Translate

Thursday, February 11, 2021

#Ali Birra/ #አሊ ቢራ

አፍረን ቀሎ እና የአቡበከር ሙሳ ገድል
------
ግን ዓሊ ቢራን ኮትኩቶ ያሳደገው የጥበብ መምህሩ ልክ የዛሬ አርባ ዓመት ሞቶ ነበር፡፡ በዚህ ጽሑፍ የዚያን የጥበብ ገበሬ ስራዎች እንቃኛለን፡፡ 
------
ዓሊ ቢራ በአማርኛ አንድ ዘፈን ብቻ ነው የተጫወተው፡፡ ከዘፈኑ ስንኞች መካከል እንዲህ የሚል ይገኝበታል፡፡
ከድሬ ስመጣ ገና ትንሽ ነበርኩ
አሁን ከኢትዮ ስታር ባንድ እዩኝ ግንድግድ ነኝ፡፡
ዓሊ እንዲህ ያለው በ1970ዎቹ አጋማሽ ነው፡፡ ታዲያ ከድሬ የመጣው የያኔው ትንሽ ልጅ ዛሬ በብዙዎች ዘንድ የሚወደስ “ግድንግድ” ሆኗል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድናቂዎችንም አፍርቷል፡፡ ይህ ተወዳጅ አርቲስት ከእውቅና ማማ ላይ ሊወጣ የቻለበት አስደናቂ ታሪክ አለው፡፡ ታሪኩንም ከስረ መሰረቱ ጀምረን እንመረምረዋለን፡፡
*****
በኦሮሞ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የተደራጀ የሙዚቃ ቡድን “አፍረን ቀሎ” በመባል ይጠራል፡፡ የኦሮሞ ሙዚቃ የራሱን ዘውግ ፈጥሮ መስፋፋት የጀመረው ይህ ቡድን ህልውናውን ካበሰረበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ቡድኑ ለስምንት ዓመታት ብቻ የቆየ ቢሆንም በኦሮሞ ኪነ-ጥበብ ላይ ያሳረፈው ተጽእኖ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በዚያ ቡድን ውስጥ የተሰባሰቡት ወጣቶች የተገኙት ከመላው የሀረርጌ ክፍለ ሀገር ነው፡፡ ሁሉንም አንድ ላይ አገናኝታ ስለ ጥበብ እንዲፈላሰፉ ያደረገችው ግን ድሬ ዳዋ ናት፡፡ 
“አፍረን ቀሎ”ን የመሰረቱት ሶስት ወጣቶች ናቸው፡፡ ዘመኑም 1954 ነው፡፡ እነዚያ ወጣቶች በጊዜው በኦሮምኛ ቋንቋ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን የሚያቀርብ ቡድን አለመኖሩ ስላንገበገባቸው “ለምን በቋንቋችን የሙዚቃና ቴአትር እድገት ላይ አተኩሮ የሚንቀሳቀስ ቡድን አናቋቁምም?” በማለት መነጋገር ጀመሩ፡፡ ሃሳቡን ለጥቂት ሳምንታት ካንሸራሸሩ በኋላም ቡድኑን መሰረቱ፡፡ ስያሜውንም በአራቱ የምስራቅ ሀረርጌ የኦሮሞ ጎሳዎች ስም “አፍረን ቀሎ” በማለት ጠሩት፡፡
