Translate

Wednesday, January 4, 2023

#Ethiopia kush:-እምዘነገደ ኩሽ- #Kush Tribe

........................እምዘነገደ ኩሽ..........................
 ኩሽ እንደ አንድ ህዝብ ፣ ኩሽ እንደ አንድ ቋንቋ ነገድ ፣ ኩሽ እንደ ሃገር  አንድም ሶስትም ነው ። የታሪክ ባለቤት ለሆነ ሕዝብ የታሪክ ባለሙያው ፍጹም  ባዕድ ሲሆን ታሪክ መወላገዱ አይቀርም ። ለዘመናት የኦሮሞ ታሪክ ነው እየተባለ፣ ሲንጋት የነበረው ነገር በፍጹም የኦሮሞን ሕዝብ አይወክልም። የኦሮሞ ሕዝብ የፈለቀው ከኩሽ ሕዝብ እንደመሆኑ መጠን ከ8000 አመታት በፊት ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ሰፍሮ የኖረ ስሆን በ3500 ዓ.ዓ. እና በ2000 ዓ.ዓ. መካከል ከምስራቅ ቅርንጫፍ ኩሽ ተለይቶ በቋንቋና በባህል እራሱን የቻለ ሕዝብ ሆኖ መውጣቱን የሥነ ልሳን ማስረጃዎች የሚያረጋግጡት ሃቅ ነው። ከዚህ አንፃር ኦሮሞ ከየት መጣ? መነሻው ምንጩ ከየት ነው? ብሎ መጠየቅ፣ ጥንታዊ ኩሽ ከየት መጣ? መነሻው ምንጩ ከየት ነው ብሎ እንደመጠየቅ ይቆጠራል። ኦሮሞ መነሻና ጥንተ መኖሪያ አገር የት ነው ብሎ መጠየቅ፣ ወፍ ይበራል ወይ፣ ዶሮ ላባ አላት ወይ ብሎ እንደ መጠየቅ ይቆጠራል። ምክንያቱም ኦሮሞ ከጥንታዊ ኩሽ የፈለቀ እንደመሆኑ የጥንታዊ ኩሽ መነሻና ጥንት መኖሪያ ተረጋገጠ ማለት፣ የኦሮሞ መነሻና ጥንት መኖሪያ ተረጋገጠ እንደማለት ስለሆነ።

ተረታችን ታሪካችንን ተጭኖት በዕውነት ሳይሆን በህልም መሰል መማለል ውስጥ የምንኖር ሕዝቦች ከሆን ቆይተናል ፣ ይሁን እንጂ አሁንም ወደ ንቃት ከማምራት ይልቅ የበለጠ እንዲጫጫነን በሚያደርጉ የተረት እሹሩሩዎች እየተባበልን እንገኛለን፡፡ ከታሪክ ሊቃውንት ይልቅ ..የተረት አባቶች.. የደብተራ ተረት.... ብሄርና ህዝብ የሚሰድቡ ድርሳናት የፀሎት መጽሃፎች በገነኑባት በዚች አገር መግባባታችን በአፈ ታሪክ ተወርሮ የኋላ ምስላችን እንደ ልጆች ትረካ ከሳይንሳዊው ዓለም የማይደባለቅ አስቂኝ ቀልድ ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ስም ላለፉት 150 አመታት በገዳማት፣ በአባተ ክርስቲያናት፣ በትምህርትቤት፣ በኮሌጅ በዩኒቪርስቲ በአውቅልሃለው በየተፃፈው ታሪክ በራሳቸው ፍላጎት የእናተ ታሪክ ይህ ነው ብለው ቆርጠው ቀጥለው መርጠው፣ አንተን መጤ ራሳቸውን ጥንታዊ ነዋሪ አድርገው፣ ማንነትህን አጠልሽተው ራሳቸውን ገዥ አንተን የበታችን ተገዥ ዜጋ አድርጎ ራሳቸው የጀግና ጀግና አድርገው አንተን ተራ አሽከር ደንገጡር ፈሪ ተሸማቃቂ አድርገው ጽፈው፤ ራሳቸውን የእግዚአብሔር የተመረጠ ምርጥ ዘር አድርገው አንተን እርጉም በእንጨት በዛፍ የምታመልክ የእንጨት ዘር አድርገው የፃፉትን ተረት እንዴት ታሪክህ ይህ ነው ተብሎ ትውልድ ይማርበታል። እውነተኛ የማንነት ታሪካችን ባህላችን እሴታችን በራሳችን ልጆች እውነተኛ ምርምር ጥናት ታሪክ ሆኖ ተጽፎ ለትውልድ ይተላለፋል እንጅ በተረት አባቶች እንደድሮው በአውቅልሃለው በደላላ ታሪካችን አይጻፍም። 

