Translate

Wednesday, April 20, 2022

#warqituu wadaajoo

የወሎ ኦሮሞ ሁለት ኃያላንና ተፎካካሪ ብርቱ ጀግና አይደፈሬ ጠንካሬ ንግስቶች ወርቂትና መስታውት ታሪክ በነጋሽ ቅማንት የተፃፈ 
×××××××××××××||||||||||||××××××××××××××××
የሊበን አመዴ ዋና ከተማ መቅደላ ፣ የወርቂት ዋና ከተማ አምባሰል ነበር : ወርቂት የባላቸው አሊ ሊበን( አባ ቡላ) በ1842 ሰለሞቱ የልጃቸው አመዴ አሊ ሞግዚት ሆነው ያስተዳድሩ ነበር። ሙሉ ስሟ ንግስት  ወርቂቱ ወዳጆ ይመር ቦሩ ትባላለች።

የመስታውት ልጅ እንደ ወርቂቱ ልጅ አመዴ ይባላል። ወርቂትና መስታውት በሽር ሊበንና አሊ ሊበን የተባሉ የሁለት ወንድማማች ሚስቶች ነበሩ ። ስለዚህ ሁለቱ አመዴዎች ከስማቸው መመሳሰል ባሻገር የስጋ ዝምድና ነበራቸው ። ከሁለቱ ግን እስከ መጨረሻው አፄ ቴዎድሮስን ያስጨነቀው የመስታውት ልጅ አመዴ በሽር ነበር ። በወሎ ኦሮሞ የአፄ ቴዎድሮስ በትር የበረታውና በርካታ ግፎችን የፈፀመው አመዴ በሽርን አሸንፈው አለመያዛቸው ነበር ። አፄ ቴዎድሮስ 7 ጊዜ በወሎ ኦሮሞ ላይ ዘምተው አንዱንም ሳያሸንፊ  አመዴ ሊበንን ለመማረክ አልቻሉም ነበር ።

~ የወርቂት ልጅ ግን አመዴ አሊ ወርቂት በተሸነፈች ጊዜ አመዴ አሊን ለንጉሱ ቴዎድሮስ ሰጥተው ክርስትና አስነስተውት ነበር ከዚያም ለጥቂት ጊዜ የአምባው ገዥ አድርገው ሹመውት ነበር ።ወዲያው ግን እናቱ ወርቂት ለምርኮኛው ምኒልክ ከመቅደላ ለማምለጥ እጇ አለበት ተባብራለች ተብሎ ልጇ አመዴ አሊ በሰንሰለት ታስሮ ሲማቅቅ ከቆዩ በኃላ በአሰቃቂ መልኩ በመቅደላ ገደል ተገድሏል። ንግስት ወርቂትም በአንድ ልጃቸው ሞት ከባድ መሪር ሃዘን ገቡ ። ወደ ሸዋ በመሄድም ለአንድ አመት ቆይተው በጉዲፈቻ አንድ ወንድ ልጅ ይዘው ወደ ወሎ ተመለሱ ።

 የወርቂት ከፓለቲካ ውድድሩ በልጇ መሪር ሃዘን መውጣት ለመስታውት ጥሩ አጋጣሚ ፈጠረላት። ወይዘሮ መስታዉትም የልጃቸው አመዴ ሊበን ሞግዚት በመሆን ከድፍን ወሎ ኦሮሞ ሙሉ ድጋፍ ተቸራቸው። የመቅደላን አምባን በተደጋጋሚ መውጋት ጀመረች ። የእንግሊዝ ጦር ወደ መቅደላ ሲቀርብም ከወሎ ኦሮሞ ባላባቶች ወርቂትና መስታውት ጋር መደራደር ነበረበትና አስጠርቶ ሁለቱንም በሰራዊቱ ካምፕ ውስጥ አነጋግሯቸዋል ታሪካዊ ፎቶግራፎችም አንስተዋቸዋል። የወርቂት ይሁን የመስታውት ጦርም መቅደላን እያንዳንዱን መግቢያ መውጫ በር መሽሎኪያ ቀዳዳዎች ሁሉ እንዲዘጉ አፄ ቴዎድሮስና ሰራዊታቸው እንዳያመልጡ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። የሚያሳዝነው ግን ጀኔራል ሮቤርት ናፒየር ከመቅደላ ድል በኃላ ለመስታውት ይሁን ለወርቂት ምንም የጦር መሳሪያ እርዳታና ድጋፍ ሳያደርጉ ይባስ ብሎ የመቅደላ አምባን በርካታ ቦታዎችን ምሽጎችን እንዳይጠቀሙባቸው በፈንጅ አፈራርሰው ነበር  የሄዱት ። 

በመጨረሻም ይህ የወራሂመኑ መሐመዶች ስርኦ መንግስት ሃረግን ተከትለው ወሎን ሲያስተዳድሩ የቆዩት መሀመድ አሊ በአፄ ዩሃንስ ክርስትና ተነስተውና የክርስትና ስማቸው ሚካኤል ተብሎ የራስነት ማዕረግ ተሰጣቸው። በተመሳሳይ ሁኔታም የባላባቷ የወይዘሮ መስታውት ልጅ የሆኑትና እና በፈረስ ስማቸው አባዋጠው በመባል የሚታወቁት አመዴ ሊበን በንጉስ ሚካኤል የክርስትና አባትነት የክርስትና ስማቸው " ኃይለማርያም " ተብለው ተጠምቀው የደጃዝማችነት ማዕረግ ተሰጣቸው። ራስ ሚካኤልም የንጉስ ሚኒልክን ሴት ልጅ አግብተው ልጅ እያሱን ወለዱ ።