ሶስቱ ወጣቶች በመሰረቱት ቡድን ዙሪያ ችሎታ ያላቸውን ወጣቶች መለመሉ፡፡ በተበታተነ ሁኔታ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን የሚሞካክሩ ወጣቶችንም መሳብ ጀመሩ፡፡ በሀርሞኒካና በጊታር እየዘፋፈኑ ሰርግና የጫጉላ ሽርሽር ሲያደምቁ የነበሩትንም አሰባሰቡ፡፡ በዚህም መሰረት ዓሊ ሸቦ፣ ማሕሙድ ቦኼ፣ ሸንተም ሹቢሳ እና ሃሚዶ መሐመድ የመሳሰሉትን የዘመኑን ውብ ዜመኞች በአንድነት አጣምረው “አጃዒበኛ” ስራዎችን ወደ ህዝብ ማድረስ ጀመሩ፡፡ ህዝቡም በከፍተኛ ወኔና ሞራል ተቀበላቸው፡፡ በተለይ በአረፋና በዒድ አል ፈጥር በዓል የሚያቀርቡት የድራማና የሙዚቃ ትርዒት ከፍተኛ ዝናና ከበሬታ አስገኘላቸው፡፡ የድሬዳዋ ባለሀብቶችም በልዩ ልዩ መልክ ይደጉሟቸው ጀመር፡፡ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ከመግዛት ጀምሮ በሀረርጌ ከተሞች ውስጥ እየተዘዋወሩ ትርዒታቸውን የሚያሳዩበትን ሁኔታ እስከማመቻቸት የሚደርስ ድጋፍ አደረጉላቸው፡፡
“የአፍረን ቀሎ” ቡድን የተመሰረተው በሶስት ወጣቶች እንደሆነ ከላይ ገልጬአለሁ፡፡ ነገር ግን ከሶስቱ ወጣቶች መካከል የአንደኛው ሚና እጅግ በጣም ግዙፍ ነበር፡፡ ይህ ሰው የቡድኑ ሊቀመንበር ሆኖ ይሰራል፡፡ የቡድኑ አስተዋዋቂም ነው፡፡ የቡድኑ አባላት የሚያዜሟቸው ግጥሞችንም በብዛት የሚጽፈው እርሱ ነው፡፡ ድራማና አጫጭር ጭውውቶችንም ይደርሳል፡፡ 
የአፍረን ቀሎ ቡድን በህዝቡ ዘንድ የነበረው ተቀባይነት እየጨመረ ሲመጣ ይህ የቡድኑ ሊቀመንበር የነበረው ሰውዬ ከአንጋፋዎቹ ከያኒያን በተጨማሪ ታዳጊዎችንም እየመለመለ ወደ ቡድኑ መቀላቀል ጀመረ፡፡ በዚህም መሰረት ሂሜ ዩሱፍ እና ኢብራሂም ሀጂ ዓሊን የመሳሰሉ ዐጃኢበኛ ከያኒዎች የቡድኑ አባላት ሆኑ፡፡ 
ቡድኑን በኋላ ላይ ከተቀላቀሉት ታዳጊዎች መካከል በድምጹ ቅላጼ ለየት ያለ ሆኖ የተገኘው ዓሊ መሐመድ ሙሳ የሚባል ጠይም ኮበሌ ነው፡፡ በመሆኑም የቡድኑ ሊቀመንበር የነበረው ሰው “ፉአዲ ቀልቢ” የሚባል የዘመኑን ተወዳጅ የግብጻዊያን የዐረብኛ ዜማ “ቢራዻ በሪኤ” (በአማርኛ “መስከረም ጠባ”፣ “ጸደይ ሆነ” እንደማለት ነው) በሚል ርዕስ ወደ ኦሮምኛ ቀይሮት ጻፈውና ለታዳጊው ዓሊ ሙሐመድ ሙሳ ሰጠው፡፡ ታዳጊውም ከህዝብ ፊት በመውጣት እንዲህ ዘፈነው፡፡
Birraadhaa bari’ee ililliin urgoytee
Dilii maalin qaba Rabbii khiyya yaa Goytee?
ይህ የዘፈኑ አዝማች ነበር እንግዲህ፡፡ ታዳጊው ይህንን ሲዘፍን ዕድሜው ከአስራ አምስት ዓመት የበለጠ አልነበረም፡፡ የዘፈኑ አዝማች በአማርኛ ሲተረጎም እንዲህ ሊሆን ይችላል፡፡
መስከረም ጠብቷል የአበቦች መዓዛ ያውዳል
“ምን ጥፋት አለብኝ አምላኬ ሆይ! ለኔ ምን ይበጃል?
ህዝቡ ዘፈኑን ሲሰማ በከፍተኛ ጭብጨባ ነው የተቀበለው፡፡ “ቢስ…ቢስ…” እያለ ደጋግሞ እንዲዘፍን አደረገው፡፡ በሌሎች መድረኮችም ተመሳሳይ ሁኔታ ቀጠለ፡፡ በሰርግ ቤትም ሆነ በበዓላት ዝግጅት “ቢራዻ በሪኤ” እጅግ ተመራጭ ዜማ ሆነ፡፡ ህዝቡ እርሱ ያልተዘፈነበትን ዝግጅት ለመታደም እምቢ ማለት ጀመረ፡፡ “ቢራዻ በሪኤ” እያለ የሚደንሰው ወጣት የሌለበትንም ዝግጅት ከማየት አፈገፈገ፡፡ ምን ይሄ ብቻ? የድሬ ዳዋ ህዝብ በስልጣኑ የታዳጊውንም ስም “ከዓሊ መሐመድ ሙሳ” ወደ “ዓሊ ቢራ” ቀየረው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ “ዓሊ ቢራ” የታዳጊው መጠሪያ ሆነ፡፡ 
*****
“ዓሊ ቢራ” የሚለው ስም የተከሰተው ከላይ በተገለጸው ሁናቴ ነው፡፡
ለዚያ ቀጫጫ ልጅ መታወቅ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ያደረገው የመጀመሪያ ዘፈኑን ጽፎ የሰጠው ደራሲ ነው፡፡ በቀጣዮቹ ዓመታትም ይኸው ደራሲ እጅግ ውብ የሆኑ ግጥሞችን እየጻፈ በዓሊ ቢራ በኩል ለህዝብ ጆሮ አድርሷል፡፡ ዝንተ-ዓለም የማይረሱ ሆነው ከኛ ጋር ያሉትን እንደ “ኮቱ ያ ቢፍቱ ቲያ”፣ “ጉያን ጉያዻ ኢኒኑ”፣ “ኮጳ ኮ ነዺፍቴ”፣ “ነጃለቴ ገመ ኬቲን”፣ “ነቲ ሂንጀባቲን ገራ”፣ “ሲንበርባዳ”፣ “ሲጃሌ ጃለላ ዴይማ”፣ “ወል አርጉ ዋ ሂንኦሉ”፣ “ያደ ኬቲን ሾረርካዌ”፣ “ያ ሂሬ ሂሪያ”፣ “ሂንያዲን ሂንያዲኒ”፣ “አማሌሌ” የመሳሰሉ ምርጥ ዜማዎችን የጻፈው እርሱ ነው፡፡ 
ያ ከዓሊ ቢራ ጀርባ የነበረው ታላቅ የጥበብ ሰው “አቡበከር ሙሳ” ይባላል፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ በኦሮሞ ህዝብ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ታላቅ ስፍራ የሚሰጠው ገጣሚ፣ ደራሲ፣ ጋዜጠኛ፣ ጸሓፌ-ተውኔትና የታሪክ ምሁር ነው፡፡ አቡበከር ሙሳ በ1935 በሀረርጌ ክፍለ ሀገር በኦቦራ (ወበራ) አውራጃ ከደደር ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው “ሌሌ ገባ” በተሰኘች ትንሽዬ የገጠር መንደር ነው የተወለደው፡፡ በልጅነቱ እስላማዊውንና የዐረብኛ ቋንቋ ትምህርቶችን አጥንቷል፡፡ ከዚያም ለተሻለ ትምህርትና ለስራ ፍለጋ ሲል የገጠሩን ህይወት ትቶ ወደ ድሬ ዳዋ ከተማ ተሰደደ፡፡ እጅግ በጣም ፈጣን አዕምሮ የነበረው ታዳጊ በመሆኑ በድሬዳዋ ከተማ በሚገኝ አንድ መድረሳ በዐረብኛ ቋንቋ አስተማሪነት ተቀጠረ፡፡
እንግዲህ አቡበከር ሙሳ የመድረሳውን ስራ እየሰራ ነው ከሁለት ጓደኞቹ ጋር የ“አፍረን ቀሎ”ን ቡድን የመሰረተው፡፡ ይህ ሰው ለስምንት ዓመታት ቡድኑን በሊቀመንበርነት በመምራት በኦሮምኛ ኪነ-ጥበብ እድገት ላይ ከፍተኛ አሻራ ጥለው ያለፉ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ 
(ይቀጥላል)
----
ማስታወሻ፡ ይህ ታሪክ “ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ዲሬ ዳዋ” ከተሰኘው የኔ መጽሐፍ የተቀዳ ነው

