Translate

Wednesday, February 2, 2022

#ቡና የ እርኩስ መጠጥ ነው ይላል።

ነብሰ ገዳይነትን ባርኮ ቡናን የሚያወግዝ ግራ ገብ ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ደብተራ ዘኮልኮሌ ወዘዝባዝንኬ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሌለን ኮተት ደርቶ ደርቶ ይፅፍና እራሱ የፃፈውን ድሪቶ ተመልሶ የሃይማኖት ማጣቀሻ መጽሐፍ አድርጎ ያቀርበዋል? ግርም ይለኛል! "ቡና አትጠጡ" ይልህና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አምጣ ስትለው "ዜና ሥላሴና ድርሳነ ማርያም ፅዮን" ይልሃል። ለመሆኑ እነዚህን መጽሐፍት ማን ፃፋቸው? እንደ ማጣቀሻ መጽሐፍ መጠቀምስ ምን ይረባል? ይሄን ስታነሳና ስትወጥረው "ተሃድሶ!" ብሎ ስም አውጥቶልህ በድንጋይ ያስወግርሃል! ~~~ እኔ በግሌ ቡና፡ ጫት፡ ጥምባሆ፡ ወዘተ አልጠቀምም። የማልጠቀመው ግን ሃይማኖቴ ከልክሎኝ ሳይሆን ሐዋርያው "ሁሉ ተሰጠኝ፡ ነገር ግን ሁሉ አይጠቅመኝም" ያለውን የህይወት መመሪያ ተከትየ ነው። ሱስ የሚያስይዙ ነገሮችን ከመጠቀም አለመጠቀም ይሻላልና ነው። ማለትም "ቡና፡ ጫት፡ ጥንባሆ፡ ሀሸሽ፡ ወዘተን ከሌሎች የዕለተ ማክሰኞ ፍጥረቶች ለይቼ ርኩሳን ናቸው" አልልም። "አምላክ የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ መልካም እንደሆነ አየ" ብሎ መጽሐፉ እየመሠከረ እነዚህን እፅዋት ለይቼ "ርኩሳን ናቸው" አልልም። አምላክ ያለ ዓላማ አልፈጠራቸውም። እኛ ከዛ ዓላማ ውጭ ስለምንጠቀማቸው እንጂ። ሰው መቼም አስቼጋሪ ነውና ዛሬ በሳይንሱ ዓለም መድኃኒት ብለን ከምንጠቀማቸው መድኃኒቶ መካከል በውስጣቸ የእባብ መርዝ የሌላቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው። ግን እየገዛን እንውጣለን። ግን አናወግዝም! ~~~ አቅም ቢስ ዘኮልኮሌ ደብተራዊች ወንጌልን ሰብከው ማስተማር ሲያቅታቸው የሽብርና የማስፈራሪያ መጽሐፍትን እየፃፉ ሕዝብ ያሸብራሉ። እንዲህ ዓይነት ድርንቁርና ያሳዝናል። በጥቃቅን ነገሮች ላይ ትልልቅ አጀንዳ እየፈጠሩ ሕዝቡን አደነቆሩት። ከወንጌል አራቁት፣ በእውቀትና ጥበብ ሆኖ የፈጣሪን መንገድ ከመከተል አራቁት። ሰው የሚገድለውን ምዕመን እየባረከና እየቀደሰ ቡና የሚጠጥውን ምስኪን ሲያወግዝ ይውላል! ይሄ ነው ወንጌል? በየመሸታ ቤቱ አልኮል ሲያንቃርር ውሎ እያደረ "ቡና የሚጠጣ የሥላሴ ልጅነት የለውም" ይልሃል። እስኪቱን ቀስሮ እህቶቹን በቡድን እየደፈረ "ቡና የጠጣ 10 ዓመት ደረቅ እንጀራ እየበላ ይፁም" ይልሃል! ይሄን ነው ደብተራ ዘኮልኮሌ የምንለው። አልተገናኝቶም! ~~~ "ቡና በአፈጣጠሩ ርኩስ ነው" ካልክ "ቡናን የፈጠረው ርኩሱ ዲያብሎስ ነው" እያልክ መሆንክን ዕወቅ! የለም "ቡናን ዲያብሎስ ነው የሚጠቀመው" ካልክም አንተ ውስጥ ስንት የሰይጣን መንፈሶች አብረውህ ተወልደው አብረውህ አድገው አንተን እየተጠቀሙህ አይደል እንኳን እፅዋቱን። ሲጀመር የዶቅማ ተቀጥላ እበጠበጥክ ስትጠጣ የኖርክ ጀግና ምነው ቡናን አወገዝጋት? ምናለ መጀመሪያ በሰው ልጆች ላይ በድግምት፡ በሟርትና በመተት ሰይጣን መጫንን አላወገዝክምሳ? ነው ይሄ ጥበብ ነው? ፍስንክቶች! ኤጭ! እንዴት ሰለቻችሁኝ!? ~~~ ቡናን ጠንቋዩ ነው የሚጠቀመው ካልከኝም "ምነው ጠንቋይ እንጀራ ይበላ፡ ውሃስ ይጠጣ የለም? ለምን እነዚህንም አልተውካቸውምሳ?" እልሃለሁ። ያልሆነ ዝብረቃ ውስጥ ገብተህ ከምትዘባርቅ 10ቱን ትዕዛዛትና 5ቱን ቃላተ ወንጌል በደንብ አስተምር! ሰዎች የአምላክ ፍቅር ሱያድርባቸው በውስጣቸው በሚያድረው የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ክፉውንና ደጉን መለየት ይችላሉ። ከዝብረቃ መንገድ ውጡ። ~~~~ አሁን ለኮልኮሌ ደብተራዎች ትልክ መከራ የሆነባቸው ሰው ባልነቃበት በጨለማው ዘመን የደረቷቸው መጽሐፍትን ዛሬም ለማስቀጠል መደናበራቸው ነው። ስህተታቸውን ላለማመንና ይቅርታ ላለማለት ያለፈ ስህተታቸውን የማስቀጠል ትግል ውስጥ ገብተው ይዳክራሉ። ውሸታሞች! ~~~ ደብተራ ዘኮልኮሌ የፃፈውን መፅሃፍ አንብበህ በማይከፈት የድንቁርና ቁልፍ ልብህን ከምትቆልፈው ሳታነብ ብትኖር ይሻላል። የደብተራ ዘኮልኮሌ መጽሐፍትን ከማንነብህ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ተማር፡ ጥሩ ክርስቲያን ሁን! ከክርስቲያናዊ አረመኔነት ውጣ! ያኔ የደብተራው ኮልኮሌ በደንብ ይገባሃል። አምላክህ ከደብተራው ለይተህ ለማየት ሞክር!

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...