ጀግና አመዴ ኮላሴ( Amade Kolase) የወሎ ኦሮሞ ወረ ሂማኖ መሪ "ማመዶች" ማነው?
ጎንደርን ተቆጣጥሮ በ ጎንደር የድል አዛን ያስደረገ
አመዴ ሙሐመድ አሊ ጎዳና ባቦ ይባላል።
የጎንደር ፉከረ ቀረርቶ ያስነፈሳት የቆነጠጣት መሪ
★By Miky Sultan Barento★
---------------------------------- -------------------------------------------
የታሪክ ፅሃፊ ብሬሊ(Brelli; ) እንደፃፈው; አመዴ ሙሀመድ አሊ ኮላሴ በስልጣን ላይ ለሃያ አምስት አመታት እንደቆየ ይናገራል።
ልክ እንደ ቀደሞቹ አባቶቹ የግዛት ዘመን፣ የወረ ሂማኖ " ማመዶች" አገዛዝ ተጨማሪ መስፋፋትን ስመለከት አመዴ ኮላሴ ጀግና ንቁ መሪ ነበር ብሏል።
በእሱ ግዛት ውስጥ የነበሩ ሌሎች ወረዳዎችን በማካተት የአባቱ የወሎ መሬት የነበሩት፣ በሰለሞናዊ ተወስዶ የነበሩ ፣ በጀግንነት ዘምቶ ያስመለሰና መልሶ እቅዱን ያጠናቀቀው ጀግና የጦር መሪ አመዴ መሀመድ አሊ ነበረ።
አመዴ የመሰረተው ፖሊሲ እስከ ደቡብ፣ እስከ ዋንቺት እና ጃማ ወንዞች እና ወደ ምዕራብ፣ እስከ አባይ ቤት ድረስ ይዘልቃል። በምስራቅ የገርፋ እና የቃሉ ገዥዎች የበላይ የሆነውን በ እሱ ስር አድርጎ ነበረ፣ ሰሜኑን ዳውንት እና ዳላንታን ።
እ.ኤ.አ. በ1798 የጎንደርን የንጉሠ ነገሥት ዋና ከተማን በሁለት የተለያዩ አጋጣሚዎች በጀግንነት በመያዝ የራሱን እጩ በዙፋን ላይ አስቀምጧል።
ወደ ጎንደር ለሚደረገው ጉዞ ሠራዊቱ በአራት ተከፍሎ ነበር፡
የመጀመርያው በ‹ኢርጎ ብርጌድ› ሥር ሆኖ ከሣይንት፣ አሊ ቤት እና አባይ ቤት ጦር አዛዥ አድርጎ አዘመተ።
ሁለተኛው በ ቢሊ አሊ የሚመራው ከለገ አምቦ ወንዝ፣ ከለገ ጎራ ወንዝ፣ ከኢሉ፣ ከጃማ እና ከቦረና የተውጣጡ ወታደሮችን ያቀፈ ነበር።
ሦስተኛው በቦሩ [ኢድሪስ] ቦሩ የሚመራው ኢንድሪስ ነው ከቃሉ እና ከ ደዌ ሪቄ የነበሩት ጋ አዘመተ።
አራተኛው በማሪዬ ትዕዛዝ ሥር የነበረ ሲሆን ከታሁላዳሬ፣ ከአቢቹ [ባቾ]፣ ከዋዩ፣ ከታያ እና ከባቦ ወታደሮችን ያቀፈና በ አንድነት የዘመተ ነበር።
ስለዚህም "አመዴ ኮላሴ" በጊዜው የነበሩትን ታላላቅ አለቆች ወታደሮችን ሁሉ ማሰባሰብ የቻለና ጀግና የጦር መሪ የነበረ፣ ይህም የእሱን ተጽዕኖ እና ሃይል የሚያሳይ ነበረ።
በአካባቢው ባህል መሰረት አመዴ ወደ ከተማዋ ወደ ጎንደር ስገበ በድል አድራጊነት መግባቱን እና ምናልባትም እምነቱን ለማጠናከር ከጎንደር ግምብ ውስጥ አንዱ ከሆነው የእስልምና ስርአት የፀሎት ጥሪ ( አዛን) አድርጓል።
ተመሳሳይ ወግ አመዴን ፣ ኢማም ባቶ የምባል ንጉስ ፣ በግዳጅ ወደ ክርስትና በ ሰለሞናዊ ንጉስ መሪዎች በመመለሱ አመዴ ያንን ለመመለስ ትግሉን አድርጓል።
Aber; አመዴ ጎንደርን ከጎንደር(ቅማንቶች) የጦር አበጋዞች እና ከማእከላዊ አስተዳደር ጋር በመተባበር ድል እንደ እደረገ ጽፏል።
አመዴ ኮላሴ ልክ እንደ አባቱ በወሎ የእስልምናን አቋም ለማጠናከር ቆርጦ የታገለ መሪ ነበር።
የኢማምነት የዘር ውርስ ሥልጣኑን ሕጋዊ ለማድረግ እና ግልጽ ለማድረግ ከ"መካ" የጽሑፍ ፈቃድ አግኝቷል ተብሎ ይታመናል, እሱ እና ዘሮቻቸው "ኢማም" የሚለውን የክብር ማዕረግ እንዲይዙ ያስችላቸዋል።
ጀግና አመዴ ኮላሴ በ 1803 ከለገ ሂዳ እና ከለገ ጎረ አለቆች ጋር በይላል(ኢላል) በተፈጠረ ግጭት ለማቆም ሲሞክር ሞተ።
Website:-https://mikysultan.blogspot.com/
The Imamate of Warra Himano
Islam and local dynasty in wallo
; Hussen Ahmed) Book
No comments:
Post a Comment