Seenaa ilma nuuh "Ham " Abbaa afrikaa qaroomina kush & kana'an የኖህ ልጅ ታሪክ ሃም የአፍሪካ አባት የኩሽ እና ከነዓናዊ ስልጣኔ! For those who want to learn more about the history, culture, way of life, and civilization of the Cushites, visit our website.https://mikysultan.blogspot.com
Translate
Monday, September 7, 2026
የቴዎድሮስ ዙፋን ምስጢር
🔥👑 የቴዎድሮስ ዙፋን ምስጢር — እቴጌ ተዋበች ባትኖር ቴዎድሮስ አይነግስም ነበር?
አፄ ቴውድሮ የራስ አሊ የጁ አሽከር ነበረ
ተዋበች ባትኖር ቴድሮስ አይነግስም ነበረ
ተዋበች ባትኖር ቴዎድሮስ አይነግስም ነበረ
ራስ አሊ አሉላ (Ali II of Yejju)
⬇️
እቴጌ ተዋበች ራስ አሊ አሉላ መርሶ ባሬንቶ
⬇️
አያቷ፦ እቴጌ መነን ሊበን አመዴ
በእናቷም በ አባቷም የባለባት ልጅ ነበረች።
★ Miky Sultan Barento ★
📜 ወደ ጋዜጠኛ ፍስሐ ስንመለስ፦
“ቅድም ነገሩ ሁሉ ከቁጥጥራቸው ውጪ እየሆነ ሲመጣ ቁጣቸው ገነፈሎ አሁንም ካህናቱን እጣን ጠባሽ፤ ፊሰ ሰፊ፤ ራሱን ታጣቂ፤ ወገቡን ስባቂ... እያሉ ይዘልፏቸዉ ጀመረ፡፡ በርካቶችን ወደ ገደል አስወረወሯቸዉ፡፡ ብዙዎችንም እሳት እንዲነድዉ ወደ እሳት ጨመሯቸዉ፡፡ የቀሩትንም በጦር አስወጓቸዉ ይላል፤
ይህን ሁሉ ግፍ በካህናቱ ላይ ቢፈፅሙም የመሳፍንቱ አመፅ እንኳን ሊቆም እየባሰበት ሄደ፡፡ አፄ ቴዎድሮስም አመፁን መቋቋም ተሳናቸዉና የጎንደር ቤተመንግስትን ለመልቀቅ ተገደዱ፡፡ እቃቸዉን ጠቅልለዉ ይዘዉ ሄደዉ መቀመጫቸዉን ደብረ ታቦር አደረጉ” ይላል፡፡
---
⚔️ የዋግሹም ጎበዜ መነሳት
ከዚህ በኋላ የሀገሪቱ የፖለቲካ ቁልፍ የቆቀመዉ ዋግሹም ጎበዜ /በኋላ አፄ ተክለጊዮርጊስ 2ኛ/ እጅ ውስጥ ገባ፡፡
ቴዎደሮስ ደብረ ታቦር ሲያፈገፍግ ሁሉም የጦር መሳሪያና አሰራሮችን ይዞ ነበር፡፡ ዋግሹም ጎበዜም /በኋላ አፄ ተክለጊዮርጊስ 2ኛ/ ቴዎድሮስን ዙሪያዉን ከቦ እየተከታተለ ግዛቶቹን ሁሉ ነጥቆ በደቡብ ወሎ መቅደላ ብቻ እንዲወሰን አደረገዉ /ዋግሹም የሰቆጣ አካባቢ የማዕረግ ስም ነዉ/፡፡
---
👑 ተዋበች ወይስ ቴዎድሮስ?