#ወሎ ደዌ ዶዶታ መስጂድ/masgiida doddota dawwee!

☾︎★የዶዶታ መስጂድ ☾︎★
★★★★★★★★★★
ይህ መስጂድ በኦሮሞ ብ/ዞን ደዌ  ሀረዋ ወረዳ በመዲኔ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን፣ ከከሚሴ በስተ ምስራቅ በኩል በ40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የገኛል። የዶዶታ መስጂድ ያረፈው በኮረብታማ ቦታ ላይ ሲሆን አካባቢው እንደ ግራር ባሉ የበረሀ ዛፎች የተከበበ ነው።
መስጂዱ በሂጂራ አቆጣጠር 1176 እንደተሰራ እና 360 አመት በላይ እድሜ እንደሆነው ይነገራል። መስጂዱን የሰሩት " አባ አሲያ"/ አባስያ/ ይባላሉ።   መስጂዱ ሰርተው ለማጠናቅ 18 አመት እንደ ፈጀባቸው  ይነገራል።   አሰራሩ በአራቱም መአዘን በሰው አቅም ተንቀሳቅሰው ተገጠሙ ለማለት በሚያስቸግሩ በትላልቅ ድንጋዮች የተሰራ ግምብ ነው። የመስጂዱ ግድግዳ ውፍረት 3 ሜትር ያህል በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል። ጣራያው በ27 ምሶሶዎች ላይ እንጨት ርብራብ የተሰራ ሆኖ ከላይ በኮረት ተደልድሏል ። በመስጂዱ ጣሪያ ላይ የጸሀይ ብርሀን ማስገቢያ ያለው በመሆኑ መስጂዱ ጨለማ እንዳይሆን ይረዳል። ★★★★★★★★★★★★★★★★★★
ይህ መስጂድ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ እንዲይዝ ካስቻለዉ አንኳር ጉዳይ መካከል:- 
• በአካባቢው የሸሪአ ስርአት እንዲተገበር ጥረት የተደረገበት:
• የሀይማኖት ትምርት በስፋት ሲሰጥ የነበረበት መሆኑ:
• አያሌ እድሜ ጠገብ በእጂ የተጻፉ  ሀይማኖታዊ መፀሀፎች በቅርስነት በውስጡ መያዙ በጥቂቱ የሚገለፁ ናቸው።
ይህ መስጂድ ጥንታዊ በመሆኑ በዉስጡ በርካታ መፀሀፍቶች ይገኛሉ። ለምሳሌ ያክል ከ200 አመት በላይ እድሜ ያለው በእጂ የተፃፈ ቁርአን ይገኛል። 
መስጂዱ የእስለምና ሀይማኖት በስፋት እንዲዳረስ የተደረገበት በመሆኑ ልዩ ቦታ እንዲሰጠው ያደርገዋል። ህረተሰቡ ቅርሱን በመጠበቅ የመንከባከብ ስራ መስራት ይጠበቅበታል።  ★★★★★★★★★★★★★★★★★★
ለቀጣይ ህብረተሰቡን በማስተባበር መሰረተ ልማት እንዲሟላ በማድረግ እና በዝርዝር እንዲጠና በማድረግ የማስተዋወቅ ስራ መሰራት አለበት።

