Translate

Saturday, September 5, 2026

ንግስት ወርቂቱ

🌳⚔️ ዋርካው ምስክር ነው! አጣዬ ሰዴን መከና የወሎዋ ንግስት ወርቂቱ 7ቱ ጦረኞች እና የመንዝ 70 ጦር — በሕዝብ ትውስታ የኖረ ታሪካዊ ግጥሚያ 🇪🇹 ━━━━━━━━━━━━━━ 📜 ታሪክ በመጽሐፍ ብቻ አይኖርም… በሕዝብም ትውስታ ይኖራል! ━━━━━━━━━━━━━━ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈው የአካባቢው ሕዝብ ትውስታ ዛሬም ይህን ቦታ ከአንድ የታሪክ ክስተት ጋር ያገናኘዋል። 👴🏾👵🏾 የአካባቢው ሽማግሌዎች ይናገራሉ፦ ምኒሊክ በአፄ ቴዎድሮስ ተማርኮ ወደ ጎንደር ተወስዶ ታስሮ ነበረ። ከመቅደላ እስር ቤት ያስወጣችው የወሎዋ ወርቂት ነበረ ፣ የወሎዋ ባላባት ወ/ሮ ወርቂቱ ለአጃቢነት የሰጧቸውን 7 ወታደሮች ይዘው በዚህ ዋርካ ሰዴን(አጣዬ) ሥር መሽገው ነበር ይባላል። ⚔️ በወቅቱ የመንዝ ጦር ቁጥሩ ከፍ ያለ ስለነበር፣ የወርቂቱን ጦር በማቃለል የተነገረው ስነ-ቃል ዛሬም በሕዝብ ትውስታ ይነገራል፦ «“አንተን አድብኜህ፣ አንተን አጭሼህ፣ ሥላሴ ያውቃል፤ አይጥ ከድመት መች ተረፎ ያውቃል?”» 🔥 ለዚህም የወርቂቱ ወታደሮች የሰጡት አጸፋ በሕዝብ ስነ-ቃል እንዲህ ይታወሳል፦ «🌳 “ዋርካ ድንኳኑ፣ ሸማ ገበታው፤ የማታ ማታ፣ እኛ ነን ጌታው!”» 🏆 ከዚያ በኋላ የወርቂቱ 7ቱ ወታደሮች 70ውን የመንዝ ጦር ድል እንዳደረጉ የአካባቢው ሕዝብ ይናገራል። 🗣️ የዚህን ድል ትውስታ ለማስቀመጥም ሕዝቡ እንዲህ በማለት አዚሟል ይባላል፦ «“አረ እናንተ ሰዎች፣ ሆዳችሁ አይባባ፤ ይዋጋ የለም ወይ ሰባት እና ሰባ?”» 🌿 ዛሬ ይህ ቦታ የገበያ ስፍራ ሆኖ ቢያገለግልም፣ ለአካባቢው ሕዝብ ግን ከዚያ በላይ ነው። ዋርካው የተፈጥሮ ዛፍ ብቻ አይደለም፤ የአያቶች ትውስታ፣ የሽማግሌዎች አስተምህሮ፣ የስነ-ቃል ቅርስ እና የአካባቢው ታሪክ ምልክት ነው። 🌳 https://mikysultan.blogspot.com 🔗 https://t.me/Oromo_geography 📜 የተነገረ ታሪክ ሲጠበቅ፣ ትውስታ ይኖራል። ትውስታ ሲኖር፣ ታሪክ አይጠፋም። 🇪🇹 የሕዝብ ትውስታ — የትውልድ ውርስ! ★ Miky Sultan Barento ★

No comments:

Post a Comment

የራስ አሊ ጀግንነት

🇪🇹⚔️ የየጁ የራስ አሊ ጀግንነት — የጦር ስልት በኢትዮጵያ ጀግና ሰራዊት የየጁ ኦሮሞ ሰራዊት ነበረ። የጎንደርና የሌሎችም አካባቢ ሴቶች በግጥም እየዘፈኑ፦ «“አሊና አሊና አሊና በሞቴ፤ የአማራ ማተብ ሰለቸዉ አን...