Translate

Tuesday, February 15, 2022

#Wollo_#Bati_#Affar_#kushtic_#Bati _#Market

#Wallo Bati Market Affar kushtic people in bati market .by miky sultan-

#Beutifull _#Wallo _#oromo_culture_#Bati

Suuraalee babbareedoo oromoota walloo naannoo qaalluu baatee uffata Aadaaf bareedinna fuulaa.by miky sultan-)

Monday, February 14, 2022

#somali_ girl

የባህል ጌጣጌጥ እና የፀጉር አሠራር ያላት የሶማሌ ልጅ t.me/Oromo_geography

#አፍሪካዊት ሴት

አፍሪካዊት ሴት አርቲስቶች/ሰሪዎች፡- ፓስካል ሴባህ (ቱርክኛ፣ 1823 - 1886) Jean Pascal Sébah (ቱርክኛ፣ 1872 - 1947) ባህል፡ ቱሪክሽ ቦታ፡ ኑቢያ፣ ግብፅ (ቦታ ተፈጠረ) ቀን፡-ወደ 1878 ዓ.ም t.me/Oromo_geography

Sunday, February 13, 2022

#አባ ቦና ማነው?

<አባ ቦና> ማነው? <አባ ቦና> የሚለውን ቃል በሁለት የተለያዩ ታሪኮች ነው የማውቀው የመጀመሪያው በራያ የሚታወቁት የኩቢ አባቦና ስም ነው። . ዓጤ ዮሀንስ በአዋጅ ራያ ላይ ባካሄዱት ዘመቻ በእርሳቸው ግፊት ወደ ክርስትና የተቀየሩትን የአካባቢውን ገዥወች “ለጉዳይ ፈልጌህ ነው ሰውን ሰብስበህ ጠብቀኝ” እያሉ መልእክት በመላላክ እንጎየ ሜዳ ተሰብስቦ የጠበቃቸውን ወደ 3000 የሚጠጋ የራያ ሰው በአንድ ቀን እንደጨፈጨፉ ታሪክ ያወሳል። በወቅቱ አብረው የተገደሉት የሕዝቡ መሪ "ኩቢ አባቦና" በመባል ይታወቃሉ። አትመነው ትግሬን ቢምል ቢገዘት ክርስትና አንስቶ ኩቢን አረዱት የሚል ስንኝ ከኩቢ አባ ቦና ሞት በኋላ የራያ ሰወች ቋጥረዋል፤ ለትውልድ ተላልፎ ዛሬ ድረስ ይነገራል። . ሌላኛው እና እኔ ስያሜውን ለፌስቡክ ስም ለማድረግ መነሻ ምክንያቱ ደግሞ የደጅ አዝማች ገልሞ ጓንጉል የፈረስ ስም ስለሆነ ነው። ትንሽ ማብራሪያ ለመሰጠት ያክል ዛሬ ድረስ ከመርሳ ከተማ ጋር ተያይዞ ስማቸው ጎልቶ የሚታወቀው ሼኹ አባ ጌትየ ወደ 48 በላይ ልጆች ነበራቸው። . ከእነዚህ መካከል ዝነኛና ታዋቂ የነበሩት እና ክርስትናም ተቀብለው የፈረሳቸው እግር የረገጠበትን ሁሉ እንዲገዙ በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በዳግማዊ ዓጤ እያሱ የተሾሙት አባ ሴሩ ጓንጉል (ጓንጉል አበየ) ናቸው። ጓንጉል በፈረስ ስማቸው አባሴሩ በመባል ነው የሚጠሩት። በፈረስ ስም የመጠራትን ባሕል ለኢትዮጵያ ነገሥታት ያወረሱት የወረሴህና የማመዶች ሥርወ መንግስታት መሳፍንቶች ናቸው