Translate

Saturday, February 26, 2022

#ራያ ገረብ ኦዳ/# Raya Oda

ገረብ(ሓንስ) ኦዳ የአባቶች ጥላ 🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳 #በራያ አላማጣና አካባቢዋ #ገረብ የሚባል የሽምግልና ስነ-ስርዓት እንዳለ እውቅ ሆኖ እነዚህ አባቶቻችን ለነፍሳቸው ሲሉ ወንድም ከወንድሙ ሲጋጭ አንተ ተው አንተ ተው እያሉ እያስታረቁ እና እያስማሙ ራዮችን አንድ እያደረጉ እያፋቀሩ ለዘመናት ኖረዋል፣ አሉ ይኖራሉም። እነዚህ አባቶች ፈጣሪ በሰጣቸው ለምለም ጥላ ሁነው ሽምግልናቸውን ሲያካሂዱ ቆይተዋል ነገር ግን በዚህ ሰዓት የሚጠለሉበት ቦታ ወድሞና ሌላኛው ደግሞ ወድቆ እየተቸገሩ እንዳሉ እያየን ነው። ለምሳሌ ይሀክል በራያ አላማጣና አካባቢዋ የዕርቅ ስነ-ስርዓት የሚጠቀሙበት ዋናዎቹ #ዓውዪ_ኦዳ እና #ሓንስ_ኦዳ እየተባሉ የሚጠሩ ሁለት አንጋፋ ጥላዎች ሲሆኑ፤ ዓውዪ ኦዳ እየተባለ የሚጠራው ስመ ገናናው የአባቶች ጥላ በቅርብ ዓመታት ወድቆ ከጥቅም ውጪ ሁኗል። ሌላኛው ደግሞ ሓንስ ኦዳ እየተባለ የሚጠራው ለህብረተሰቡ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እየሰጠ የነበረ ሲሆን ከነዚህም ሁሌ አዲስ ዓመት ላይ ማህበረሰባችን ከከተማውና ከገጠሩ አሰባስቦ በፍቅር የሚውልበትና እሸት ጥንቅሹ እየተበላ ባህላዊ የራያ ዘፈኖች እየተዘፈኑ ትግል እየተታገሉ እየተጫወቱ የምያሳልፉበት ቦታ ነው። ሌላኛው ዋነኛው ጥቅሙ ደግሞ ብዙዎች ሲጣሉና ሲጋጩ አባቶች የዕርቅ ስነ-ስርዓት የሚያካሂዱበት ትልቅ የተከበረ ጥላ ነው። ስለዚህ ወገኖች እኔ ይህ ፕሮጀክት ከጀመርኩት የቆየሁ ብሆንም ነገር ግን አሁን ተቀናጅተንና ተጋግዘን ለሰላማችንና አንድነታችን ለቆሙልን የአባቶች ጥላ ብናስከብርላቸው አይበዛባቸውምና ካሁን ብኋላ ላለው ብንተጋገዝ ምን ይመስላችኋል

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...