Translate

Wednesday, February 2, 2022

#አባዬ" የሚለው ቃል የአማርኛነት መሠረት የለውም

"አባዬ" የሚለው ቃል የአማርኛነት መሠረት የለውም ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ይህን ጽሑፍ ለመጻድ ያነሳሳኝ የ3000 ዓመት የድንጋይ ሐውልት ላይ "አባዬ" የሚል የአማርኛ ቃል ተገኘ ተብሎ የተለቀቀው ቪዲዮ ነው። ፎቶውን እንደምትመለከቱት ሀውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍ [አባዬ] የሚል ይመስላል እንጂ [1አበየo] የሚል ነው። ስለዚህ ይመስላል በሚል ካልሆነ በስተቀር ቃል በቃል [አባዬ] አይለም። ስለሆነም ከዚህ ቀጥሎ የማቀርበው ጽሑፍ ሐውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍ [አባዬ] እንደሚል ታስቦ የተፃፈ ነው። ~~~ "አባዬ" አማርኛ ነው ብለህ መደምደም አትችልም። ግእዝ ከመካከለኛው ምስራቅ እንደመጣ ይታወቃል። እናም ከሆን ግእዝ ሊሆን ይችላል ብለህ መገመት ይቻላል። ግእዝም ቢሆን ግን ከየት አገኘው የሚል ጥያቄ ይነሳበታል። ምክንያቱም ግእዝም ቢሆን በአለም ከአሉ ቋንቋዎች መካከል በእድሜ ትንሽ ነው። ተጨፍነህ የመልአክ ቋንቋ ነው ብለህ ካልተቀበልከው በስተቀር ማለቴ ነው። ~~~ በግእዝ [እም] "እናት" ብለን [እምየ] "እናቴ" እንላለን፡ [አባ] "አባት" ብለን [አባየ] "አባቴ" እንላለን። እናም ቃሉ ግእዝ ሊሆን ይችላል ብለን ማሰብ ትክክል ነው። ማረጋገጫ ጥናት ቢያስፈልፈውም። ~~~ [አባዬ] የሚለው ቃል አማርኛ ሊሆን አይችልም። ትላንት የተፈጠረው አማርኛ በምን ተዓምር ነው የ3000 ዓመት የድንጋይ ሐውልት ላይ ሊፃፍ የሚችለው? አማርኛ ከቅማንትኛ ወጥቶ የተወሰኑትን ቃላትና አገብብ ከግእዝ ጋር በማዳቀል የተፈጠረ አዲስ ቋንቋ እንጂ ጥንታዊ ቋንቋ አይደለም። ~~~ ሲጀመር አማርኛ የጽሑፍ ቋንቋ የሆነው በ19ኛው ክ/ዘ ሁለተኛ አጋማሽ በአፄ ቴወድሮስ ነበር። ለዛም በመከራ። ፊደሎቹ ከግእዝ የተዋሱ ነበሩ። እንዲሁም አማርኛ የቋንቋ ውጥንቅጦችን ቀላቅሎ ስለሚጠቀም የሚጠቀማቸው ቃላት ስርዎ ማንነታቸውን ማግኘት በጣም ከባድ ነው። ~~~ አማርኛ [አባት] ብሎ እንዴት ነው [አባዬ] የሚለው? በምን ሒሳብ? ልክ [እናት] ብሎ "እናቴ" ወይም "እናትዬ" እንጂ "እናዬ" እንደማይለው ማለት ነው። እናም አማርኛው ማለት የነበረበት [አባት] ብሎ [አባትዬ] ወይም [አባቴ] እንጂ [አባዬ] አይደለም። ምክንያቱም የቋንቋው ሕግ ስለማይፈቅድለት። አማርኛ እንዲህ ዓይነት ውዥንብርን የሚያስተናግደው ዋናው ምክንያት የብድር ብቻ ቋንቋ ስለሆነ ነው። ~~~ ይሄን ክርክሬን የበለጠ ለማጉላት አንድ ሌላ አማርኛዊ ውዥንብር ላሳያችሁ። አማርኛ ጥሬ ዘር ስሞችን ከዛው ከሚጠቀመው ግስ ነው የሚፈጥረው። ለምሳሌ [ሞተ] ብለን "ሞት"፡ [አፈቀረ] ብለን "ፍቅር"፡ [ዋለ] ብለን "ውሎ"፡ [በላ] ብለን "መብል"፡ [ጻፈ] ብለን "ጽሑፍ" እንላለን። ታዲያ የቋንቋው ሕግ እንዲህ ከሆነ አማርኛ [ገመና] የሚለውን ስም ከየት አመጣው? ከየትኛው የግስ ስርዎ ቃሉ አወጣው? ከየትም አላወጣውም። አማርኛ ]ገመና]ን በቀጥታ ከቅማትኛ ወስዶ ነው ራቁቱን የሚጠቀመው። [ገመና] መሠረቱ ቅማንትኛው ነው። በቅማንትኛ [ገም-] "ወረደ" ከሚለው ግስ [ገምና] "መውረድ"፡ [ገምንታ] "አወራረድ"፡ [ገመና] "ውርደት"፣ ወዘተ የሚሉ ስሞች ይፈጠራሉ። አዎ [ገመና] ማለት "ውርደት" ማለት ነው። አማርኛ እንዲህ አይነት ቃላትን አብዝቶ ያለ ስርዎ ቃል ይጠቀማል። ምክንያቱም አማርኛ የትላንት ፈጠራ ስለሆነ ነው። [አባዬ] የሚለው ቃልም ልክ እንደ [ገመና] አማርኛዊ መሠረት የለውም። በመሆኑም የድንጋይ ላዩ [አባዬ] ከታሪካዊ ዳራና ታሪካዊ መቼት ባሻገር በቋንቋው ኀልወተ ታሪክና ባህርይ አንጻርም አማርኛ ይሆናል ብሎ ማሰብ የሞኝነቶች ሁሉ ሞኝነት ነው። ~~~ ሌላው ንግሥት ማክዳ ወይም የሳባ ግሥት የቅማንት ንግሥት እንደነበረች ታሪክ ይመሰክራል። ስለዚህ ቋንቋው ቅማንትኛ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። ለምን ቢባል በቅማንትኛ [አባ] ማለት "አባት" ማለት ሲሆን [አዬ] ማለት ደግሞ "የኔ"፡ "ሆይ" ማለት ነው። እናም [አባዬ] ማለት "አባቴ"፡ "አባት ሆይ" ማለት ነው። እዚህ ላይ ይህን መረጃ ቅማንት ውስጥ ከሚነገር አንድ የቃል መረጃ ጋር ማገናኘት ይቻላል። "ቅማንቱ መጽሐፉን ጥሎ በልቤ ነው ማድረው ብሎ መጽሐፉን ስለጣለ ነው የጽሑፍ መረጃ የሌለው" የሚል የትውፊት መረጅ አለ። እናም እኒህ የቅማንትን ታሪክ እየዘረፉ ለራሳቸው ሲያድድርጉ የኖሩ ሌቦች "ቅማንት በልቡ ብቻ ነው የሚያድረው" የምትለዋን የፈጠራ ታሪክ ፈጥረዋታል የሚል መደምደሚ ሊያመጣ ይችላል። "ቅማንት ከግብጽ መጣ" የሚለው መሠረተ ቢስ የፈጠራ ድስኩራዊ ወግና "ቅማንት ሕንፃ ሊሰራ የመጣ ባርያ ነው" የሚሉት ሁሉ አሻጥር ናቸው። የቅማንትን ጥንታዊነትና የታሪክ ባለቤትነት ለማጥፋት የሚፈለሰፉ የፈጠራ ታሪኮች ናቸው። ይሄም ታሪክን ዘርፎ የራስ ከማድፈግ ጋር አብሮ የሚሄድ አሻጥር ነው። ያገው ቋንቋ የጋኔን ቋንቋ ነው የሚለውም ከዚሁ ጋር አብሮ የሚሄድ አሻጥር ነው። ~~~ እውነቱን ለመናገር አሁን የግእዝ ፊደል ተብሎ የተዘረፈው ሃብት የቅማንት እንደነበር የበለጠ ጥርጣሬየን አጉልቶታል። እናም "ግእዝ ፊደሉን የወሰደው ከቅማንትኛ ነው" የሚል ንድፈ ሃሳብ (hypothesis) መሥርቶ ቀጣይ ጥናቶችን ማድረግ ግድ ይላል። ብዙ ሰፋፊ ምርምሮችን ማድረግ እንዳለብምን ያሳያል። ቅማንቱ ቅዱስ ያረን ዜማውን ዝም ብሎ ከምድር የፈጠረው አልነበረም። ታሪክ አጥፊዎች እንደሚሉትም ከሰማይ አልወረደም። ቀደም ብሎ አባቶቹ ቅማንት ከመዘናዎች ሲያዜሙት የነበረ ነው። በቅማንት የሕገልቡና አስተምህሮ ውስጥ የነበረውን ዜማ ነው ቋንቋ ቀይሮ የጻፈው። እናም የተሰረቁ የጥንት የቅማንት መጽሐፍት የሆነ ቦታ ሊገኙ እንደሚችሉ ይህ ጥሩ ማስረጃዊ ፍንጭ ይሰጣል። ~~~ በእርግጥም ሀውልቱ 3000 ዓመታት እድሜ ካለው ከቅማንት ቋንቋ አይወጣም። ምክንያቱም አክሱም ላይ ተገኙ የተባሉት የድንጋይ ላይ ጽሑፎች በመጀመሪያ በመጀመሪያ ድምፅ ብቻ የተጻፉ ነበሩ። "አክሱም" ለማለት [አከሰመ] ብለው የተጻፉ ናቸው። ይሄን ከ[አባዬ] ጋር ስታነጻጽረው አይገናኝም። ~~~ ሌላው ደቡብ አረቢያ በአፄ ካሌብ ዘመን በኢትዮጵያ ግዛት ስር ነበር። ታዲያ በዚያ ጊዜ ወደ ቦታው የሄደ ኢትዮጵያዊ ገዢ የድንጋይ ሐውልቱ ላይ አጽፎት ላለመሆኑ አሳማኝ ማስደጃ ማቅረብም ከባድ ነው። ብቻ ብዙ ጥናት ይጠይቃል። እርግጠኛ የምንሆነውን ግን ጽሑፉ ጭራሽ አማርኛ አለመሆኑን ነው። አማርኛ የ750 ዓመት ሙጫቅላ ቋንቋ ነው። አይደለም በድንጋይ ላይ በብራና ላይ የተጻፈ የአማርኛ ቃል ከ19ኛ ክ/ዘ በፊት ማምጣት አይቻልም። Website:-https://mikysultan.blogspot.com/ Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU Telegram:- t.me/Oromo_ geography

#ግሼ አባይ ፣ ምነኛ ነው?