ተብሎ ይታመናል። . አባሴሩ ጓንጉል የታወቁ ፈረሰኛ እና መልከ መልካም የሚያምሩ ሰው እንደ ነበሩ በትውፊት ሰምተናል። በተለያየ ጊዜ በርካታ ሚስቶችን አግብተው ከ20 በላይ ልጆችን ወልደዋል። ሚስቶቻቸው ከአምባሰል፣ ከላስታ፣ ከራያ፣ ከየጁ ከቃሊምና ሀብሩ ወዘተ አካባቢወች ነበሩ። አባ ሴሩ ጓንጉል አምባሰልን ጨምሮ ዛሬ ሰሜን ወሎ የሚባለውን አካባቢ እስከ ጨጨሆ በር ድረስ የገዙ ናቸው። . ጓንጉል ከራያ ጉራ ወርቄ ያገቧት ሚስታቸው ወይዘሮ ራጂያ ትባል ነበር፣ ከላስታ ያገቧት ደግሞ ወይዘሮ ገለቡ ፋሪስ ትባል ነበር። ወይዘሮ ገለቡ የላስታው ገዥ የራስ ፋሪስ እህት ነች እያሉ የጻፉ ስወች ቢኖሩም፤ እውነታው ግን የራስ ፋሪስ ልጅ ናት የሚለው ነው። ጓንጉል አባሴሩ ክርስትያን ቢሆኑም የታወቁት የሼኹ አባጌትየ ልጅ በመሆናቸው እስላማዊ ልማዶችና ትውፊቶች በቤታቸው የሚስተዋል ነበር፤ አኗኗራቸውም እንደ ሙስሊም ነበር ይባላል። የላስታው የራስ ፋሪስ ልጅ የሆነችው ባለቤታቸው ወይዘሮ ገለቡ የባሏ ቤተሰቦች የሆኑት ሼኾቹ በቤቷ ዱዐ ሲያደርጉ ጥሩ ሙሪድ ነበረችና በደምብ አድርጋ ስለምትካድማቸው በሼኾቹ ተወዳጅ ነበረች። የጉራ ወርቄዋ ባለቤታቸው ወይዘሮ ራጂያ ደግሞ፤ በሼኾቹ ተመራጭም ተወዳጅም አልነበረችም። ታዲያ ሼኾቹ የጓንጉል ዘመዶች አንድ ቀን በዱዐ መሀል ሀድራው ሲግል . ራጂያ ራጂያ ወለደች አህያ አህያ ገለቡሳ ገለቡሳ ወለደች አምበሳ አምበሳ . በማለት ዋሪዳው በሉ ያላቸውን ብለው ገለቡን በቱፍታቸው አዳረሷት አሉ። መቼም የወረሴሆች ታሪክ ከመዐና ጋር የተያያዘ ነውና የሼሆቹ ዱዐ ሰምሮ ከወ/ሮ ገለቡ የተወለዱት የአባ ሴሩ ልጆች እነ ራስ ቢትወደድ ቀዳማይ ዓሊ ጓንጉል፣ እነ ራስ ቢትወደድ ዓሊጋዝ ጓንጉል፣ የልጅ ልጆቿ እነ ራስ ቢትወደድ ጉግሣ መርሶ የጎንደርን ቤተ መንግስት ተቆጣጥረው፣ ከ65 ዓመት በላይ ማዕከላዊ መንግስትን በበላይነት እየመሩ፣ የፈለጉትን እያነገሡ ያልፈለጉትን እያወረዱ አድራጊ ፈጣሪ ሆነው የዚያኔዋን ኢትዮጵያ ገዙ። ከወ/ሮ ራጂያ የተወለዱት እነ ደጃዝማች ወሌ ጓንጉል፣ እነ ደጃዝማች ገልሞ ጓንጉል ገዥነታቸው በአካባቢያቸው የተወሰነ በመሆኑ በየጁ፣ ራያ እና ላስታ ብቻ አልፈው አልገዙም። . በተለይ የአባ ሴሩ ጓንጉል ወራሽ ይሆናል የተባለው የደጃዝማች ወሌ የአምበሳ ደቦል ካላመጣችሁ እያለ ሕዝብ የሚያስቸግር ተንኮለኛ ነበረና መጨረሻው የማያምር ነበር። የደጃማች ወሌ ወንድም የወይዘሮ ራጂያ ልጅ የደጃዝማች ገልሞ ጓንጉል የፈረስ ስሙ አባቦና ይባላል። ደጃዝማች ገልሞ ጓንጉል በተለምዶ በዜና መዋዕልም ጭምር <አባቦና ገልሞ> እየተባለ ነበር የሚጠራው። ቦና በዚህ አገባብ ትርጉሙ <ኩራት> ማለት ነው።

#ዋለልኝ መኮንን ካሳ ኩራሽ ጅማ ማነው?

