ቦለ ቀያ
የቦለቀያ ጭስ የመታጠን ጥቅም እና ስርዓቱ
by( miky sultan &Abdu moh)
ቦለቀያ የኦሮምኛ ቃል ሲሆን #ቦለ ማለት ጉድጓድ #ቀያ ማለት ደግሞ የወይባ እንጨት (ጪሰ) ማለት ነው ። ሲጠቃለል የጪስ ጉድጓድ እንደማለት ነው ። #ቦለ_ቀያ በአማራ ክልል በወሎ ኦሮሞ አስተደዳደር ዞን በተለይ በገጠሩ ማኅበረሰብ ዘንድ እጅግ በጣም የሚወደድ እና የሚዘወተር በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ባህላዊ ጭስ የመታጠን ስርዓት ነው።
እርግጥ ነው ቦለ ቀያ በወሎ ባብዛኛው አከባቢ እንዲሁም በኦሞሚያ ክልል ይጠቀሙታል።
ባከባቢው ባህል መሰረት የቦለ ቀያን ጭስ ያላገቡ ሴቶች አይታጠኑም ፣ በዋናነት የሚታጠኑት ያገቡ ሴቶች ሲሆኑ አግብተው የሚያውቁም ይጠቀማሉ። አዲስ ያገባች ሙሽራ በጫጉላ /ቁልፎ/ ውስጥ እያለች /ባገባች ማግስት/ ጀምራ ቦለ ቃያ መጠቀም የዘወትር ተግባሯ ነው፡፡ ለዛም ሲባል ባልዪው ለሙሽሪት ከሚያዘጋጃቸው ነገሮች መካከል የቦለቂያ ጉድጓድ እና መለሆ ዋነኞቹ ናቸው ማለት ነው።
በተጨማሪም የሙሸሪት ቤተሰቦች ሊጠይቋት ባገባች በሶስተኛ ቀኗ ሲመጡ ይዘው ከሚመጡት ቁሳቁሶች መካከል አንዱ ወይባ (መለሆ) መሆኑ ደግሞ ማህበረሰቡ ለቦለቀያ የሰጠውን ትኩረት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል።
እንዴት እንደሚከወን ደግሞ በዝርዝር እንመልከት
መጀመሪያ ለጭስ ማጨሻነት እንዲያገለግል ተደርጎ በጠባቡ ጉድጓድ ይቆፈራል፣ ለእግር ማሳረፊም ከታች ከወለሉ ከፍ ብሎ አግድም በአንድ እንጨት ይሰራል፣ በመጨረሻም የጠባቡን ጉድጓድ ዙሪያ ተከትሎ ከፍ ተደርጎ በጭቃ ዙሪያውን በጭቃ ይመረጋል፣ በመጨረሻም ለመቀመጣ ይሆን ዘንድ ጠርዙ ላይ የእንጨት ርብራብ ተሰርቶና ተስተካክሎ በደንብ ይዘጋጃል ።
ለማጨስ የሚጠቀሙት የእንጨት አይነቶች < ቢሬንሳ (መለሆ) አገምሰ፣ እና ምስራች፣ የሚባሉትን ሲሆን በዋናነት ግን "መለሆ" በመባል የሚታወቀውና ቢጫ መልክ ያለውን የእንጨት አይነት ይመርጡታል ። መለሆም ሆነ ሌላ በአቅራቢያ ያለውን ከላይ ከጠቀስኩት የእንጨት አይነት አንዱን በጣም ሳይቀጥን ይሰነጣጠቃል፡፡ ከዚያም በጠባቡ በተቆፈረው ጉርጓድ ውስጥ በተያያዘው የእሳት ፊም ላይ በማስቀመጥ በደንብ እስኪጫጫስ ይጠበቃል፡፡