 ልጅ እያሱም ኢትዮጵያን ከ1913-1916 በመፈንቅለ መንግስት እስኪወገዱ ድረስ አስተዳደሩ በርካታ ለውጥም አምጥተው ነበር ለምሳሌ ኃላቀር የፍርድ ስርዓትን የቁራኛ ስርዓትን ( ከሳሽና ተከሳሽ ታስረው የሚቆዩበት) አስቀሩ ፣ ሌባን የሚያውጣጡበትን ሌባ ሻይ የሚባለውን ስርዓት አስቀሩ ይህ ስርአት አንድን ህፃን ልጅ እጽ ወይም አደንዛዥ መጠጥ ይሰጠውና በርካታ ሰዎች ይሰበሰቡና ከእነዚህ ውስጥ ሌባውን ጠቁም ይባል ነበር፣ ልጅ እያሱ የመንግስት ኦዲት ያስጀመሩ ነበሩ ፣ የከተማ ውስጥ ደንብ አስከባሪ ፓሊስ ያስጀመሩ ነበሩ ።

ባላምባራስ ነጋሽ( ገሞራው ቅማንት) 

Sunday, April 3, 2022

#ሼኽ ጀማሉዲን አንይ

ጀማሉዲን ሙሀመድ አኒ (አራርሶ ሮውብሶ) https://t.me/Oromo_geography * ــــــــــــــــــــــــــــــــــــ * ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የዒልም ኮኮብና የጅሀዱ ጀግኖችን አውጥታ በታሪኳ አሳይታናለች። ከነዚህ ዘመነኞች ሙስሊም ጀግኖች መካከል: ታላቁ አባታችን ጀማሉዲን ሙሀመድ አል-ዐኒ (ረሂመሁላህ) በግንባር ቀደምነት እናገኛቸዋለን። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና እስልምና ታሪክ ስናስብ አባዬ ለእያንዱ ትውልድ ተምሳሌትና ታላቅ ባለውለታ ናቸው። በተለየም በኢስላም መድረሳ ፍሬያማ-ፍሬዎቹን ኮትኩተው፡ በዲኑ ሥርዓታማ ዘዴዎች ላይ ተንከባክበው በሁሉም የጥበብ ዘርፍ የተካኑ ብቁዎችን ቀርጸው … ሙስሊሙ ዑማ የሚመሩ ፣ ኢስላምን የሚያስፋፉና ዘብ የሚቆሙ የቁርጥ ቀን ልጆችን በማብቀት እና እንዲሁም በየ ጉራንጉሩ በየ ኮሮብታው ከመሾም አንፃር እርሳቸውን የሚመስል የሀገሬ ታሪክ እንዳጣ በተከታዩ ጽሑፉ እናያለን። . . . #ጀማሉዲን_ሙሀመድ_አኒይ ------------------ እንደ ሒጅሪያ ዘመን አቆጣጠር 1211 ወይም በሀገራችን 1781 ዓ.ም በራያ ምድር፡ ወርሳ-ሜሳ መንደር ፡ በልዩ ስሟ ‹ገልገሎ› ተብላ ከምትታወቅ ስፍራ ፡ ከሮውብሶ ኦቦ እና ሃዋ አብዱልቃድር አብራክ ወንድ ልጅ ተገኘ። ስሙም ‹አራርሶ› ተባለ። - ጀማሉዲን ሙሀመድ አኒ የልደት ስማቸው «አራርሶ» ነው። የትምህርት ዕድሜ ላይ ሲደርሱ «ሙሀመድ» የሚለዉን አንጋፈው ስያሜ በመምህራቸው ተለገሱ። የሗላሗላ ለአያሌ ህዝቦች አባት ፣ ዓይንና ጆሮ ፣ ኃይልና ጉልበት ሆነው ትሩፋተ-አያልነታቸው ገዝፎ ሲታይ እጅግ በርካታ የክብር ስያሜ እንደጉድ ተዥጎደጎደላቸዋል። ተገቢ የሆኑና ባልተቤታቸውን ያገኙ ገላጭ ሞክሼ ስያሜዎች ነበሩ። ለአብነት ያህል ፣ እውቀት ተግባር ሁለተናቸው ኢስላማዊ ሆነው ሲገኙ «ጀማሉል-ዲን» የሚል እካያ ተቸረ። ነገረ ሁሏቸው መምህራቸውን ይመስሉ ነበረና ‹አንይ› የሚል ተጥሮተ-ስም ተደለበ። አባዬ ፣ የዲኑ-ችቦ ፣ የኢስላም-እንፅብራቅ ፣ ጸሐይ ፣ የፍቅር እርሾ ፣ የእዉነት-ጥራዝ ፣ የዕዉቀት ማማር ፣ የእውቀት ውበተ-ጉልላት ፣ የቡራኬ ልዕል እና . . . . . . ወዘተ ሌሎች የተለዩ ክብረ ስያሜዎችን ወዳጅ ገበር ሁሉ ባፈቀረ ቀልቡ አንዳሻው ስያሜም ይጠራቸዋል። እኛም በዚህ አብዣኛው ዘንድ በሚታወቁት ፣ ጀማሉዲን ሙሀመድ አኒይ እና አራርሶ እንዲሁም አባዬ የሚሉ መጠርያዎችን ተጠቅመናል። #አራርሶ_ሮውብሶ (ጀማሉዲን አኒይ) ------------------------- ጀማሉል-አኒይ አባታቸዉ ሮውብሶ (ቃዲ-ኢብራሒም) ፣ ባቦ ፣ ቦሩ ፣ ዱዮ ፣ በረንቶ ፣ ሃሞ ፣ ሸኽ ሀሰን #ሐሰኒይ (ከነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ የዘር ሀረግ የተመዘዙ) ናቸው። ከኦሮሞ ከታወቁ ጎሳ ሆርሶ-ሴሮ የተገኙ ናቸው። እናተቸው ደግሞ ሃዋ ሸኽ አብዱል-ቃድር ሸኽ ሙስጠፋ ሸኽ ኡመር ሸህ አይፈራ ሸህ ሙሀመድ ሰኢድ ትባላለች። ቤተሰቦቿ መግሪብ (ሞሮኮዊ) አረቦች ናቸው ይባላል። የዘር ሀረጓ ከፈቂህ ሙሳ አልጀበርቲ ዘር የተመዘዘ #አዴ_ከቤሬ ከተባሉት ከነቢዩ ሙሀመድ (ሶለላሁ አለይ ወዓሊሂ ሰለም) ዘር #አህለልቤይት ናት። ለኢማሙ የጀማሉዲን-አኒይ ስኬት ትልቁ አስተዋጽኦ፡ የእናታቸው ጥረትና ትግል ዋነኛው ነበር። እርሷም ለሁሉም ሙስሊም ምርጥ ተምሳሌት ናት። የልጇ ታላቅነት የርሷ ጥረት ዉጤት በመሆኑ ለኢትዮጵያ እስልምና ባለዉለታ ነች። የጀማሉዲን አኒይ እናት ሃዋ ሸኽ አብዱል-ቃድር (የአላህ እዝነትና ቱሩፋት በእርሳቸዉ ላይ ይጉረፍና) ልጇም የትምህርት እድሜ ላይ ሲደርስ፡ ከትውልድ መንደሯ ወደ ዕዉቁ ዓሊም ሸኽ ሰይድ አል-ፈቂህ ዙበይር አስቃሬ ዘንድ ለዚያራ (ጉብኝት) እና ልጇም ከቡራኬያቸው እንዲሳለምና ዱዓ ያደርጉለት ዘንድ መጡ። ከዚያም እናታቸውም እንዲህ አለች፦ «ለዚህ ለልጄ ጸልዩለት። አላህ በእስልምና መንገድ እንዲቀርፀው። የሱ አያቶቹና አጎቶቹ የጦር ሰዎች ስለነበሩ የሞቱትም በጦርነት ነው። ስለዚህ ይህ ልጄም የቤተሰቡ አይነት እጣ እንዳይገጥመው ስጋት ይዞኛል » አለቻቸው። ሸይኽ አስቃሬም ዱዓ አደረጉላቸውና እንዲህ አሉ፦ «ይህ ልጅ ላይ ስጋት የሆነብሽ ፍርሃት መድሃኒቱ ይህ ቁርዓን። የዚህ እውቀት ነው ፈውሱ። እኔ አስተምረዋለሁ» አሏት። ከዚያም የልጃን መጠርያ ስሙን ጠየቋት። እርሷም፡ « ስሙ አራርሶ ሮውብሶ ባቦ ነው። (አራርሶ የኦሮምኛ ቃል ሲሆን ፣ አስታራቂ ማለት ነው።) ስሙን አራርሶ ያልኩት ይህን በሁለቱ ጎሳ መካከል ያለው ጦርነት በስሙ በርከት ሰላም ይለግሰን ዘንድ በመሻት ነው» አለቻቸው። ሸኽ አስቃሬም « እኔ ሙሀመድ ብዬ ሰይመዋለሁ» አሏት። እሷም በዚህ ተስማማች። ( እንዴትስ አትስማማ ? የማን ስም ሆኖ ? ) ልጃንም ለሸኩ አስረክባ ተመለሰች። ቁርዓንም በእረሳቸው ላይ አከተሙ (ጨረሱ)። ቁርዓን ያስቀሯቸው እናተው ናት። እንዲሁም አክስታቸው ናትም ይባላል። ሸኽ አስቃሬ ፣ ተማሪያቸውን ጀማሉል-አኒ የቁርዓንን ንባብ ተምረው እንደጨረሱ ፣ የፊቂህ ትምህርት ሊቅ ወደሆኑት ሸኽ ፈቂህ ገንደ-አውልዮ (የአውልዮ መንደር ሸኽ) ዘንድ ላኳቸው። በእርሳቸዉም ላይ የመጀመርያ ደረጃ የፊቂህ ትምህርት (ከሻፊዒይ መዝሃብ) ሚንሃጁ-አጧሊቢን ድረስ ተማሩ። በዚህም የመማር ልክፍት ፣ የምሁርነት ጥማት ፣ የኢልም ፍቅር በረታባቸው። ይሁን እንጂ መምህራቸው በወቅታዊ ሙስሊሞች ሁኔታ ከሀገር ሀገር ይቀያይሩ ነበር። ትምህርት ማስተማሩን አቁመው ከአገራቸው ርቀው ወደ ተለያዩ አከባቢ እየተንቀሳቀሱ የዑማውን ሁኔታ ጥናት ያደርጉ ስለነበረ፡ ጀማሉዲን ሙሀመድ አኒን የማወቅ ጉጉት እና የመማር ጥማት አላረካም። በየእለቱ የመማር እድልን ይናፍቁ ነበርና በዚህም ቅር ይሰኛሉ። ሆኖም ወደ ኃይሉ አላህ (ሱ·ወ) ብቁ የሆነ ቋሚ መምህር እንዲገጥማቸው ይጸልዩ ነበር። በዚሁ መካከል ወደዚች መንደር ብዙ ተጓዥ መንገደኛ ጭፍሮች ይመጣሉ። ለሐጅ (ወደ ቅድስቷ ከተማ መካ) ተጓዥ መንገደኛ ሓጃጆች ሲሆኑ። እንግዶቹም ወደዚህ ከመምጣታቸው አስቀድመው ወደ #ሙፍቲል_አናም ሐጂ ዳዉድ አቡበከር ዘንድ በመሄድ፡ ዱዓ እንዲያደርጉላቸው ዚያራ አድረገው ነበር። ሐጂ ሙፍቲ ዳውድ (ረሂመሁላህ)ም « … ከራያ አውራጃ ውስጥ ስትደርሱ ባልደረባዬን ሸህ ሐጂ ጧሂርን ፈልጋችሁት ዘይሩት። ሰላምታዬን አድርሱልኝ። ለናንተም ከሱ ዱዓ ፈልጉ።» ብለዋች ስለነበረ ፣ ከራያ ግዛት እንደደረሱ ስለተጠቆሙት ሰው ማጠያየቅ ያዙ። ሐጂ ጧሂር ከሰዎች ተጠልለው ጧትማታ አላህን በማውሳት ላይ የተጠመዱ ስለሆኑ እምብዛም አያውቃቸውም ነበርና እያፈላለጉ ቀናቶችን ካሳለፉ በሃላ፡ #ገንደ_ሶቶላ ከተባለች መንደር ውስጥ አገኙዋቸው። ሐጅ ተጓዥ እንግዶቹም ጎብኝተዋቸው ከተመለሱ በሃላ ፣ ሰዉ ሁሉ ስለ ሐጂ ጧሂር ማንነት መወራት ይጀምራል። ይህን ስም ተማሪው ሙሀመድ ሮብሶ (ጀማሉል አኒ) ሰማ። ሐጂ ጧሂርም ዘንድ በመሄድ ቂርዓት ጀመረ። መምህሩንም በሁሉም ሸሪዓዊ የጥበብ ዘርፍ እና እነዲሁም በአረበኛ የቋንቋ ጥናት በጠንቃቄና በጥልቀት መርምሮ የፈተሸ እና ለጥቃቅን ነገር ሁሉ የሚጨነቅ ጥንቁቅ ምሁር ሊቅ ሆነው አገኘው። ያጣውንና በናፍቆት ሲፈልግ የነበረው ገጠመው። አስራ ሁለት (12) አመት ከርሳቸው ላይ ተማረ። ከነብዩ (ሶ·ዐ·ወ) ሀዲስ በስተቀረ በሁሉንም የጥበብ ዘርፎች ተካነ። እናማ ይህን ሁሉ ኢልም በመሰብስ ሙጅተሂድ ደረጃ የደረሰው ከሀገሩ ራያ ምደር ሳይርቅ ነበር። የጀማሉዲን ሙሀመድ አኒ የደለበ ወፍራም እጣ ጅመማሮ ከዚህ ይጀምራል። ጥልቅ ከሆነው የህይወት ታሪካቸው መርፌ ባህር ውስጥ ነክሮ የማውጣት ያህል ተሞክሯል። በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል። #ይህ ጽሁፍ የተወሰደው 1· በወሌኔ ሸይኽ (ረሂመሁላሁ) የተዘጋጀ፣ «ታላላቅ የሐበሻ ኡለማወች ታሪክ (ጥሮኖ) መጽሐፍ። 2· የኢማም ጀማሉል አኒ «ሪሳለቱል መይሙን» ለተባለው ኪታባቸው ሙቀዲማ/መቅደም መግቢያ ከተዘጋለት። መሰረት አድርጌ የተወሰዱ ናቸው። በመጨረሻም ምዕራፍ ግርጌ ማን ምን አለ ? የሚለውን ለማመልከት እሞክራለሁ። በይበልጥ ሊንኩን ጠቅ ያድርጉት። https://t.me/Oromo_geography