ዋለልኝ መኮንን ካሳ ኩራሽ ጅማ ማነው? 1. ትውልድና እድገቱ በከፊል ዋለልኝ መኮንን የተወለደው መጋቢት 11 ቀን 1938 ዓ.ም ደቡብ ወሎ ቦረና ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሲሆን የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደሴ ከተማ በሚገኙት ስመ ጥሮቹ ንጉስ ሚካኤልና ወይዘሮ ስህን ትምህርት ቤት ተከታትሏል። የ12ኛ ክፍል ትምህርቱንም ያጠናቀቀው በ 1958 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ስር ይተዳደር በነበርው በልዑል በዕደማርያም ቅድመ ዝግጅት ትምህርት ቤት (Preparatory School) ውስጥ ነበር። በዚህ ትምህርት ቤት ቆይታው በሥነ ፅሁፍ ዝግጅት የላቀ ሚና ተጫውቷል። የክርክር ክበብ ምክትልና ዋና ፕሬዝዳንትም በመሆን አገልግሏል። በዚሁ ክበብ አማካኝነት በተለይም የሥነ አመክኗዊ ውይይት አካሄድን ልቅም አድርጐ እንደተማረ ይነገርለታል። ትምህርት ቤቱ ዋለልኝን ተከራካሪ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ፀሃፊም እንዲሆን ረድቶታል። በሁለት ዓመት ቆይታው የትምህርት ቤቱ የጋዜጣ ረዳት አዘጋጅ በመሆንም አገልግሏል። ዋለልኝ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በ Political Science የትምህርት ክፍል ትምህርቱን ቀጥሏል። ከዚያም በኋላ በ ሕዳር 18, 1961 ዓመተ ምሕረት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በተደረገው የሥነ ጽሁፍ ውድድር ኢትዮጵያውያን ከጣሊያን ወታደር ጋር ያደረጉትን ተጋድሎ፣ መስዋዕትነት፣ ጀግንነት፣ ለአገር ታማኝነትና ፍቅርን የሚያሳይ ሰነ ጽሁፍ ጽፎ ከተወዳዳሪዎቹ ውስጥ የአንደኝነት ማዕረግ በመጐናጽፉ ሽልማት አግኝቷል። በየዓመቱ በሚከበረው የዩኒቨርሲቲው ቀን ላይም በመወዳደር ካሸነፉት ስመጥር ገጣሚዎችና ባለቅኔዎች አንዱ ነበር። .ዋለልኝ መኮንን ካሳ ኩራሽ ጅማ ማነው? ውሎ የከረዩ ልጅ ነው፡፡ የባሬንቱ የልጅ ልጅ፡፡ ከከረዩ ልጆች መካከል ባሶና ዱለቻም ይገኙበታል፡፡ ዱለቻ ውስጥ እነ ሊበን አሉ፡፡ ሰባት ቤት ወሎ፡- ወረ ኢሉ፣ ወረ ሂማኑ፣ ወረ ባቦ፣ ወረ ቃሉ፣ለገ ሂdhaa፣ ለገ ጎራ እና ለገ አምቦ ናቸው፡፡ ከከረዩ ልጆች ወሎን አልፈው ጎንደር ድረስ የሄዱት ሊበኖች ናቸው፡፡ ሊቦ ከመከምን ፡፡ ከመ ከም “Warra Akkam akkam jedhu” “እንዴት እንዴት ነው? የሚሉት” ፡፡ የጃዊ ሽመል የሚባሉትን ሎጋዎችም፡፡ ጎጃም ባሶ ሊበን ወረዳ አለ፡፡ በተሻለ ጥበቡ መጽሀፍ የጎጃም አዛውንቶች “Gojam ጋ* ነው” ይላሉ ሲል ደምድሟል፡፡ ወሎ ያለው ሜታ በደራ በኩል የተሻገረው ቡድን ነው፡፡ ደራ ደግሞ ዋጂቱ ነው፡፡ የበቾ ዋጂቱ ኦሮሞ፡፡ ደራ “አደሬ ዋጂቱ” የሚባል ገበያ አለ፡፡ “አደሬ” ማለት ገበያ ማለት ነው፡፡ ትንሽዬ ገበያ፡፡ እነሱ "ሚዳ ኦረሞ" በማለት የሚጠሩት ዋጂቱዎች ናቸው፡፡ ) . የዋለልኝ አባት የሜታ ኦሮሞ ናቸው፡፡ መኮንን ካሳ ኩራሽ ጅማ፡፡ አስራ ሶስተኛ ትውልዱ “ጭላሎ” ነው፡፡ በእናቱም እንዲሁ “ኛአ”የሚል ስም አለ፡፡ደራሲ አለማየሁ ኀይሌ እስከ 13 ትውልዱ መዝግቧል፡፡ 2. የተማሪዎች ንቅናቄ ላይ የነበረው ተሳትፎ ዋለልኝ መኰንን በዩኒቨርስቲ ቆይታው የኢትዮጵያን አርሶ አደሮችና ላብ አደሮች ነፃ ለማውጣት በ1960ዎቹ ውስጥ በተደረገው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ውስጥ ዓብይ ሚና የተጫወተ ወጣት ነበር። ጥላሁን ግዛው የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ ከተመረጠ በኋላ ባደረገው ከፍተኛ የትግል ተሳትፎ ከባድ ክትትል ይደረግበት ነበር። አፍንጮ በር አካባቢ ታህሳስ 19, 1961 ዓ.ም ጥላሁን ግዛው በጥይት ይመታል። ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ሲፈጠር ዋለልኝ መኰንን አምስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ቤቱ ከጓደኞቹ ጋር ነበር። አንድ ወጣት ወደ ቤት ይመጣና ስለ ጥላሁን ግዛው በጥይት መመታት ይነግራቸዋል። እነሱም በድንጋጤ ተያይዘው ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ይሄዳሉ። ሐኪሞቹ ሕይወቱን ለማትረፍ ሞክረው እንዳልተሳካላቸው ይነግሯቸዋል። በዚህ ወቅት ዋለልኝና ጓደኞቹ የጥላሁንን አስከሬን ከሆስፒታሉ በመውሰድ ዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ በስርዓት ያስቀምጡታል። ከዚያ በኋላ የተቃውሞ ትዕይንትና የቀብሩን ሥርዓት ዝግጅት ያደርጋሉ። ለኮሌጅና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ። የጥላሁን ሞት ትግላቸውን እንደማይገታው፣ ጥላሁን ቢሞት ሽህ ጥላሁኖች እንደሚፈጥሩ በመግለጽ ጽሁፎችን በሕዝብ መሃል ያሰራጫሉ። በዩኒቨርስቲው ውስጥ ያለውን የጥላሁንን አስከሬን ለመውሰድ ወታደሮች በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገባሉ። በዚህ አጋጣሚ ዋለልኝ ከፎቅ ላይ ሆኖ በድምፅ ማጉያ ጥላሁንን የሚቀብሩት የትግል ጓዶቹና ሕይወቱን የከፈለለት ሕዝብ እንጂ ገዳዮቹ መቅበር እንደማይችሉ ይናገራል። የክብር ዘበኛ ወታደሮች በተማሪዎቹ ላይ ተኩስ ከፍተው አበበ በርሔ፣ ስብሃቱ ውብነህ፣ ጀማል ያሲን የተባሉ ሶስት ተማሪዎችን ይገላሉ። በዚያ ሽብር ወቅት ዋለልኝ መኰንን ይተርፋል ያለ ሰው አልነበረም። ነገር ግን ዋለልኝና ጓደኞቹ ኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማሰልጠኛ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይታሰራሉ። ዋለልኝ ከአሁን በፊት በገደብ ስለተለቀቀ እንደገና ወደ ከርቸሌ እስር ቤት ይላካል። ዋለልኝ መኰንን ከእስር ቤት ከተለቀቀ በኋላ ወደ ትምህርቱ እንዳይመለስ ታገደ። 3. የዋለልኝ የብሔረሰቦች ጥያቄ በኢትዮጵያ ፅሁፍ (Walelign On the question of nationalities in Ethiopia) ዋለልኝ መኮንን ይህንን አወዛጋቢና ዝነኛ የሆነ አጭር ፅሁፍ “ታገል” (Struggle) ተብሎ በሚታወቀው የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መፅሄት ላይ ሲያወጣ ገና የ 24 ዓመት ወጣትና በዩኒቨርስቲው ደግሞ የ4ኛ አመት የ (Political Science) ተማሪ ነበር። በዚው ፅሁፉ ውስጥ ዋለልኝ እልል ያለ ማርክሲስት (Marxist) እንደነበረና በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብሎ ያመነው “የብሄረሰቦች ጭቆና” በተባበረ የህዝብ አመፅና (Popular Armed Violence) በሶሻሊስት ፖለቲካዊ ርዮተ-አለም (Socialist Political Ideology) ብቻ ሊፈታ እንደሚችል በግልፅ አስቀምጧል። ብሄራዊ ጭቆናውን ለማስረዳት ኢትዮጵያዊ ማን ነው? የሚል የዜግነት ጉዳይና ኢትዮጵያ ከምን ከምን ነው የተሰራችው ? የሚሉ መሰረታዊ ጥያቄዎችን አንስቷል። "What are the Ethiopian peoples composed of? I stress on the word peoples because sociologically speaking, at this stage, Ethiopia is not really one nation. It is made up of a dozen nationalities with their own languages, ways of dressing, history, social organization and territorial entity. And what else is a nation? It is not made of a people with a particular tongue, particular ways of dressing, particular history, particular social and economic organization? Then, may I conclude that, in Ethiopia, there is the Oromo Nation, the Tigrai Nation, the Amhara Nation, the Gurage Nation, the Sidama Nation, the Wellamo [Wolayta] Nation, the Adere [Harari] Nation, and however much you may not like it, the Somali Nation.” ከዚያም በመቀጠል የመፍትሄ ሃሳቦች ያላቸውን በወቅቱ ሲደረጉ ከነበሩት የፖለቲካ ትግሎች ጋር እያዛማደ ለማስረዳት ይሞክራል። ለምሳሌ ስለ መፈንቅለ መንግስት ያነሳና፤ መፈንቅለ መንግስት ቢካሄድ የታሰበውን ለውጥ እንደማያመጣ ይልቁንም ሃገሪቱን ወደ ባሰ ችግር ውስጥ ሊከታት እንደሚችል ይገልፃል። “Can we do it through military? No!! A military coup is nothing more but a change of personalities.” በመቀጠልም በወቅቱ ይደረጉ ስለነበሩት የጎጃምና የባሌ አመፆች ያነሳና አስፈላጊነታቸውን አምኖና ተቀብሎ ነገር ግን የመጨረሻ ግብ የላቸውም ብሎ ያልፋቸዋል። “Can the Eritrean Liberation Front and the Bale armed