Seenaa ilma nuuh "Ham " Abbaa afrikaa qaroomina kush & kana'an የኖህ ልጅ ታሪክ ሃም የአፍሪካ አባት የኩሽ እና ከነዓናዊ ስልጣኔ! For those who want to learn more about the history, culture, way of life, and civilization of the Cushites, visit our website.https://mikysultan.blogspot.com
Translate
Thursday, September 10, 2026
Ras Gugsa Wole
👑⚔️ ራስ ጉግሣ ወሌ ⚔️👑
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🐎 ታናሹ ጉግሣ — የወሎ የየጁ ኦሮሞ ወረ ሼህ ጀግና!
★Miky Sultan Barento★
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#ራስ_ጉግሣ_ወሌ በወረ ሼሆች ታሪክ “ታናሹ ጉግሣ” በመባል ይታወቃሉ።
“ታላቁ ጉግሣ” ደግሞ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል እና የራስ ወሌ ብጡል ቅድመ አያት የሆኑት ራስ ቢትወደድ ጉግሣ መርሶ ናቸው።
🔸 ራስ ወሌ ጉግሳ
የየጁው ባላባት ራስ ወሌ ከበጌምድር፣ የጁ፣ ዋድላና ዳውንት የተውጣጣ ሠራዊታቸውን በመያዝ በአድዋ ጦርነት 7 ሺህ ጦር በመያዝ ተካፍለዋል። በዚህም ታላቅ ጀብዱና አኩሪ ድል አስመዝግበዋል። በግዛትም በጌምድርን፣ ከዚያም ለብዙ ግዚያት የጁን እየተሾሙ በግዛት ወሰን ለብዙ ጊዜ ከወሎው ንጉሥ ከራስ ሚካኤል ጋር ይጣሉ ነበር።
ራስ ወሌ በጀግንነት ስመጥር ከመሆናቸው የተነሳ...
«"ሰባት ደጃዝማች አስር ፊታውራሪ የጠመቁትን፣
የወሌ ፈረስ ጠጣው ብቻውን፤
ወሌ በቡሎ ዘሎ ሲወጣ፣
ይመስላል ሐምሌ ክረምት የመጣ፤
ወሌ ወሌ ወሌ ቢሏችሁ፣
የ'ሳቱ ጉማጅ መርጦ አለላችሁ፤
የወሌ ፈረስ ቀጭኑ ቡሎ፣
ዥራቱ አውሳ ግንባሩ ወሎ።"»
.....ተብሎ ተገጥሞላቸዋል።
ራስ ወሌ የንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ባለቤት የነበሩትና በአንቺም ጦርነት ከአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ጋር ተዋግተው ህይወታቸው ያለፈው ራስ ጉግሣ ወሌን፣ የራስ መንገሻ ዮሐንስ ባለቤት የነበሩትን ወይዘሮ ከፈይ ወሌን፣ እና ደጃዝማች አመዴ ወሌን ወልደዋል።
👑 ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል መርሶ ባሬንቶ
▼ የራስ ወሌ ብጡል (አባ ጠጣው) ልጅ
▼ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድም ልጅ
▼ የራስ ናደው አባወሎ ባለቤት
▼ የራስ መንገሻ ዮሐንስ ባለቤት
▼ የእቴጌ ተዋበች አሊና እቴጌ ጥሩወርቅ ዉቤ የቅርብ ዘመድ...