Sunday, March 20, 2022

#ituu_Qaalluu_sagal

"#ITUUN_SAGALI_QAALLUUTI_KUDHAN" Jechuun Yoom Dhufte? Maaliif Ja'aame?. Haaroomsa Gadaa Ituu kan jalqabaatiin dura Gosti Oromoo Ituu Qaalluu Keesssaa nama Qaallichummaa qabu malee kan biraa akkumma gosa Ituu tan birooti Abbaa Bokkuummaa Caffee Gadaa Ituutiif ni falamu ture. Haaroomsi Sirna Gadaa Ituu Finna Sirna Caffee Gadaa Ituu jechuun beekama. Haaroomsi Gadaa Oromoo jaarraa 10ffaa keessa akka gaggeefame hayyoonni ni seeneessu. Yeroo sanitti Caffeen Oromoo takka qofa turte. ishiinis Odaa Nabee ti. Sababa Ilmaan Oromoo Adda faffagaachaa qubachaa dhufaniin, Haaroomsa Gadaa Oromoo kanarratti murtiin dabarfamtee, Odaan Shanan Oromoo jidfugala Caffee Gadaa tahun tajaajila kennuu jalqaban. Bareentuma keessaa yeroo sanitti kan goodaanee carcar gahe Murawwaa dha. Hundeefamni Sirna Caffee Gadaa Ituutis haaroomsa gadaa Oromootiin booda, Jaarraa 10ffaa keessa ture jechuun ni dandayyama. Haaroomsi gadaa Ituu (Finna) jaarraa sadiin booda jaarraa 13ffaa keessa gaggeefame(Kan sirni Caffee Gadaa Ituu itti jalqabame hin jannee qalbiifadhaa, Sun kana dura). Seenaa Caffee Gadaa Ituu tan jaarraa 10nii oliif jirtu keessatti, Finni Gadaa Ituu marraa Sadii gaggeefame. kun dhalootaan lakkaa'amee Manguddoodhaan taa'ee jira. Finni Caffee Gadaa Ituu kan jalqabaa sababa waldiddaa ilmaan Warree fi Kura Galaaniin gaggeefamuu jalqabe. Ituun Sirna gadaa isaatiin Carcaritti walbulchuu jalqabee dhaloota 5nii booda Finni Gadaa isaanii kun raawwatame. Dhaloota tokkoo jechuun waggaa 80 jechuudha akka manguddoon tiyya jattuti(Maxxarrii - Gadaa Moojii). Duuba Barri Finnaa kun jaarraa 13ffaa (1200-1300) keessatti akkeekama akkan manguddoorraa oddeefadhee, heerreegga isaa hojjadhetti. Finna Gadaa Ituu kan jalqabaa kana keessatti ture murtiin gurguddoon caffee Gadaa Ituu tan odaa bultum maadheeffateen laatamte, akka Odaan Bultuum hanga ammaa kabajaa fi maqaa guddaa saba Oromoo keessatti qabaate itti fufu tan goote. Murtii laataman keessaa takka gosa Qaalluu duraan jilbuu Kuraa Keessatti yaamamtu Kura, Galaanii fi Warree keessaayyis walaba akka taate ofdandeessee dhaabbattu tahe. Sababni kun murtaaheefis osoo amba ifjidduu hin galchiin waldhabdee hortee Ituu Warree fi Kuraa Galaan jidduutti uumamte walabbummaan akka ilaalan, murtii badii raawwatamte madaaltu Qaallichi, Hayyoonni fi Manguddoonni gosa Qaalluu keessas walitti bahaanii akka ilmaan warree irratti kennamtu tahe. Murtii Qaallichi, Hayyoonni fi manguddoonni gosa Qaalluu Ituu tahan kun dabarsan kamuu gosti Ituu hundi akka fudhattu fi hojjiira oolchan kakhatanii, irbuu waliif seenan. Isaaniis Darrabaati hassaasanii, yaa'ii Ituun hundi Odaa jala teessarratti murtii laatan. Murtiin Kennamte ta akkami?. Yeroo kana boode gosa Qaalluu Ituu keessaa Abbaa bokkuu filamuun hafte. gosti Qaalluu Ituu achumaan gosa akkaataa waaqni Oromoo fadhurratti ummata haqaan tajaajiltu akka taatu, siyaasaa gaggeesuurraa bilisa taatee, muuda qofaa fi dhimma waaqaan walqabatu tan gaggeessitu akka taatu tahe. San booda Heerri Oromoo Ituu Saddeeti Saddeetiitti Heerame. Waggaa Saddeettiti Akkaataan Sirni Bokkuu Gadaa Ituu wal Harkaa fuudhuudhaa bifaa fi qabiyyee amma mul'atuun akka kabajamuu kan akkeekkame ja'u Hayyoonni. Jechamni ITUUN SAGALII QAALLUU WAJJIIN KUDHAN ja'uu kunnis gosti Qaalluu Ituu man boobbaa (Jilbuu) Warree, Kuraa fi Galaan jalaa baatee murtii ilmaan warreerratti kennitu akka taatu Finna Gadaa Ituu kan jalqabaa kana keessatti waan mul'ateef, san booda "Ituun Sagalii Qaalluu wajjiin kudhani" jechamni ja'u (man boobbaa jalaa bahuu ishii baada) jalqabame. Finna Gadaa Ituu kan jalqabaatiin dura Gosa Qaalluu Ituu keessaa Abbaan bokkuu fi abbaan duulaatis kan filamaa ture tahu manguddoonni tiyya mirriiggaan mirkaneessan. Akkana