የኢትዮጵያ ታሪክ ተረት የሚመስል ታሪክ እንጂ ትክክለኛ የሆነ ታሪክ አይደለም። በኢትዮጵያ የታሪክ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ ታሪክ ፀሀፊዎች ከነገስታቱ እና ከወቅቱ ሹማምንት ጋር ጥብቅ ቁርኝነት የነበራቸው በመሆኑ ታሪክን የፃፉት ከተቆራኙበት አካል ፍላጎት አንፃር እንጂ ከታሪክ ጥናት አንፃር ነበር የሚል እምነት የለኝም። በዚህ የተነሳ እነዚ የሹማምንት አጎብዳጆች የፃፉትን ተረት እንጂ ታሪክ እንደሆነ ለመቀበል ያስቸግራል። ቀዳማዊ ምኒልክና ጓደኞቹ የእሥራኤል ወጣቶች ከኢየሩሳሌም ታቦት ሰርቀው አክሱም ከተማ ቤተ መቅደስ አኖሩት በሚባልበት ጊዜ አክሱም አልተቆረቆረችም፡አክሱም ከተማና የታሪክ ዘመን የሚጀምረው የቀዳማዊ ምኒልክ አባት ነው ከሚባለው ከንጉሥ ሰለሞን 800 ዓመታት ያህል ቆይቶ ነው፡፡ የአይሁዶችም ሃይማኖት በዚያን ጊዜ ተመሥርቶ፣ ንጉሡ፣ ተከታዮቹና ሕዝቡ ሁሉ ቋንቋ ወደ ግዕዝ ተተርጉሞ ነበር የሚባለውም እንዲያው የሃይማኖት ነው እንጂ የታሪክ መሠረት የለውም፡፡ ሕዝቡ ሳይቀር ከጥንት እስራኤል አገር የመጣ ነው እያሉ ይተርታሉ፡፡ የንግሥት ሳባና ቀዳማዊ ምኒልክ [ታሪክ] ይህንን ነው የሚያስተምረው፡፡ ካህናቱ እንደ እውነት አድርጎ ተቀብለውታል፡፡ በየመድረኩም ይሰብኩታል፡፡ 

በካህናት አንደበት የሚነገር ደግሞ እንደ ሃይማኖት አጥብቆ ስለሚያዝ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ትውፊትና አፈ ታሪክ ውስጥ በጣም ዘልቆ ገብቷል፡፡ ነገሥታቱ፣ መኳንንቱ፣ ካህናቱና ተራው ህዝብ እንኳ ሳይቀር፣ ዘር ሲቆጥር ወይም ከንግሥት ሳባና ከልጇ ከቀዳማዊ ምኒልክ ወይም ከምኒልክ ጋር የእስራኤል ታቦት ሰርቀው መጡ ከሚባሉት ከአሥራ ሁለቱ ነገደ እሥራኤል ካንደኛው ነው የሚጀምሩት፡፡ ሰለሞናዊ የሚባለው ሥርወ መንግሥት መነሻው ከዚሁ ተረት ነው፡፡ የፈላሻ ሕዝብም እንደዚሁ፡፡ እስከማውቀው ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ራሱን ችሎ ገለልተኛ በሆነ መንገድ ታሪክን የፃፈ ግለሰብ ወይም ተቋም ነበረ ማለት አይቻልም። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የታሪክ ጥናት በራሱ ያልተለመደ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ታሪክ ፀሀፊዎች ራሳቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የውጪ አገር የታሪክ ፀሀፊዎችን እንደ መረጃ በስፋት ሲጠቀሙ ታዝቢያለሁ። ስለዚህ ይህ የሚያሳየው አሁን የምናውቀው የኢትዮጵያ ታሪክ የታማኝነት ችግር ውስጥ ያለፈ በመሆኑ ትክክለኛ ታሪክ እንደሆነ ለመቀበል ያስቸግራል።

ኢትዮጵያ ለውሸትም፣ በውሸትም የሚኖሩ፣ ለውሸትም በውሸትም የሚሞቱ ቡዙ ውሸታሞች፣ ተወልደውባት እንጂ የኦሮሞ ሕዝብ ቀደምት የአገሪቱ ነዋሪ መሆኑን ታሪክ ይመሰክራል። ዳሩ ምን ያደርጋል ዛሬም ድረስ ይሄንን ሀቅ ላለመቀበል ሲሉ አባቶቻቸው የጀመሩትን የውሸት ትርክት በልጆቻቸው እና በልጅ ልጆቻቸው ከመቶ ዓመት በኋላም ሲደገም ስታይ ለካስ ውሸትም ይወረሳል እንዴ? ከማለት ውጭ ምን ይበላል ኦገኖቸ ?
ከኑማ  ✊
Negash Qemant

በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!!~ ደስታን በልግስና ውስጥ ያገኙት የአለማችን ቁጥር አንድ በጎ አድራጊ፣#ethiopia

በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!!

~ ደስታን በልግስና ውስጥ ያገኙት የአለማችን ቁጥር አንድ በጎ አድራጊ፣

#Ethiopia  | ሼይኽ ሱለይማን አልራጅሂ ይባላሉ:: ሳዑዲ አረቢያ ካፈራቻቸው ቢኒየነሮች መካከል አንዱ ናቸው:: ከንጉሳውያን ቤተሰብ ሳይሆኑ ቢሊየነር መሆን የቻሉ ሰው ናቸው:: በአለም ግዙፉን  አልራጅሂ ኢስላማዊ ባንክ መመስረት ችለዋል:: 

በህይወታቸው ያጋጠማቸውን አንድ አስተማሪ ክስትተት እንዲህ ሲሉ ያካፍሉናል -

"በልጅነቴ እጅግ በድህነት ውስጥ ነው ያደኩት:: ቤተሰቦቼ ድሆች ነበሩ:: በአንድ ወቅት ትምህርት ቤት ተማሪ እያለው ትምህርት ቤቱ የመዝናኛ ጉዞ ስላዘጋጀ በዚህ የሽርሽር ጉዞ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ 1ሪያል ማዋጣት እንደሚጠበቅበት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አስታወቀ:: እኔም በዚህ ጉዞ ላይ ለመሳተፍ እጅግ ስለጓጓው ለወላጆቼ አንድ ሪያል እንዲሰጡኝ እያለቀስኩኝ ጠየኳቸው:: ነገር ግን ወላጆቼ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ህይወት የሚኖሩ ሚስኪኖች ስለነበሩ ይህን አንድ ሪያል ስለሌላቸው ሊሰጡኝ አልቻሉም:: የጉዞ ቀናት መቃረቡን ተከትሎ አንድ ሪያሉን የሚሰጠኝ በማጣቴ እጅግ በጣም አለቀስኩኝ ፤አዘንኩኝ::