ግሼ አባይ፣ ምንኛ ነው? ግሴ አባይ ማለት በቅማንትኛ ግልገል አባይ ወይም ድንክ አባይ ማለት ነው። ደብተራው ግን ሊያጥፋፋ ይዳክራል። እውነት የትኛውንም ያክል በገድል ልትሸፍነው ብትሞክር አይሸፈንም። ~~~~ ግሼ ዓባይ፡ ምንኛ ነው? ~~~~~~~~~~~~ መቼም የእኛ አገር ውስጥ ብዙ ነገሮች ትክክለኛ ማንነታቸውና የስማቸው ትርጉም በውል አይታወቅም። ምክንያቱም ሀገሪቱ ላለፉት አያሌ ምእት ዓመታት የሆነ የታሪክ ነቀዝ አፍርታ ትክክለኛውን የታሪካችን ፍሬ በልቶ እንክርዳዱንና ግርዱም ጥሎልን በመሄዱ ነው። ከሰዎች የስም ስያሜዎች እንኳ ብንነሳ አያሌ ትርጉም የለሽ ስሞች ሞልተዋል። ለምሳሌ ጋሼ፡ ፈንቴ፡ ፈንቲ፡ ወሰንጌ፡ ጀጃው፡ ገልሞ፡ ኮልቫ፡ ጉርባ፡ አስሜ፡ ሰጤ፡ ወዘተ የሚሉትን ስሞች ብንመለከታቸው በአማርኛ፡ በትግርኛ፡ በግዕዝ ወይም በሌላ ማንኛውም ቋንቋ ትርጉም የላቸውም። ይሄ ለምን ሆነ? የሚል ጥያቄ ስናነሳ መልሳችን የሚሆነው "የታሪክ ቀበኞች የሆነን ታሪካዊ ሕዝብ ደዝባ ለማጥፋት ስለሠሩ ነው" የሚል ይሆናል። ~~~ ይሄ ትርጉም አልባነት በሰዎች ስታሜዎች ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን በተለያዩ መልክዓ ምድራዊ ስያሜዎችም ላይ ጎልቶ ይታያል። ለምሳሌ ከመካከለኛው ኢትዮጵያ እስከ ግብፅ ድንበር ያሉ የተለያዩ መልክዓ ምድራዊ ሥያሜዎችን ስንመለከት ከላይ በጠቀስኳቸው ቋንቋዎች ምንም ዓይነት ትርጉም የላቸውም። ሸዋና ሸዋ ውስጥ ያሉ ቦታዎች፡ ጎጃምና ጎጃም ውስጥ ያሉ ቦታዎች፡ ጎንደርና ጎንደር ውስጥ ያሉ ቦታዎች (ካና ሰጌ)ን ጨምሮ፡ ወሎና ወሎ ውስጥ ያሉ ቦታዎች፡ ትግራይና ትግራይ ውስጥ ያሉ ቦታዎች፡ ኤርትራና ኤርትራ ውስጥ ያሉ ቦታዎች፡ ወዘተ አብዛኛዎቹ ብዙዎቻችን በምናውቃቸው ቋንቋዎች ትርጉም የላቸውም። ለምን? እውን ትርጉም የሌላቸው ናቸውን? ~~~ በእርግጥ ትርጉም አላቸው። ትርጉማቸውም አንዳንዶች ራሳቸውን አጥፍተው ሌላውን ለማጥፋት ታሪክ የሚደልዙና የሚደርቱ የታሪክ ድሪቶ ጸሓፍት እንደሚሉት በአረብኛና በኢብራይስጥ ሳይሆን በጥንታዊው የሰው ልጆች አባት ቋንቋ በቅማንትኛ( ኬሜንት) ኩሽ የሚፈታ ነው። ይሄን እውነታ ስጽፍ ብዙ የውሸት ታሪክ ተስፈኞች የተለመደ የስድብና የፉከራ መርዛማ ምላሳቸውን መቀሰራቸው የተለመደ ነው። በእርግጥ እነሱ ስለተሳደቡና ስለሚዝቱ ፈርቼ እውነትን ከመናገር አልገታም። እውነት ያሸንፋልና ለኢትዮጵያ የኋላቀርነትና የድንቁርና መሠረት የሆነውን የታሪክ ድሪቶ ማፈራረስና እውነታን የማውጣት ኅሊናዊ ኃላፊነት ስላለብኝ በህይወት እስካለሁ ድረስ እውነታውን ከማውጣት የሚያግደኝ ፉከራም ሽለላም፡ መተትም ድግምትም አይኖርም። እውነት ከኮልኮሌያም ጠንቋዮችና ደብተራዎች በላይ ናትና አልፈራም። ~~~ በርእሰ ጉዳዩ ላይ ወደ አነሳሁት "ግሼ ዓባይ" ልመለስ። ዓባይ የሚለው ቃል በኋላ የተሰየመ ከግዕዙ "ዓበየ" ተለቀ ከሚለው ግስ ወጥቶ የተሰጠ ስያሜ እንደሆነ ደብተራው ጽፏል። በመሆኑም ዓባይ ትልቅ እንደማለት ነው። ትግርኛውም "ዓባይ ገረብ፡ ዓባይ ገለመሌ" ሲል ይሰማል። የዓባት ጥንታዊ ስሙ ግን "ጊዮን" ነው። ለዚህ ማስረጃ በታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 2 ቁጥር 13ን ተመልከትልቹ። እንዲህ ይላል። "ወስሙ ለካልእ ፈለገ ጊዮን ውእቱ ዘየዐውድ ኩሎ ምድረ ኢትዮጵያ" ይላል። ትርጉሙም "የሁለተኛው ስሙ የጊዮን ወንዝ ይባላል፡ እርሱም የኢትዮን ምድር የሚከበው ነው" ማለት ነው። ~~~ ለመሆኑ "ጊዮን" ማለት ምን ማለት ነው? "ጊዮን" ከ"ሌጊዮን" ጋር የሚያያዝ ትርጉም አለው። "ሌጊዮን" ማለት የአጋንንት መንጋ ማለት እንደሆነ ቅዱስ ወንጌላችን ይነግረናል። ነገር ግን በምን ቋንቋ መሆኑን አናውቅም። ያም ይሁን ይህ ግን "ሌግዮን ማለት በቅማንትኛ "መቶ አጋንንት" ማለት ነው። (ሊጝ + ጊዮን = መቶ + አጋንንት)። ይህ የሚያሳየን "ሌጊዮን" ማለት የ100 ጋኔኖች መንጋ በአንድ ብርጌድ ማለት መሆኑን ነው። ~~~ ይሄ "ሌጊዮን" የሚባለው ርኩር መንፈስ በጣናው ዘጌ ለብዙ ዘመናት ሰዎችን ነጭ በሬ እና ጥቁር ዶሮ እያሳረደ ሲመለክ የኖረ የዲያብሎስ መንፈስ ነው። ዛሬም ድረስ ጣና ሰው ሲበላ የአካባቢው ሰው የዋጠውን ሰው አስከሬን ከጣና የሚረከበው ጥቁር ዶሮ አርዶ ወደ ሐይቁ በመወርወር ነው። ይሄን በተመለከተ ከዚህ በፊት "ካና ሰጌ" በሚል ርእስ የፃፍኩትን ጽሑፍ ማንበብ ጥሩ ነው። የቀደሙ ቅማንቶች ለምን ይህን ወንዝ "ጊዮን" ወይም "አጋንንት አሉት?" ብለን ስናስብ ብዙ ታሪካዊና ስነልሳናዊ ምርምሮችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን መረዳት ግድ ይላል። እንዲያው ኅሊናየ የሚጠረጥረውን ለመናገር ያክል ግን ከላይ ካነሳሁት በአድ አምልኮት ጋር መያያዙን እምብዛም አልጠራጠርም። ዙሮ ዙሮ ግን ትርጉሙ ምንም ይሁን ምን "ጊዮን" አሁን "ዓባይ" ብለን የምንጠራው የአንድ ትልቅና ረዥም ወንዝ ሥያሜ ነው። ~~~ ዓባይ ከሚለው ወንዝ ላይ በመጨመር የምንጠቀምበው "ግሼ" የሚለው ስም አጎላማሽ ወይም አኮሳሽ ቅጽል ምን ማለት እንደሆነ ድግሞ ከዚህ ቀጥለን እንመልከት። "ግሼ" የሚለው ቃል ብዙዎቻችን ደጋግመን እንሰማዋለም። "ግሼ ዓባይ፡ ግሼን ደብረ ከርቤ፣ ወዘተ" እየተባለ ሲጠራ እንሰማለን። በነገራችን ላይ "ግሼን" ማለት የ"ግሼ" ብዙ ቁጥሩ መሆኑን ማሳሰብ እፈልጋለሁ። ~~~ በቅማንትኛ "ግሼ/ግሴ" ማለት "አጭር፡ ድንክ፡ በአካል ትንሽ የሆነ" ማለት ነው። ቅማንቶች "ድንክ ሰው" ሲያዩ "ግሴ ይር" ይሉታል። "ድንክ አልጋ" ለማለትም ደግሞ "ግሴ አርግ" ይላሉ። ቃሉ የስም ገላጭ ወይም ቅጽል ነው። ከስም ጋር እየገባ ስምን ይገልፃል። ለዚህም ነው "ግሼ ዓባይ" የሚባለው። የሆነን የዓባይ ክፍል ከሌላው የዓባይ ግፍል ለመለየት ይረዳ ዘንድ አባቶቻችን ዓባይ በሚለው ስም ላይ "ግሴ" የሚል ቅጽል ቀጽለውበታል። ~~~ "ግሴ ዓባይ" ወይም "ግሼ ዓባይ" የሚለውን ቃል በቃል ስንተረጉመው "ድንክ ዓባይ፡ ትንሹ አባይ፡ አጭሩ አባይ" ማለት ነው። ይሄ የዓባይ ስያሜ የሚያገለግለው ከዓባይ ምንጭ ከሰከላ (ሰቀላ) እስከ ጣና ዘጌ (ካና ሰጌ) ላለው የዓባይ ወንዝ ክፍል ብቻ ነው። ይሄን የዓባይ ክፍል የአካባቢው ሰው በተለምዶ "ግልገል ዓባይ" እያለ ይጠራዋል። ቢኮሎ (መሬት ሰብሮ) ዓባይ የምትባለው ትንሽዬ ከተማ ደርሳችሁ " ይህ ወንዝ ማን ይባላል?" ብላችሁ ማንኛውንም ሰው ብትጠይቁ ያለምንም ጥርጥር "ግልገል ዓባይ ይባላል!" ይሏችኋል። ይሄ ትክክለኛው የ"ግሴ/ሼ ዓባይ" ትርጉም ነው። "ግልገል ዓባይ" ማለትና "ትንሹ ዓባይ" ወይም "ድንኩ ዓባይ" ማለት አንድ ናቸው። ግልገል ከእናቱ ወይም ከአባቱ አንፃር ሲታይ ድንክ ወይም በጣም ትንሽ ነው። ስለዚህ ይሄ የአማርኛው "ግልገል ዓባይ" እና የቅማንትኛው "ግሴ ዓባይ" ምንም ዓይነት የትርጉም ልዩነት የላቸውም። እናም "ግሴ/ግሼ ዓባይ" የሚለው ስያሜ ለ"ግልገል ዓባይ" የተሰጠ ስያሜ መሆኑን ልብ ይሏል። ~~~ የ"ግሼ/ግሴ ዓባይ" ትክክለኛው ትርጉም ይሄ ሆኖ እያላ የታሪክ ላጲስ ደብተራዎች ያልሆነ ድሪቶ ታሪክ ፈጥረው ሲንደፋደፉና ሲያደነቁሩን ይስተዋላሉ። እነርሱ እንዲህ ይላሉ፡ "አንድ የበቁ መነኩሴ ዳዊታቸውን ሰከላ ለሚገኘው የዓባይ ምንጭ አደራ ሰጥተውት ወደ ሌላ አገር ሄዱ። ከብዙ ዓመታት በኋላ ወደ ሰከላ ተመልሰው የዓባይን ምንጭ 'በአደራ የሰጠሁሽን ዳዊቴን ግሺ'! ቢሏት ምንጯ ዳዊታቸውን አውጥታ ሰጠቻቸው። ከዚህም የተነሳ ቦታው 'ግሼ ዓባይ' ተባለ" ይሉናል። ሲጀመር ይሄ አባባል በብዙ መንገዶች ስህተት ነው። 4ቱን ስህተቶች አንስቼ ላብራራ። ~~~ አንደኛው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የበቃ መነኩሴ ዳዊት አንጠልትሎ አይሄድም። የበቃ መነኩሴ ማለት ሁሉም የተገለጠለት ሁሉን ጸሎቶች በልቡ የተጻፉለት ቅዱስ ሰው ማለት ነው። ስለዚህ የዚህ ትፈታሪክ ዋና የክርክር ነጥብ ተቀባይነት የሌለው የክርክር መነሻን የያዘ በመሆኑ ታሪኩ የተፈለሰፈ ኢ-አመክንዮአዊ ነው። ~~~ ሁለተኛው ምንጯ አማርኛውን አጣማ ነው የተረዳችው። ምክንያቱም መነኩሴው "ግሽልኝ!" እንጂ "ትፊልኝ ወይም አስመልሽልኝ ወይንም አቀርሽልኝ!" አላላትም። እሱ ያላት "ግሽልኝ!" ነው። "ማግሳት" ማለት የሆነ ምግብ በልተን ወይም መጠጥ ጠጥተን ስናበቃ ከምግቡ ወይም ከመጠጡ ጋር ወደ ጨጓራችን ውስጥ የገባው አየር ተመልሶ በአፋችን ሲወጣ የሚፈጠር የድምጽ ክስተት ነው። የበላነውን ካስታወክነው ወይም ካቀረሸነው ግን ወደ ጨጓራችን ያስገባነውን ምግብ ወይም መጠጥ መልሰን ባፋችን ማውጣታችን የሚያሳይ ነው። እናም መነኩሴው ማለት የነበረበት "ግሺ" ሳይሆን "አስታውኪልኝ!" ወይም "አቀርሽልኝ!" ነበር። እርሱ በተበላሸ አማርኛ "ዳዊቴን ግሺ" ሲላት ምንጯ ከዳዊቱ ጋር ወደ ሆዷ የገባውን አየር ብቻ ቡልቅ ማድረግ ነበረባት። ነገር ግን ምንጯም እንደ አለቆቿ ቀጣፊ ነች ማለት ነው። "ግሽልኝ!" ስትባል የምታስታውክ ወይም የምታቀረሽ "ሳይጠሯት አቤት ሳይልኳት ወዴት!" የምትል ቅላጥቤ የሆነች ምንጭ መሆኗ አያስገርማችሁም!? መነኩሴውም ቢሆኑ "የሰጠሁሽ ዳዊት መልሽ!" ብሎ በቀጥታ ከማዘዝ ይልቅ ለምን "ግሽልኝ፣ ፍሽልኝ!" ማለት አስፈለጋቸው? ይሄ ሁሉ ዝባዝንኬ የሚወራው የፈጠራ ድሪቶ ታሪክ እንጂ እውነት አለመሆኑን በዚህ እንረዳለን። ~~~ ሦስተኛው "ግሼ" የሚለው ስያሜ የሚገኘው በዚህ በሰከላው የዓባይ ምንጭ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላው የሃገሪቱ ክፍሎች ይገኛል። ለምሳሌ የግሼን ደብረ ከርቤ ማርያምን ስያመ መመልከት እንችላለን። በነገራችን ላይ ቀደም ሲል እንደጠቆምኩት "ግሴ/ግሼ" (ድንክ/በጣም አጭር) ብለን "ግሴን/ግሼን" ስንል "ድንኮች" ማለታችን መሆኑን አይተናል። ለማንኛውም ግን ደብተራው ለምን "ግሼን ደብረ ከርቤ" እንደተባለ የደረተው ታሪክ ይኑር አይኑር አላነበብኩም። ሳስበው ግን ሳይደርቱ አይቀሩም። ሳገኘው አጋራችኋለሁ። በዚህ በሁለተኛው ምክንያት አንፃርም ስናየው የግሼ ዓባይ ተረት ተረት ከድሪቶነት ታሪክ አያልፍም። ~~~ አራተኛው ደብተራው ይሄን የፈጠራ ድሪቶ ታሪክ ሲደርት ምንጯ ከመነኩሴውና ከእርሷ ግንኙነት በፊት ማን ተብላ ትጠራ እንደነበር የነገረም ምንም ፍንጭ የለም። ልክ "አፄፋሲለደስ አሁን ፋሲል ግንብ የተሠራበት ቦታ ሲደርስ የበቁ መነኮሳትን በዛው ሲፀልዩ አገኝቶ የሚሆነውን ነገሩት" ብለው እንደደሰኮሩት ድሪቶ ታሪክ ማለት ነው። ምክንያቱም አሁን ፋሲል ግን የተሰራበት ቦታ "ምዝገኒ" በመባል የሚታወቅ የቅማንት የህገልኑና የጸሎትና የመስዋእት ማቅረቢያ ድግና የነበረ እንጂ የክርስቲያን መነኮሳት መኖሪያ ገዳም አለነበረው። "የበቁ የቅማንት ባቲዋዎችን አግኝቶ እንዲህ አሉት" ላለማለት ዝም ብለው ወደ ራሳቸው መደረታቸው ልማድ ነውና እንዲህ ሲያደርጉ ኖሩ። የግሼውም ተረት ተረት "ግሴ/ግሼ" ቅማንትኛ ነው ላለማለት ያለፈውን እውነተኛ ስያሜ አይናገሩም። ዓላማቸውም የቀደመውን እውነተኛ ታሪክ ማጥፋት ስለሆነ ፈጠራቸውን እንጂ የቀደመውን አይነግሩንም። ለመንገርም ወኔና ሞራል የላቸውም። ~~~ ይሄ የግሼው ተረት ተረት እነዚህ ደብተራ ዘኮልኮሌና ዘዝባዝንኬዎች በምን ያክል ደረጃ የኢትዮጵያን ታሪክ ገድለው በትልቅ የድሪቶ ታሪካዊ ጉድጓድ እንደቀበሩት የሚያሳይ ጥሩ አብነት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ ሕዝቦችና ታሪኮቻቸው እንዲህ ተደርጎ በመቀበሩ ምክንያት በድንቁርና አዙሪት ውስጥ ወድቀን ተቸግረናል። ታሪካዊ፡ ባህላዊ፡ ማህበራዊ፡ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ሕይወታችን ሁሉ እንደተጎለጎለ ልቅ ዐይኑ ጠፍቶብን እንደራገማለን። በዚች ሃገር እርስ በርስ መገዳደል የተጀመረው በእነዚህ የታሪክ ድሪቶ ጎታቾች መፈጠር ምክንያት ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። እነዚህ ናቸው በህዝቦች መካከል ክፍፍልን የፈጠሩት። ያልሆኑትን ሰልሙነው ቅጥቅጥ ሰሎሞናዊያን ሆነው ሌላውን በግደል ጀመሩ። መድሃኒቱ አሁኑኑ ነቅተን ወደ ትክክለኛ ታሪካችን መመለስ ነው። ደብተራው በራሱብቁመቱና ወርዱ ልክ ሰፍቶ ያለበሰንን የታሪክ ድሪቶ አውልቀን መጣል ይኖርብናል። ከደብተራ ታሪክ ካልወጣን መፍትሔ የለውም። Website:-https://mikysultan.blogspot.com/ Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU Telegram:- t.me/Oromo_ geography

#አማራነትና ሰሎሞናዊነት ሲመዘኑ

አማራነትና ሰሎሞናዊነት ሲመዘኑ ~~~~~~~~~~~~~~~~~ አሁን ሀገራችን የተፈጠረው ምስቅልቅል ታሪካዊ ዳራው ከ13ኛው ክ/ዘ የሰሎሞናዊነት የፈጠራ አፈ-ታሪክና ተያይዞ ከተፈጠረው ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው። በወቅቱ ከአክሱም ዘመን ጀምሮ ክርስትናን ወደ ቤተ መንግሥት አስጠግቶ ያላመነውን ሕዝብ መረሸን፡ መመዝበር፡ ማፈናቀልና ልዩ ልዩ የስም ማጥፊያ ስሞችን መለጠፍ በጣም የተለመደ ነበር። በተለይም በኦሪትና ሕገልቡና ተከታይ ቅማንቶች ላይ የተፈጸመው ግፍ በቃል የሚገለፅ አለነበረም። በዚህ ግፍ የተመረሩት የኦሪት እምነት ተከታይ ቅማንቶች ዮዲት ጌዲዮንን አንግሠው የመልሶ ማጥቃት ርምጃ ወስደው አክሱም ላይ ተቀምጦ ሲበጠብጥ የነበረውን ሥርዎ መንግሥት ገርስሳውታል። በዚህም ምክንያት እስከ 13ኛው መቶ ክ/ዘመን ሠላማቸውን አግኝተው ሀገሪቱንም ሠላም አድርገዋታል። ዋና ጠባቸውም በክርስትና ሰበብ ሲገድላቸው ከነበረው ከአክሱሙ የቅማንት ገዢ መድብ ጋር እንጂ ከክርስትና ጋር እንዳልነበር ግልጽ ነው። ከክርስትና ጋር ጠብ ቢኖራቸው ኖሮ ከዛግዊ ሥርዎ መንግሥት ጋር ሲዋጉና ሲገዳደሉ እንደነበር እናይና እንሰማ ነበር። ~~~ የአክሱም ስርዎ መንግሥት ሲገረሰስ ቤተመንግሥቱን ከበው ሲደሰኩሩና ሲተነኩሉ የነበሩ መለካዊያን ካህናት ፈርጥጠው ወደ ሸዋ ቅማንት በመሔድ በጥገኝነት ተቀመጡ። በዚህ ቦታ በነበራቸው ረጅም ቆይታም የሸዋን ቅማንት በእነሱ እሳቤና አመለካከት ሥር እንዲሆንላቸው ትልቅ ሥራ ሰርተው ከጎናቸው አሰለፉት። ለረጅም ዘመናት ሥልጣንን እንዴት አድገው ወደ እጃቸው ማስገባት እንደሚችሉ መንገድ ሲፈልሁ ኖረዋል። በመጨረሻም የግብፅ ኮፕት ቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ቅኝ ገዢዎቻችን ጋር በመገናኘት አንድ ተንኮል ወጠኑ። በወቅቱ የዛግዌ ሥርዎ መንግሥት ነገሥታት "እኛ በራሳችን ጳጳስ ነው መመራትና መባረክ ያለብን፡ ከግብፅ ለሚመጡ ጳጳሳት ግብርና ሥጦታ አንከፍልም። ግብፆች ይሄን የማያደርጉ ከሆነ ደግሞ አባይን እንገድበዋለን" እያሉ ይከራከሩና ተግባራዊ ርምጃዎችን ይወስዱ ስለ ነበር፣ የግብፅ ሃይማኖታዊ ቅኝ ገዢ ደብተራዎች የዛግዌ ሥርዎ መንግሥትን ገልብጠው ለሌላ ተላላኪ ቡድን ማስረከብ ፈለጉ። በዚህ ጊዜ ከሸዋው ደብተራ ተክለሃይማኖት ጋር ይገናኛሉ። የዛግዌን ሥርዎ መንግሥት ገርስሰው መንግሥትን ወደ ሸዋው የደብተራ ቡድን በሚያሸጋግሩበት ሁናቴ ተወያይተው ተስማሙ። ~~~ የግብፅ ሃይማኖታዊ ቅኝ ገዢዎች ክብረ ነገሥት የሚባል የድራማና ተውኔት መፅሃፍ እንዲያዘጋጁ እነ ተክለሃይማኖትና ሞአ እየሱስ ይህን አፈታሪክ በሃይማኖት ስብከት አሥመስለው በህዝቡ ዘንድ ለማስረጽ ተስማሙ። የአፈ ታሪኩ ዋናው ጭብጥ "በኢትዮጵያ መንገሥ ያለበት ትክክለኛው ዘር የሸዋው ዘር ነው። ምንያቱም በፈጣሪ ከተቀባው ከእስራኤላዊው ንጉሥ ሰሎሞን ዘር የሚመዘዘው ይህ የሸዋው የንግሥት ማክዳ ልጅ የቀዳማዊ ምኒልክ ዘር ስለሆነ ነው። የዛግዌ ሥርዎ መንግሥት ከንግሥት ማክዳ ገረድ የተውለዱት አገዎች የመሠረቱት ስለሆነ እግዚአብሔር አልተቀበለውም።" የሚል ነበር። መጽሐፉን ግብፃዊያን በአረብኛ ጽፈው ለነተክለሃይማኖት ሰጧቸው እነ ተክለሃይማኖትም ወደ ግዕዝ አስመልሰው ይህን የፖለቲካ ድስኩር ሃይማኖት አስመስለው በመላው ሃገሪቱ ሰበኩት። እንዲያውም "ጋኔን መሀሮሙ ልሣኖሙ ለሰብአ አገው እስም ሰብአ አገው እኩያን እሙንቱ።" እያሉ አገዎችን ከዲቃላነት ፕሮፓጋንዳ በተጨማሪ "ጋኔኖች ናቸው፡ ቋንቋቸውም የጋኔን ነው" እያሉ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳና መርዝ ረጩ። ለምንድነው የአገው ቋንቋን ጋኔን አስተማረው ያሉት? ምክንያቱም በዛ ጊዜ አዲሱ የወታደሩና የወዲላው ቡድን ቋንቋ አማርኛ ገና ዳዴ እያለ የነበረ ስለሆነና ሕዝቡም ይህን የወዲላ ቋንቋ መናገር ስለማይፈልግ አሸማቀው አማርኛ እንዲናገር ለማድረግ ነው። ቋንቋውን ሲጥልላቸው በቀላሉ የአገውና ቅማንት ማንነቱን አስጥለው "ሰሎሞናዊ ነህ" ይሉታል ማለት ነው። ሕዝቡም ከጋኔንነት ወደ "ጋኔን አሳሪው" ሰሎሞንነት በቀላሉ ይመለሳል ማለት ነው። በዛ ጊዜ የወሎ ህዝብ ቅማንትኛና አገውኛ ተናጋሪ ሕዝብ ነበር። የሸዋው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ቅማንትኛ ተናጋሪ ነበር። የጎንደር ሕዝብ ቅማንትኛ ተናጋሪ ነበር። ጎጃም የዳሞት ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝብ ነበር። ዳሞትኛ ከአሁኑ የአዊኛ ቋንቋ ጋር ተመሳሳይ ነበር። እናም ለአዲሱ ሥርዎ መንግሥት ምሥረታ ያገለግላል ተብሎ የታሰበው ከዛግዌ ወታደሮች መካከል የተገኘው አማርኛ ቋንቋ ነበር። ይሄን በደንብ ለመረዳት የንቡረ እድ ኤርሚያስ ከበደን መጽሐፍ ማንበብ ይጠቅማል። ስለዚህ አማርኛ ለማስፋፋትና አገውኛና ቅማንትኛን በማጥፋት ሕዝቡን ሰሎሞናዊ ለማድረግ "አገው ጋኔን ነው፡ ቋንቋውም የጋኔን ነው" ማለት ነበረባቸው። ~~~ በዚህም ተክለሃይማኖትና ተከታዮቹ ውጤታማ ሆኑ። በ1262 ዓ ም ዋድላ ደላንታ ላይ ንጉሥ ይትባረክን ገድለው የሸዋውን ሰሎሞናዊ ይኩኖ አምላክን አነገሡ። ይሄን የበለጠ ለመገንዘን ገድለ ተክለሃይማኖትን አንብቡት። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሰሎሞናዊነትን በሃይማኖት ሰበብ በህዝቡ ላይ በግድ መጫን ጀመሩ። እምቢ ያለውን ዛሬ ላይ እንደሚያደርጉት በጭካኔና አረመኔነት ይገድሉታል፡ መንደሩና አገሩን በሙሉ ያቃጥሉታል። ፈርቶ እሺ ያለውን ቋንቋውን ያስጥሉታል። አስገድደው ያጠምቁትና "አማራ ሆንክ" ይሉታል። በነገራችን ላይ ያኔ አማራነት የጥሙቃን ሰለሞናዊነት ማንነት ነበር እንጅ ብሔር አልነበረም። የተጠመቀ ሁሉ "አማራ" ይባላ እንጂ የዘር አንድነት የለውም። ከመነሻውም አማራ የሚባል ዘር አልነበረም። አማራ ብሔር ሆኖ መታየት የጀመረው ከ1977ቱ የደርግ የቤትና ሕዝብ ቆጠራ በኋላ ነው። ይልቁንም አማራን ብሔር አድርጎ የራሱ ክልል እንዲኖረው ያደረገው ኢህአዴግ ነው። ሂደቱ ረጅም ጊዜ ቢወስድም አማራነት ብሔር የሆነው በሚገርም መንገድ ነው። ዛሬም ድረስ ኦሮሞዎች የተጠመቀውን ኦሮሞ "አማራ" ነው የሚሉት። እስኪ አስቡት ሙስሊም ብሔር ሲሆን! እንደዛ ነው የሆነው። አማራነትን ወይም ክርስቲያን መሆንን ብሔር እንዲሆን ያገዘው የአማርኛ መፈጠርና ከክርስትናው ጋር አብሮ መስፋፋቱ ነበር። ተጠምቆ አማራ ሲሆን አማርኛን እንዲናገር ግድ ሆነ። ~~~ በዚህ ክስተት ውስጥ የምንረዳው ነገር ሰሎሞናዊነትን በቤት ምልክናው፡ በቤተ መንግስቱና በቤተ ሕዝቡ ዘንድ ለማስረጽና ትክክለኛ አድርጎ ለማሳየት ዋናውን ሚና የተጫዎቹት ክርስትናና አማርኛ ናቸው። ሁለቱም የነባር ዝዝቦችን የቀደመ ትክክለኛ ማንነታቸውን ማስጣያ ናቸው። የአንድን ሕዝብ ማንነት ለመቀየር ባህሉን፡ ሃይማኖቱንና ቋንቋውን መቀየር መሠረታዊ ነው። እናም እነዚህን በሚገባ ተግባር ላይ በማዋል ብዙውን ነባር ሕዝብ ማንነቱን አስጥለው አማራ አደረጉት። ነባር ባህሉን አጥፍተው አዲስ የአማራነት ሰሎሞናዊነት ባህል ፈጠሩለት፡ የቀደመ ሃይማኖቱን አጥፍተው አማራ የሚባል ሃይማኖት ሰጡት፡ ቅማንትኛ፡ አገውኛና ዳሞትኛ ቋንቋውን አጥፍተው አማርኛን ሰጡት። ታዲያ እንዴት አይጠፋ? በትክክለም ቀስ በቀስ ሙልጭ ብሎ ጠፋ። ይሄን የሌሎችን ነባር ባህልና ቋንቋ እያጠፉ አማራ የማድረግ ሂደት በዋናነት የመንግሥትና የቤተክህነት ሰዎች በሚገባ መርተውታል። በየጊዜው ልዩ ልዩ የማፈኛ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ አስኪደውታል። ~~~ ሰሎሞናዊነትም በሉት ማስፈጸሚያዎቹ አማራነት (ክርስትና) እና አማርኛ በራሳቸው የዚህ ቡድን የመጨረሻ ዓላማዎች አይደሉም። እነዚህ ነገሮች ዋና ዓላማውን ለማሳካት የተጠቀሟቸው መንገዶች ናቸው። ዋና ዓላማቸው የሥልጣን የበላይነትን ተቆጣጥሮ ለዘለዓለም በህዝቦች ላይ ነግሦ መኖር ነው። ለዚህ ነው "ንጉሠ ነገሥት እከሌ ሥዩመ እግዚአብሔር ሞአ አንበሳ ዘእም ነገድ ይሁዳ" እያሉ ሲነግሩን የኖሩት። ለዚህ ነው "አማራ ከሌለ ኢትዮጵያ አትኖርም" የሚሉን። ክርስትናው የመንግሥትን ሥርዓት ለመጠበቅ ዋና አፈቃላጤና ወታደር ሆኖ ሲያገለግል ነው የኖረው። አማርኛውም እንዲሁ በዘፈኑ፡ በሽለላው፡ በፉከራ፡ ወዘተ የመንግሥት ወታደው ነው። ሰሎሞንነቱ ደግሞ "ንጉሡ ከዘሎሞን ዘር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በፈጣሪ ቅዱስ ቅባት የተቀባ ነው" ብለን እንድናምን የአእምሮ አጠባ ሥራ ከክርስትናው ጋር ተቀናጅቶ ሰርቷል። ~~~ በዚህ ሂደት የዚህ ቡድን ታሪክ ፀሐፊዎችም ይሄን የተወላገደውን ጠፍቶ የማጥፋት የሰሎሞንነት ታሪክ እውነት ለማስመሰል ያልፃፉልን ኮተት የለም። "ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ" እያሉ ሲተርቱልን ኖሩ። አንድም ቀን ደፍረው ስለ ጥንቱ ትክክለኛ ታሪክ ጽፈውልን አያውቁም። ይልቁንም የቀድሞው እውነተኛ ታሪክ እንዳይወጣ የማዳፈን ሥራ ሲሰሩ ነው የኖሩት። ~~~ ከፍ ሲል እንደገለጽኩት እነዚህ የሥልጣን ጥመኞችና ሥልጣን አመለኮች የኖሩት ለክርስትናው ሳይሆን ለሥልጣናችው ብቻ ነው። ክርስትናን ከአፍ በዘለለ ኑረውበት አያውቁም። ስለቅድስናቸውና ንጹህነታቸው ሲያወሩን እንሰማቸዋለን እንጂ በተግባር የሚታይ ቅድስና የላቸውም። ምክንያቱ ክርስትናን የኖሩት ለምድራዊ ንጉሣዊ ሥልጣን ማስጠበቂያ እንጂ ለሠማያዊው መንግሥት መግቢያ አልነበረም እና ነው። ክርስትና ሥልጣንህን የምታስጠብቅበት አንዱ መንገድ (means) እንጂ መድረሻ (goal) አልነበረም። ሰሎሞንነት ወይም አማራነትም እንዲሁ ነው። አማራነት በራሱ መድረሻ አልነበረም። ሥልጣንን በህዝቦች ላይ ጭነህ በንጉሥነት ዙፋን ላይ ተፈናጠህ ለዘለዓለም ለመኖር የተጠቀሙበት አንዱ መንገድ ነበር። የዛሬውን "አማራን ለማዳን ነው" የሚሉትን ፕሮፓጋንዳ ተውት። አማራን ለማዳን ቅማንትን መግደል ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው። ይሄ የአሁኑ ድርጊታቸው የዓላማና የመንገድ መቀያየር (goal displacement) ነው። ድሮ አማራነት የፖለቲካና የሥልጣን የበላይነትን ለማስጠበቅ ይጠቅም ነበር። ዛሬ ደግሞ አማራነትን ለማስጠበቅ የፖለቲካ፡ የሚዲያና የሥልጣን የበላይነትን እንደ መሳሪያ ወይም መንገድ ይጠቀሙታል። ለዚህ ነው የዓላማ መቀየር ያልኩት። አሁን ላይ ግራ ገብቷቸዋል የምንለውም ለዚህ ነው። ~~~ እነዚህ ሰዎች ለክርስትናው ምንም ግድ አይሰጣቸውም። ጉዳያቸውም አይደለም። በመሠረቱ ራሳችውን ከሰቃልያነ ክርስቶስ አይሁዶች ዘር ጋር ሲያገናኙ አይሁድነታቸውን እንጂ ክርስቲያንነታችውን በፍጹም አያሳይም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ነው የሚለው "ወደ ወገኖቹ መጣ፣ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ሥልጣንን ሰጣቸው። እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከሥጋና ከደማዊ ግብር ወይም ከወንድና ከሴት ፈቃድ አልተወለዱም።" (ዮሐ 1፡ 11-13)። ይሄን የወንጌል ቃል በጭራሽ አያስቡትም። ምክንያቱም ክርስትና ዓላማቸው አይደለምና ነው። ክርስትና አይገዳቸውም የምለውም ለዚህ ነው። ክርስትና ለነሱ እንደ ማጭድ፡ አካፋ፡ መጥረቢያ፡ መኪና፡ ወዘተ መሳሪያ ነው። ሰው ለማምረት ማረሻ እንደሚጠቀመው ሁሉ እነዚህ ሰዎችም በስልጣን ለመኖር ክርስትናን መሳሪያ አድርገው ተጠቀሙበት እንጂ ክርስትናን አያውቁትም። ለዚህ እኮ ነው ንጉሦቻቸው 30 እና 40 ሚስቶችንና እቁባቶችን ሲያገቡ የኖሩት። አይሁዳዊ ናቸዋ። ኦሪታዊ ናቸዋ! እነርሱ ከአይሁዳዊያን ነገሥታቶች ከሥጋና ከደም ግብር ወይም ከወንድና ከሴት (ከሰሎሞንና ማክዳ) ፈቃድ ለመወለድ የፈለጉና እንደተወለዱ አድርገው የተቀበሉ ናቸው። እነርሱ "የአግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ክርስቶስ ስልጣን አልሰጣቸውም። የተወለዱት በመንፈስ ሳይሆን በሥጋ ነውና። በሥጋ ከአይሁድ መወለድ ለክርስቶስም አልጠቀመው። ራሳቸው ወገኖቹ የተባሉት በጭካኔ ሰቀሉት። እነዚህም አይሁድነትን በመንፈስ ተቀብለዋልና የአይሁድ ንጹሃንን የሚገድለው የነብሰ ገዳይነት መንፈስ ተዋርሰዋልና ይሄው በክርስትና ስም ይገድላሉ። ያርዳሉ። ይዘርፋሉ። ይዘፍናሉ። ይፎክራሉ። Website:-https://mikysultan.blogspot.com/ Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU Telegram:- t.me/Oromo_ geography

