Translate

Wednesday, February 2, 2022

#አባዬ" የሚለው ቃል የአማርኛነት መሠረት የለውም

"አባዬ" የሚለው ቃል የአማርኛነት መሠረት የለውም ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ይህን ጽሑፍ ለመጻድ ያነሳሳኝ የ3000 ዓመት የድንጋይ ሐውልት ላይ "አባዬ" የሚል የአማርኛ ቃል ተገኘ ተብሎ የተለቀቀው ቪዲዮ ነው። ፎቶውን እንደምትመለከቱት ሀውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍ [አባዬ] የሚል ይመስላል እንጂ [1አበየo] የሚል ነው። ስለዚህ ይመስላል በሚል ካልሆነ በስተቀር ቃል በቃል [አባዬ] አይለም። ስለሆነም ከዚህ ቀጥሎ የማቀርበው ጽሑፍ ሐውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍ [አባዬ] እንደሚል ታስቦ የተፃፈ ነው። ~~~ "አባዬ" አማርኛ ነው ብለህ መደምደም አትችልም። ግእዝ ከመካከለኛው ምስራቅ እንደመጣ ይታወቃል። እናም ከሆን ግእዝ ሊሆን ይችላል ብለህ መገመት ይቻላል። ግእዝም ቢሆን ግን ከየት አገኘው የሚል ጥያቄ ይነሳበታል። ምክንያቱም ግእዝም ቢሆን በአለም ከአሉ ቋንቋዎች መካከል በእድሜ ትንሽ ነው። ተጨፍነህ የመልአክ ቋንቋ ነው ብለህ ካልተቀበልከው በስተቀር ማለቴ ነው። ~~~ በግእዝ [እም] "እናት" ብለን [እምየ] "እናቴ" እንላለን፡ [አባ] "አባት" ብለን [አባየ] "አባቴ" እንላለን። እናም ቃሉ ግእዝ ሊሆን ይችላል ብለን ማሰብ ትክክል ነው። ማረጋገጫ ጥናት ቢያስፈልፈውም። ~~~ [አባዬ] የሚለው ቃል አማርኛ ሊሆን አይችልም። ትላንት የተፈጠረው አማርኛ በምን ተዓምር ነው የ3000 ዓመት የድንጋይ ሐውልት ላይ ሊፃፍ የሚችለው? አማርኛ ከቅማንትኛ ወጥቶ የተወሰኑትን ቃላትና አገብብ ከግእዝ ጋር በማዳቀል የተፈጠረ አዲስ ቋንቋ እንጂ ጥንታዊ ቋንቋ አይደለም። ~~~ ሲጀመር አማርኛ የጽሑፍ ቋንቋ የሆነው በ19ኛው ክ/ዘ ሁለተኛ አጋማሽ በአፄ ቴወድሮስ ነበር። ለዛም በመከራ። ፊደሎቹ ከግእዝ የተዋሱ ነበሩ። እንዲሁም አማርኛ የቋንቋ ውጥንቅጦችን ቀላቅሎ ስለሚጠቀም የሚጠቀማቸው ቃላት ስርዎ ማንነታቸውን ማግኘት በጣም ከባድ ነው። ~~~ አማርኛ [አባት] ብሎ እንዴት ነው [አባዬ] የሚለው? በምን ሒሳብ? ልክ [እናት] ብሎ "እናቴ" ወይም "እናትዬ" እንጂ "እናዬ" እንደማይለው ማለት ነው። እናም አማርኛው ማለት የነበረበት [አባት] ብሎ [አባትዬ] ወይም [አባቴ] እንጂ [አባዬ] አይደለም። ምክንያቱም የቋንቋው ሕግ ስለማይፈቅድለት። አማርኛ እንዲህ ዓይነት ውዥንብርን የሚያስተናግደው ዋናው ምክንያት የብድር ብቻ ቋንቋ ስለሆነ ነው። ~~~ ይሄን ክርክሬን የበለጠ ለማጉላት አንድ ሌላ አማርኛዊ ውዥንብር ላሳያችሁ። አማርኛ ጥሬ ዘር ስሞችን ከዛው ከሚጠቀመው ግስ ነው የሚፈጥረው። ለምሳሌ [ሞተ] ብለን "ሞት"፡ [አፈቀረ] ብለን "ፍቅር"፡ [ዋለ] ብለን "ውሎ"፡ [በላ] ብለን "መብል"፡ [ጻፈ] ብለን "ጽሑፍ" እንላለን። ታዲያ የቋንቋው ሕግ እንዲህ ከሆነ አማርኛ [ገመና] የሚለውን ስም ከየት አመጣው? ከየትኛው የግስ ስርዎ ቃሉ አወጣው? ከየትም አላወጣውም። አማርኛ ]ገመና]ን በቀጥታ ከቅማትኛ ወስዶ ነው ራቁቱን የሚጠቀመው። [ገመና] መሠረቱ ቅማንትኛው ነው። በቅማንትኛ [ገም-] "ወረደ" ከሚለው ግስ [ገምና] "መውረድ"፡ [ገምንታ] "አወራረድ"፡ [ገመና] "ውርደት"፣ ወዘተ የሚሉ ስሞች ይፈጠራሉ። አዎ [ገመና] ማለት "ውርደት" ማለት ነው። አማርኛ እንዲህ አይነት ቃላትን አብዝቶ ያለ ስርዎ ቃል ይጠቀማል። ምክንያቱም