Seenaa ilma nuuh "Ham " Abbaa afrikaa qaroomina kush & kana'an የኖህ ልጅ ታሪክ ሃም የአፍሪካ አባት የኩሽ እና ከነዓናዊ ስልጣኔ! For those who want to learn more about the history, culture, way of life, and civilization of the Cushites, visit our website.https://mikysultan.blogspot.com
Translate
Wednesday, February 2, 2022
#ቅድስት፣ ሀገር፣ ኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?
"ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ"
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
ደብተራ ሲያደነዝዝህ "ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ" ይልህና "የስሟ ትርጓሜ ምንድነው?" ስትለው አይጥ የዋጠች ድመት መስሎ ዝም ጭጭ ይላል። አንዳንዴም "በልሳነ ... ግዕዝ... " ይልህና ተወጃብሮ ተወጃብሮ አንተን አወዛግቦህ ላሽ ይላል። ጠበቅ አድርገህ ከያዝከው "ዘወር በል መናፍቅ" ብሎ ይሰድብህና ሊያሸማቅቅህ ይሞክራል።
÷
ቅድስት ሀገር ማለት የለማኝ መፈልፈያ መሆን ነው እንዴ? ልመና የቅድስና መገለጫ ነው እንዴ? ቅድስና ጉስቁልና ነው እንዴ? ቅድስት ሀገር ውስጥ ወንድሙን ወንድሙ ይገድለዋል እንዴ? ምግባር የለሽ ሃይማኖተኛነት የቅድስት ሀገር መገለጫ ይሆናል ወይ? ነው በገድልና በተዓምር ተራራ ያሳከልካቸውን ፖለቲከኞች 6 ክንፍ ተክለህላቸው ታቦት መቅረጽ ነው ቅድስና?
÷
አሁን ያሉት መለካዊያን ለአብይ አህመድ ታቦት መቅረጻቸው ይቀራል ብላችሁ ነው? እነ ቅዱስ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በቅርቡ ታቦት ይቀረጽላቸዋል የሚል ተስፋ አለኝ። ምንያቱም የቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መሪዋ ነው እና! ይደልዎ በከመ ይሠየም ቅዱስ ወይትወሀብ ስድስቱ አክናፍ ለዳንኤል ክብረት እስመ መራሂሃ ውእቱ ለኢትዮጵያ! ሃሃሃሃ!
÷
እነዚህ ደብተራዎች እንዲህ እየፃፉ ነው "ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ" እያሉ ጆሯችን ያበሸቀጡት። በውኑ ኢትዮጵያ ከሌላው ዓለም በተለየ ቅድስት ናት? አሜሪካስ? የሚገርመው የቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሠባኪዎች አብዛኛዎቹ የአሜሪካ ፓስፖርት ያላቸው ናቸው። እናባ ዘነዘና ሁሉ እዛ ማዶ ነው የሚሞሩት።
÷
የቅድስቷ ሀገር ልጆች በአረብ አገራት ተቀጥረው እየማቀቁ ይገኛሉ። ይሄም የቅድስና መገለጫው ሆኖ ይሆን? መሪዎቿ በደብተራዎችና በጠንቋዮች ተከበው በሰው ልጆች ላይ የፈለጉትን እያደረጉ ሕዝባቸውን የሚያዋርዱባት ሀገር ቅድስት ከተባለች እርሷ ነክሳ ያሳደደቻቸውን ልጆቿን ተቀብለው በሠላም የሚያኖሩት ሀገራት ምን ይባሉ? ልጆቿን የምትበላው ደም መጣጯ ሀገር ኢትዮጵያ ቅድስት ከተባለች ኢትዮጵያዊያንን በስደት ተቀብላ የምትንከባከበው ሱዳን ቅድስተ ቅዱሳት መሆን ሲያንሳት አይደል
÷
ለመሆኑ ኢትዮጵያ የምትባለው በደብተራ ተንኮል የጎበጠች ሀገር ቅድስት ናትን? ከአለም ሀገራት የረከሱት ሀገራት እነማን ናቸው? የጅምላ ፅድቅ አለ ወይ? የቅድስና መገለጫወቿ ምን ምን ናቸው?
÷
ደብተራ ያገነናት አገር ለዛም ሰው ሳይሆን ጋራውና ሸንተረሩ ቅዱስ ከሆነ ሰዎችን የሚያከብሩና በመከባበር የሚኖሩባቸው ሀገራት እንዴት የበለጡ ቅዱሳን አይሆኑም?