Monday, January 31, 2022

#አፄ ቴውድሮስ _ የቅማንት ልጅ

ቅማንት +አጼ ቴዎድሮስ =ነገደ ኩሽ :-fb_Miky_sultan የቅማንት ጎሣ አጼ ቴዎድሮስ ካሣ እወነተኛ ሥሙ ገምባሮ ነበር ሲወሳ የፈረሱ ሥም ይባላል ጉተማ የኩሽ ዘር መጠሪያው አርማ። የንግሥት ማኪዳ አጋባሲ የዘር ሀረግ ከትውልድ የወረሰ የጀግንነት ማእረግ የቅርብ ወገኑ ይባላል ራስ ጋልሞ በጦር በጎራዴ የሚዋጋ አልሞ ሁለቱ ከቅማንት ተፈልፍለው የወጡ ኩሽ መሆናቸው እወቁ በቅጡ የቅማንት እውነተኛ ሥም ነበረ ካም'አት(kement) በአማረ** ተንኮል ከመለወጡ በፊት። በኩሽ ከምኣት( ኬሜንት) ማለት የተባረከ የአማልክት ሀገር ማለት ነው። የኩሽ ዘር የሚባሉ ቅማንቶች የኩሽ ልጆች ናቸው ። አማራ አይደሉም። ስለዚህ የቅማንት አፄ ቴዎድሮስ( ገልሞ) የአማራ ጀግና አይደለም ታሪክ በ ስርቆት ለራስ ማድረግ ወረዴት ነው። ቴዎድሮስ አይደለም የአማራ ጀግና ከታሪክ አጣሩ እንደገና እንደገና አማራ በጥቅሉ ነገድ አይደለም አማራ የምባል ነገድ ከ ኩሽም ከ ሴምም የለም። አማራ ግማሹ ከ ኦሮሞ፣ከ አገው፣ከ ሌሎች ነገዶች የተውጣጣ ስብስብ ነው። ለመረጃ DNA ፈትሹ የውሸት ታሪክ አፍርሱ። ተጨባጭ መረጃ ተመልከቱ። የውሸት ሊቃውንቶች የተረት ባላባቶች የሆኑ የአማራ ደብተራዎች ለእውነት መገዛት አለባቸው። አበሲኒያን የመሠረቱ 19 የኦሮሞ (ኩሽ)ጎሳዎች አገው ፣ቅማንት፣ አዊ፣ ዋታ ፣ጃዊ፣ ቤጂያ/ቤጃ ጋፋታ ፣ኢፋቲ ፣ቡልጋ ፣ዱሙጋ፣ ሙረቴ፣ ወራየጁ፣ ወራኢሉ፣ ዋራሂማኖ ፣ወራባቦ ፣ወራኖሌ ፣ወራቃሉ ፣ወራአልቡኮ፣ ወራከራዩ ናቸው። አንድ የአማራ ነገድ የለም። ለምን ብባል አማራ ነገድ የለውም።በዚህ ነባራዊ ተጨባጭ መረጃ መሰረት የአበሲኒያ ሕዝብ የሚባለው 999% ኦሮሞ መሆናቸውን አውቀው እውነቱን ተቀብለው ታሪክ መለወጥ አለባቸው። የአማራ እሌቶች ያለፈው ዘመን የውሸት ታሪክ አልበቃ ብሏቸው አይናቸውን በጨው አፋቸውን በበረኪና ታጥበው የውሸት ስልቻ ተሸክመው የፈጠራ ታሪክ አዝለው አዲስ ዘመቻ ጀምረዋል። ሸዋ ፣ጎንደር፣ ጎጃም፣ወሎ ፣ የአማራ ሀገር ነበር እያሉ ይበዝናሉ ውሸት ይነሰንሳሉ። ምን ቢደረግ ተለውጠው በአውነት ያምናሉ? ከምንልክ በፊት አማራ የሚባል ጎሣ ወይም ብሔር በኢትዮጵያ አልነበረም። ሳይፈጠሩ ክርስትና ተነሳን ይላሉ። ሳይኖሩበት የሀገር በላቤት አማራ ነው እያሉ ይሟገታሉ፡ የጎንደር የጎጃም የሸዋ ነገሥታት በአማሪኛና በግእዝ ሥም የሚጠሩ የኦሮሞ ነገሥታት መሆናቸውን ደብቀው የአማራ ነገሥታት ነበሩ ይላሉ። አማራ የሆነ ራሱን የሰለሞን ዘር ነኝ ብሎ ከሚንሊክ ከሃይለ መለኮትና ከሣህለ ሥላሴ በስተቀር ሌላ ንጉሥ የለውም እሱም በ ነገድ ሳይሆን በመቀባት ነው። በውሸት ታሪክ አዝለው የሚኖሩት የስነ ልቦና ችግር አለባቸው። በዚህ ምክንያት በተጨባጭ መረጃ አያምኑም ተለውጠው ለእውነት አይገዙም። የአማራ ነገሥታት ከሚባሉት ውሰጥ አንዱ አጼ ቴዎድሮስ ወይም ጋምባሮ አባጉታማ የቅማንነት ጎሳ የኩሽ ዘር መሆኑን አወቀው የውሸት ፕሮፖጋንዳቸውን ማቆም አለባቸው። ዘሬ እንደምንሊክ ዘመን በውሸት ሕዝብ ማታለል አይቻልም።አፄ ቴውድሮስ በ ጎጃምና ጎንደር ብዙ ቤተ ክርስትያንን አቃጥሏል። ለስልጣን ብሎ የወሎ ነግስታቶችን ተዋግቷል። በውሃላ በ ወሎዋ ንግስት ወርቅቱ በ መቅደላ ጦርነት ላይ ተገደለ በ ንግሷ ጦር።

#ቤጃምድር( በጌምደር) ጎንድር

ቤጃ ምድር( በጌምድር) ጎንደር አባ ጃኖ:miky sultan የአርዋዲ ልጅ የከነዓን የልጁ ልጅ የቅማንቶች አባት አይነር ከ ከነዓን ወደዚች አገር የመጡ ጥንታዊ ሕዝብ ናቸው። ቅማንት ወደዚች አገር ከመጡት ህዝቦች የመጀመራዎቹ ኩሳዊ( ዘ ነገደ ኩሽ ነው) የ ጎንደር የአገሩ ባለባት ነው። ቅማንት የ ከነዓን የልጅ ልጅ ነው። የ አይነር ልጆች።