#የጁ_#ወረ ሴህ/# worseh

"የጁ ምድር
by miky sultan.
በ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ኦሮሞ  አንዱ የ የጁ ኦሮሞ ነው።
በ 13ኛው ክፍለ ዘመን በፊት በተፃፈው ታሪክ  ይመሰክራል ፡
እንደ ታሪክ ፃፈው የየጁ ኦሮሞ  ከ ቦቆጂ ከምባሉ ጎሳዎች እንደሆነ  ምን አልበት፣ የ የጁ ኦሮሞ የ ሙስሊሞች የ ወረ ሴህ( ሼህ) ነገድ ይሆናሉ። ።በመጀመሪያ ከ ቦቆጂ ጎሳዎች  የመጀመሪያዎቹ ,ቁንቢ,መርሶ,ሸካ,አባ ድምበር መልዬ, ገመዳና እልማን ኦሮሞ ተብሎ መጣራተቸውን ይነገራል።ቁንቢ መቻሬ በምትባል አሁን በስተ ምስራቅ  ወልደያ የምትገኝ  ይኖሩ ነበር ። አባ ድምበር  መሊዬ ደግሞ ጉባላፍቶ ላይ ይኖሩ ነበር ።የ የጁ ኦሮሞ የዘር ሀረገቸው ወደ ኀለ ሥቆጥሩ "ገመ ገሊ"(Gamaa gali) ወደ ምባል የሰገባሉ።የጁ በአራት ጎሳዎች ይከፈላል እነሱም :-ወራ ዶረን ቦጁ, ወራ ሩፎ ሮባ,ወራ ካሎ,ወራ ኡጊ በመባል ይጠራሉ ።
በ የጁ ሰዶማ አባቶች የ ዘር ጎሳዎቻቸውን ስቆጥሩ ወደ ካራዩ ያስገበሉ።እንዲህ ብሎ ነው የምቆጥሩት። ብዳሩ  ሀዴ ካራዩ ነጎ ኣመ ላፍቶ ገመ ገልቴ። ብሎ ዘራቸውን ያስወቀሉ።

#ዶባዓ ጎሳ/ ራያ

ዶባዓ ጎሳዎች
ዶባዎች በ ምዓራብ ሀርርጌና በ ወሎናራያ አከባቢ በበዛት ሰፍሮ የምገኙ የኦሮሞ ጎሰሰዎች ናቸው። ለምሳሌ በ ሀረርጌ ዶባዓ የምባል ወረዳ አለ፣ህዝቡም  በዶባነተቸው የምኮሩ የጀግኖች ዘር ናቸው።ኣኖሌ ጦርነት ላይ ከዶባ የተወለዱ እንደነ ያያ አሊ ስሬ፣ብዙዎች ጦርነቱን ተሳትፎ የተሰውበት የጀግና መንደርና የጀግና ግኝት ጎሳ ነው።
"Maqaan baduu mannaa mataan baduu wayya " ስም ከምጠፋ ህዬት መጠፋት ይሻላል ያሉት የዶባዓ ልጆች ናቸው።
ሰፈ ባለ መልኩ በቅርብ ቀን።

#ወሎና ራያ/ #wollo/ # wallo

ራያና ወሎ  ምን እና ምን ናቸው?
ራያ የወሎ ልጅ አይደለም።
ራያ የባሬንቱ ልጅ ነው።
Miky sultan Worsheh( barento)
*********-**********-
ባሬንቱ 7 ልጆች አሉት እነሱም:
ከረዩ፣አርሲ፣ ኢቱ፣ሁንበና፣ራያ፣የጁ፣አኪቹ ናቸው።
.
ወሎ ደግሞ የ ባሬንቱ ቅርንጫፍ ሁኖ የካራዩ ልጅ ነው። ወሎ 7 ልጆች አሉት እነሱም። ወረ ኢሉ፣ ወረ ሂበኖ፣ለገ አምቦ፣ለገ ጎረ፣ወረ ኖሌ አሊ፣ ወረ ቃሉ ፣ወረ ባቦ፣ የምባሉ ልጆች አሉት።