struggle achieve our goal? Not with their present aims and set-up. Both these movements are exclusive in character, led by the local Bourgeoisie in the first instance and the local feudal lords in the second.” “. . . The same can be said for the Gojjam uprising.” ሌላው ዋለልኝ በዚው ፅሁፉ ውስጥ ያነሳው፤ በአሁኑ ወቅት በኢፌዴሪ ሕገ-ማንግስት አንቀፅ 39 በግልፅ የተቀመጠዉን “የራስን እድል በራስ የመወሰን ብሎም እስገመገንጠል” የሚለውን ሀረግ ነው። ዋለልኝ ሲገልፀው እንዲህ ይላል፤ “There is nothing wrong with secessionism as such. For that matter secession is much better than nationally oppressive government. I quote Lenin, “…People resort to secession only when national oppression and national antagonisms make joint life absolutely intolerable and hinder any and all economic intercourse. In that case the interests of the freedom of the class struggle will be best served by Secession.” በመጨረሻም ዋለልኝ ፅሁፉን ወደ ማጠቃለሉ ሲመጣ How can we form a genuine egalitarian national-state? a genuine Nationalist Socialist State? ሲል ጥያቄ ያቀርባል። ለጥያቄውም መልስ ሲሰጥ “It is clear that we can achieve this goal only through violence, through revolutionary armed struggle.” ብሎ ይደመድማል። 4. የዋለልኝ ያልተሳካው ያውሮፕላን ጠለፋ ዋለልኝ መኰንን፤ የጥላሁን ግዛውን መገደል ተከትሎ በተነሳው አመፅ ዋና ተሳታፊ ስለነበር ታስሮ ከርሟል። ከዛም በተጨማሪ “የአዋጁ አዋጅ” የሚል አፄ ሀይለስላሴ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ አስመልክቶ የተቃወሙብትን ንግግር የሚያጣጥል ፅሁፍ በመፃፉ ምክንያት የከፍተኛው ፍርድ ቤት አምስት አመት ፈርዶበት ነገር ግን አፄው በሴራ ለማስገደል ባደረጉለት ይቅርታ ከሶስት ወር እስራት በኋላ ከእስር ሊፈታ ችሏል። ዋለልኝ ከእስር ቤት ከተለቀቀ በኋላ የተማሪዎቹ ልሳን የነበረው ታገል መጽሄት ታገደ እሱም እንደዚሁ ከትምህርት ቤቱ ታገደ። ከዚያ በኋላ፤ በወቅቱ የመንገድ ማመላለሻ አስተዳደር ተብሎ ይጠራ በነበረው መንግሥታዊ ድርጅት ሥራ መስራት ጀመረ። በዚሁ ድርጅት ሥራ እየሰራ እያለ ብርሃነ መስቀል ረዳና (የኢሃፓ መስራችና ካዛ አስቀድሞ አውሮፕላን ጠልፎ ከሃገር የወጣ) ሌሎች የትግል ጓዶቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ድርጅት መሥራች ጉባዔ ስብስባ በርሊን ላይ በመጥራታችው ፤ ዋለልኝም በዚህ ስብስባ ላይ ለመገኘት ወሰነ። ወደ ስብሰባው ለመቀላቀል አውሮፕላን ከመጥለፍ ሌላ አማራጭ አልነበረውም። ሕዳር 29, 1965 ዓመተ ምሕረት ከጥዋቱ አንድ ስዓት ተኩል ላይ ከአዲስ አበባ ተነስቶ (በአሥመራ በኩል ወደ አቴንስ ሮም ፓሪስ) ለመሄድ የተነሳውን የበረራ ቁጥር 708 ቦይንግ ጄት አውሮፕላን፣ ዋለልኝ መኰንን፣ ማርታ መብራቱ (በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ተማሪ የነበረች)፣ታደለች ኪዳነ ማርያም (በማስታወቂያ ድርጅቶች ትሰራ የነበረች)፣ አማኑኤል ዮሐንስ (የዩንቨርሲቲ ተማሪ የነበረ)፣ ጌታቸው ሀብቴ (የዩንቨርስቲ ተማሪ የነበረና ከውጭ ሃገር ጋዜጠኞች ጋር ይሰራ የነበረ)፣ ፣ ዮሐንስ ፈቃዱና (የዩንቨርስቲው 4ኛ አመት ተማሪ የነበረ) ተስፉ ቢረጋ (በመድሐኒያለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ያስተምር የነበረ) ሊያስገድዱት ሞክረው ባለመሳካቱ ታደለች ኪዳነ ማርያም ስትተርፍ ዋለልኝ መኰንን እና ሌሎቹ በአውሮፕላን ውስጥ በጸጥታ አስከባሪዎች በተተኮሰ ጥይት አየር ላይ ሕይዎታቸው አለፈ። በመጨረሻም የዋለልኝ መኮንን ቤተሰቦች አባቱን ጨምሮ አስክሬኑን ከምኒልክ ሆስፒታል ተቀብለው ከአዲስ አበባ አገሩ ወሎ ተወስዶ በደሴ ከተማ መድሃኒዓለም ቤተክርስትያን ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት በተወለደ በ27 ዓመቱ በክብር ተቀብሯል።

