Translate

Wednesday, March 9, 2022

የወሎ: የጎንደር ቅማንት (ካምኣት ) የጎጃም አገው ኦሮሞ ህዝብ ታሪክ

የወሎ: የጎንደር ቅማንት (ካምኣት ) የጎጃም አገው ኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ~~~~~~~~~~~~~√√√√~~~~~~~~~~~~~ ወሎ የከረዩ አንጋፋ ልጅ ነው : ከረዩ ደግሞ የበሬንቱ የበኩር ልጅ ነው። ወሎ፣ ከሚሴ ፣ ባቲ ፣ ቀርሳ፣ሰንበቴ፣ ደዌ፣ ጃርሳ፣ ኡርጌሳ፣ ወረ ቃሉ፣ ወራ ባቦ፣ ወራ ወረሴህ፣ ወረባያ፣ ወረምኛ፣ ቦረና፣ጭቀታ፣ግምባ፣ለገ አምቦ፣ ጭሮ፣ ቱሉ አውልያ፣ኮምቦልቻ፣ ገርባ፣ ወራ ዋዩ፣ ወራ ገርፋ፣ ወራ ኢሉ፣ ወራ ቆቦ፣ ወራ ራያ፣ ወራ የጁ፣ ወራ ቃሉ፣ጉጉፍቱ፣ሱሉለ፣ ጉባ ላፍቶ፣ጨርጨር፣ወልደያ፣ ሮቢቴ ። በወሎ ስር ሰባት ጎሳዎች አሉ። ወረ ኢሎ፣ ወረ ሂመኖ፣ ወረ ቃሉ፣ ወረ ኖሌ አሊ፣ ለገ ጎራ፣ ለገ ሂዳ እና ወረ ኩዩ ይባላሉ። ጎንደር የኦሮሞ ጎሣ የቦጂያ ብሔረሰብ ግዛት ነበር፡፡አበሲኒያ ቦጂያን ሥም ወደ “ቤጃ” ለዉጣ ጎንዳርን የቤጃ ምድር አለች፡፡ ቀጥላ ቤጃን ምድርን “በጌምድር” አለች፡፡በመጨረሻ በጌምድር ማለቱን ትታ ጎንደር አለች፡፡ጎንደር በቅማንትኛ ጓንግዳር ( በሁለት ወንዞች መካከል አንገረብና ቃሃ) የሚል ትርጉም ሲኖረው በአፋን ኦሮሞ “ከጉንዶ” የመጣ ሥም መሆኑን ታሪክ ይናገራል፡፡ጉንዶ የኦሮሞ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ሰፌድ ማለት ነዉ፡፡ በጎንደር በዘር ተለይቶ ለዘመናት ማንነቱን መሰረት ተደርጎ እየተጮቆነ የሚኖረዉ የኩሽ ዘር የሚባለዉ ቅማንት (ካምኣት )የኦሮሞ ጎሣ ነዉ፡፡አበሲኒያ ካምአትን ወደ “ቅማንት” ለዉጣ አሮሞ መሆኑ እንዳይታወቅ አደረገች፡፡ካም አት ማለት “አንተ የትኛዉ ነህ” ማለት ነዉ፡፡ጎንዳር የኦሮሞ ሀገር እንደ ነበር የሚያረጋግጡ እስከ ዛሬ ድረስ በኦሮሞ ቃል የሚጠሩ በርካታ ስፍራዎች ይገኛሉ፡፡ የቅማንት ህገልቦና እምነትና የሸንጎ ወንበር ስርዓት ከኦሮሞ ዋቄፈና እና የገዳ ስርዓት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ያላቸው ሃይማኖታዊ :ማህበራዊና ፓለቲካዊ አንድ እሴቶች ናቸው ። አገው ኦሮሞ እንጅ አገው አማራ የሚባል በታሪክ የለም አገው ኩሽ ብቻ ሳይሆን ከኦሮሞ ጎሳዎች አንዱ ነው። አገው የሚለው ቃሉ ሃ-ገኡ (Haa ga’u) ከሚል የafaan Oromoo ቃል የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም ይብቃ ማለት ነው። አገው ስሙን ያገኘውም የአገው-ኦሮሞ ማሕበረሰብ ከሌሎች የኦሮሞ ማሕበረሰብ ትንሽ ነጠል ብሎ በመኖሩ ምክንያት ከሌሎች ብሔሮች በተለይም ድንበር ከሚጋራቸው ሌሎች ብሔሮች ጋር ይደርስበት የነበረው የመዋጥ (assimilate) አደጋዎች እንዲበቃ ትግል ሲጀምር የመዋጥ አደጋ ይብቃ (Haa ga’u) ብሎ በመነሳቱ ተቀናቃኞቹ Haa ga’u ዎች ተነሱ ሲሉ በዚያው ከዘመናት ቆይታ የማሕበረሰቡ ስም አገው ሆኖ ቀረ። በጎጃምና ጎንደር በኦሮምኛ ቃል የሚጠሩ አያሌ ቀበሌዎችና ቦታዎች መካከል እኔ የማውቃቸውን ጥቂቶችን እንመልከት:- √ማጫ √ዲማ √ሰቃላ √ቆራቲ √ጃዊ √ቡሬ √ቄሮ √ጂጋ √ባሶ √ጋሌ √ሊባን √ሜታ √ዳሞቴ √ሙጣ/ሞጣ √ቡሬ ዝጉርጉር √ኢለማን ዲንሳ የሚባሉት ስያሜዎች ይገኛሉ። በጎንደር የቅማንት አካባቢዎች በአፋን ኦሮሞ ትርጉም ያላቸው የአካባቢ መጠሪያዎች - ማጫ -እንተላ -አይራ -ብልኮ -ጋላገር -አምቦ በር -ከበጁ -ፎገራ -ደምቢያ -ሮቢት -ወለቃ -ሳቤራ -ሌንጫ -ጉባይ -ደለጉ -መቃ -ኮኪት -ጋባ እናም በጣም በርካታ ስሞች አሉ በደንብ የማላስታውሳቸው ። ባላምባራስ ነጋሽ Negash Qemant

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...