለሃይማኖትና ተከታዮቹ ውጤታማ ሆኑ። በ1262 ዓ ም ዋድላ ደላንታ ላይ ንጉሥ ይትባረክን ገድለው የሸዋውን ሰሎሞናዊ ይኩኖ አምላክን አነገሡ። ይሄን የበለጠ ለመገንዘን ገድለ ተክለሃይማኖትን አንብቡት። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሰሎሞናዊነትን በሃይማኖት ሰበብ በህዝቡ ላይ በግድ መጫን ጀመሩ። እምቢ ያለውን ዛሬ ላይ እንደሚያደርጉት በጭካኔና አረመኔነት ይገድሉታል፡ መንደሩና አገሩን በሙሉ ያቃጥሉታል። ፈርቶ እሺ ያለውን ቋንቋውን ያስጥሉታል። አስገድደው ያጠምቁትና "አማራ ሆንክ" ይሉታል። በነገራችን ላይ ያኔ አማራነት የጥሙቃን ሰለሞናዊነት ማንነት ነበር እንጅ ብሔር አልነበረም። የተጠመቀ ሁሉ "አማራ" ይባላ እንጂ የዘር አንድነት የለውም። ከመነሻውም አማራ የሚባል ዘር አልነበረም። አማራ ብሔር ሆኖ መታየት የጀመረው ከ1977ቱ የደርግ የቤትና ሕዝብ ቆጠራ በኋላ ነው። ይልቁንም አማራን ብሔር አድርጎ የራሱ ክልል እንዲኖረው ያደረገው ኢህአዴግ ነው። ሂደቱ ረጅም ጊዜ ቢወስድም አማራነት ብሔር የሆነው በሚገርም መንገድ ነው። ዛሬም ድረስ ኦሮሞዎች የተጠመቀውን ኦሮሞ "አማራ" ነው የሚሉት። እስኪ አስቡት ሙስሊም ብሔር ሲሆን! እንደዛ ነው የሆነው። አማራነትን ወይም ክርስቲያን መሆንን ብሔር እንዲሆን ያገዘው የአማርኛ መፈጠርና ከክርስትናው ጋር አብሮ መስፋፋቱ ነበር። ተጠምቆ አማራ ሲሆን አማርኛን እንዲናገር ግድ ሆነ። ~~~ በዚህ ክስተት ውስጥ የምንረዳው ነገር ሰሎሞናዊነትን በቤት ምልክናው፡ በቤተ መንግስቱና በቤተ ሕዝቡ ዘንድ ለማስረጽና ትክክለኛ አድርጎ ለማሳየት ዋናውን ሚና የተጫዎቹት ክርስትናና አማርኛ ናቸው። ሁለቱም የነባር ዝዝቦችን የቀደመ ትክክለኛ ማንነታቸውን ማስጣያ ናቸው። የአንድን ሕዝብ ማንነት ለመቀየር ባህሉን፡ ሃይማኖቱንና ቋንቋውን መቀየር መሠረታዊ ነው። እናም እነዚህን በሚገባ ተግባር ላይ በማዋል ብዙውን ነባር ሕዝብ ማንነቱን አስጥለው አማራ አደረጉት። ነባር ባህሉን አጥፍተው አዲስ የአማራነት ሰሎሞናዊነት ባህል ፈጠሩለት፡ የቀደመ ሃይማኖቱን አጥፍተው አማራ የሚባል ሃይማኖት ሰጡት፡ ቅማንትኛ፡ አገውኛና ዳሞትኛ ቋንቋውን አጥፍተው አማርኛን ሰጡት። ታዲያ እንዴት አይጠፋ? በትክክለም ቀስ በቀስ ሙልጭ ብሎ ጠፋ። ይሄን የሌሎችን ነባር ባህልና ቋንቋ እያጠፉ አማራ የማድረግ ሂደት በዋናነት የመንግሥትና የቤተክህነት ሰዎች በሚገባ መርተውታል። በየጊዜው ልዩ ልዩ የማፈኛ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ አስኪደውታል። ~~~ ሰሎሞናዊነትም በሉት ማስፈጸሚያዎቹ አማራነት (ክርስትና) እና አማርኛ በራሳቸው የዚህ ቡድን የመጨረሻ ዓላማዎች አይደሉም። እነዚህ ነገሮች ዋና ዓላማውን ለማሳካት የተጠቀሟቸው መንገዶች ናቸው። ዋና ዓላማቸው የሥልጣን የበላይነትን ተቆጣጥሮ ለዘለዓለም በህዝቦች ላይ ነግሦ መኖር ነው። ለዚህ ነው "ንጉሠ ነገሥት እከሌ ሥዩመ እግዚአብሔር ሞአ አንበሳ ዘእም ነገድ ይሁዳ" እያሉ ሲነግሩን የኖሩት። ለዚህ ነው "አማራ ከሌለ ኢትዮጵያ አትኖርም" የሚሉን። ክርስትናው የመንግሥትን ሥርዓት ለመጠበቅ ዋና አፈቃላጤና ወታደር ሆኖ ሲያገለግል ነው የኖረው። አማርኛውም እንዲሁ በዘፈኑ፡ በሽለላው፡ በፉከራ፡ ወዘተ የመንግሥት ወታደው ነው። ሰሎሞንነቱ ደግሞ "ንጉሡ ከዘሎሞን ዘር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በፈጣሪ ቅዱስ ቅባት የተቀባ ነው" ብለን እንድናምን የአእምሮ አጠባ ሥራ ከክርስትናው ጋር ተቀናጅቶ ሰርቷል። ~~~ በዚህ ሂደት የዚህ ቡድን ታሪክ ፀሐፊዎችም ይሄን የተወላገደውን ጠፍቶ የማጥፋት የሰሎሞንነት ታሪክ እውነት ለማስመሰል ያልፃፉልን ኮተት የለም። "ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ" እያሉ ሲተርቱልን