ስለዚህ ራያ የባሬንቱ ልጅ ነው እንጂ የወሎ ልጅ አይደለም። ወሎ 7 ልጆች ውስጥ ራያና የጁ የሉም። ራያና የጁ የባሬንቶ ልጆች ናቸው።
የካራዩ ፣የ ኢቱ፣ሁንበና፣የጁ፣አርሲ ወንድሞች።
ራያ ልክ እንደ ወሎ በሰሜን ኢትዬጵያ ሰፊውን ሜዳ መሬት ይዞ የምቀመጥ ነው።
ወሎ ውስጥ  ቱለማና መጫ ኦሮሞ ጎሳዎች አሉ። እንደነ ገላን፣ እንደነ ቦረና።
ራያ ወደ 8 ትልልቅ የጎሳ ንዑስና ፣ 15 ታነናሽ የጎሳ ቅርንጫፎች አሉት ።
የጁም የባሬንቱ ልጅ ነው።
የጁ አፍረን ( 4) የጁ ተብሎ ይጠረሉ።
የጁ በአራት ጎሳዎች ይከፈላል እነሱም :-ወራ ዶረን ቦጁ, ወራ ሩፎ ሮባ,ወራ ካሎ,ወራ ኡጊ በመባል ይጠራሉ ።
ጮሬ የጁ ሰዶማ( 30) ሶዶማ።
በ የጁ ሰዶማ አባቶች የ ዘር ሀረገቸውን ስቆጥሩ ወደ ካራዩ ያስገበሉ።
" የጁ ሰዶማ የዘር ሀረግ አቆጣጠር!!
ዋሬ
 ሀዴ
 ፣ ከረዩ
 ፣ ነጎ
፣ ኣመ
ላፍቶ
 ፣ገመ  
ገልቴ።
--------------------- በ ብዳሩ በኩል ያሉት
ብዳሩ 
ሀዴ 
ከረዩ 
 ነጎ 
 አመ 
ላፍቶ 
 ገመ 
ገልቴ።
በ ሰዶማ ያሉ የዘር ሀረጎች  ቁርቁራ ሞመጂ ወይ ሞመጂ ቁርቅራዎች በ ባቲ ወረ ዋዩ ውስጥም በብዛት  አሉ። ብዙ ቁርቁራ ሞመጂዎች ኣሉ። ሞመጂ የ ኢቱ ጎሳ ነው።

#Hortee_ Baareentummaa

Walaloo Hortee Bareentumaa!!
☆☆☆☆☆☆☆
Hortee Bareentumaa
Sab-boontoota walloo
Madda Sab-boonummaa
Raayyaa fi Azaboo
Qobboof warra Yejjuu
Ilmaan Abbaa waaxoo
Iluuf warra Hebanoo
Yaa gootoota walloo
Baabboof wayyuu
Ilmaan dhiiga tokkoo
Gabrummaa buqaasaa
Itti fufaa qabsoo!!2

Walloo biyya gootaa
Biyya gootowwaanii
Jaalattoota haqaa
Jaallawwaan qaqqaalii
Jaallan hedduu dhabnee
Kan Sabaaf kufanii
Nutti dhiise madaa
Yaadannoon isaanii
Qabsoo itti fufaa
Daandii jaallawwanii
Bilisummaa jennaa
Gumaa dhiiga Saanii
Seenaan haa yaadatuu
Jaallawwan kufanii!!2

Jaallawwan warraaqoo
Kan qabsoof kufanii
Irraaffachuun qabnuu
Jaallewwan kufanii
Dirree gubbaa Ciisaa
Lafeen jaallawwanii
Warra Ofii kufee
Xurree nuuf Saaqanii
Warra dhiiga Saaniin
Qabsicha jaaranii
Yoomuu hin dagannuu
Galata isaanii!!2

Maqaa Saanii kaafnaa
Haa yaadannuu Saanii
Jaal M/d dirree(Goota babbaas)
Hiddee Liibantichaa
Sab-boontoota Sabaa
Urjii lola keessaa
Jaal Abduu Idiris
Jaal Yuusuf M/d
Jaal Adamii Leencaa
Jaalattoota Sabaa
Burqaa Sab-boontootaa
Jaal Umar Hiddiyyee
Jaal Sayyoo Aliyyee
Qabsoo Sabaaf jecha
Goota baay'ee dhabnee
Jaal Adamii maammaa
Jaal Huuseen Sooressaa
Gumaa dhiiga Saanii
Bilisummaan baasaa
Jaal Ahmad Siraajuu
Jaal Hiddee Adamee
Jaal Huusanee Idris
Isaan kufan malee
Qabsoon hin dhaabbannee
Jaal Idiris Abduu
Jaal Badhaasoo Idiris
Warra lolee kufee
Qabsoo Saba Saaniif
Jaal mahammad Abdoo
Jaal Ahimad Idiris
Seenaan haa yaadatuu
Jaallawwan kufanii
Jaal Aluwwaa Ussoo
Jaal Huuseen Fantaa'ee
Jaallan kana Cufa
Qabsoof jecha dhabnee
Jaal Idirs mahammad
Jaal Abduu Hiddee
Jabaadhaa Saba koo
Qabsoof jecha dhabnee
Itti fufaa qabsoo
Akka hin dhaabbannee
Jaal Adam Idiris
Jaal Sayyoo Alii
 Warraaqxoota haqaa
Gootowwan qaqqaalii
Bilbilaatii jiraa
Daandiin gootowwanii
Sab-boontoota walloo
Haa yaadannuu Saanii
Yoomuu hin dagatuu
Galmeen Saba Saanii!!2