📜 አለቃ ተክለየሱስ እና አለቃ ገብረ እግዚአብሔር እንደጻፉት፣ ራስ ቢትወደድ ጉግሣ መርሶ ደብረ ታቦርን ቆርቁረው የአስተዳደር ከተማ አድርገዋታል።
👑 ታላቁ ጉግሣ አራት ነገሥታትን በመሾምና በመሻር ለ28 ዓመታት በዘመነ መሳፍንት የኢትዮጵያን ፖለቲካ በተፅዕኖ ውስጥ አድርገው ነበር ይባላል።
⛪ እንዲሁም ታዋቂውን ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የተከሉትም ታላቁ ጉግሣ መርሶ እንደሆኑ በታሪካዊ ትውፊት ይጠቀሳሉ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
👑 ታናሹ ጉግሣና እቴጌ ዘውዲቱ
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#ታናሹ_ጉግሣ የራስ ወሌ ብጡል ልጅ ናቸው።
ራስ ጉግሣ የንግሥት ዘውዲቱ ምኒልክ ባል ነበሩ። በኋላም በፖለቲካዊ ሁኔታዎች ምክንያት ከሚስታቸው ጋር በሰላሌ ይኖሩ ነበር።
⚔️ የሸዋ መኳንንት በልጅ ኢያሱ ላይ ያደረጉትን የ1916 ዓ.ም. የሥልጣን ለውጥ ተከትሎ፣ ንግሥት ዘውዲቱ ንግሥት ሆነች፤ ተፈሪ መኮንንም አልጋ ወራሽ ሆኑ።
ይህንን የፖለቲካ ለውጥ ለማስቻል ዘውዲቱ ከሚወዱት ባሏ ራስ ጉግሣ ወሌ እንድትለያይ ተደረገ።
💔 እሷም “ከአባቶቼ ትዕዛዝ አልወጣም” በማለት ሳትፈልግ ከባሏ ተለያየች የሚል ትውፊት አለ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🏇 ከአማራ ሳይንት እስከ በጌምድር
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ራስ ጉግሣ የተፈጠረባቸውን ስሜት ቋጥረው የአማራ ሳይንት ገዥ ሆነው ተሾሙ።
ብዙም ሳይቆይ የበጌምድር ገዥ የነበሩት ንጉሥ ወልደጊዮርጊስ አቦዬ ሞቱ። በዚህም ራስ ጉግሣ የበጌምድር ገዥ ሆኑ።
⚔️ ከዚያም የሠራዊታቸውን አቅም ማጠናከር ጀመሩ። ወደ ዘመዶቻቸው አገር የጁ በመሄድ ቆራጥ ተዋጊዎችን ሰበሰቡ።
በራያ ወርደውም ከፊታውራሪ ኩቢ፣ ከአባ ጉሽሽና ከፊታውራሪ ይመር መሸሻ ጋር ተመካከሩ፤ ቃልኪዳንም ፈጸሙ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
⚔️ የራስ ጉግሣ አመፅ
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ራስ ጉግሣ አቅማቸውን ካደራጁ በኋላ ወደ ዙፋኑ ላይ የነበረውን የአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ሥልጣን ለመቃወም ክተት አሉ።
ከጎጃሙ ራስ ኃይሉ ተክለ ሃይማኖት እና ከትግሬው ራስ ስዩም መንገሻ ጋርም ተላልከው ተስማሙ ተብሎ ይጻፋል።
🚩 ራስ ጉግሣ ጦራቸውን አደራጅተው ከደብረ ታቦር ወደ ጋይንት አቅጣጫ ገሰገሱ።
በዚህ ወቅት አልጋ ወራሽ ተፈሪ ሁኔታውን አስጊ በማየት የሰሜን አውራጃ ገዥ የነበሩትን ደጃዝማች አያሌው ብሩ ከዳባት ተነስተው በላስታ አቋርጠው ራስ ጉግሣን እንዲገጥሙ አዘዙ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💥 መቄት አንቺም — የመጨረሻው ጦርነት
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
📅 መጋቢት 31 ቀን 1930 ዓ.ም.
በመቄት አንቺም ማርያም አካባቢ የራስ ጉግሣ ጦር ከተለያዩ የመንግሥት ኃይሎች ጋር ተጋጨ።
የላስታው ደጃዝማች ወንደወሠን፣ የሸዋው ጦር፣ የደጃዝማች አያሌው ብሩ ጦር እና የየጁ የደጃዝማች ከበደ ጦር በአንድ ወገን ተሰልፈው ከራስ ጉግሣ ጦር ጋር ተዋጉ።
✈️ አውሮፕላንም በውጊያው ተሳተፈ። የእንግሊዝ አውሮፕላን ለመንግሥት ኃይል ድጋፍ ሰጥቶ በራስ ጉግሣ ሠራዊት ላይ ቦምብ ወረወረ።
በዚህም የራስ ጉግሣ ጦር ተበተነ።
🐎 ራስ ጉግሣ — “አባ ደልድል” በሚል የፈረስ ስም የሚጠሩት — እስከመጨረሻው ተዋግተው፣ ቋና አካባቢ በጥይት ተመትተው ሞቱ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🕯️ የእቴጌ ዘውዲቱ ሞት
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
የራስ ጉግሣን ሞት ዜና አዲስ አበባ ለነበረችው እቴጌ ዘውዲቱ ደረሰ።
እቴጌ ዘውዲቱም ብዙም ሳይቆይ ሚያዝያ 2 ቀን 1930 ዓ.ም. አረፉ።
የጉግሣ ወገን ባለሥልጣናት መካከልም ደጃዝማች ኃይለማርያም ወሌ፣ ፊታውራሪ ሹምዮ ጃሎ እና ሌሎች ተማረኩ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🗣️ የቁጭት አዝማሪ
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ራስ ጉግሣን ለጦርነት ያደፋፈሯቸውና የሚደግፏቸው ብለው ያመኗቸው ራስ ኃይሉ ተክለ ሃይማኖት እና ራስ ስዩም መንገሻ ግን በጦርነቱ ላይ አልተገኙም።
ይህም በራስ ጉግሣ ወገን ታላቅ ቁጭት ፈጠረ።
ከዚያም የእልፍኝ አዝማሪያቸው ቀኝ አዝማች ምስጋናው ለራስ ጉግሣ የተናገረው የሚከተለው አዝማሪ በታሪክ ትውስታ ቀርቷል፦
««“በሴት ጠሩኝ ብለሽ ለምን ይቆጭሻል፣
እንዴት ያለውን ወንድ አንቺም ሰው ገድለሻል፤
በሸዋ በትግሬ መሳበቡ ምነው፣
ጉግሣን የገደለው አያሌው ዘመድ ነው።”»»
🔥⚔️ ራስ ጉግሣ ወሌ — በፖለቲካ ትግል፣ በጦርነት እና በታሪክ ትውስታ የተለየ ስም የተወሰነላቸው የዘመነ መሳፍንት መጨረሻ ዘመን መሪ ናቸው።
https://mikysultan.blogspot.com
🔗 https://t.me/Oromo_geograph
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
★ Miky Sultan Barento ★
📜 ታሪክን እንመርምር፣ ትውስታን እንጠብቅ።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Amade kolase
👑⚔️ ጀግና አመዴ ኮላሴ (Amade Kolase) ⚔️👑 ጎንደርን አሸንፎ የድል አዛን ጥሪ ያስደረገው የወሎ ኦሮሞ ጀግና የወሎ ኦሮሞ ወረ ሂመኖ ማመዶች ሥርወ-መንግሥት መሪ ★ Miky Sultan Barento ★ ━...
-
ጀማሉዲን ሙሀመድ አኒ (አራርሶ ሮውብሶ) https://t.me/Oromo_geography * ــــــــــــــــــــــــــــــــــــ * ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የዒልም ኮኮብና የጅሀዱ ጀግኖ...
-
የባሬንቶ ልጆች እና የሰሜኑወሎናራያ ውልድ ዘር ሀረግ የሰበት ወሎ ጎሳ ኮንፍድሬሽን ታሪክ … ቦረና እና ባሬንቶ ኦሮሞ ትላልቅ ሁለት ልጆች ወይም ጎሳዎች አሉት፣ እነሱም። ቦረነና ባሬንቶ ...
-
®የ ወሎ የዘር ሀረግ☜ አዘጋጅ ፤miky sultan/wollo oromo.********** የካም ልጆች ኩሽ ፣ፋጥነ ከነዓን ናቸዉ፣ ከነዚህ መሃል የወሎ የዘር ሀረግ ከኩሽ ይመዘዛል ኦሮሞ የ ኩሽ ዘር ነው...

No comments:
Post a Comment