Translate

Sunday, September 6, 2026

የየጁ ኦሮሞ ታሪክ

🇪🇹📜 የወሎ ታሪክ — ታሪክን የኋሊት የጁ ዘመነ መሳፍንት በሚባለው የየጁዎች መንግስት ወቅት እንዲህ ሆነ፤ ራስ አሊ የጁ የተባለ ጀግና ጎፈሬ መስፍን አገሪቱን ይመራ ነበር፤ ከእሱ በታች፤ በነ ራስ አሊ ትዛዝ ደጃች ውቤ የተባለ ባለሹርባ መስፍን፤ ከስሜን እስከ ምፅዋ ያለውን ግዛት ያስገብራል። የሆነ ጊዜ ላይ ውቤ ደጃዝማችነቱ አላረካው አለ፤ መፈንቀለ መንግስት ማድረግ ፈለገ፤ ደጁን ብቻ ሳይሆን ሙሉውን ግቢ ፈለገው፤ ለመንገስ በጣም ሻፈደ። በምፅዋ በኩል ብዙ ጠመንጃ እየሰበሰበ አካማቸ፤ ብዙ ጭፍራ መለመለ፤ የሚቀማውን ስልጣን የተገባ Legitimate ለማድረግ አባ ሰላማ የተባለ የግብፅ ቅጥረኛ ጳጳስ አሰናዳ፤ የሚቀረው ምንድነው? ራስ አሊን ከስልጣን ማባረር። ታሪኩን ላሳጥረውና፤ ራስ አሊና ውቤ ደብረታቦር ላይ ገጥመው ተፈሳፈሱ! በጦርነቱ ላይ የውቤ ባለነፍጥ ሰራዊት የራስ አሊን ፈረሰኛ እንደ ቅጠል ያረግፈው ጀመር፤ የራስ አሊ ፈረሰኛ በጎራዴ ነበረ የምዋጋ፤ የራስ ውቤ በግብፆችና በክሪስትያን ሀገሮች እገዛ የተገኛ መሳርያ ነበረ። ነገሩ ያላማረው ራስ አሊ ብረት-ለበሱን ማለቴ ፈረሱን የኋሊት አዞረና ቆሰቆሰው፤ አብዛኞቹም ወታደሮቹም ተከትለውት ሸሹ፤ የጦርነት ስልት ነው። ውቤ፤ ነገሩ አሸወይና እንደሆነ ሲመለከት ድንኳኑን ጥሎ አስደግሶ ወታደሮቹን የድል ምሳ ጋበዘ። ምሳው እየተበላ፣ ጠጁ እየተጠጣ፣ ወታደሮች እየመጡ ይፎክራሉ፤ ምርኮኞችም ደግሞ መሳርያቸውን እየጣሉ በውቤ ፊት ይንበረከካሉ። በዚህ መሀል፤ የወሎው ጀግና አሊጋዝ ብሩ የተባለ እውቅ፤ የየጁ ጀግና ወደ ደጃች ውቤ ቀረበ። ሌሎች ምርኮኞች እንደሚያደርጉት መሳርያውን የሚያስቀምጥ ይመስል በርከክ እንደማለት አለና፦ “እጅ ወደላይ!” ብሎ ጮኸ! ውቤ ቁጭ ባለበት ደርቆ ቀረ፤ ምንም ማድረግ አልቻለም። እየጋጠ የነበረውን የዶሮ ቅልጥም ማእዱ ላይ አስቀምጦ እጁን ወደ ላይ አነሳ። (የቅልጥሙን ቀደዳ እንኩዋን እኔ ነኝ የጨመርኩት) ራስ አሊ፤ ከሸሸበት ቦታ ሆኖ አንድ መልክት ደረሰው፦ “ውቤ ተማርከዋልና ይመለሱ” ይላል መልእክቱ። ላኪው አሊጋዝ ብሩ የየጁ ጀግና ነው። ይህ በሆነ በማግስቱ አንዲት ባልቴትና እና አንድ ሰውየ መንገድ ላይ ተገናኙ። “እቴዋ! የራስ አሊና የደጃች ውቤ ጦርነት እንዴት አለፈ?” አለ ሰውየው። “ራስ አሊ ሸሹ፤ ደጃች ውቤ አሸንፈው ተማረኩ” አሉ ባልቴቲቱ። “እረ ባክዎ በቅጡ በቅጡ አድርገው ያውጉኝ!” “ተወኝ ባክህ! እነሱ በቅጡ ያልተዋጉትን እኔ እንዴት በቅጡ ላውጋው?” --- 🧠 ከዚህ አጭር የታሪክ ገጠመኝ የምንማረው የዘመናዊ ፖለቲካ ንድፈ ሀሳብ “የሚሸሽ ሁሉ የተሸነፈ አይደለም፤ የሚያሸንፍ ሁሉም አሸናፊ አይደለም።” ይህ የውቤ ታሪክ እንደ ተራ የጦርነት ገጠመኝ ብቻ ከተመለከትነው ብዙ ነገር እናጣለን። ነገር ግን ከፖለቲካ ስልት አንፃር ስናነበው የሚያስተምረን ነገር አለ። ውቤ የጦር ሜዳውን አሸነፈ ብሎ አሰበ። ስለዚህ የድል ምሳ አዘጋጀ። ራስ አሊ ግን ወደኋላ ተመለሰ። ይህ ሽንፈት ይመስል ነበር። ነገር ግን ጨዋታው እዚያ አልተጠናቀቀም። የውቤ ድል ወደ የድል ምሳ ሲቀየር፣ የራስ አሊ ሽንፈት ወደ የፖለቲካ ውጤት ተቀየረ። ይህ ነው የፖለቲካ ስልት። አንድ ኃይል በዛሬው የጦር ሜዳ ሊያሸንፍ ይችላል፤ ሌላው ደግሞ በዛሬው ጦርነት ሊሸሽ ይችላል። ግን የመጨረሻውን ውጤት የሚወስነው የመጀመሪያው ቅጽበት አይደለም። የሚወስነው፦ ማን እስከመጨረሻ አስቦ ነው? ማን የተቃዋሚውን ቀጣይ እርምጃ አይቷል? ማን በድል ስሜት አልተዘናጋም? ማን የሕዝብን ድጋፍ ማቆየት ችሏል? የዛሬ ኢትዮጵያ ፖለቲካም በዚህ መነፅር ሊታይ ይችላል። የዛሬን ድል ብቻ አትመልከት፤ የነገን እርምጃ ተመልከት። የዛሬ ሽንፈትንም የመጨረሻ ሽንፈት አድርገህ አትቁጠር። ምክንያቱም፦ የፖለቲካ ጨዋታ እስካልተጠናቀቀ ድረስ የድል ምሳ ማዘጋጀት አደገኛ ነው። https://mikysultan.blogspot.com 🔗 https://t.me/Oromo_geography 🔥 ታሪክን የኋሊት ስናየው፣ የዛሬን ፖለቲካ የበለጠ እንረዳለን። — Miky Sultan Barento

No comments:

Post a Comment

የራስ አሊ ጀግንነት

🇪🇹⚔️ የየጁ የራስ አሊ ጀግንነት — የጦር ስልት በኢትዮጵያ ጀግና ሰራዊት የየጁ ኦሮሞ ሰራዊት ነበረ። የጎንደርና የሌሎችም አካባቢ ሴቶች በግጥም እየዘፈኑ፦ «“አሊና አሊና አሊና በሞቴ፤ የአማራ ማተብ ሰለቸዉ አን...