jechuun, dheeraadha keessaa muraasa;- " ...Tuqoo wayyuu innaayyee Lammii siree iyyaaguu Guuta innoo guyyoo Lammii Abbaa bokkuu Hayyisa Abbaa dulaa Bita'oo jiloo huloo Qaalluu beerii hidhabu Lammii dooyyoo daarimuu..." Askeessatti, Qaalluu Beerrii Hidhabuu, Lammii Dooyyoo Daarimuu... kan ja'uu jira. Dooyyoo Daarimuu Abbaa Gadaa Caffee Gadaa Ituu kan qosa Qaalluu Ituu keessaa tahe tahuu manguddoonni Ituu ni seeneessu. Dooyyoo Daarimuu jaarraa 13ffaa keessa bara 1225-1232 Abbaa Gadaa Caffee Gadaa Ituu tahuu Seeneessitoonni hammayyaa baayyeen kitaaba isaanii hedduu keessatti barreessanii jiru. Qosti Qaalluu Ituu Qaallicha Abbaa Muuda Ituu tahu wallabummaadhaan kophatti taa'aanii if keessaa muudu. gosa Biraa keessaa Abbaa muudaa tahuun san duras hin turre, san boodas Qaalluu Ituu keessaa malee hin taane. Qaalluun Ituu Muuda gandaa fi gosa Sadeen bareentummaa keessatti gaggeefamu kamuu, isaantu sirna muudaa fi eebbaatiis raawwata. Sababni Qaalluun Ituu Ona Ituutiin malee Afran Qalloo keessa, Humbannaa keesee hanga Wallootti Ona Ilmaan Bareentummaa bakka hedduu qubatanii argamaniif keessaa tokko muudaa fi eebbaaf bakka hedduutti dur muudamanii hojjachaa waan turaniifi jechuun ni dandayyama. Sirni Muudaa gaggeefamu kan Abbaa Gadaa itti muudan qofa hin sahinaa, guyyaa daa'iimni Bareentummaa dhalate, umrii Maxxarriirraa kaasee hanga gadaa moojiitti marsaa gadaa hunda keessa hogu dabran hunda sirni Qaalluun gaggeefamu hedduu tu jira. sirna kaneen hunda ganda saddeen bareentumaa hunda keessatti kan gaggeessuu warra Qaalluu Ituu ti. Bakka Gosti Qaalluu Ituu hin gahinitti, Noolee Keessaa ibiddi tokko bakka bu'ee sirna muudaa gaggesssuu mala Afran Qalloo keessatti. Kana Malees, Qaalluun Ituu Amantaa islaamaa warri saddeen bareentumaa keessaa jalqaba fudhataniis isaanuma keessaayi waan tahaniif, Islaamummaa Barachuu, barsiissuu fi babal'issuuf jecha bakka hedduu qubachuu dandayyanii jiru. Murtiin Heeraa Finna Gadaa Ituu kan jalqabaa kana keessatti kennamte tan biraa, murtii Ilmi Ituu Tokkoo mirga amantaa fadhe qabaachuu ti. Murtii tanaan dura kan amantaa waaqqeefatarraa jijiirate oromummaan isaa irraa mulqamee maqaa warra amantii isa jijjiirsiiseetiin yaamamu ture. Murtii tana keessatti mirga amantaa biraa hordoofuutu labsame waan tahef, ilmi Ituu Eenyummaan Oromummaa isaa osoo hin tuqamiin, amantaa biraa qabaachuu dandayya jechuun heeramte. warra amantaa biraa qabanis ilma gosa ituu godhanii mooggaassuun jalqabamte, kan akka Aw Sa'iid faa. Haa tahuu malee Kaneen Akka Obbo Lukkuu [(Biyyoo Galamsootti, (Qabrii Lukkuu)], Nama dhalootaan Ituu tahe kan jalqaba Amantii islaamaa jaarraa 15ffaa keessa qeebale)] faa yoo taate malee, Irra guddaan Oromoo Ituu Hanga dhuma jaarraa 19ffaa osoo islaamummaa hin fudhatiin hafan. Roorroo Minilik Oromoota Ituu walloo keessa jiranii fi Oromoo walloo, akkasummattis gaafa hararghee too'atu irrattti gaggeessuu jalqabe san akka waan Minilik moormuutti danuun nama Ituu Islaamummaati seene. Murtii fi Heerroonni Finna Gadaa Ituu kan jalqabaa kana keessatti dabran Keessaa tokko murtii ajjaa'ibsiisaa fi seena qabeessa tan taatee fi siyaasa addunyaa hammayyaa amma jiru kana dura tarkaanfattuu tahuu Caffee tanaa mul'iissu dha. Kunnis ilmaan Warree irratti murtii laatamte. Murtiin laatamte tan akkami?. ilmaan Warree san booda yoo akkam tahan?. amma yoo eessa jiran?. Finni Gadaa Ituu kan Lammaffaa fi Saddaffaa yoo jaarraa kam gaggeefame?. Murtii akkam faatu isaan keessatti yoo laatame?. Kitaaba Kiyya kan gaafa Harki Naguute Maxxansuuf taa'uu keessaa kaniin isinitti raabseerraayi. Hanganaahuu qorqooda dhabuu fi icciitii qabachuu dadhabuu kiyyaafiin isinitti jabaa ja'e. Kitaabni kun yoomuma maxxanfama naan hin ja'iinaa. Akka tokkootu akka tokko tahee!!. Ituu Oromoo Post