 ለጉዞ አንድ ቀን ሲቀረው በትምህርት ቤቱ የወሰድነው ፈተና ውጤት ደርሶ ስለነበር የፈተና ውጤታችንን ስንቀበል ከሌሎች ተማሪዎች የላቀ ውጤት በማምጣቴ ፍልስጤማዊ የሆነው መምህራችን ተደስቶብኝ በተማሪዎች ፊት አስጨብጭቦ ውጤቴን ሰጠኝ:: ለማበረታታም አንድ ሪያል በሽልማት መልኩ አበረከተልኝ:: 

ለጉዞ መዋጮ የሚያስፈልገኝን አንድ ሪያል በሽልማት መልኩ በማግኘቴ እጅግ በጣም ተደሰትኩኝ:: ያንን የተሸለምኩትን ኣንድ ሪያልም ለትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በፍጥነት ሄጄ በመስጠት ብዙ በጓጓሁለት ጉዞ ላይ መሳተፍ ቻልኩኝ::

ለቀናት ሳነባ የነበረው እንባ በደስታ ተቀየረልኝ:: የቀናት ለቅሶዬ በዛች አንድ ሪያል ሽልማት የተነሳ ለረጅም ጊዜያት ውስጤ በቀረ ደስታ ተለወጠልኝ::

ጊዜያት ነጎዱ:: እኔም ትምህርቴን አጠናቀኩኝ::  ጠንካራ እና ታታሪ ሆኜም በስራ ዘርፍ ላይ ተሰማራው:: የአላህ ፀጋ ብዙ ነውና ስራዬን በረካ አደረገልኝ:: ፀጋውንም በኔ ላይ አንቧቧልኝ:: ከትንሽ ስራ ተነስቼ በሳኡዲ አረቢያ የመጀመሪያው የሸሪዓ መር ባንክ በመመስረት በመላው ሳኡዲ አረቢያ ቅርንጫፎች በዙልኝ::

በአንድ ወቅት በልጅነቴ ተማሪ እያለው አንድ ሪያል የሰጠኝ መምህሬን በማስታወስ በወቅቱ የሰጠኝ አንድ ሪያል ሽልማት ነው ወይስ እርዳታ ? በሚል ከእራሴ ጋር ሙግት ውስጥ ገባው:: እራሴን ደጋግሜ ጠየኩኝ:: ግን ፈፅሞ መልስ ላገኝለት አልቻልኩም:: 

መምህሩ ያንን አንድ ሪያል የሰጠኝ ምንም አስቦ ቢሆን  ለእኔ ግን በወቅቱ የነበረብኝን ትልቅ ችግሬን ቀርፎ አስደስቶኛል ፤ ያንን የደስታ  ስሜት ደግሞ ከእኔ ውጪ ማንም ሊረዳው አይችልም ስል ለራሴ ነገርኩት::

ውስጤ ለሚመላለሰው ትዝታ እና ጥያቄ  ምላሽ ሊሆነኝ የሚችለው ይህን መምህር ካለበት አፈላልጌ አግኝቼው ስጠይቀው ነው በሚል ወደ ቀድሞ ትምህርት ቤቴ በመሄድ ፍልስጤማዊ መምህሬን ማፈላለግ ጀመርኩኝ::
በአላህ እገዛ መምህሬ ያለበትን ቦታ አፈላልጌ ማግኘት ቻልኩኝ:: እሱን ለማግኘትም ቀድሜ ተዘጋጀሁና ወዳለበት ስፍራ አቀናው::

 ፍልስጤማዊው መምህሬ በጡረታ ላይ ሆኖ፣ እጅግ በድህነት እና በችግር ላይ ሆኖ አገኘውት:: 

 የእርሱ ተማሪ እንደነበርኩኝ በማብራራት እንዲያስታውሰኝ አደረኩት ::
 
 የተከበርከው ውዱ መምህሬ ሆይ ፣እኔ እኮ ለረጅም አመታት የቆየ ያንተ ባለእዳ ነኝ አልኩት::

 አንድ ደሃ ሰው ምን የሚያበድረው ነገር ኖሮት ነው የማበድርህ ሲል ተገርሞ ጠየቀኝ::

እኔም  ተማሪ እያለው በውጤቴ ምክንያት የሰጠኝን አንድ ሪያል አስታወስኩት::

መምህሬም :- ክስተቱን በማስታወስ እየሳቀ ባለእዳ ነኝ ያልከኝ ታዲያ አሁን ያቺን አንድ ሪያል ልትከፍለኝ ነው ? በማለት ተገርሞ እየሳቀ ጠየቀኝ::

እኔም አዎ ውዱ መምህሬ በማለት መለስኩለት::

ወደ መኪናዬ እንዲገባ በማድረግ እጅግ ዘመናዊ መኪና በግቢው ውስጥ የቆመበት ግዙፍ ዘመናዊ ቪላ ቤት ውስጥ ይዜው ገባው:: 

 መምህሬ ሆይ  ተማሪ እያለው ለሰጠኸኝ አንድ ሪያል ምላሽ ባይመጥንም፤ ይሄ ግዙፍ ቪላ እና መኪና ላንተ ይሆን ዘንድ ያዘጋጀሁት ነው፤ በህይወት ዘመንህም የሚበቃህን ያህል ገንዘብ እኔ ዘንድ ተዘጋጅቶልሀል ብዬ ነገርኩት::

