Translate

Saturday, February 26, 2022

#ኦዳ ገራዶ( ዋርካ) #Odaa Gerado

<< የ ኦዳ ገራዶን ታሪክ >> "ኦዳ ገራዶ" አባቶችን ስንጠይቅ የሰጡን ምላሽ >> በዛ የብሄር እና የሃይማኖት እኩልነት ባልነበረበት በአስከፊው የፊውዳል ስርአት ዘመን የወሎ ኦሮሞዎች ላይ ይደርስ የነበረው ስቃይና በደል እጅግ ከፍተኛ ነበር እናም ከዚህ አስከፊ ሁኔታ ራሳቸውን ፣ታሪካቸውን (ማንነታቸውን) ለመጠበቅ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት የ"ገዳ" አይነት ስርአት ነበራቸው ። እናም በዚህ በምታዩት ዋርካ ስር በመሰባሰብ በማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ ፣ ህግ አርቅቀውና አፅድቀው ለማህበረሰቡ አዋጅ ይናገሩበታል፣ ራሳቸውንም ከጠላት እንዴት መከላከል እንዳለባቸው ይመክሩበታል ፣ ያጠፍ ሰዎችን ዳኛ ሰይመው ይቀጡበታል ፣ የተጣሉትም ግለሰቦች በዛፍ ስር ተሰባስበው ያስታርቁበታል ። እንደው በጥቅሉ "ኦዳ ገራዶ" የወሎ ኦሮሞዎች የ "ፖርላማ" መእከል እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል ። ኦዳ ገራዶ የሚገኘውም በወሎ በኦሮሞ ዞን ዋና መዲና በሆነችው ከሚሴ ከ "ሒጅራ" መንደር ከፍ ብሎ ከ "ቀሎ" ቀበሌ ዝቅ ብሎ ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው በዋናው አስፖልት ዳር ነው ።

No comments:

Post a Comment

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...