Translate

Sunday, September 13, 2026

Albukko _ Salmane

🌿🔥 አልቡኮ–ሳልመኔ 🔥🌿 🏞️ የጀግኖችና የአይናማዎች አገር 📍 አልቡኮ ወረዳ በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከሚገኙ 24 ወረዳዎች አንዷ ስትሆን፣ የወረዳዋ ርዕሰ ከተማ ሳልመኔ ትባላለች። 📜 የአልቡኮ ስም አመጣጥ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ አሊ እና ቡኮ የሚባሉ የኦሮሞ ባለባት ተወላጆች፣ አሁን አልቡኮ ብለን በምንጠራው አካባቢ መስርተው ይኖሩ እንደነበር ይነገራል። የእነዚህን ሰዎች ስም፣ “አሊ” እና “ቡኮ” በማጣመር “አልቡኮ” የሚል ስያሜ እንደተሰጣት የአካባቢው ትውፊት ይገልጻል። 🏘️ አልቡኮ ወረዳ እንዴት ተቋቋመች? አልቡኮ በወረዳነት ከመቆርቆሯ በፊት፣ እስከ 1993 ዓ.ም. ድረስ የአልቡኮ ግማሾቹ ቀበሌዎች በወረኢሉ ወረዳ፣ ግማሾቹ ደግሞ በደሴ ዙሪያ ወረዳ ሥር ይተዳደሩ ነበር። ከደሴ ዙሪያና ከወረኢሉ ወረዳዎች 18 ቀበሌዎችን በማዋቀር፣ በ1994 ዓ.ም. አልቡኮ እራሷን ችላ ወረዳ ሆናለች። 🤝 የአልቡኮ ሕዝብ የአልቡኮ ሕዝብ በጣም ጨዋና እንግዳ ተቀባይ በመሆኑ፣ “ብሉልኝ፣ ጠጡልኝ” በማለቱ የሚታወቅ ሕዝብ ነው። ❤️🤝 ⚔️ የጀግኖችና የአይናማዎች አገር አልቡኮ የጀግኖችና የአይናማዎች አገር ናት። ለአብነትም፦ ⚔️ ሐጅ ሰይድ ሙጃሒድ ⚔️ ደጃዝማች ብሬ አደም ⚔️ ደጃዝማች መንገሻ አቡየ ⚔️ ቀኝ አማች ተፈሪ እና ሌሎችም ብዙ ጀግኖችን ያፈራች አገር ናት። 🌾 የአልቡኮ የምድር ስሞች አልቡኮ፣ ሳልመኔ፣ ደጋጋ፣ ጎሴ፣ ሶባ፣ ፈላና (Fallaanaa) ከተማና ገጠሩ በኦሮምኛ የተሰየሙ ናቸው። 🌱 ወረዳችን አልቡኮ ካሏት ለም መሬቶች መካከል ሶባ እና ፈላና ሜዳ ዋነኞቹ ናቸው። 🌾 013 ቀበሌ — ሶባ ወይም ጎሴ ከጫፍ እስከጫፉ የሚገርም ለም መሬት ያለው፣ በተፈጥሮ የታደለ አካባቢ ነው። ለተለያዩ ፋብሪካዎችም ብዙዎች የሚመኙት ምቹ መሬት እንዳለው ይነገራል። https://mikysultan.blogspot.com 🔗 https://t.me/Oromo_geography 🌿 አልቡኮ–ሳልመኔ 🏞️ የታሪክ፣ የትውፊት፣ የጀግንነትና የለም መሬት አገር! ✍️ ★Miky Sultan Barento★

No comments:

Post a Comment

Albukko _ Salmane

🌿🔥 አልቡኮ–ሳልመኔ 🔥🌿 🏞️ የጀግኖችና የአይናማዎች አገር 📍 አልቡኮ ወረዳ በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከሚገኙ 24 ወረዳዎች አንዷ ስትሆን፣ የወረዳዋ ርዕሰ ከተማ ሳልመኔ ትባላለች። 📜 የአልቡኮ ስም አመ...