Saturday, February 12, 2022

#Abay-#አባይ(አባያ) በ #ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድሕን ሮበሌ ቀዌሳ

~~~~~አበያ (አባይ)በሎሬት ፀጋዬ ሮበሌ ቀዌሳ~~~~~ አባይ የማን ነበር? አሁንስ የማነው? ኦሮሞ(የኩሽ ታላቅ ልጅ) እና አባይ የነበራቸው ቁርኝት ምን ይመስል እንደነበር ሎሬት ፀጋዬ ሮበሌ ቀዌሳ በሚገርም መልኩ በብዕሩ ከትቦልን አልፏዋል። 🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 አባይ የምድር አለም ሲሳይ የቅድመ-ጠቢባን አዋይ አባይ የጥቁር ዘር ብስራት የኢትዮጵያ ደም የኩሽ እናት የዓለም ስልጣኔ ምስማክ ከጣና በር እስከ ካርናክ በጡትሽ እቅፍ እንዲላክ ለራህ ለፀሐዩ ግማድ ፥ ለጣህ ለክዋክብት አምላክ ከጥንተ-ፍጡራን ጮራ ፥ የመነጨሽ ከኩሽ አብራክ። አባይ የምድረ-ኩሽ መኩሪያ በቅደመ-ታሪክሽ ጥርጊያ ከደም-ቢያ እስከ ኑ-ቢያ ከሜምፊስ እስከ ሜሮኤ በስልጣኔሽ ትንሳኤ ከዴልታሽ እስከ ዴር-ሡልጣን ከኡመ-ራህ እስከ ኡመ-ዱርማን፤ አባይ የአቴስ የጡቶች ግት ለዓለም የስልጣኔ እምብርት፤ ጥቁር አባይ የጥቁር ምንጭ የካም የስልጣኔ ምንጭ፤ አንቺ የምድረ ዓለም ሲሳይ በረሃውን ጥለሽ ግዳይ ሰሃራን እንዳክርማ ተልም ሰንጥቀሽው በወዝሽ ደም ፥ በጥበብሽ ስርወ-ፋና አንቅተሽ በአንቀልባሽ አዝለሽ ፥ የቅድመ ታሪክን ዝና የራምሴስን አበ-ሲምቦል፥ የመነስን ልዕልና በአልፋ የአልሙጋን ሐውልት፥ የቢያ-ሃንኬን ፍልስፍና በኮማምቦ የሶባቃን፥ በናፖታም የኤዛና ፊላኤ የአቴሰን ምኩራብ፥ በልቅጾር የአሞንን ዜና፤ አባይ ታላቅ ቅድመ-ተስፋ የኪነት ጉባኤ አልፋ፥ ረቂቅ አባይ ያንቺ መገን ምጥቀትሽ አይተንተን፥ የእጅ ማስነሻሽ በረከት ግብርሽ ከአድማሳት ሲክትት መንጣለያሽ ከዕለት ዕለት መሻገሪያሽ ካመት-አመት በመስዋዕት ሲወድቅልሽ በዝማሜ ሲፈስልሽ በመመለክ በመመስገን ጽላትሽ ከዘመን ዘመን በአዝርእት አበቅቴሽ ሲታጠን አቤት አባይ ላንቺ መገን አባይ ረቂቅ የጠቢብ ዘንግ የጨረቃን ጉዞ ፈለግ አስቀምረሽ በጠቢብ ዘንድ በፍሳሽሽ ውጣ ውረድ በሙላት ሚዛን ረገድ የሰማይን ጥርጊያ መንገድ ፥ የጊዜ መለኪያ ሰዓት ፥ ዜኒት ባንቺ ተቀምራ ከቴቤስ እስከ ዳንዳራ ብስራትሽን እንደደመራ ሥልጣኔሽ አንዳበራ፥ የመጽሐፈ-ሙታን ዜና አድርጎሽ ቅድመ-ገናና ዛሬ ወራቱ ራቀና ምድረ-ዓለም ያንቺን አድናቆት ፈለጉን መሻት ተስኖት እንዲህ ባንቺ መንከራተት ታሪክ ወሮታሽ ጠፍቶበት ትላንት በባዕድ ጩኸት ዛሬም ባላዋቂ ሁከት ቋንቋ ለቋንቋ ቢራራቅ የቅድሚያሽ ንድፍ ላይፋቅ እዚህ ደሜም እዚያ ተማም መባልሽ ብቻ ባይበቃም የቅርስሽ ጭብጥ ይዞታ ሆሄታሽ እስካልተፈታ፥ አባይ ፋናሽ የሕልም ርቅ ፈለግሽም ቢሆን ደቂቅ እንዴት እንዴት ነበር ብለን ካልደረስንበት ፈልፍለን፥ የጥንቷ አባይ እንዴት ትሆን አባይ-አቢይ አባይ-ግዮን ከምንጩ የጥበብ ሳሎን ግሪክ ፋርስና ባቢሎን ጭረው በቀዱበት ሸሞን፥ አባይ የአማልክት አንቀልባ የቤተ-ጥበባት አምባ ከኩሽ የቅድመ-አበው ብሁል ከተራራሽ አናት ቁልቁል የሰው ዘር የታሪክ-ፊደል ፥ ገና ከፅንሱ ሲረቀቅ ሲሳይም የእትብቱን ቆባ፥ ምጥቀቱን ለማንፀባረቅ ዘለዓለሙን ለማሳወቅ እስከሜዲትራኒያ፥ ጢሰ እሳትሽ ሲፍለቀለቅ፥ አባይ-አብይ ፥ አባይ ግዮን ለአማልክቶች አምላክ ለአሞን የኪነት ምንጩ እምትሆን፤ ለኦሩሰ ርቱእ አክናፋት ለነዳዮናይሶስ አባት ከእምብርትሽ የፀሐይ አምላክ ፥ ተቀስቶ በሰማያት ያረበበብሽ እንደ እሳት፤ ጥቁር አባይ ነጥቁር ምንጭ የካም የስልጣኔ ፍንጭ የቅድመ ታሪክሽ ጥርጊያ ከደም-ቢያ እስከ ኑ-ቢያ፥ የኢትዮጲስ ደም የኩሽ እናት አባይ የጥቁር ዘር ብስራት የዓለም ስልጣኔ ምስማክ ከጣና በር እስከ ካርናክ በጡትሽ እቅፍ እንዲላክ ለራህ ለፀሐዩ ግማድ፥ ለጣህ ለከዋክብት አምላክ፤ ከጥንተ-ፍጡራን ጮራ፥ የመነጨሽ ከኩሽ አብራክ፤ ሰሃራን እንደምሁር ተልም ያለመለመሽ በወዝሽ ደም የቅድመ-ጠቢባን አዋይ አባይ የምድር ዓለም ሲሳይ። ተነስ ንቃ አስመልስ ንገስ... ባላምባራስ ነጋሽ Negash Qemant~~~~~አበያ (አባይ)በሎሬት ፀጋዬ ሮበሌ ቀዌሳ~~~~~ አባይ የማን ነበር? አሁንስ የማነው? ኦሮሞ(የኩሽ ታላቅ ልጅ) እና አባይ የነበራቸው ቁርኝት ምን ይመስል እንደነበር ሎሬት ፀጋዬ ሮበሌ ቀዌሳ በሚገርም መልኩ በብዕሩ ከትቦልን አልፏዋል። 🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 አባይ የምድር አለም ሲሳይ የቅድመ-ጠቢባን አዋይ አባይ የጥቁር ዘር ብስራት የኢትዮጵያ ደም የኩሽ እናት የዓለም ስልጣኔ ምስማክ ከጣና በር እስከ ካርናክ በጡትሽ እቅፍ እንዲላክ ለራህ ለፀሐዩ ግማድ ፥ ለጣህ ለክዋክብት አምላክ ከጥንተ-ፍጡራን ጮራ ፥ የመነጨሽ ከኩሽ አብራክ። አባይ የምድረ-ኩሽ መኩሪያ በቅደመ-ታሪክሽ ጥርጊያ ከደም-ቢያ እስከ ኑ-ቢያ ከሜምፊስ እስከ ሜሮኤ በስልጣኔሽ ትንሳኤ ከዴልታሽ እስከ ዴር-ሡልጣን ከኡመ-ራህ እስከ ኡመ-ዱርማን፤ አባይ የአቴስ የጡቶች ግት ለዓለም የስልጣኔ እምብርት፤ ጥቁር አባይ የጥቁር ምንጭ የካም የስልጣኔ ምንጭ፤ አንቺ የምድረ ዓለም ሲሳይ በረሃውን ጥለሽ ግዳይ ሰሃራን እንዳክርማ ተልም ሰንጥቀሽው በወዝሽ ደም ፥ በጥበብሽ ስርወ-ፋና አንቅተሽ በአንቀልባሽ አዝለሽ ፥ የቅድመ ታሪክን ዝና የራምሴስን አበ-ሲምቦል፥ የመነስን ልዕልና በአልፋ የአልሙጋን ሐውልት፥ የቢያ-ሃንኬን ፍልስፍና በኮማምቦ የሶባቃን፥ በናፖታም የኤዛና ፊላኤ የአቴሰን ምኩራብ፥ በልቅጾር የአሞንን ዜና፤ አባይ ታላቅ ቅድመ-ተስፋ የኪነት ጉባኤ አልፋ፥ ረቂቅ አባይ ያንቺ መገን ምጥቀትሽ አይተንተን፥ የእጅ ማስነሻሽ በረከት ግብርሽ ከአድማሳት ሲክትት መንጣለያሽ ከዕለት ዕለት መሻገሪያሽ ካመት-አመት በመስዋዕት ሲወድቅልሽ በዝማሜ ሲፈስልሽ በመመለክ በመመስገን ጽላትሽ ከዘመን ዘመን በአዝርእት አበቅቴሽ ሲታጠን አቤት አባይ ላንቺ መገን አባይ ረቂቅ የጠቢብ ዘንግ የጨረቃን ጉዞ ፈለግ አስቀምረሽ በጠቢብ ዘንድ በፍሳሽሽ ውጣ ውረድ በሙላት ሚዛን ረገድ የሰማይን ጥርጊያ መንገድ ፥ የጊዜ መለኪያ ሰዓት ፥ ዜኒት ባንቺ ተቀምራ ከቴቤስ እስከ ዳንዳራ ብስራትሽን እንደደመራ ሥልጣኔሽ አንዳበራ፥ የመጽሐፈ-ሙታን ዜና አድርጎሽ ቅድመ-ገናና ዛሬ ወራቱ ራቀና ምድረ-ዓለም ያንቺን አድናቆት ፈለጉን መሻት ተስኖት እንዲህ ባንቺ መንከራተት ታሪክ ወሮታሽ ጠፍቶበት ትላንት በባዕድ ጩኸት ዛሬም ባላዋቂ ሁከት ቋንቋ ለቋንቋ ቢራራቅ የቅድሚያሽ ንድፍ ላይፋቅ እዚህ ደሜም እዚያ ተማም መባልሽ ብቻ ባይበቃም የቅርስሽ ጭብጥ ይዞታ ሆሄታሽ እስካልተፈታ፥ አባይ ፋናሽ የሕልም ርቅ ፈለግሽም ቢሆን ደቂቅ እንዴት እንዴት ነበር ብለን ካልደረስንበት ፈልፍለን፥ የጥንቷ አባይ እንዴት ትሆን አባይ-አቢይ አባይ-ግዮን ከምንጩ የጥበብ ሳሎን ግሪክ ፋርስና ባቢሎን ጭረው በቀዱበት ሸሞን፥ አባይ የአማልክት አንቀልባ የቤተ-ጥበባት አምባ ከኩሽ የቅድመ-አበው ብሁል ከተራራሽ አናት ቁልቁል የሰው ዘር የታሪክ-ፊደል ፥ ገና ከፅንሱ ሲረቀቅ ሲሳይም የእትብቱን ቆባ፥ ምጥቀቱን ለማንፀባረቅ ዘለዓለሙን ለማሳወቅ እስከሜዲትራኒያ፥ ጢሰ እሳትሽ ሲፍለቀለቅ፥ አባይ-አብይ ፥ አባይ ግዮን ለአማልክቶች አምላክ ለአሞን የኪነት ምንጩ እምትሆን፤ ለኦሩሰ ርቱእ አክናፋት ለነዳዮናይሶስ አባት ከእምብርትሽ የፀሐይ አምላክ ፥ ተቀስቶ በሰማያት ያረበበብሽ እንደ እሳት፤ ጥቁር አባይ ነጥቁር ምንጭ የካም የስልጣኔ ፍንጭ የቅድመ ታሪክሽ ጥርጊያ ከደም-ቢያ እስከ ኑ-ቢያ፥ የኢትዮጲስ ደም የኩሽ እናት አባይ የጥቁር ዘር ብስራት የዓለም ስልጣኔ ምስማክ ከጣና በር እስከ ካርናክ በጡትሽ እቅፍ እንዲላክ ለራህ ለፀሐዩ ግማድ፥ ለጣህ ለከዋክብት አምላክ፤ ከጥንተ-ፍጡራን ጮራ፥ የመነጨሽ ከኩሽ አብራክ፤ ሰሃራን እንደምሁር ተልም ያለመለመሽ በወዝሽ ደም የቅድመ-ጠቢባን አዋይ አባይ የምድር ዓለም ሲሳይ። ተነስ ንቃ አስመልስ ንገስ... ባላምባራስ ነጋሽ Negash Qemant

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...