#irrecha kush orginis culture/# ኢሬቻ

. . የኢሬሳ/ኢሬቻ በዓል ትውፊትና አከባበር ፀሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ ----- የኢሬቻን በዓል በማስመልከት አንድ ጽሑፍ እናበረክታለን ባልነው መሰረት ይህንን ኢትኖግራፊ ቀመስ ወግ ጀባ ልንላችሁ ነው፡፡ ታዲያ እኛ ባደግንበት አካባቢ በሚነገረው ትውፊት በዓሉ “ኢሬሳ” እየተባለ ስለሚጠራ በዚህ ጽሑፍ ውስጥም “ኢሬሳ” የሚለውን ስም መጠቀሙን መርጠናል፡፡ ወደ ነገራችን ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ የሚወሱት ጉዳዮች Carcar and the Ittu Oromo በተሰኘው የኢትኖግራፊ ጥናት ውስጥ በሰፊው የሚዳሰሱ በመሆናቸው ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች የጥናቱን የመጨረሻ ውጤት እንድትጠባበቁ እጠይቃለሁ፡፡ ምክንያቱም በጽሑፉ ውስጥ ከቀረበው ትረካ በላይ ሄጄ ወደ ዝርዝር ጉዳዮች እንዳልገባ ጥናቱን የማከናውንበት ደንብ ስለሚያግደኝ ነው፡፡ ---- ጽሑፋችንን የተሳሳቱ ምልከታዎችን በማስተካከል እንጀምራለን፡፡ የዋቄፈንና እምነት ተከታይ የሆኑት ኦሮሞዎች በሙሉ የኢሬሳን በዓል ያከብሩታል፡፡ ይሁንና በዚህ ዘመን በዓሉ በከፍተኛ ድምቀት የሚከበረው የቱለማ ኦሮሞ ይዞታ በሆነው የቢሾፍቱ ወረዳ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ታዲያ የበዓሉ ማክበሪያ በሆነው ስፍራ ቆሪጥን የመሳሰሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ስምና ዝና ያላቸው ጠንቋዮች የከተሙ በመሆናቸው ብዙ ሰዎች ኢሬቻን ጠንቋዮቹ የዛር መንፈሳቸውን በህዝቡ ላይ የሚያሰፍኑበት ዓመታዊ የንግሥ በዓል አድርገው ይመለከቱታል፡፡ አልተገናኝቶም!! ጠንቋዮቹ በቅርብ ዘመን የበቀሉ ሀገር አጥፊ አራሙቻዎች ናቸው፡፡ ከበዓሉ ጋር አንድም ግንኙነት የላቸውም፡፡ ኖሮአቸውም አያውቅም፡፡ የኢሬቻ በዓል ግን ከጥንቱ የኦሮሞ ህዝብ የዋቄፈና እምነት የፈለቀ እና ለብዙ ክፍለ ዘመናት ሲተገበር የኖረ ነው፡፡ ጠንቋዮቹ በዚያ አካባቢ የሰፈሩት ከጣሊያን ወረራ ወዲህ ባለው ጊዜ ነው፡፡ እነዚህ ጠንቋዮች እዚያ የሰፈሩበት ምክንያት አለ፡፡ የገላን፤ የቢሾፍቱ እና የዱከም ወረዳዎች በጥንታዊው የቱለማ ኦሮሞ ደንብ መሰረት የነገዱ ፖለቲካዊና መንፈሳዊ ማዕከላት ናቸው፡፡ እነዚህ መሬቶች በቱለማ ኦሮሞ ዘንድ “ቅዱስ” ተብለው ነው የሚታወቁት፡፡ “ቃሉ” የሚባለው የህዝቡ መንፈሳዊ መሪም የሚኖረው በዚህ አካባቢ ነው፡፡ የቱለማ ኦሮሞ ኢሬቻን የመሳሰሉ ታላላቅ በዓላት የሚያከብረውም በዚሁ ስፍራ ነው፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ህዝብ በነዚህ መሬቶች የሚያካሄደውን በዓላትን የማክበርና “ዋቃ”ን የማምለክ ተግባራት እንዳያከናውን ታገደ (ዝርዝሩን ለማወቅ የጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሤን “ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ”፣ ወይንም የኤንሪኮ ቼሩሊን The Folk Literature of The Oromo ያንብቡ)፡፡ ይሁንና ልዩ ልዩ የኦሮሞ ጎሳዎች እየተደበቁም ቢሆን ወደ ስፍራው መሄዳቸውን አላቋረጡም፡፡ በጣሊያን ዘመን ደግሞ እንደ ጥንቱ ዘመን ሰብሰብ ብለው በዓሉን ማክበር ጀመሩ፡፡ ጣሊያን ሲወጣ እንደገና በጅምላ ወደስፍራው እየሄዱ በዓሉን ማክበሩ ቀረ፡፡ ነገር ግን ኦሮሞዎች ከጣሊያን በኋላም በተናጠልና በትንንሽ ቡድኖች እየሆኑ መንፈሳዊ በዓላቸውን በስፍራው ማክበራቸውን አላቋረጡም (እዚህ ላይ ጣሊያንን ማድነቃችን አይደለም፤ ታሪኩን መጻፋችን ነው እንጂ)፡፡ እንግዲህ በዚያ ዘመን ነው ጠንቋዮቹ በአካባቢው መስፈር የጀመሩት፡፡ እነዚህ ጠንቋዮች ይህንን ስፍራ ምርጫቸው ያደረጉበት ዋነኛ ምክንያት አለ፡፡ ጠንቋዮቹ ህዝቡ መሬቱን እንደ ቅዱስ ምድር የሚመለከት መሆኑን ያውቃሉ፡፡ “ቃሉ” የሚባለው የጥንቱ የኦሮሞ ሀገር በቀል እምነት መሪ በስፍራው እየኖረ የህዝቡን መንፈሳዊ ተግባራት ይመራ እንደነበረም ያውቃሉ፡፡ የኦሮሞ ቃሉ በህዝቡ ከፍተኛ ክብር እንደሚሰጠው እና ንግግሩ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት እንዳለውም ይገነዘባሉ፡፡ “ቃሉ” አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት ጊዜ ከ“ዋቃ” የተሰጠውን ገደብ ሳይጥስ “ራጋ” የማከናወን ስልጣን እንዳለውም ይረዳሉ፡፡ እንግዲህ ጠንቋዮቹ የዘረፋ ስትራቴጂያቸውን ሲወጥኑ በጥንታዊው የኦሮሞ የዋቄፈና እምነት ተከታዮች ዘንድ እንደ ቅዱስ የሚወሰደው ያ ማዕከላዊ ስፍራ ብዙ ገቢ ሊዛቅበት እንደሚችል ታያቸው፡፡ በመሆኑም በዚያ ቅዱስ ስፍራ ከትመው ከጥንቱ የኦሮሞ ቃሉ ስልጣንና ትምህርት የተሰጣቸው እየመሰሉ ህዝቡን ማጭበርበርና ማወናበድ ጀመሩ፡፡ ለረጅም ዘመን ማንም ሃይ ባይ ስላልነበራቸው የውንብድና ስራቸውን በሰፊው ሄደውበታል፡፡ አሁን ግን ሁሉም እየነቃባቸው ነው፡፡ ታዲያ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የሚኖሩት ጠንቋዮች ተመሳሳይ ስትራቴጂ የሚጠቀሙ መሆናቸውን ልብ በሉ፡፡ ለምሳሌ በወሎ፣ በሀረርጌ፣ በባሌና በጂማ የሚኖሩት ጠንቋዮች እነ ሼኽ ሑሴን ባሌ፣ እነ ሼኽ አባዲር፣ እነ አው ሰዒድ፣ እነ ሼኽ አኒይ ወዘተ… የመሳሰሉት ቀደምት ሙስሊም ዑለማ በመንፈስ እየመሯቸው መጪውን ነገር እንደሚተነብዩና ድብቁን ሁሉ እንደሚፈትሹ ይናገራሉ፡፡ በሰሜን ሸዋ፣ ጎንደር፣ ጎጃም ወዘተ… አካባቢዎች ያሉ ጠንቋዮች ደግሞ ቅዱስ ገብርኤልና ሚካኤል ራዕይ እያስተላለፉላቸው መጻኢውን ነገር ለመተንበይ እንዳበቋቸው ያወራሉ፡፡ ነገር ግን ሁላቸውም አጭበርባሪዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ጠንቋዮች ከክርስትናም ሆነ ከእስልምና ጋር የሚያገናኛቸው ነገር እንደሌለ ሁሉ ከዋቄፈንና እምነትም ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡፡ ሶስቱም እምነቶች ጥንቆላን ያወግዛሉ፡፡ እናም የቢሾፍቱ ቆሪጦች እና ኢሬቻ በምንም መልኩ አይገናኙም፡፡ ስለዚህ ኢሬቻን ከጥንቆላም ሆነ ከባዕድ አምልኮ ጋር ማያያዝ ስህተት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ መወሳት ያለበት ጉዳይ ለጠንቋዮች መጠሪያ ሆኖ የሚያገለግለውን “ቃልቻ” የተሰኘውን ስም ይመለከታል፡፡ ይህ ስም በአንድ ጎኑ “ቃሉ” የሚለውን የኦሮሞ መንፈሳዊ አባት ያመለክታል፡፡ በሌላኛው ጎኑ ይህ መንፈሳዊ አባት የተወለደበትን ጎሳም ያመለክታል፡፡ የቃሉ ሹመት እንደ አባገዳ በምርጫ የሚከናወን ሳይሆን ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍ ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ አባት አባል የሆነበት ጎሳም በዚሁ ስም “ቃሉ” እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡ የጎሳው አባላት የሆኑ ሰዎች ሃላፊነት ህዝቡን በመንፈሳዊ ተግባራት ማገልገል ነው፡፡ የዚህ ጎሳ ተወላጆች በከፍተኛ ደረጃ ይከበራሉ፡፡ ቃላቸው በሁሉም ዘንድ ተሰሚ ነው፡፡ ይሁንና የፖለቲካ መሪ እና የጦር መሪ ለመሆን አይችሉም፡፡ የአባገዳ ምርጫ ሲከናወንም ለእጩነት አይቀርቡም፡፡ እንግዲህ “ቃሊቻ” የሚባሉት ከዚህ የተከበረ ጎሳ የተወለዱ ወንዶች ናቸው፡፡ ሴቶቹ ደግሞ “ቃሊቲ” በሚለው የማዕረግ ስም ይጠራሉ፡፡ የሁለቱም ትርጉም “የቃሉ ሰው” እንደማለት ነው፡፡ ጠንቋዮቹ “ቃሊቻ” ነን ማለት የጀመሩት ቃሉዎች በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ያላቸውን ክብር ስለሚያውቁ ነው፡፡ ነገር ግን “ቃሊቻ” እና ጠንቋይ የሰማይና የመሬትን ያህል የተራራቁ ናቸው፡፡ ******* እነሆ አሁን ወደ ኢሬሳ ገብተናል!! በጥንቱ የኦሮሞ የዋቄፈንና እምነት መሰረት ብዙዎቹ በዓላት ወርሃዊ ናቸው፡፡ እነዚህ ወርሃዊ በዓላት የሚከበሩት በየአጥቢያው ባሉት መልካዎች፣ በኦዳ (ዋርካ) ዛፍ ስር እና “ገልመ ቃሉ” በሚባለው ቤተ እምነት ነው፡፡ ኢሬሳን የመሳሰሉት ታላላቅ በዓላት የሚከበሩት ግን በነገድ (ቆሞ) ደረጃ ሲሆን በዓላቱን የማክበሩ ስርዓቶች የሚፈጸሙትም በዞን ደረጃ ባሉ የበዓል ማክበሪያ ስፍራዎች ነው፡፡ እነዚህ የክብረ በዓል ስፍራዎች የሚገኙትም የእያንዳንዱ የኦሮሞ ነገድ የፖለቲካና የመንፈሳዊ ማዕከላት ባሉበት አቅራቢያ ነው፡፡ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ሀረር ስትመጡ “አዴሌ” እና “ሀረማያ” የተሰኙትን ሐይቆች ታገኛላችሁ አይደል?