 መምህሬ እጅግ በመደንገጥ ይሄ ፈፅሞ ለእኔ አይገባም፣ ይህ በጣም ከልክ ያለፈ ብዙ ነው በማለት አይኑ በእንባ ተሞልቶ መቀበል እንደሚከብደው ነገረኝ::: 

መምህሬ ሆይ በወቅቱ አንድ ሪያል ስትሰጠኝ የነበረኝ ደስታ ዛሬ አንተ ይህን ቪላ እና መኪና ስታገኝ ከተሰማህ ደስታ በላይ ነው:: የዛኔ የነበረኝ የልጅነት ደስታ እና ሀሴት ዛሬም ድረስ አይረሳኝም በማለት ለመምህሬ ስጦታዬን አበረከትኩለት::ይላሉ 

በመጨረሻም ሼይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ ምክር ሲመክሩ

"ምን ጊዜም ለሌሎች ደስታን ፍጠር፣ የሌሎችን ጭንቀት አሶግድ ፣ ምንዳህን እጅግ ከሰጪው ፣ከለጋሹ እና ከደጉ ጌታ ጠብቅ ይላሉ'

ለመረጃ ያህል

ሼይኽ ሱለይማን አልራጅሂ ያላቸውን ሀብት ግማሹን ለልጆቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ግማሹን ደግሞ ለበጎ አድራጎት አበርክተዋል::

በአለማችን ታሪክ ግዙፉ የተባለለትን እና በአለም ድንቃ ድንቅ መዘገብ ላይ ሊሰፍር የቻለ ለበጎ አድራጎት አገልግሎት የሚውል በሳኡዲ አረቢያ በቀሲም ግዛት የሚገኘውን 5466 ሄክታር ስፋት ያለው የእርሻ ማሳቸውን፤ ይህም የእርሻ ማሳ በአመት 10ሺህ ቶን የቴምር ፍሬ የሚሰጥ እና በውስጡም 45  አይነት የተለያዩ  የተምር ፍሬዎችን የያዘ፣ 200,000 የሚሆን የተምር ዛፍ ለበጎ አድራጎት ይውል ዘንድ  ወቅፍ ማድረግ የቻሉ ሰው ናቸው:: 

ሸይኽ ሱለይማን አራጅሂ ለዳእዋና ለበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ቋሚ ድጋፍ እንዲሆን ወቅፍ  ያደረጉት ካፒታል አሁን ላይ 60 ቢሊዮን ሪያል ደርሷል። ይህ በአለማችን እስካሁን ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ወቅፍ ነው::

ሼይኹ ወቅፍ ካደረጉት የተምር እርሻ የሚገኘው የቴምር ምርት ተሽጦም ገቢው  ለበጎ አድራጎት ማህበራት የሚከፋፈል ሲሆን ቀሪው ተምርም ለሁለቱ ቅዱሳን መስጂዶች   መካ እና መዲና ለሚገኙት   ሀረሞች የረመዳን ኢፍጣር ፕሮግራም አገልግሎት ይውል ዘንድ ለምዕመናን በነፃ ይከፋፈላል:: 

በሳዑዲ አረቢያ ባሉ ከተሞች ላይ በሼይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ እና ቤተሰባቸው አማካኝነት መስጂድ እና መድረሳ ያልተገነባበት ከተማ ማግኘት ያዳግታል:: በሁሉም ቦታዎች ላይ መስጂዶችን አስገንብተዋል:: 

በስራቸው ላለው ሰራተኞቻቸውም ደሞዛቸውን ወሩ ከመጠናቀቁ በፊት በመክፈል ይታወቃሉ::  

ሽይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ በአንድ ወቅት ቃለመጠይቅ ሲደረግላቸው 

 ግማሹን ሀብታችሁን ለቤተሰባችሁ፤ ግማሹን ደግሞ ለወቅፍ ለግሰውታል:: ለራስዎት የግል ወጪ የሚሆንስ ምን አስቀምጠዋል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ

ውብ በሆነ ፈገግታ ተሞልተው "ባጭሩ ምላሼ ምንም ነው!" የምለብሳቸው ልብሶች ብቻ እኔ ጋር አሉኝ::  እድሜዬ በሰማኒያዎቹ ውስጥ ነኝ! ከዚህ ቡኃላ ምን ልፈልግ እችላለሁ? የወቅፍ ፕሮጀክቴ  ወጪዬን ይሸፍናል፣ መጠለያ፣ ምግብ፣ ህክምና እና መጓጓዣ አገኛለው::በትንሹ ለመኖር በደንብ የተብቃቃው ነኝ:: ሲሉ መልሰዋል::

 ”  ቢሊየነር ሆነው ግን ምንም ገንዘብ የሌለው ሰው በመሆኖት! "ምን ይሰማዎታል?" ሲባሉም

 "ፈገግ እያሉ  በናፍቆት እይታ ውስጥ ሆነው ውስጤን ብርሃን ይሰማኛል! ነፃነት ይሰማኛል! የበራሪ ወፍ ያህል ነፃነት ይሰማኛል…በህይወት ዘመኔ ሁለት ጊዜ ምንም ገንዘብ የሌለው ሰው ሆኜ አውቃለው:: በፊት ላይ የድህነትን ስሜት እና ሁኔታ በደንብ በህይወቴ አውቀዋለው:: ያሁኑ ግን በፍላጎቴ እና በምርጫዬ ነው:: ምንም ለራሴ ባይኖረኝም እጅግ መረጋጋት፣ የዐዕምሮ ሰላም እና ደስታ ይሰማኛል::ሀብት ሁሉ የአላህ ነው:: የእሱን ሀብት እንድንጠብቅ ነው የተሰጠን:: አሁን ላይ ጌታዬ አላህ ሲጠራኝ ያለ ምንም እክል ጥሪውን መመለስ እችላለሁ! ይህ ታዲያ እንዴት ያለ እፎይታ እና እረፍት የሚሰጥ ነው!!በማለት አስደናቂ ምላሻቸውን ሰጥተዋል::

በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!!