ለዚህም ነዉ እንግዲህ እቴጌ ተዋበችን እንደ ዋና ቴዎድሮስን እንደ ተጨማሪ /አጋዥ/ ለማድረግ የምንገደደዉ፡፡ በእርግጥ የፖለቲካዉን ስራ ሙሉ በሙሉ ለእቴጌ ልቀዉት ስለነበረ እሱ ነበር አድራጊፈጣሪዉ፡፡
ነገር ግን ተዋበች ባልኖረች ጊዜ ቴዎድሮስ ንጉስ ሆኖ መቀጠል አልቻለም፤ መጀመሪያም ዝም ያሉት እሷ ስለሰጠቻቸዉ ነበር ማለት ነው፡፡
ምክንያቱም እሷ ከሞተች በኋላ ወዲያው በሚለከፉበት የማደሪያ ሙከራዎች ምክንያት ጭንቀት ውስጥ ገባ፤ ቤተመንግስቱንና መላውን ግዛቱንም አስለቀቁት።
ስለዚህ ቴዎድሮስን ያነሱት እሷ ነበሩ ማለት ነው። እናም የቴዎድሮስ መንግስት የቆመው እሷ እስካለችበት ጊዜ ድረስ ብቻ ከሆነ ዋናዋ እሷ ነበረች ማለት ነው፡፡
ልክ በዘመነ መሳፍንት ጊዜ መንግስቱ የሚቆመዉ በተቀባዉ በእንጅንሊቱ ንጉስ ላይ ሳይሆን ባነሳዉ መስፍን ላይ ነበር፡፡
አሻንጉሊት ንጉሱ ኖረም አልኖረም ችግር የለዉም ነበር፤ ካስፈለገ አሻንጉሊት ንጉሱ ሊቀየር ይችላል፡፡ አሻንጉሊት ንጉሱ እንደተቀባ ንጉስ የሚኖረዉ ደግሞ ያነሳዉ መስፍን እስካለ ድረስ ብቻ ነበር፡፡
---
🔥 የእቴጌ ተዋበች ሚና
የእነ ቴዎድሮስን ጉዳይ ስናየዉ ከተዋበች አሊ ይልቅ ቴዎድሮስ ባይኖር ይሻል ነበር፡፡ ቴዎድሮስ ባይኖርም ሰራዊቱ አይበተንም ነበር፡፡ መሳፍንቶቹም ለአቴጌ ተዋበች አሊ መገዛታቸዉን ይቀጥሉ ነበር፡፡
ስለዚህ ምን ይሻላል ? አሻንጉሊቱ ማን ይሁን ?
ተዋበች ከሞት ስላኖረችና በዘመኑ የነገስታት ልጆች የእናት-የአባትን ስልጣን ለመወረስ ይሽቀዳደሙ ስለነበር ነዉ ቴዎድሮስን እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሱት፡፡
እናም ቴዎድሮስ እቴጌ ተዋበችን ተጠግቶ ነበር ንግስና የኖረዉ ማለት ነው፡፡
/ልክ አሻንጉሊቱ ንጉስ ወራሹን መስፍን ተጠግቶ ንግስ እንደሚኖረዉ/
አሻንጉሊቱ ንጉስ ንግስ /ተቀብሎ/ የሚቆየዉ ደግሞ ያነሳዉ መስፍን እስካለ ጊዜ ድረስ ብቻ ነበር፡፡
ቴዎድሮስም ንግስ /ተቀብሎ/ የኖረዉ ተዋበች እስካለች ጊዜ ድረስ ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ ከመስፈርቱ አንጻር መሳፍንቱን /ገዢን/ መከተል ስላለብን የቴዎድሮስን ሙሉ በሙሉ አሻንጉሊት ንጉስ ለማለት ባይቻልም የእቴጌዋ ረዳት /አጋዥ/ ለማድረግ እንገደዳለን፡፡
ለዚህም ነዉ ቴዎድሮስ ከእቴጌ መነን ሊበን አመዴ እጅ ወጥቶ አያዉቅም የሚባለዉ፡፡
⚔️ ከ150 ሺህ ወደ 10 ሺህ
እንግዲህ ከላይ እንዳየነዉ ተዋበች ከሞተች በኋላ የየጁ ጦር(የተዋበች) ጦር ነበሩ እየመሸሸ መጥቶ ከ150ሺ ወደ 10ሺ በመውረዱና ቴዎድሮስ ባለባት ስላልሆነ ሁሉም መሳፍንቶች መገበር አቁመዉ ቴዎድሮስን ቤተመንግስቱን አስለቅቀዉ ለዋግሹም ጎበዜ /በኋላ አፄ ተክለጊዮርጊስ 2ኛ/ መገዛት ጀመሩ፡፡
ቴዎድርሶም እስከ እንግሊዞች መምጣት ድረስ ወሎ መቅደላ ላይ መሸጎ ነበረ የሚኖረዉ፡፡ ግዛቱም ሁለት አውራጃዎች ማለትም ከበጌምድርና ከዋድላ ደላንታ አይበልጥም ነበር፡፡
🇬🇧 የቴዎድሮስ የእንግሊዝ ግንኙነት
ቴዎድሮስ ቀደም ብለዉ /ቤተመንግስቱን ከመልቀቃቸዉ በፊት/ የእንግሊዝ ንግስት ለነበሩት ለንግስት ቪክቶሪያ ደብዳቤ ፅፈዉ የወቅቱ ቆንሲል ዳንኤል ካመሩን መርጠዉ "...የጦር መሳሪያ እርዳታ፣ የጦር መሳሪያ የሚያመርቱ የአጅ ጥበብ ባለሙያዎች ...ወዘተ..." በማለት በዲፕሎማሲያዊ ቃላት የተጀበበ ደብዳቤ አስይዘዉ ልከዉ ነበር፡፡