÷
ደብተራ ጠላውን ተጎንጭቶ በስካር ጆሮው ሲግል፡ አይኑ ሲፈጥ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጥና በግሳቱ አቧራ ተከልሎ ማንበብ ይጀምራል። በረሃ የሚለውን ኢትዮጵያ እያለ ያነበዋል። ትንሽ ቆይቶም ኢትዮጵያ 44 ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሳለች እያለ ያላዝንብሃል። ታዲያ በዚህ ጊዜ ጌታቸው ረዳ በሚዲያ ብቅ ይልና "በመጽሐፍ ቅዱስ በመጠቀስ ቅድስና ካለ ሦሪያ ከ380 በላይ ተጠቅሳለች፡ ግብጽም ከዚያ በላይ" ብሎ ያሳርፍልኛል።
÷
እነዚህ የምላስ እንጂ የተግባር ክርስትናን የማያውቁ ደብተራዎች ኢትዮጵያን ቅድስት ብለው መጥራት የጀመሩት ከነ ይኩኖአምላክና ተክለሃይማኖት በኋላ መሆኑ ታውቋል። ነገሥታቱ በምድር በሚሠሯቸው ተግባራት እንዳይመዘኑ መለኮታዉ ሆነው ያርፋሉ። ደብተራዎችም ይሄን ይለፍፋሉ። ንጉሳቸውንም "ሥዩመ እግዚአብሔር" ይሉትና ማንም እንዳይቀናቀነው ያደርጉታል። "ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ!" በሚል ድንቁርናችን ተቀብለን እንድንገዛ ይሰብኩናል። አንዳንዴም ቅዱስ ዘርዓያዕቆብ፡ ቅዱስ እከሌ ወዘተ እያሉ እንድንሰግድላቸው ይስልሰብኩናል። "ኢይንሰግድ ለአምላከ ነኪር" ስንላቸው ደግሞ ይገድሉናል።
÷
ለመሆኑ ደብተራው ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት ነው እንዲበዛላቸው ሲጥሩ የኖሩት? ይሄን ለማየት ኪንግ ጄምስ ቨርሽን የሚባለውን እንግሊዝና መዝሐፍ ቅዱስ ከእኛው ጋር ለማነፃፀር ሞክሬ ነበር። ብዙውን እነርሱ እንዲመቻቸው እያደረጉ አስተካክለዋል። ለምሳሌ
#1ኛ መዝ. 73፥14 በአማርኛ እንዲህ ይላል፡ "አንተ የዘንዶውን እራስ ቀጠቀጥክ፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።" እንግሊዝኛው ደግሞ "Thou breakest the heads of leviathan in pieces, [and] gavest him [to be] meat to the people inhabiting the wilderness." ታዲያ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ከየት አመጡት። እንግሊዝኛው የሚለው "...በበረሃ ለሚሞሩ ሰዎች ሥጋ እንዲሆናቸው ሰጠሃቸው" ነውና።
÷
#2ኛ መዝ. 71፥9 እንዲህ ይላል፡ "በፊቱ ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፡፡ ጠላቶቹም አፈርን ይልሳሉ።" እንግሊዝኛው ደግሞ እንዲህ ይላል፡ "They that dwell in the wilderness shall bow before him; and his enemies shall lick the dust." ታዲያ ኢትዮጵያ የምትለውን ቃል ከየት አመጧት? "...በበረሃ የሚኖሩት..." የሚለውን ኢትዮጵያ ብሎ መተርጎም ምን ማለት ነው? ኢትዮጵያ በረሃ ነበረች እንዴ?
÷÷
እንግዲህ "ቅድስት ሀገር" የሚሉት ደብተራዎች እንጂ መጽሐፍ አይደለም። ሲጀመር ኢትዮጵያ የሚለውን ሥያሜ ትርጉም ጭራሽ አያውቁትም። በማያውቁት ሀገር ስለሚኖሩ ዝም ብለው ነው የሚቀባዥሩት። ማስረጃ የላቸውም። የተደረተ የተሰረዘ ወግ ነው የሚጠርቁት። እንኳን "ኢትዮጵያ" የሚለውን የመንደራቸውን ስም እንኳ መተርጎም አይችሉም።
÷
ለመሆኑ ነብሰገዳይ እንዴት ብሎ ነው የሀገርን ቅድስና ሊሰብከን የሞክረው? ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ባንዴራው ከሰማይ የወረደ ነው ብሎን ያርፋል።
Website:-https://mikysultan.blogspot.com/
Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU
Telegram:- t.me/Oromo_ geography
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
mootittii saba'a Queen of sheba
"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...
-
#Hiika Maqaa #Gosaa ★******************-****************★ #Baareentuu=Jiraattoota warra bahaa kara aduun bariituun jiraatan jechuudha. #Wal...
-
#Horte # ituu #murawwaa Harargeef Walloof Raayyaa ~ ★Miky Sultan Wallo★ Gosa oromoo keessaa ituu n damee ilmaan bareentumaa yeroo tah...
-
Walloof Hararghee (Kutaa 1ffaa) Jaarraa 16ffaa dura lafa amma Walloo jechuun beekamturra ummanni Oromoo bal’inaan akka jiraachaa ture seenaa...
No comments:
Post a Comment