አላህ ከችሮታው አሁንም ይጨምርላቸው

ለኛም የመለገስን ልብ ይወፍቀን

(ኡስታዝ አቡበከር አህመድ)

ጥቅምት 10, 1909 እለተ ጁምዓ ሐረር

ጥቅምት 10, 1909 እለተ ጁምዓ 
                    ሐረር
  

የባለግዜው መንግስት ቀሚስ ስር ፍርፋሪ እየለቀሙ ያሉ አስመሳዩች ሐረርን የሚመለከት ፅሁፎችን በለቅሶ መልክ እና ፌደራሊዝምን አስታከው ሲቀበጣጥሩ እያየን ነው ። የዚህ ሁሉ መንስኤ የአባታቸው ተፈሪ መኮንን እና የአያታቸው ራስ መኮንን ሐውልቶች መፈራረስ አንጀታቸውን ስለበላቸው ነው ። 

▫️

የፖለቲካው መስመር አጉልቶ ስላላሳየው እንጂ ተፈሪ መኮንን የሐረር ህዝብ ላይ የሰራው አባቱ ጨለንቆና ሐረር ላይ ከሰራው ቢብስ እንጂ የሚያንስ አልነበረም ። 

▫️

ጉዳዩ እንዲህ ነው … 

▫️

የሸዋ ክርስትያኖች በእንግሊዞች አጋዥነት በተቀናበረ የፎቶ ፖለቲካ ምክንያት ልጅ እያሱን ከሐዲ አድርገው ከዙፋኑ ባወረዱበት ወቅት ሐረር ላይ ሙስሊሙ ልጅ እያሱ ጎን ሲቆም እስከ አፍጢሙ ታጥቆ የሰፈረው የሸዋ ክርስትያን (ሁሉም ወታደር እና የወታደር ቤተሰብ ነበር) ከተፈሪ መኮንን ጋር በማበር አንድ ግፍ ፈፅሟል ።

▫️

በግዕዝ አቆጣጠር  ጥቅምት 10, 1909 እለተ ጁምዓ ላይ ሙስሊም ኦሮሞ ፣ ሶማሌ ፣ ሐረሪ ፣ አርጎባ እና የመኖች ላይ ቤት ለቤት ሳይቀር በተካሄደ ፍጅት የጁምዓ ሰላት ከመድረሱ በፊት ከቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ ብቻ ከ500 በላይ ሙስሊሞች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ። ይህ ሲደረግ ሁሉም የጀጎል መግቢያና መውጫ በሮች ተዘግተው ነው ። ፍጅቱን  እንዲቆም ያደረገው የእንግሊዝ ቆንስላ ባስተላለፈው ትዕዛዝ ነው ( ከሴራው ጀርባ ዋነኛ አጋዦችም ስለነበሩ) ። ይህ ትዕዛዝ ባይመጠላቸው ኖሮ ግባቸው ምን ይሆን ነበር የሚለውን ወደፊት የምናየው ይሆናል ። 

▫️

የራስ መኮንን እና የልጁ ተፈሪ መኮንን አይደለም ሐውልታቸው ስማቸው በዚህች ከተማ የመነሳት እድል ሊያገኝ አይገባውም ።

▫️

👉 ማስታወሻ

▫️

ይሄ መረጃ በወቅቱ የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ በሚገመግምበት ወቅት ሐረር ከሚገኝ የወቅቱ ትልቁ የንግድ ተቋም በነበረው G.M. Mohammedally & Co. የተባለ ድርጅት በኩል በቴሌግራም ከደረሰው ሪፖርት ላይ ይገኛል ።

#ልጅ እያሱ እና ደጃች ተፈሪ መኮንን-

ልጅ እያሱ እና ደጃች ተፈሪ መኮንን
------
(አፈንዲ ሙተቂ)
---------
ልጅ ኢያሱ ሚካኤል ከበርካታ ሙስሊም ባላባቶች ጋር የተነሳቸው ፎቶግራፎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ሀረር ውስጥ ገራድ አብዱላሂ አሊ ሳዲቅ ከሚባል የሀረር ገዥ ቤተሰብ ጋር የተነሳው ፎቶግራፍ በብዙ ስፍራዎች ተለጥፎ አይቼዋለሁ፡፡ አንዳንድ ምንጮች ያ ፎቶግራፍ ልጅ እያሱን ለመወንጀል “montage” በሚባለው የፈጠራ ጥበብ የተሰራ ነው የሚል ታሪክ ያስነብባሉ። ለምሳሌ “የሃያኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ” የተሰኘው መጽሐፍ ደራሲ “ፎቶውን የሰራው ዝነኛው እንግሊዛዊ ወታደር ቶማስ ለውሬንስ (በዓለም ታሪክ መጻሕፍት Lawerence of Arabia በሚል ቅጽል ስም የሚታወቅ) ነው” በማለት ጽፈዋል።