ኖሩ። አንድም ቀን ደፍረው ስለ ጥንቱ ትክክለኛ ታሪክ ጽፈውልን አያውቁም። ይልቁንም የቀድሞው እውነተኛ ታሪክ እንዳይወጣ የማዳፈን ሥራ ሲሰሩ ነው የኖሩት። ~~~ ከፍ ሲል እንደገለጽኩት እነዚህ የሥልጣን ጥመኞችና ሥልጣን አመለኮች የኖሩት ለክርስትናው ሳይሆን ለሥልጣናችው ብቻ ነው። ክርስትናን ከአፍ በዘለለ ኑረውበት አያውቁም። ስለቅድስናቸውና ንጹህነታቸው ሲያወሩን እንሰማቸዋለን እንጂ በተግባር የሚታይ ቅድስና የላቸውም። ምክንያቱ ክርስትናን የኖሩት ለምድራዊ ንጉሣዊ ሥልጣን ማስጠበቂያ እንጂ ለሠማያዊው መንግሥት መግቢያ አልነበረም እና ነው። ክርስትና ሥልጣንህን የምታስጠብቅበት አንዱ መንገድ (means) እንጂ መድረሻ (goal) አልነበረም። ሰሎሞንነት ወይም አማራነትም እንዲሁ ነው። አማራነት በራሱ መድረሻ አልነበረም። ሥልጣንን በህዝቦች ላይ ጭነህ በንጉሥነት ዙፋን ላይ ተፈናጠህ ለዘለዓለም ለመኖር የተጠቀሙበት አንዱ መንገድ ነበር። የዛሬውን "አማራን ለማዳን ነው" የሚሉትን ፕሮፓጋንዳ ተውት። አማራን ለማዳን ቅማንትን መግደል ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው። ይሄ የአሁኑ ድርጊታቸው የዓላማና የመንገድ መቀያየር (goal displacement) ነው። ድሮ አማራነት የፖለቲካና የሥልጣን የበላይነትን ለማስጠበቅ ይጠቅም ነበር። ዛሬ ደግሞ አማራነትን ለማስጠበቅ የፖለቲካ፡ የሚዲያና የሥልጣን የበላይነትን እንደ መሳሪያ ወይም መንገድ ይጠቀሙታል። ለዚህ ነው የዓላማ መቀየር ያልኩት። አሁን ላይ ግራ ገብቷቸዋል የምንለውም ለዚህ ነው። ~~~ እነዚህ ሰዎች ለክርስትናው ምንም ግድ አይሰጣቸውም። ጉዳያቸውም አይደለም። በመሠረቱ ራሳችውን ከሰቃልያነ ክርስቶስ አይሁዶች ዘር ጋር ሲያገናኙ አይሁድነታቸውን እንጂ ክርስቲያንነታችውን በፍጹም አያሳይም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ነው የሚለው "ወደ ወገኖቹ መጣ፣ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ሥልጣንን ሰጣቸው። እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከሥጋና ከደማዊ ግብር ወይም ከወንድና ከሴት ፈቃድ አልተወለዱም።" (ዮሐ 1፡ 11-13)። ይሄን የወንጌል ቃል በጭራሽ አያስቡትም። ምክንያቱም ክርስትና ዓላማቸው አይደለምና ነው። ክርስትና አይገዳቸውም የምለውም ለዚህ ነው። ክርስትና ለነሱ እንደ ማጭድ፡ አካፋ፡ መጥረቢያ፡ መኪና፡ ወዘተ መሳሪያ ነው። ሰው ለማምረት ማረሻ እንደሚጠቀመው ሁሉ እነዚህ ሰዎችም በስልጣን ለመኖር ክርስትናን መሳሪያ አድርገው ተጠቀሙበት እንጂ ክርስትናን አያውቁትም። ለዚህ እኮ ነው ንጉሦቻቸው 30 እና 40 ሚስቶችንና እቁባቶችን ሲያገቡ የኖሩት። አይሁዳዊ ናቸዋ። ኦሪታዊ ናቸዋ! እነርሱ ከአይሁዳዊያን ነገሥታቶች ከሥጋና ከደም ግብር ወይም ከወንድና ከሴት (ከሰሎሞንና ማክዳ) ፈቃድ ለመወለድ የፈለጉና እንደተወለዱ አድርገው የተቀበሉ ናቸው። እነርሱ "የአግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ክርስቶስ ስልጣን አልሰጣቸውም። የተወለዱት በመንፈስ ሳይሆን በሥጋ ነውና። በሥጋ ከአይሁድ መወለድ ለክርስቶስም አልጠቀመው። ራሳቸው ወገኖቹ የተባሉት በጭካኔ ሰቀሉት። እነዚህም አይሁድነትን በመንፈስ ተቀብለዋልና የአይሁድ ንጹሃንን የሚገድለው የነብሰ ገዳይነት መንፈስ ተዋርሰዋልና ይሄው በክርስትና ስም ይገድላሉ። ያርዳሉ። ይዘርፋሉ። ይዘፍናሉ። ይፎክራሉ። Website:-https://mikysultan.blogspot.com/ Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU Telegram:- t.me/Oromo_ geography

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...