ነገር ግን የላኩት ሰዉ የዉሀ ሽታሆነባቸዉ፡፡ ምላሽ ሲጡፉ በአካባቢያቸዉ ያገኙትን ምድር ቆንሲል ሌቃወመዉ 30 የሚያደርሱ የዉጭ ዜጎችን ወሎ መቅደላ አምባ በሚገኘዉ እሰር ቤታቸዉ እስረዉ የጦር መሳሪያ ለማስራት ሞከሩ፡፡ እንግሊዛዊያኑም በርከት ያሉ ነበር፡፡
---
🔥 የመጨረሻው ጥያቄ
ከተዋበች ሞት በኋላ ምንም አይነት ሰላምና ስልጣን ኖሮት የማያዉቀዉና ቤተመንግስቱንና መላዉን ግዛቱን እስኪለቅ የደረሰዉ ቴዎድሮስ፤ የተሻለ የጦር መሳሪያ አስመጥቶ፤ ካልተቻለ ደግሞ አስፎ፤ መሳፍንቱን ሁሉ በማንበርከክ ወደ ጎንደር ቤተመንግስት ለመመለስ በእጁ ያሉትን አማራጮች ሁሉ በሙሉ መሞከሩን ቀጠለ፡፡
በዲፕሎማሲ ማግኘት ያልቻሉትን የዘመናዊ መሳሪያ ጥማት፤ ሙያዉ በሌላቸዉ ሰዎች በግድ ለማግኘት "እንደምንንም መድፍ ስሩ" ብለዉ እስረኞችን አስገደደ፡፡
እንግሊዞች ደግሞ ሁሉም መረጃ /information/ ነበራቸዉ፡፡ ቴዎድሮስ አሁን መንግስት አይደለም፤ ቤተመንግስቱንና መላዉን ግዛቱን ለቆ ወሎ መቅደላ አምባ ላይ መሸጎ ነዉ የሚኖረዉ፡፡
በፊት መንግስት በነበረበት ሰአት ባለሙያ ጠይቀዉ ቢሆን ኖሮ ምናልባት ሊልኩልት ይችሉ ነበር፤ እሱ ግን በፊት ሰላም በነበረበት ሰአት ይህን መሳሪያ የማስራት ጉዳይ አስቦት አያዉቅም፤ አሁን ግን መንግስት ስላልሆነና ገና እንግሊዞችን የጦር መሳሪያ አስርቼ ወደ ቤተመንግስተ እመለሳለሁ ብሎ ተስፋ ያደረገ ሽፍታ ቡድን ነበረ።
ወሎዬን የካደ የወሎ አሽከር ነበረ።
🔥 እንግዲህ ጥያቄው እንደገና ይመለሳል፦
ቴዎድሮስ የራሱ ኃይል ያለው ንጉሥ ነበር? ወይስ የእቴጌ ተዋበች የፖለቲካ ጥላ ውስጥ የቆመ ንጉሥ?
https://mikysultan.blogspot.com
🔗 https://t.me/Oromo_geography
💬 እናንተ ምን ትላላችሁ?
★ Miky Sultan Barento ★
#አፄቴዎድሮስ #እቴጌተዋበች #ራስአሊ #የየጁ #ወሎ #መቅደላ #ዋግሹምጎበዜ #ዘመነመሳፍንት #MikySultanBarento
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
የእምባቦ ጦርነት
🔥⚔️ የሸዋ ወሎና የጎጃም ጦር ግጥምያ ⚔️🔥 ጎጃሞች ዘራፍ አበዙ የወሎ ሰው ዘምቶ አፉን አስያዘው 📜 የእምባቦ ጦርነት (Battle of Embabo) ★ Miky Sultan Barento 🕔 ከቀኑ 5 ሰዓት ━━━━...
-
ጀማሉዲን ሙሀመድ አኒ (አራርሶ ሮውብሶ) https://t.me/Oromo_geography * ــــــــــــــــــــــــــــــــــــ * ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የዒልም ኮኮብና የጅሀዱ ጀግኖ...
-
የባሬንቶ ልጆች እና የሰሜኑወሎናራያ ውልድ ዘር ሀረግ የሰበት ወሎ ጎሳ ኮንፍድሬሽን ታሪክ … ቦረና እና ባሬንቶ ኦሮሞ ትላልቅ ሁለት ልጆች ወይም ጎሳዎች አሉት፣ እነሱም። ቦረነና ባሬንቶ ...
-
®የ ወሎ የዘር ሀረግ☜ አዘጋጅ ፤miky sultan/wollo oromo.********** የካም ልጆች ኩሽ ፣ፋጥነ ከነዓን ናቸዉ፣ ከነዚህ መሃል የወሎ የዘር ሀረግ ከኩሽ ይመዘዛል ኦሮሞ የ ኩሽ ዘር ነው...

No comments:
Post a Comment