… አዎን! የአዴሌን ሐይቅ አልፋችሁ ወደ ሀረማያ ከመድረሳችሁ በፊት ወደ ጋራሙለታ አውራጃ የሚገነጠለው የኮረኮንች መንገድ ይገጥማችኋል፡፡ መንገዳቸው ወደ ጋራ ሙለታ የሆነ ተጓዦች እዚያ ከመድረሳቸው በፊት የአውቶቡሱ ረዳት በዚያ ስፍራ እንዲያወርዳቸው ይነግሩታል፡፡ ታዲያ ስፍራውን ምን ብለው እንደሚጠሩት ታውቃላችሁ?….. Mudhii Irreessaa ነው የሚሉት፡፡ ቃል በቃል ሲተረጎም “የኢሬሳ ወገብ” እንደማለት ነው፡፡ አውዳዊ ፍቺው ግን “የኢሬሳ በዓል ማክበሪያ ስፍራ” እንደማለት ነው፡፡ በዚህ ስፍራ በአሁኑ ወቅት የኢሬሳ በዓል አይከበርም፡፡ በጥንት ዘመናት ግን የምስራቅ ሀረርጌው የአፍረን ቀሎ ኦሮሞ የኢሬሳን በዓል የሚያከብረው በዚህ አካባቢ ነው፡፡ በዓሉ ይከበርበት የነበረውን ትክክለኛ ስፍራ ለማወቅ ካሻችሁ በዋናው የአስፋልት መንገድ ላይ ለጥቂት ሜትሮች እንደተጓዛችሁ ከመንገዱ በስተቀኝ በኩል ፈልጉት፡፡ በዚያ ስፍራ ላይ ከትንሽዬ ኮረብታ ስር የተጠጋ ሰፊ መስክ ራቅ ብሎ ብሎ ይታያል፡፡ ይህ ረግረጋማ ስፍራ በጥንቱ ዘመን አነስተኛ ሐይቅ እንደነበረበት ልብ በሉ፡፡ ሐይቁ ከጊዜ ብዛት ስለደረቀ ነው በረግረግ የተዋጠው መስክ እንዲህ አግጥጦ የሚታየው፡፡ እናም የአፍረን ቀሎ ኦሮሞ የዋቄፈንና እምነት ተከታይ በነበረበት የጥንት ዘመናት የኢሬሳን በዓል የሚያከብርበት ቅዱስ ስፍራ በዚህ የደረቀ ሐይቅ ዳርቻ የነበረው መሬት ነው፡፡ Mudhii Irreessa የሚባለው ስፍራ ከደረቀው ሐይቅ አቅራቢያ መሆኑና ይኸው ስፍራ አሁን ካሉት የሐረማያ እና የአዴሌ ሐይቆች አቅራቢያ መገኘቱ የአጋጣሚ ነገር እንዳይመስላችሁ፡፡ በነገድ ደረጃ የኢሬሳ በዓል የሚከበርባቸው ማዕከላት በሙሉ በሐይቅ ዳርቻ የሚገኙ ናቸው፡፡ ይህም ምክንያት አለው፡፡ አንደኛው ምክንያት የጥንቱ የኦሮሞ የዋቄፈንና እምነት “ፍጥረት የተገኘው ከውሃ ነው” የሚል አስተምህሮ ያለው በመሆኑ “ዋቃ” ፍጥረተ ዓለሙን በጀመረበት የውሃ ዳርቻ በዓሉንና የአምልኮ ተግባሩን መፈጸም ተገቢ ነው ከሚል ርዕዮት የመነጨ ነው፡፡ ይሁንና ሁሉም የውሃ አካል ለዚህ ክብር አይመጥንም፡፡ ኦሮሞ ከሰው ልጅ ነፍስ ቀጥሎ ለከብቶቹ ነፍስ በእጅጉ ይጨነቃል፡፡ በመሆኑም ኢሬሳን የመሳሰሉ ታላላቅ በዓላት በዳርቻው የሚከበርበት የውሃ አካል ከሰዎች በተጨማሪ ለከብቶች ህይወት አስፈላጊ መሆኑም ይጠናል፡፡ ይህም ማለት ውሃው በኦሮሞ ስነ-ቃል “ሃያ” (ቦጂ) እየተባለ የሚጠራው ጨዋማ ንጥረ ነገር ያለው ሊሆን ይገባል ለማለት ነው፡፡ በዚህ ማዕድን በአንደኛ ደረጃ የሚታወቁት ደግሞ “ሆራ” የሚባሉት በከፍተኛ ስፍራዎች ላይ ያሉ ሐይቆች ናቸው፡፡ ታዲያ የእነዚህ “ሆራ” ሐይቆች ልዩ ባህሪ ነጠላ ሆነው አለመገኘታቸው ነው፡፡ በተለያዩ ክልሎች ያሉት ሆራዎች በቡድን ተሰባጥረው ነው የሚገኙት፡፡ በአንዳንድ ስፍራዎች እስከ ሶስት ያህል ሆራዎች አሉ፡፡ በአንዳንድ ስፍራዎች ደግሞ እስከ ስምንት የሚደርሱ ሆራዎች ይገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ የኦሮሞ ነገዶች እነዚህን በማዕድናት ክምችት የበለጸጉ ሐይቆች ወጥ በሆነ ሁኔታ “ሆረ” (Hora) እያሉ ነው የሚጠሩት፡፡ የአፍረን ቀሎ ኦሮሞ ግን “ሀረ” ነው የሚለው፡፡ “ሀረ ማያ” የሚለው የሐይቁ ስያሜም የሚያመለክተው ይህንኑ ነው፡፡ እንግዲህ ኢሬቻ የሚከበረው በእንዲህ ዓይነት ሐይቆች አቅራቢያ ነው፡፡ ******* ከላይ ስጀምር “የኢሬሳ በዓል ማክበሪያ ስፍራ ለነገዱ የፖለቲካና የሃይማኖት ማዕከል የቀረበ ነው” ብዬ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የ“ሀረ ማያ”ን ሐይቅ ያየ ሰው በአባባሌ መደናገሩ አይቀርም፡፡ ነገሩ ግን እውነት ነው፡፡ በዛሬው ዘመን “ሃረ ማያ” በትውፊት ውስጥ ያለው አስፈላጊነት እየተረሳ የመጣው የአፍረን ቀሎ ኦሮሞ የኢኮኖሚ ስርዓቱን ከከብት እርባታ ወደ ግብርና ማዞር በጀመረበት ዘመን እስልምናንም እየተቀበለ በመምጣቱና የፖለቲካ ማዕከሉም በዚሁ ሂደት ውስጥ በመረሳቱ ነው፡፡ ነገሩን ጠለቅ ብሎ ያየ ሰው ግን የጥንቱን የአፍረን ቀሎ የፖለቲካ ማዕከል ከሀረማያ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ያገኘዋል፡፡ ይህም “ቡሉሎ” የሚባለው ስፍራ ነው (ስፍራው ለወተር ከተማ ይቀርባል)፡፡ በዚህ መሰረት የዛሬዎቹ የሀረማያ እና የቀርሳ ወረዳዎች የጥንቱ የአፍረን ቀሎ ኦሮሞ የፖለቲካና የመንፈሳዊ ማዕከላት ነበሩ ማለት ነው፡፡ ከአፍረን ቀሎ ኦሮሞ ምድር ወደ ምዕራብ ተጉዘን “ጨርጨር” በሚባለው የኢቱ ኦሮሞ መሬት ውስጥ ስንገባ ደግሞ ነገሩ በግልጽ ይታየናል፡፡ የኢቱ ኦሮሞ የኢሬሳን በዓል የሚያከብርበት ስፍራ በአሁኑ የምዕራብ ሀረርጌ ዞን የቁኒ ወረዳ፣ በደነባ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል፡፡ ስፍራው እስከ አሁን ድረስ Mudhii Irressa እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ ስፍራ ከዝነኛው “ኦዳ ቡልቱም” በሁለት ኪሎሜትር ያህል ብቻ ነው የሚርቀው፡፡ “ኦዳ ቡልቱም” የኢቱ ኦሮሞ ጥንታዊ የፖለቲካና የእምነት ማዕከል ሲሆን በኢቱ ኦሮሞ ትውፊት መሰረት ስድስት “ሆራዎች” አሉት፡፡ እነርሱም “ሆረ ባዱ”፣ “ሆረ ቃሉ”፣ “ሆራ ቁኒ”፣ “ሆረ ባቴ”፣ “ሆረ ጎሄ” እና “ሆረ ዲማ” ይባላሉ፡፡ እነዚህ ሃይቆች በበጋ ወቅት አነስ ብለው ቢታዩም ሙሉ በሙሉ የጠፉበት ሁኔታ አልተከሰተም፡፡ ከነርሱ መካከል ትልቁ “ሆራ ዲማ” ሲሆን በተለምዶ “ሀሮ ጨርጨር” እየተባለም ይጠራል፡፡ “ሆረ ዲማ” የምስራቅ ኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ ነው (የአስፋልቱ መንገድ ወደዚያ ስለማይደርስ የመሃል ሀገር ሰዎች በአብዛኛው ሃረማያን ነው የሚያውቁት፤ ይሁንና “ሆረ ዲማ” በስፋቱ የሀረማያን ሶስት እጥፍ ይሆናል)፡፡ “ሆራ ባዱ” ደግሞ ለኦዳ ቡልቱም በጣም የቀረበው ሐይቅ ነው፡፡ የኢቱ ኦሮሞ የኢሬሳን በዓል የሚያከብረው ግን “ሆረ ቃሉ” ከተሰኘው ሐይቅ አጠገብ ነው፡፡ ይህም ሃይቅ ከሆረ ባዱ በስተምስራቅ ይገኛል፡፡ ስድስቱ ሐይቆች ካሉበት ስፍራ ጀምሮ እስከ ገለምሶ ከተማ ድረስ ያለው መሬት በኢቱ ኦሮሞ አጠራር “ፎዱ” ይባላል፡፡ “ማዕከል” ማለት ነው፡፡ ይህ ማዕከላዊ ወረዳ ለሶስት ጉዳዮች ብቻ የተከለለ ነው፡፡ አንደኛ “አባ ቦኩ” የሚባለው ርእሰ መስተዳድርና “ቃሉ” የተባለው መንፈሳዊ መሪ መኖሪያ ነው፡፡ ሁለተኛ የኦዳ ቡልቱም የገዳ ስርዓት ማዕከላዊ ተቋማት፣ የህዝቡ መንፈሳዊ ተቋማት እና የዞን አቀፍ በዓላት ማክበሪያ ስፍራዎች የሚገኙበት ክልል ነው፡፡ ሶስተኛ ለህዝብ ጠቀሜታ ብቻ የሚውሉት ስድስቱ ሆራዎች የሚገኙበት ክልል ነው፡፡ በመሆኑም የኢቱ ኦሮሞ ተወላጆች በሙሉ በዓመት ወይንም በሁለት ዓመት አንዴ ከብቶቻቸውን ወደነዚህ ሐይቆች እያመጡ ውሃ ያጠጧቸዋል፡፡ የኢቱ ሽማግሌዎች እንደሚናገሩት ከብቶች የሆራን ውሃ ካልጠጡ እንዳሻቸው ሳር አይመገቡም፡፡ ስለዚህ ከብቶቹን ወደ ሆራ መውሰዱ እጅግ አስፈላጊ ተግባር ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ይህ ስርዓት Nadha Baasuu ይባላል፡፡ የቱለማ ኦሮሞ የኢሬቻን በዓል የሚያከብርበትንም ስፍራ ካያችሁ ተመሳሳይ ነገር ታገኛላችሁ፡፡ በኦዳ ቡልቱም ዙሪያ ያሉት ስድስት ሐይቆች በቱለማ ምድርም አሉ፡፡ እነርሱም “ሆረ አርሰዲ”፣ “ሆረ ኪሎሌ”፣ “ሆረ ሀዶ”፤ “ሆረ ገንደብ”፣ “ሆራ ዋርጦ” እና “ሆረ ኤረር” ይባላሉ፡፡ የቱለማ ኦሮሞ ኢሬቻን የሚያከብረው “ሆረ አርሰዲ” በተሰኘው ሐይቅ ዳርቻ ነው፡፡ እነዚህ ስድስት ሐይቆች የቱለማ ኦሮሞ የፖለቲካ ማዕከል ከሆነው “ኦዳ ነቤ” በቅርብ ርቀት ላይ ነው የሚገኙት፡፡ ይህ ኦዳ ነቤ በዱከም ወረዳ ውስጥ ከሸገር በ37 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ የፖለቲካ ማዕከል ዙሪያም ህዝቡ ሃይማኖታዊ ጉዞ የሚያደርግባቸው Sadeettan Tulluu Waaqaa (ስምንቱ የአምላክ ተራራዎች) የሚባሉት የሸዋ ከፍተኛ ስፍራዎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም “ቱሉ ጩቃላ”፣ “ቱሉ ኤረር”፣ “ቱሉ ፉሪ”፣ “ቱሉ ገላን”፣ “ቱሉ ዋቶ ዳለቻ”፣ “ቱሉ ፎየታ”፣ “ቱሉ ወጨጫ” እና “ቱሉ ኤግዱ” የሚባሉት ናቸው፡፡ የህዝቡ አባ ገዳዎች መቀመጫ የሆኑት የአዋሽ መልካ በሎ እና የገላን ደንጎራ መስኮች የሚገኙትም በዚሁ ወረዳ ነው፡፡ እንግዲህ የቱለማ ኦሮሞ የኢሬቻን በዓል የሚያከብርበት “ሆራ አርሰዲ” ያለው እነዚህ የፖለቲካና የሃይማኖት ማዕከላት ባሉበት መሬት ላይ ነው፡፡ እላይ ከጠቀስናቸው ሶስት ነገዶች በተጨማሪ ሌሎች የኦሮሞ ነገዶችም በዓሉን ያከብሩታል፡፡ ይሁን እንጂ ከኦሮሞ ነገዶች መካከል ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያላቸው የአርሲ እና የመጫ ነገዶች በዓሉን በአንድ ስፍራ የሚያከብሩት አይመስለኝም (መረጃው ያላችሁ አካፍሉን)፡፡ታዲያ ከቱለማ በስተቀር ሁሉም ኦሮሞዎች በዓሉን “ኢሬሳ” እያሉ ነው የሚጠሩት፡፡ ቱለማ ግን “ኢሬቻ” ነው የሚለው፡፡ ይህ ልዩነት ግን ሌላ ሚስጢር የለውም፡፡ በሌሎች ዘዬዎች በምንናገርበት ጊዜ በ“ሳ” ድምጽ የምናሳርገውን ቃል በቱለማ ዘዬ “ቻ” እያሉ መናገር የተለመደ በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ “ለሜሳ”፣ “ከሌሳ”፣ “በሬሳ”፣ “ሙርቴሳ” የመሳሰሉት ቃላት በቱለማ ዘዬ “ለሜቻ”፣ “በሬቻ”፣ “ሙርቴቻ”፣ “ከሌቻ” በሚል ድምጸት ነው የሚነገሩት፡፡ ******* ለመሆኑ የኢሬሳ በዓል የሚከበረው ለምንድነው?…… የኦሮሞ ሽማግሌዎች ይህንን ጥያቄ ሲመልሱን “የኢሬሳ በዓል የሚከበረው ለዋቃ ምስጋና ለማቅረብ ነው” ይላሉ፡፡ መነሻውንም ሲያስረዱ “ዋቃ ክረምቱን በሰላም ስላሳለፈልንና ከሰማይ ባዘነበው ውሃ መልካም ፍሬ ስለሰጠን ያለ ክፍያ በቸርነቱ ለሚንከባከበን አምላክ ምስጋና ማቅረብ የተገባ በመሆኑ ነው” ይሉናል፡፡ “ዋቃ” ፍጥረተ ዓለምን ያስገኘውና ሂደቱንም የሚያስተናብረው አንድ አምላክ ማለት ነው፡፡ ኦሮሞ ችግር ሲገጥመው አቤቱታውን የሚያቀርበው “ለዋቃ” ነው፡፡ በደስታ ጊዜም ተሰብስቦ “ዋቃ”ን ያመሰግናል፡፡ ኢሬሳ የዚህ ዓይነቱ የምስጋና ማቅረቢያ በዓል ነው፡፡ ኢሬሳ በክረምቱ የወንዞች ሙላት ምክንያት ተቆራርጠው የነበሩ ቤተ ዘመዶችና ልዩ ልዩ ጎሳዎች የሚገናኙበት በዓል ነው፡፡ በመሆኑም በበዓሉ የተገኙት ሁሉ ይቅር ይባባሉ፡፡ ገንዘባቸውን ለሌሎች ያበደሩ ሰዎችም በሌሎች ላይ ያላቸውን እዳ ይሰርዙላቸዋል፡፡ በዓሉ የሚከበርበት ቀን የዓመቱ መጀመሪያ ተደርጎ የሚቆጠር በመሆኑ ዓመቱ የደስታና የብልጽግና ይሆን ዘንድ የመልካም ምኞት መግለጫዎች ይጎርፋሉ፡፡ የህዝቡ መንፈሳዊ መሪ የሆነው “ቃሉ” ለህዝቡና ለሀገሩ “ኤባ” (ምርቃት) ያደርጋል፡፡ ታዲያ ማንኛውም ሰው ወደ በዓሉ ስፍራ ሲሄድ አለባበሱን ማሳመር ይጠበቅበታል፡፡ በእጁም የወይራ ቀንበጥ፣ እርጥብ ሳር አሊያም የአደይ አበባን ይይዛል፡፡ በነገራችን ላይ በጥንቱ ዘመን ከዚሁ የኢሬሳ በዓል ትይዩ ሌላ በዓል ይከበር እንደነበርም ልብ በሉ፡፡ ይህኛው በዓል የሚከበረው የክረምቱ ዝናብ ሊጀምር በሚያስገመግምበት የሰኔ ወር መግቢያ ላይ ነው፡፡ የበዓሉ ማክበሪያ ስፍራዎች ደግሞ ተራሮችና ኮረብታዎች ናቸው፡፡ ይህ በዓል “መጪው ክረምት መልካም የዝናብና የአዝመራ ወቅት እንዲሆንልን ለዋቃ ጸሎት ማድረስ” በሚል መንፈስ ነው የሚከበረው፡፡ በዓሉ በምዕራብ ሀረርጌው የኢቱ ኦሮሞ ዘንድ “ደራራ” እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡ የቱለማ ኦሮሞ ደግሞ “ኢሬቻ ቱሉ” (የተራራ ላይ ኢሬሳ) ይለዋል፡፡ በዓሉ በሌሎች ኦሮሞዎች የሚጠራበትን ስም ግን አላውቅም፡፡ በደራራ ጊዜ የሚፈለገው ትልቁ ነገር “ጸሎት” (Kadhaa) ማብዛት ነው፡፡ መዝፈንና መጨፈር አይፈቀድም፡፡ በኢሬሳ ጊዜ የሚፈለገው ግን “ምስጋና” (Galata) ማብዛት እና ደስታን ማብሰር ነው፡፡ በዚህኛው በዓል ዘፈንና ጭፈራ ይፈቀዳል፡፡ በሁለቱም በዓላት የዋቃ ስም ይለመናል፡፡ ለዋቃ መስዋእት ይቀርባል፡፡ ለመስዋእት የሚታረደው ጥቁር በሬ አሊያም ጥቁር ፍየል ነው፡፡ ይህም በጣም መሰረታዊ ነገር መሆኑን ልብ በሉ፡፡ በበሬው ቆዳ ላይ ቀይ ወይንም ነጭ ነጥብ በጭራሽ መኖር የለበትም፡፡ የበሬው ገላ ከጭረትና ከእከክ የነጻ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም በሬው በደንብ የበላና የደለበ ሊሆን ይገባል፡፡ አንዳንድ ሰዎች “የበሬው ቆዳ ጥቁር መሆን አለበት” የሚለውን አስተርዮ እንደ ባዕድ አምልኮ እንደሚያዩት ይታወቃል፡፡ ነገሩ ግን እንዲያ አይደለም፡፡ የበሬው ቆዳ ጥቁር መሆኑ የሚፈለገው በዋቄፈንና እምነት መሰረት “ሰዎችን የፈጠረውና በሰዎች የሚመለከው አምላክ ጥቁር ነው” ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ ይህም “አምላክ በመልኩ ጥቁር ነው” ማለት ሳይሆን “ዋቃ በስራው እንጂ በአካሉም ሆነ በሚስጢሩ ለሰው ልጅ በጭራሽ አይታወቅም” ለማለት ነው፡፡ በመሆኑም የጥንቱ ኦሮሞዎች ዋቃን ሲለማመኑት እንዲህ ነበር የሚሉት፡፡ Yaa Waaqa (አንተ አምላክ ሆይ) Jabaa hundaa olii (ከሁሉም በላይ ጥንካሬ ያለህ) Tolchaa bobbaa fi galii (ወጥቶ መግባቱንም የሚያሳምረው) Guraacha garaa garbaa (ጥቁሩ እና ሆደ ሰፊው) Tokicha maqaa dhibbaa (በመቶ ስም የሚጠራው አንድዬ) ይህ የጥቁር ነገር ከተነሳ ዘንዳ በኦሮሞ ባህል መሰረት ጥቁር በሬ ከፍተኛ ዋጋ ያለው መሆኑን ልብ በሉ፡፡ የቢሾፍቱና የገላን አካባቢ የኦሮሞ አርሶ አደር ሁለት ነጭ በሬዎች የሚገዙበትን ዋጋ ለአንዱ ጥቁር በሬ ብቻ ሊያወጣ ይችላል፡፡ ******* የኢሬሳ እና የደራራ በዓላት በጥንቱ ዘመን ከኦሮሞ ህዝብ በተጨማሪ የምስራቅ ኩሻዊያን (Eastern Cushitic People) በሚባሉት የቤጃ፣ የሳሆ እና የሶማሊ ህዝቦችም ይከበሩ እንደነበረ ተረጋግጧል፡፡ እነዚህ ህዝቦች ቀደም ብለው የእስልምናን እምነት በመቀበላቸው በዓላቱን ማክበሩን ትተውታል፡፡ ይሁንና እንደነርሱ የኩሻዊ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነው የአፋር ህዝብ እስከ ቅርብ ዘመን ድረስ የኢሬሳን በዓል ያከብር እንደነበረ ልዩ ልዩ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ሁለቱ በዓላት የሚከበሩባቸውን ወቅቶች፣ የየበዓላቱን ዓላማ እና በዓላቱ የሚከሩባቸውን አውዶች ያጠኑ ምሁራን በዓላቱ በጥንት ግብጻዊያንም ይከበሩ እንደነበረ አረጋግጠዋል፡፡ ይሁንና ተመራማሪዎቹ “የበዓላቱ ምንጭ ጥንታዊት ግብጽ ነች ወይንስ ከግብጽ በታች የሚኖሩት የኩሽ (ኑቢያ) ህዝቦች?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ተቸግረዋል፡፡ ጥያቄውን አስቸጋሪ ያደረገው የግብጻዊያኑ እምነት ብዝሃ አማልክት (Polytheism) የተቀላቀለበት መሆኑ ነው፡፡ ኩሻዊያኑ ግን “ዋቃ”፣ “ዋቅ፣ “ዋቆ” እያሉ በተቀራራቢ ቃላት ከሚጠሩት አንድ አምላክ በስተቀር ሌሎች አማልክት የሏቸውም፡፡ በዚህ ረገድ የሚደረገው ጥናት ሲጠናቀቅ ውጤቱ የሚታወቅ ይሆናል፡፡ ለሁሉም ግን ኢሬሳን ለሚያከብሩት የኦሮሞ ወገኖቻችንን መልካም በዓል እንዲሆንላቸው እመኛለሁ!! ----- አፈንዲ ሙተቂ መስከረም 22/2008 ሀረር -ምስራቅ ኢትዮጵያ ------ ምንጮች 1. Afendi Muteki: The Ittu Oromo of Carcar, Origin, Institutions and Dispersions (A Project on Progress) 2. Gada Melba: Oromia, An Introduction to History of the Oromo People: Khartum፡ 1988 3. Enrico Cerulli: A Falk Literature of the Oromo People: Harvard: 1922 4. Johann L. Krapf, :Travels, Researches and Missionary Labors during an Eighteen Year's Residence in Eastern Africa, London, 1860 5. Mohammed Hasasan: The City of Harar and the Islamization of the Oromo in Hararge, Atlanta, 1999 6. የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ “በገዳ ስርዓት የቱለማ ኦሮሞ ፖለቲካ”፤ ፊንፊኔ፣ 2000 7. ልዩ ልዩ ቃለ ምልልሶች Photo :-miky sultan