ሆኖም የልጅ እያሱ የልጅ ልጅ የሆኑት ፕሮፌሰር ግርማ ዮሐንስ እያሱ እንደዚህ ዓይነት ፎቶዎች እርግጠኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ከአስር ዓመታት በፊት “ጎህ” ለተሰኘ መጽሔት በሰጡት ቃለ-ምልልስ ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ግርማ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ እንዲህ ነበር ያሉት።

“ከሼኮችና ከሌሎችም ጋር የተነሱአቸው ፎቶግራፎች ብዙዎች አሉ። ስለዚህ ከቄስ ጋር መነሳትም የተለመደ ነበርና ልጅ እያሱ ሁለቱንም እኩል አድርጎ ለማየት የነበራቸው ፖሊሲ አካል ነው”። (ጎህ መጽሔት፣ ቅጽ 1፣ ቁጥር 5፣ ጥቅምት 1993፣ ገጽ 13)

በቅርብ ጊዜ ስለልጅ እያሱና የአፋሮች ግንኙነት የጻፉት አራሚስ ሁመድ ሱሌ (Aramis Houmed Soulé) የተባሉ ምሁር ልጅ እያሱ ከአፋር ባላባቶችም ጋር እኝህን መሰል ፎቶግራፎች መነሳቱን አረጋግጠዋል። ስለዚህ ፎቶው “ፎርጅድ” አልነበረም ማለት ነው። ሁለቱ ምሁራን (ፕሮፌሰር ግርማ እና አራሚስ ሁመድ ሱሌ) በትክክል እንደገለጹት ልጅ እያሱ ፎቶግራፉን የተነሳበት ዓላማ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር እኩል መሆናቸውን ለማሳየት በሚል ነው። ታዲያ ልጅ እያሱ በመናፍቅነት በተከሰሰበት ወቅት እንዲህ ዓይነት ፎቶዎች እየተለቀሙ እንደማስረጃ ቀርበውበት ነበር።

ይህ የልጅ እያሱ መስለም በዘመኑ ብዙ የተባለለት ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ከአፍ ታሪክ የበለጠ ማስረጃ ሊቀርብለት አልቻለም። የእርሱ የስልጣን ባለጋራ የሆኑት ራስ ተፈሪ መኮንን (አጼ ኃይለ ሥላሴ) በጻፉት “ህይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ” የተሰኘው ግለ-ታሪካቸው ውስጥ የእያሱ ወንጀሎች በማለት ከዘረዘሯቸው አስራ አንድ ነጥቦች መካከል አስሩ አቀራረባቸው ቢለያይም ይዘታቸው አንድ ነው። ይኸውም የልጅ እያሱ መስለም ነው። እነዚህ ነጥቦች የልጅ እያሱን አራት ሴቶች ማግባት፣ መስጊድ ገብቶ መስገድና ቁርአን ማንበብ፣ መስጊድ ማሰራት፣ በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ “ላኢላሃ ኢለላህ” የሚል ጽሁፍ ማስጠለፍ ወዘተ… የመሳሰሉት ናቸው።

ይሁንና የልጅ እያሱ የልጅ ልጅ የሆኑት ፕሮፌሰር ግርማ ዮሐንስ “እነዚህ ሁሉ የፈጠራ ክሶች ናቸው” ነው የሚሉት። በተለይ ከተፈሪ መኮንን ጋር ከተዋጉ በኋላ ተሸንፈው በሸሹበት የአፋር በረሃ ያስጠለሏቸው የዘመኑ የአፋር ሱልጣን አቡበከር የወንድም ልጅ የሆኑት ሀንፍሬ አሊሚራህ ስለልጅ እያሱ ፍጹም ክርስቲያን መሆን ምስክርነታቸውን እንደሰጡአቸው ይገልጻሉ። አራሚስ ሁመድ ሱሌ የተባሉት ምሁርም የፕሮፌሰር ግርማን አባባል የሚያጠናክር ምስክርነት ሰጥተዋል። እኝህ ምሁር እንደጻፉት ክርስቲያኑ ልጅ እያሱ በአፋር ምድር ሳለ በክርስትና እምነቱ ከመጽናቱም በላይ አገልጋዮቹ የሰሩለትን የማሽላ ጠላ ይጠጣ ነበር። ስለዚህ ልጅ እያሱ ሙስሊሙን ከክርስቲያኑ ጋር እኩል ለማድረግ ጥረት ከማድረጉ ውጪ ለራሱ ክርስቲያን ሆኖ ነው የኖረው ማለት ነው።

ሆነም ቀረ ግን የእያሱ መስለም እርሱን ከስልጣን ለማውረድ የተደረገው ትግል ማጠንጠኛ ሆኖ ነው ያረፈው። ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ክሱ በዚህ ስልት የተቀናበረው እያሱን በህዝቡና በጦር ሀይሉ ዘንድ ለማስጠላት አመቺ መሳሪያ ሆኖ በመገኘቱ ነው ይላሉ። እንደ ፕሮፌሰሩ ገለጻ ልጅ እያሱ ቀጨኔ መድኃኒዓለምን የመሳሰሉ ደብሮችን እንዳልተከለ ሁሉ ከፍ ብሎ የሚወራው መስጊዶችን ማሰራቱ ነው። ለክሱ ማስረጃ አምጡ በሚባልበት ጊዜ “ድሮውንስ ከሙሐመድ ዓሊ ልጅ ምን ይጠበቅ ኖሯል?!” የሚል ቃለ አጋኖ ይደሰኮር ነበር። “ይሁንና” ይላሉ ፕሮፌሰር ባህሩ “ለሸዋ መኳንንት የእያሱ አደገኛነት የፖለቲካ የበላይነታቸውን ከመፈታተኑ ላይ ነበር። ስለዚህ የመናፍቅነቱ ክስ የመነጨው ለሃይማኖት ከመጨነቅ ሳይሆን ለተፈጠረው የፖለቲካ ስጋት ርዕዮተ ዓለማዊ ሽፋን ሆኖ ለማገልገል ካለው አመቺነት ነው።” (ባህሩ ዘውዴ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847-1983፡ ገጽ 134-135)