Gootowwan walloodhaa
Hedduu isaan dhabnee
Kaanis galmeef dhiifnee
Kaanis fakkiif kaafnee
Dhaamsa Sab-bootootaa
Akka hin dagannee
Irbicha diiginaa
Eegaa nuti kufnee
Qabsoo itti fufaa
Akka hin dhaabbannee
Eegaa maal Abbaasaa
Qabsoof jecha dhabnee
Aadaa du'aa taanaan
Qonnee wal-Awwaallee
Murticha diiginaa
Eegaa nu dabarree
Jechuun dhaammatanii
Warri qabsoof dhabnee!!2

Dhaamsa gootowwanii
Sinitti dhaammannee
Imaanaa jaallewwan
Akka hin dagannee
Sab-boontoota walloo
Jaallan hidduu dhanee
Qabsoo itti fufaa

Sunday, February 7, 2021

# አፄ ቴውድሮስ# ጎንደር ኃውልት

ጎንደር ያለው የአፄ #ቴዎድሮስ ኃውልት ይገርመኛል! አፄው ጎንደር ላይ ከፈጸሙት ጭካኔ አንፃር ከተማዋ ለምን እንደምታገናቸው አይገባኝም! በጎንደር ካደረሱት ጭፍጨፋ የተነሣ ውሾች እንኳ የሰው ሥጋ መብላት ለምደው እንደነበር ተጽፏል። 😱
.
#ፌክኢትዮጵያኒስቱ የሚያንቆላጵሳቸው #ቴዎድሮስ ደም የተጠናወታቸው አረመኔ ገዢ እንደነበሩ ሊያሳይ ከቻለ  እስቲ «ኪነት ያገነነው አፄ» ከተሰኘው መጽሐፍ ካገኘሁት ሁለቱን ልጥቀስ... አፄው ጎንደርን እንዲህ ነበር ያደረጓት👇
.
.
«ክረምቱ ሁሉ ወታደሩ በመከራ ከረመ፤ የሚቃጠልም ሲያቃጥሉ፣ የሚደበደብም ሲደበደብ ከረመ። በዚያው ጊዜ ውሾች ሰው አላሳልፍም እያሉ እንደዱር አውሬ ሁነው ነበር፤ የሰው ሥጋና የከብት ሥጋ ለምደው።» 
.
ሉዊጂ ፉሲላ | ያጤ ቴዎድሮስ ታሪክ | ገጽ 40
.
.
«የጎንደር ሲራራ ነጋዴዎች የሚስቶቻቸውን እና በእጃቸው የሚገኘውን ወርቅ እንዲሰጧቸው አዘዙ። ወርቁን ካሰረከቡ በኋላ እጅና እግራቸውን ታስረው በአንድ ቤት ውስጥ ታጉረው በእሳት እንዲቃጠሉ አደረጉ። በአጠቃላይ ጎንደር ከተማን በእሳት አወደሟት። አፄ ቴዎድሮስን በደማቅ ሁኔታ ለመቀበል ወጥተው የተሠለፉት እንኳን አልቀሩም። ሁሉም ቤቱ እየተዘጋበት በእሳት እንዲቃጠል አድርገው ከተማይቱን አወደሙ። በእሳት በጋየችው ከተማ ፍርስራሽ አመድ ላይ የነገሠው የሙት መንፈስ ብቻ ነበር።» 
.
ፊሊፒ ማርሲዲን፤ ገጽ 313
.
የአካባቢው ኤሊት «ያጎነበሰው ነፍጥ ዘቅዛቂ ሽማግሌ ስድብ ነው» ብሎ ያስነሣ መሆኑን ስታስታውስ ነው የቴዎድሮስ ፍቅር  እና ኃውልት ግራ የሚገባህ! #Ironic ይላል ፈረንጅ ☺️

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...