#ጀቡቲ የማን ነበረች/ Djobouty

የኢትዩጵያ ግዛት አካል ለነበረችው ጂቡቲ መገንጠል ማን ነው ተጠያቂው ??????? https://www.facebook.com/wallo.lion.9 ጂቡቲ እስከ 1897 ድረስ የኢትዩጵያ ግዛት አካል ስትሆን በተለይም የኢፋትና አዳል ሙስሊም ሱልጣኔቶች ዋና የባህር በር እና መቀመጫ ስትሆን የእስልምና ሃይማኖት ወደ መሃል ሃገር እንዲገባና እዲስፋፋ ትልቅ ቦታ ነበራት ። ከ13ኛው ክፍለ ዘመን እስከ 16ኛው .ክ.ዘ የክርስቲያን መንግስት በኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂ አልጋሃዚል በመጨረሻ በ1529 እሲኪሸነፍ ድረስ ዋና የሃገሪቱ የባህር በር ነበረች ። እንዲያውም በተደጋጋሚ በክርስቲያን ነገስታት እነ አምደፂዎንና ዘርያቆብ እና በሙስሊም ሱልጣኔት መካከል የነበርው ፍልሚያና ጦርነት ይህንን ዋና የባህር በር ንግድ ለመቆጣጠር ነበር ። እንደሚታወቀው የጂቡቲ ህዝብ ከአፋር ፣ከሱማሌው ፣ከሃደሬ ፣ከአርጎባና ኦሮሞ በተወሰነ የዘር ሃረጉ ይመዘዛል ። ሌላው ይቅርና ግብጻዊያን የጂቡትን እስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ በመርዳት የጥንቱን ኦቦክና ታጁራን (የአሁኑን ጂቡትን ) ለመውረር ብዙ ጥረት አድርገዋል፣ በኃላም በዚሁ በኩል አድርገው ነው ሃረርንም ለመውረር የሞከሩት ። በዋናነት ፈረንሳይ የአሁኗ ጂቢቲ ለመውረር ፍላጎት ያሳየችው ገና በ1860 መጨረሻ ጀምሮ ነው ። በመቀጠልም ግዛቴ ነው የሚል አዋጅ አስነግራ ጂቡቲን እንደ አንድ ግዛቷ ማስተዳደር ጀመረች በመጨረሻም በ1897 ከሚኒልክ ጋር በመስማማት የኢትዩጵያና ጅቡቲ የደንበር ወሰን ተካለለ ። ይህ ስምምነትም እንደገና ፈረንሳይ ከኃይለስላሴ ጋር በ1945 እና 1954 ዓ.ም ዳግም በውል ስምምነት ፀና ። ከእነዚህ የውል ስምምነቶች በኃላ ጅቡቲ ራሷን የቻለች በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር ያለች ሃገር ሆነች ። በመጨረሻም በ1977 ሉአላዊ ሃገር ሁና ከእናት ሃገር ኢትዩጵያ ተገንጥላ ራሷን ችላ ተመሰረተች ። እስኪ ይህንን የሚከተለውን ታሪክ አንብቡት ።

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...