በልጅ እያሱ ላይ የሚደረገው ዱለታ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው ልጅ እያሱ አባቱን “ንጉሥ ሚካኤል” በማለት በወሎና በትግሬ ላይ ባነገሠበት ጊዜ ነው። የሸዋ መኳንንት ራስ ሚካኤል ሰሜን ኢትዮጵያን በቀጥታ ሌላኛውን የኢትዮጵያ ክልል በልጁ በኩል መቆጣጠሩን አሰመሩበት። በመሆኑም የሸዋ መኳንንት “ይህ ወጣት ከቤተ መንግሥቱ ጠራርጎ ሳያስወጣን እንቅደመው” በማለት መሯሯጥ ጀመሩ። የዚህ አድማ ዋነኛ መሪና አቀናባሪ የጦር ሚኒስትሩ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ስለመሆኑ ምሁራን የሚስማሙበት ሐቅ ነው። 
***** ***** *****
ከዚህ በፊት እንዳጫወትኳችሁ ልጅ እያሱ የዕድሜ ልክ ባላንጣው ሊሆን የበቃውን ደጃች ተፈሪ መኮንንን በጋብቻ ጠልፎ ዝም ሊያሰኘው ሞክሮ ነበር። ይሁንና ተፈሪ የእያሱ እህት ልጅ የሆነችውን ወ/ሮ መነን አስፋውን ቢያገባም ሁለቱ ወጣቶች ፍጹም ሊጣጣሙ አልቻሉም። ተፈሪ የዘመኑ ሀብታም ክፍለ ሀገር የነበረው ሀረርጌ የዕድሜ ልክ ግዛቴ ነው ብሎ ያስብ ነበር። እያሱ ደግሞ ተፈሪ በሀረር ሀብት መበልጸጉን አልወደደውም። በተለይም ደጃች ተፈሪ ከባቡር መስመር መዘርጋት ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ የሀገሪቱ መንግሥት ግምጃ ቤት አለኝታ ሊሆን የበቃውን የድሬዳዋ ጉምሩክ ገቢ በቀጥታ ሊቆጣጠረው መቻሉ ለልጅ እያሱ አልተዋጠለትም።

ነገር ግን ከዚህ ክስተት በላይ እያሱን በተፈሪ ላይ ያነሳሳው የልጅ እያሱን ስም የሚያጠፋ ሚስጢራዊ ደብዳቤ ለእንግሊዝ መንግሥት ተጽፎ መገኘቱ ነው። ይህንን ደብዳቤ የጻፉት የደጃች ተፈሪ መኮንን ጸሓፊና አንድ ማንነቱ በውል ያልተገለጸ ሌላ ሰው ናቸው። ደብዳቤው በማን ትዕዛዝ እንደተጻፈ ግን የታሪክ ሰነዶች በይፋ የሚገልጹት ነገር የለም። ልጅ እያሱ “ትዕዛዙን ያስተላለፈው ተፈሪ መኮንን ነው” ባይ ነው። በዚህም ወደ አዲስ አበባ አስጠርቶት ስለጉዳዩ ቢጠይቀው ደጃች ተፈሪ ከነገሩ ንጹህ መሆኑን በመሀላ ገለጸለት። ቢሆንም እያሱ አላመነውም። በመሆኑም በሁለቱ መካከል የነበረው ቅራኔ በጣም ተባባሰ።

ነገሮች በዚህ ላይ እንዳሉ ልጅ እያሱ ተፈሪ መኮንንን ወደ አዲስ አበባ አስጠርቶት እርሱን ሳያነጋግር ወደ ሀረር ወረደ። ከሀገሬው ህዝብ ጋር ከተማከረ በኋላም ደጃች ተፈሪ መኮንንን ከሀረር ገዥነቱ ሻረው። በምትኩም የከፋ ገዥ አድርጎ ሾመውና በአስቸኳይ ወደ ተሾመበት ክልል እንዲሄድ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጠው። የድሬ ዳዋ ጉምሩክንም ወዳጁ በነበረው ሶሪያዊው ሀሲብ ይዲልቢ ስር እንዲሆን አደረገው።

የልጅ እያሱ እርምጃ ተፈሪን በጣም አስደነገጠው። “ይህ መስፍን ሊውጠኝ እያመቻቸኝ ነው” በማለት እንዲያስብም አደረገው። ስለዚህ ደጃች ተፈሪ ወደ ከፋ መሄዱን ተወና አዲስ አበባ ሆኖ የሚበጀውን መንገድ ማፈላለግ ጀመረ። ልጅ እያሱ በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ ቢያዥጎደጉድለትም ደጃች ተፈሪ ልዩ ልዩ ሰበቦችን እያመካኘ በዋና ከተማይቱ ሰነበተ። የእያሱንም ልብ ለማቀዝቀዝ የስጋ ዘመዱ የሆነውን ቀኛዝማች እምሩ ኃይለ ሥላሴን (የኋለኛው ራስ እምሩ) የቃልና የጽሑፍ መልዕክት አስጨብጦ ልጅ እያሱ ወደሚገኝበት ድሬዳዋ ላከው። እያሱም የተፈሪን መልዕክት ከሰማ በኋላ እንዲህ አለ።

