Translate

Saturday, September 19, 2026

አቢቹ ነጋ ነጋ — የሰላሌ ጀግና ወረ ጃርሶ

🇪🇹⚔️ አቢቹ ነጋ ነጋ — የሰላሌ ጀግና ወረ ጃርሶ 📜 ከትምህርት መንገድ ወደ ጦር ሜዳ ★ Miky Sultan Barento ★ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 👦 ልደቱና የቤተሰብ ሐረጉ አቢቹ የተወለደው በ1912 ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ፣ ወራ ጃርሶ አካባቢ፣ Dhaaye( ጣዬ) በሚባል ስፍራ ነው። የአቢቹ ጎሳ ከሦስቱ የቱለማ ልጆች መካከል በዳጪ ቤት ይወለዳል ፤ ከዳጪ ቤት ገላን፣ ከገላን ቤት ደግሞ ወረ ጃርሶ(Jarsa) ይገኛል። አባቱ በየና ቆሪቾ የወራ ጃርሶ የትግል መሪ ነበሩ። ⚔️ የአባቱ የትግል ውርስ የጣሊያን ወረራ ሊጀምር በተቃረበበት ወቅት አባቱ በሕመም ዓለምን ተለዩ። የአባታቸውን የትግል ዓላማ ለማስቀጠልም ሁለቱ ታላላቅ ወንድሞቹ የወረ ጃርሶን ተዋጊዎች መምራት ጀመሩ። 📚 አቢቹ ግን በዚያን ጊዜ ተማሪ ነበር። አባቱ በሕይወት እያሉ አቢቹን ወደ ፊንፊኔ ልከው በዘመናዊ ትምህርት እንዲማር አድርገው ነበር። ትምህርቱን ከፍ ለማድረግም ወደ ፈረንሳይ ሄዶ ለመማር እየተዘጋጀ ነበር። 🇮🇹 የጣሊያን ወረራ ግን የሕይወቱን አቅጣጫ ቀየረ! አቢቹ፦ «“Obbolowwan koo gara dirree waraanatti deeman biraa hin hafu.”» ብሎ የትምህርት ጉዞውን አቋርጦ ወንድሞቹን ተከትሎ ወደ ጦር ሜዳ ወረደ። ❤️ የእናቱ ልብ ተሰበረ። እናቱ ይህ ገና ወጣት ልጇ ወደ ጦርነት እንዳይሄድ ብትለምነውም፣ አቢቹ ግን ውሳኔውን አልቀየረም። እናቱም ልጇን ለደጃዝማች አበራ አደራ ሰጥታ ሸኘችው። እየተሰናበተችውም በልብ ሰባሪ ሁኔታ እንዲህ ብላ ዘመረች ተብሎ ይተረካል፦ 🎶 “Abbichuu nagaa nagaa, ijakoorra hin maarmaarinii; achittuu nagaa nagaa, qoreen si hin waraninii…” 💔 ይህ የእናት ልቅሶ በኋላ የአቢቹ ናጋ ናጋ ታሪክ መስታወሻ ሆነ። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ⚔️ ደብረ አምባ — የሕይወቱ ትልቅ ሀዘን በደብረ አምባ በተደረገው ውጊያ አቢቹ ሁለቱንም ወንድሞቹን አጣ። ከእነሱ አንዱ አስከሬኑ ተገኝቶ በአንድ ዛፍ ሥር ተቀበረ፤ ሌላው ግን የት እንደወደቀ ማወቅ አልተቻለም። ይህ ከባድ ሀዘን አቢቹን የበለጠ አጠነከረው። ከደጃዝማች አበራ ጋር ተባብሮም የወራ ጃርሶን ተዋጊዎች መምራት ቀጠለ። 🏔️ የደፈጣ ውጊያ መሪ አቢቹ በተለይ የደፈጣ ውጊያ ዘዴ በመጠቀም በጣሊያን ወታደሮች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ያደርግ ነበር። ጣሊያኖችም አቢቹን ለመያዝ በተደጋጋሚ ቢፈልጉም ማግኘት አልቻሉም ተብሏል። ከታንበን ተራሮች አካባቢ ተደብቆ የጣሊያን ኃይሎችን ሲያደፈጥ እንደነበርም በትውፊታዊ ዘገባዎች ይገለጻል። አቢቹ ናጋ ናጋ በተለይ በፈጣን እንቅስቃሴና በደፈጣ ውጊያ የሚታወቅ መሪ እንደነበር የትውፊት ዘገባዎች ይገልጻሉ። 🤝 ከሌሎች የጦር መሪዎች ጋር የአቢቹ ጽናትና የትግል ችሎታ የተለያዩ የጦር መሪዎችንም ቀልብ ሳበ። በተለይ ራስ ካሳ፣ ራስ ሲዩም ማንጋሻ እና ደጃዝማች አበራ ከአቢቹ ቡድን ጋር በተያያዘ የሚጠቀሱ ስሞች ናቸው። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ⚔️ የማይጨው ጦርነት በማይጨው ጦርነት የአቢቹ ተዋጊዎች ብዙ ተጋድሎ አድርጓል ተብሎ ይነገራል የታሪክ ምንጮች ይጠቀሳል። 🏡 ወደ ወራ ጃርሶ ከጦርነቱ በኋላ የአቢቹ ተዋጊዎች ወደ ወራ ጃርሶ ተመለሱ። አቢቹም ከእነሱ ጋር ተመለሰ። የአቢቹ ታሪክ ግን በዚህ አያበቃም… ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📖 የአቢቹ ናጋ ናጋ ታሪክ የሰላሌ ሕዝብ የትግል፣ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ትውስታ ነው። 🔗 https://mikysultan.blogspot.com 🔗 https://t.me/Oromo_geography ★ Miky Sultan Barento ★ #AbichuuNagaaNagaa #GootaSalaalee #Oromoo #WaraJaarsoo #SeenaaOromoo #Salalee #Resistance #EthiopianHistory

No comments:

Post a Comment

ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ — “አባ ቦራ”

🇪🇹⚔️ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ — “አባ ቦራ” 🛡️ የምዕራብ ሸዋ ታላቅ አርበኛ ★ Miky Sultan Barento ★ 📜 ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረች ጊዜ አርበኛው ጀግና የኦሮሞ ልጅ ገረሱ ዱኪ ወደ ሰሜን ዘምተው ...