Wednesday, March 9, 2022

የወሎ: የጎንደር ቅማንት (ካምኣት ) የጎጃም አገው ኦሮሞ ህዝብ ታሪክ

የወሎ: የጎንደር ቅማንት (ካምኣት ) የጎጃም አገው ኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ~~~~~~~~~~~~~√√√√~~~~~~~~~~~~~ ወሎ የከረዩ አንጋፋ ልጅ ነው : ከረዩ ደግሞ የበሬንቱ የበኩር ልጅ ነው። ወሎ፣ ከሚሴ ፣ ባቲ ፣ ቀርሳ፣ሰንበቴ፣ ደዌ፣ ጃርሳ፣ ኡርጌሳ፣ ወረ ቃሉ፣ ወራ ባቦ፣ ወራ ወረሴህ፣ ወረባያ፣ ወረምኛ፣ ቦረና፣ጭቀታ፣ግምባ፣ለገ አምቦ፣ ጭሮ፣ ቱሉ አውልያ፣ኮምቦልቻ፣ ገርባ፣ ወራ ዋዩ፣ ወራ ገርፋ፣ ወራ ኢሉ፣ ወራ ቆቦ፣ ወራ ራያ፣ ወራ የጁ፣ ወራ ቃሉ፣ጉጉፍቱ፣ሱሉለ፣ ጉባ ላፍቶ፣ጨርጨር፣ወልደያ፣ ሮቢቴ ። በወሎ ስር ሰባት ጎሳዎች አሉ። ወረ ኢሎ፣ ወረ ሂመኖ፣ ወረ ቃሉ፣ ወረ ኖሌ አሊ፣ ለገ ጎራ፣ ለገ ሂዳ እና ወረ ኩዩ ይባላሉ። ጎንደር የኦሮሞ ጎሣ የቦጂያ ብሔረሰብ ግዛት ነበር፡፡አበሲኒያ ቦጂያን ሥም ወደ “ቤጃ” ለዉጣ ጎንዳርን የቤጃ ምድር አለች፡፡ ቀጥላ ቤጃን ምድርን “በጌምድር” አለች፡፡በመጨረሻ በጌምድር ማለቱን ትታ ጎንደር አለች፡፡ጎንደር በቅማንትኛ ጓንግዳር ( በሁለት ወንዞች መካከል አንገረብና ቃሃ) የሚል ትርጉም ሲኖረው በአፋን ኦሮሞ “ከጉንዶ” የመጣ ሥም መሆኑን ታሪክ ይናገራል፡፡ጉንዶ የኦሮሞ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ሰፌድ ማለት ነዉ፡፡ በጎንደር በዘር ተለይቶ ለዘመናት ማንነቱን መሰረት ተደርጎ እየተጮቆነ የሚኖረዉ የኩሽ ዘር የሚባለዉ ቅማንት (ካምኣት )የኦሮሞ ጎሣ ነዉ፡፡አበሲኒያ ካምአትን ወደ “ቅማንት” ለዉጣ አሮሞ መሆኑ እንዳይታወቅ አደረገች፡፡ካም አት ማለት “አንተ የትኛዉ ነህ” ማለት ነዉ፡፡ጎንዳር የኦሮሞ ሀገር እንደ ነበር የሚያረጋግጡ እስከ ዛሬ ድረስ በኦሮሞ ቃል የሚጠሩ በርካታ ስፍራዎች ይገኛሉ፡፡ የቅማንት ህገልቦና እምነትና የሸንጎ ወንበር ስርዓት ከኦሮሞ ዋቄፈና እና የገዳ ስርዓት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ያላቸው ሃይማኖታዊ :ማህበራዊና ፓለቲካዊ አንድ እሴቶች ናቸው ። አገው ኦሮሞ እንጅ አገው አማራ የሚባል በታሪክ የለም አገው ኩሽ ብቻ ሳይሆን ከኦሮሞ ጎሳዎች አንዱ ነው። አገው የሚለው ቃሉ ሃ-ገኡ (Haa ga’u) ከሚል የafaan Oromoo ቃል የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም ይብቃ ማለት ነው። አገው ስሙን ያገኘውም የአገው-ኦሮሞ ማሕበረሰብ ከሌሎች የኦሮሞ ማሕበረሰብ ትንሽ ነጠል ብሎ በመኖሩ ምክንያት ከሌሎች ብሔሮች በተለይም ድንበር ከሚጋራቸው ሌሎች ብሔሮች ጋር ይደርስበት የነበረው የመዋጥ (assimilate) አደጋዎች እንዲበቃ ትግል ሲጀምር የመዋጥ አደጋ ይብቃ (Haa ga’u) ብሎ በመነሳቱ ተቀናቃኞቹ Haa ga’u ዎች ተነሱ ሲሉ በዚያው ከዘመናት ቆይታ የማሕበረሰቡ ስም አገው ሆኖ ቀረ። በጎጃምና ጎንደር በኦሮምኛ ቃል የሚጠሩ አያሌ ቀበሌዎችና ቦታዎች መካከል እኔ የማውቃቸውን ጥቂቶችን እንመልከት:- √ማጫ √ዲማ √ሰቃላ √ቆራቲ √ጃዊ √ቡሬ √ቄሮ √ጂጋ √ባሶ √ጋሌ √ሊባን √ሜታ √ዳሞቴ √ሙጣ/ሞጣ √ቡሬ ዝጉርጉር √ኢለማን ዲንሳ የሚባሉት ስያሜዎች ይገኛሉ። በጎንደር የቅማንት አካባቢዎች በአፋን ኦሮሞ ትርጉም ያላቸው የአካባቢ መጠሪያዎች - ማጫ -እንተላ -አይራ -ብልኮ -ጋላገር -አምቦ በር -ከበጁ -ፎገራ -ደምቢያ -ሮቢት -ወለቃ -ሳቤራ -ሌንጫ -ጉባይ -ደለጉ -መቃ -ኮኪት -ጋባ እናም በጣም በርካታ ስሞች አሉ በደንብ የማላስታውሳቸው ። ባላምባራስ ነጋሽ Negash Qemant

Saturday, February 26, 2022

#ራያ ገረብ ኦዳ/# Raya Oda

ገረብ(ሓንስ) ኦዳ የአባቶች ጥላ 🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳 #በራያ አላማጣና አካባቢዋ #ገረብ የሚባል የሽምግልና ስነ-ስርዓት እንዳለ እውቅ ሆኖ እነዚህ አባቶቻችን ለነፍሳቸው ሲሉ ወንድም ከወንድሙ ሲጋጭ አንተ ተው አንተ ተው እያሉ እያስታረቁ እና እያስማሙ ራዮችን አንድ እያደረጉ እያፋቀሩ ለዘመናት ኖረዋል፣ አሉ ይኖራሉም። እነዚህ አባቶች ፈጣሪ በሰጣቸው ለምለም ጥላ ሁነው ሽምግልናቸውን ሲያካሂዱ ቆይተዋል ነገር ግን በዚህ ሰዓት የሚጠለሉበት ቦታ ወድሞና ሌላኛው ደግሞ ወድቆ እየተቸገሩ እንዳሉ እያየን ነው። ለምሳሌ ይሀክል በራያ አላማጣና አካባቢዋ የዕርቅ ስነ-ስርዓት የሚጠቀሙበት ዋናዎቹ #ዓውዪ_ኦዳ እና #ሓንስ_ኦዳ እየተባሉ የሚጠሩ ሁለት አንጋፋ ጥላዎች ሲሆኑ፤ ዓውዪ ኦዳ እየተባለ የሚጠራው ስመ ገናናው የአባቶች ጥላ በቅርብ ዓመታት ወድቆ ከጥቅም ውጪ ሁኗል። ሌላኛው ደግሞ ሓንስ ኦዳ እየተባለ የሚጠራው ለህብረተሰቡ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እየሰጠ የነበረ ሲሆን ከነዚህም ሁሌ አዲስ ዓመት ላይ ማህበረሰባችን ከከተማውና ከገጠሩ አሰባስቦ በፍቅር የሚውልበትና እሸት ጥንቅሹ እየተበላ ባህላዊ የራያ ዘፈኖች እየተዘፈኑ ትግል እየተታገሉ እየተጫወቱ የምያሳልፉበት ቦታ ነው። ሌላኛው ዋነኛው ጥቅሙ ደግሞ ብዙዎች ሲጣሉና ሲጋጩ አባቶች የዕርቅ ስነ-ስርዓት የሚያካሂዱበት ትልቅ የተከበረ ጥላ ነው። ስለዚህ ወገኖች እኔ ይህ ፕሮጀክት ከጀመርኩት የቆየሁ ብሆንም ነገር ግን አሁን ተቀናጅተንና ተጋግዘን ለሰላማችንና አንድነታችን ለቆሙልን የአባቶች ጥላ ብናስከብርላቸው አይበዛባቸውምና ካሁን ብኋላ ላለው ብንተጋገዝ ምን ይመስላችኋል