አማርኛ የትላንት ፈጠራ ስለሆነ ነው። [አባዬ] የሚለው ቃልም ልክ እንደ [ገመና] አማርኛዊ መሠረት የለውም። በመሆኑም የድንጋይ ላዩ [አባዬ] ከታሪካዊ ዳራና ታሪካዊ መቼት ባሻገር በቋንቋው ኀልወተ ታሪክና ባህርይ አንጻርም አማርኛ ይሆናል ብሎ ማሰብ የሞኝነቶች ሁሉ ሞኝነት ነው። ~~~ ሌላው ንግሥት ማክዳ ወይም የሳባ ግሥት የቅማንት ንግሥት እንደነበረች ታሪክ ይመሰክራል። ስለዚህ ቋንቋው ቅማንትኛ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። ለምን ቢባል በቅማንትኛ [አባ] ማለት "አባት" ማለት ሲሆን [አዬ] ማለት ደግሞ "የኔ"፡ "ሆይ" ማለት ነው። እናም [አባዬ] ማለት "አባቴ"፡ "አባት ሆይ" ማለት ነው። እዚህ ላይ ይህን መረጃ ቅማንት ውስጥ ከሚነገር አንድ የቃል መረጃ ጋር ማገናኘት ይቻላል። "ቅማንቱ መጽሐፉን ጥሎ በልቤ ነው ማድረው ብሎ መጽሐፉን ስለጣለ ነው የጽሑፍ መረጃ የሌለው" የሚል የትውፊት መረጅ አለ። እናም እኒህ የቅማንትን ታሪክ እየዘረፉ ለራሳቸው ሲያድድርጉ የኖሩ ሌቦች "ቅማንት በልቡ ብቻ ነው የሚያድረው" የምትለዋን የፈጠራ ታሪክ ፈጥረዋታል የሚል መደምደሚ ሊያመጣ ይችላል። "ቅማንት ከግብጽ መጣ" የሚለው መሠረተ ቢስ የፈጠራ ድስኩራዊ ወግና "ቅማንት ሕንፃ ሊሰራ የመጣ ባርያ ነው" የሚሉት ሁሉ አሻጥር ናቸው። የቅማንትን ጥንታዊነትና የታሪክ ባለቤትነት ለማጥፋት የሚፈለሰፉ የፈጠራ ታሪኮች ናቸው። ይሄም ታሪክን ዘርፎ የራስ ከማድፈግ ጋር አብሮ የሚሄድ አሻጥር ነው። ያገው ቋንቋ የጋኔን ቋንቋ ነው የሚለውም ከዚሁ ጋር አብሮ የሚሄድ አሻጥር ነው። ~~~ እውነቱን ለመናገር አሁን የግእዝ ፊደል ተብሎ የተዘረፈው ሃብት የቅማንት እንደነበር የበለጠ ጥርጣሬየን አጉልቶታል። እናም "ግእዝ ፊደሉን የወሰደው ከቅማንትኛ ነው" የሚል ንድፈ ሃሳብ (hypothesis) መሥርቶ ቀጣይ ጥናቶችን ማድረግ ግድ ይላል። ብዙ ሰፋፊ ምርምሮችን ማድረግ እንዳለብምን ያሳያል። ቅማንቱ ቅዱስ ያረን ዜማውን ዝም ብሎ ከምድር የፈጠረው አልነበረም። ታሪክ አጥፊዎች እንደሚሉትም ከሰማይ አልወረደም። ቀደም ብሎ አባቶቹ ቅማንት ከመዘናዎች ሲያዜሙት የነበረ ነው። በቅማንት የሕገልቡና አስተምህሮ ውስጥ የነበረውን ዜማ ነው ቋንቋ ቀይሮ የጻፈው። እናም የተሰረቁ የጥንት የቅማንት መጽሐፍት የሆነ ቦታ ሊገኙ እንደሚችሉ ይህ ጥሩ ማስረጃዊ ፍንጭ ይሰጣል። ~~~ በእርግጥም ሀውልቱ 3000 ዓመታት እድሜ ካለው ከቅማንት ቋንቋ አይወጣም። ምክንያቱም አክሱም ላይ ተገኙ የተባሉት የድንጋይ ላይ ጽሑፎች በመጀመሪያ በመጀመሪያ ድምፅ ብቻ የተጻፉ ነበሩ። "አክሱም" ለማለት [አከሰመ] ብለው የተጻፉ ናቸው። ይሄን ከ[አባዬ] ጋር ስታነጻጽረው አይገናኝም። ~~~ ሌላው ደቡብ አረቢያ በአፄ ካሌብ ዘመን በኢትዮጵያ ግዛት ስር ነበር። ታዲያ በዚያ ጊዜ ወደ ቦታው የሄደ ኢትዮጵያዊ ገዢ የድንጋይ ሐውልቱ ላይ አጽፎት ላለመሆኑ አሳማኝ ማስደጃ ማቅረብም ከባድ ነው። ብቻ ብዙ ጥናት ይጠይቃል። እርግጠኛ የምንሆነውን ግን ጽሑፉ ጭራሽ አማርኛ አለመሆኑን ነው። አማርኛ የ750 ዓመት ሙጫቅላ ቋንቋ ነው። አይደለም በድንጋይ ላይ በብራና ላይ የተጻፈ የአማርኛ ቃል ከ19ኛ ክ/ዘ በፊት ማምጣት አይቻልም። Website:-https://mikysultan.blogspot.com/ Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU Telegram:- t.me/Oromo_ geography

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...