ለመታጠን የምትፈልገው ሴት ወደ ጭሱ ከመግባቷ በፊት ገላዋን ትታጠብና ሰውነቷን በሙሉ በ "ቀሉ" ቅቤ በደንብ ትለቀለቃለች ። ከዚያም በጭሱ ዙሪያ በተዘጋጀው ማረፊያ (መቀመጫ)ላይ ትቀመጣለች ፣ ጭሱ እንዳይወጣ ተደርጎ በቁርበት /የቆዳ ምንጣፍ/ አሊያም በተለያዩ ልብሶች ማለትም ጋቢ ወይም ብርድ ልብስ በመሳሰሉት ተጀባቡና ለተወሰኑ ሰዓታት ትቆያለች ፡፡ ከታች ወደላይ የሚጨሰው ጭስ ግለቱ ሰውነቷን ሙሉ በሙሉ በላብ እንዲጠመቅ ያደርጋል፣ በደንብ ካላባት በኋላ እንደተጀቧቦነች ንፍስ እንዳያገኛት በጥንቃቄ ትነሳና እንደተጠቀለለች ለተወሰነ ደቂቃ (ላቧ አስኪደርቅ) ጋደም ትላለች (ትተኛለች) ።በዛ ቆይታ መካከል ግን በሕህሉ መሰረት ገንፎ ፣ሙቅ፣ ጨጨብሳ ወይም ሌሎች መሰል ምግቦችን በመመገብ ሰውነቷን ካቀዘቀዘች በኋላ ተነስታ ገላዋን ታጥባ ልብሷን ትለብሳለች፡፡
ባከባቢው ባህልመሰረት ቦለቀያ የማተትጠቀም ሴት ራሷን የማትጠብቅ፣ለውበቷና ጠረኗ የማትጨነቅ፣ለባሏ ክብር
/ግድ/ የሌላት፣ ሰነፍና ዝርክርክ እንደሆነች ተደርጋ ነው የምትታሰበው ፣ ውግዘትም ይገጥማታል ፣ሴት ልጅ ካገባች እጅና እግሮቿን በእንሶስላ ማቅላትና የወይባ ጠረን ሊኖራት የግዴታ ያህል ይጠበቃል። ቦለቅያ መሞቅ ለሴት ልጅ ጥሩ መዓዛዋ እንዲያውድ የፈካ ውበት እንዲኖራት ከማስቻሉም በላይ በርካታ ጥቅሞች እንደሚሰጥም ያነገራል ። ቆዳን ያጠራል፣ ቡጉር ያጠፍል፣ ፀጉር ያረዝማል፣ የማህፀን በሽታ ይከላከላል፣ የንፍስ በሽታን ያድናል፣ ከወሊድ ቦሃላ የሚፈጠሩ ቁስሎችን በቶሎ ይፈውሳል፣ ሰውነት ያጠነክራል ፣በተለይ በባልና ሚስት መካከል ያለውን መቀራረብ ያሳምራል (ፍቅር) እንዲጨምር እጅግ ይረዳል ።
ይህ የቦለቅያ መታጠን ስርዓት የወሎ ኦሮሞ አስተዳደር ዞን ከሚታወቅበት የባህል እሴቶቹ መካከል አንዱ ቢሆንም ዛሬ ላይ ከገጠር ወጥቶ በዛው በወሎ የተለያዩ አከባቢዎች እንዲሁም በራያ ፣በኦሮሚያ ክልል ደግሞ በጉጂ፣ አርሲ፣ እና ቦረና ፣ በስፍት አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል ።ከተወሰነ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ እውቅናው ጨምሮ በትላልቅ ያገራችን ከተሞች ጭምር እየተለመደ መጥቷል፡፡
በተለይም በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ የሃገራችን ከተሞች የቦለቅያ መሞቂያ ቤቶች ተከፍተው ለሴቶች የውበት መጠበቂያነት እየዋሉ ሲሆን የገቢም ምንጭም ለመሆን ችሏል ። አስፈላጊው ምርምርና /ጥናት/ ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ተከናውኖ ስለ ጥቅምና ጉዳቱ የተባለ ነገር ባይኖርም ከተጠቃሚዎቹ በተገኘው መረጃ መሰረት ከላይ የዘረዘርኳቸውን ጥቅሞች እንደሚሰጥ ይታመናል፡፡ አበቃሁ ።።።
ባህላችን ዉበታችን እና የማንነታችን መገለጫ ነው ።
@Oromo_graphya1
@Odaatiktok