#ኦዳ ገራዶ( ዋርካ) #Odaa Gerado

<< የ ኦዳ ገራዶን ታሪክ >> "ኦዳ ገራዶ" አባቶችን ስንጠይቅ የሰጡን ምላሽ >> በዛ የብሄር እና የሃይማኖት እኩልነት ባልነበረበት በአስከፊው የፊውዳል ስርአት ዘመን የወሎ ኦሮሞዎች ላይ ይደርስ የነበረው ስቃይና በደል እጅግ ከፍተኛ ነበር እናም ከዚህ አስከፊ ሁኔታ ራሳቸውን ፣ታሪካቸውን (ማንነታቸውን) ለመጠበቅ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት የ"ገዳ" አይነት ስርአት ነበራቸው ። እናም በዚህ በምታዩት ዋርካ ስር በመሰባሰብ በማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ ፣ ህግ አርቅቀውና አፅድቀው ለማህበረሰቡ አዋጅ ይናገሩበታል፣ ራሳቸውንም ከጠላት እንዴት መከላከል እንዳለባቸው ይመክሩበታል ፣ ያጠፍ ሰዎችን ዳኛ ሰይመው ይቀጡበታል ፣ የተጣሉትም ግለሰቦች በዛፍ ስር ተሰባስበው ያስታርቁበታል ። እንደው በጥቅሉ "ኦዳ ገራዶ" የወሎ ኦሮሞዎች የ "ፖርላማ" መእከል እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል ። ኦዳ ገራዶ የሚገኘውም በወሎ በኦሮሞ ዞን ዋና መዲና በሆነችው ከሚሴ ከ "ሒጅራ" መንደር ከፍ ብሎ ከ "ቀሎ" ቀበሌ ዝቅ ብሎ ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው በዋናው አስፖልት ዳር ነው ።

Friday, February 25, 2022

#Yejju/#የጁ

#የጁ የየጁ ኦሮሞ ህዝብ የባሬንቶ ቅርንጫፍ ንኡስ ጎሳ ነው ። እነሱ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩት በሰሜን ካሉት የኦሮሞ ህዝብ ማህበረሰቦች አንዱ ናቸው።የጁ በ ሰሜን ወሎ መረሳ፣ጉባ ላፍቶ፣ሐብሩና እስከ ሰዶማ ሀረና ሀሮ፣ ድሬ ሮቃ እስከ ጃራ በ ሰፊው የምኖሩ ሕዝቦች ናቸው። በ17ኛው ክፍለ ዘመን የየጁ ስርወ መንግስት በተለይም የዋራ ሼክ ወይም የሼኩ ልጆች በዘመነ መሳፍንት ወይም "ዘመነ መሳፍንት" ጊዜ አብዛኛውን የኢትዮጵያ ኢምፓየር ያስተዳድሩ ነበር፣ በጎንደር አደባባይ የነበረውን ቋንቋ ወደ ኦሮምኛ [2] በዘመኑ የተለያዩ ብሄረሰቦች፣ ጎሳዎች እና ማህበረሰቦች ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን እና የፖለቲካ ስልጣንን ለማግኘት የአጭር ጊዜ ጥምረት ፈጥረዋል።የየጁ ስርወ መንግስት ገዥዎች ወደ ክርስትና የተለወጡ ቢሆንም የስልጣን መሰረታቸው እንደ የጁ፣ ወራ ያሉ ኃያላን የወሎ ሙስሊም ርዕሰ መስተዳድሮች ነበሩ። ሂማኖ እና ራያ። እ.ኤ.አ. በ1890 ዓ.ም በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግስት የየጁ የትውልድ ሀገር ለነሱ ተብሎ በኢትዮጵያ ግዛት (አውራጃ) ተደራጅቷል። በሰሜን በኩል ከአለውሃ ወንዝ ጋር ትዋሰናለች፣ ከራያ ቆቦ አውራጃ፣ ወደ ደቡብ ከሚሌ ወንዝ በመለየት፣ ወራ ባቦ ወረዳን፣ የአፋር ጭንቀትን በምስራቅ፣ እና ደጋውን የአምባሰልን ወደ ምዕራብ ። ወልድያ የየጁ ዋና ከተማ ሆና አገልግላለች። በ1994 የብሄረሰብ ፌደራሊዝም ጸድቆ የአውራጃ አስተዳደር መዋቅር ሲወገድ የጁ በሐብሩ፣ ወልድያ ከተማ እና በጉባ ላፍቶ መካከለኛ ከፍታ ባለው ክፍል መካከል ተከፋፈለ። ከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ የየጁ ኦሮሞዎች ወደ ዋናው የሴም ሕዝብ ባህል በመዋሃዳቸው ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙት የጁ አማራዎች ናቸው ብለው ይጠሩታል ግን ኦ ርጅናሊ ሕዝቡ ኦሮሞ ነው።

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...