“ደጃች ተፈሪ አሳቡ ሁሉ ሌላ ነው። ያንዳንድ ወስላቶች ነገር እየሰማ ወዲያ ወዲህ ቢል ብርቱ ነገር ያገኘዋል። የአዲስ አበባ ወስላታ ሁሉ ፍሬ ያለው መስሎታል።” (ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ “ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ”፣ በኢትኦጵ መጽሔት የቀረበ ጽሁፍ፣ ጥቅምት 1993፣ ገጽ 37)

ይህ የልጅ እያሱ አነጋገር በሁለቱ ልዑላን መካከል የነበረው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ያመላክታል። የእያሱ ንግግር ለደጃች ተፈሪ ጆሮ ከደረሰው በኋላ ተፈሪ በስውር ማድባቱን ትቶ እያሱን ከስልጣን ለመፈንገል የሚዶልቱትን መኳንንት በይፋ ተቀላቀለ። በአስገራሚ ፍጥነትም የዱለታውን መሪነት ከፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ እጅ ወሰደው።
***** ***** *****
የሁለቱ ወጣቶች መገፋፋት ይፋ ሆኗል። ቀጣዩ ነገር “ማን ቀድሞ አጥቅቶ የአሸናፊነቱን ዘውድ ይቀዳጃል” የሚለው ብቻ ነበር። የሸዋና የምዕራብ ኢትዮጵያ ባላባቶች በተፈሪ ዙሪያ ተሰልፈዋል። የወሎ፣ የአፋር፣ የኦጋዴንና የሀረርጌ ባላባቶች የእያሱን ጎራ ተቀላቅለዋል። ቢሆንም ሁለቱ ጎራዎች በራሳቸው ወኔ ፍልሚያውን መጀመር አልቻሉም። የመጨረሻውን ፍልሚያ ለማስጀመር ሌላ ስውር እጅ አስፈልጓል። የዘመኑ ታላላቅ ቅኝ ገዥዎች እጅ!

እንግሊዝ፣ ኢጣሊያና ፈረንሳይ ሁለቱ ልዑላን ሲጣሉ መጀመሪያ ላይ አይተው እንዳላዩ ሆነው ስራቸውን ማከናወኑን ነበር የመረጡት። ከቆይታ በኋላ ግን የልጅ እያሱ የእኩልነት ፖሊሲ (በሁሉም ኢትዮጵያዊያን መካከል እኩልነትን ለማስፈን በሚል የሚወስዳቸው እርምጃዎች) የነርሱን ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን ተገነዘቡ። የጠረፍ አካባቢ ገዥዎች ከቅኝ ገዥዎች ጋር ለሚያደርጉት ውጊያ የሞራል ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑ አስቀየማቸው። በተለይ እንግሊዝ ሶማሌላንድን ከብሪታኒያ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ለ30 ዓመታት ሲዋጋ ለኖረው ሰይድ አብዱሌ ሐሰን የተሰኘ የኦጋዴን ሶማሊዎች ብሔራዊ ጀግና የመሳሪያ ድጋፍ በገፍ ማቅረቡ ቅኝ ገዥዎቹን በጣም አስበረገጋቸው። “ይህ ወጣት ዝም ተብሎ ከተተወ ከዚህ አካባቢ ሊያስነቅለን ነው” እንዲሉም አደረጋቸው። አልፎ ተርፎም ልጅ እያሱ በዘመኑ ከነዚህ ቅኝ ገዥዎች ጋር በአንደኛው የዓለም ጦርነት የሚዋጉትን ጀርመንና ቱርክን የመደገፍ አዝማሚያ ማሳየቱ ሶስቱ ሀያላን እርሱን ከስልጣን ለመንቀል በሚደረገው ትግል በቀጥታ እንዲሳተፉ አነቃነቃቸው።

በመሆኑም ሀያላኑ ጳጉሜ 1908 የእያሱን የጠላትነት እርምጃ በማስመልከት በጻፉት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አድማውን መቀላቀላቸው ይፋ ሆነ። ከመጋረጃ ጀርባ ኩዴታ ጠንስሰው ወደ ተግባር መለወጥ ላቃታቸው የሸዋ መኳንንት ኩዴታው ወደ ተግባር የሚለወጥበትንም ስልት አስጨበጧቸው። በተለይ በእያሱ ላይ የቀረበው የመናፍቅነት ክስ ትክክል መሆኑን ለማስረገጥ የእያሱን መስለም የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን እያባዙ በአዲስ አበባና በሌሎችም ከተሞች አሰራጩ። 
***** ***** *****
ይህ ውጥረት በተፈጠረበት ወቅት ልጅ እያሱ ኦጋዴን ነበር። ከበረሃ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በቤቱ ላይ የተለኮሰውን እሳት እንዲያጠፋ ወዳጆቹ መልዕክት ቢሰዱለት “የሸዋን መኳንንት በአፉ ላይ ብሸናበት የሚናገረኝ የለም” የሚል የንቀት መልስ መለሰላቸው። በዚህም የስልጣን ፍጻሜውን አቃረበው። ታዲያ እያሱ የጠላቶቹን አሰላለፍ በደንብ የተገነዘበው አይመስልም። በርሱ ሐሳብ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ለማመጣጠን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች የሚቃወሙት የሸዋ መኳንንት ብቻ ነበሩ።

ነገሩ ግን እንዲያ አልነበረም። ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ እንደሚሉት ልጅ እያሱ ፖሊሲውን በግልጽ ባለማብራራቱ ተራው ህዝብ እንኳ ሀገሩን ለማስለም ሌት ተቀን የሚደክም አድርጎ ነው የወሰደው። በዚህ ላይ እነ ደጃች ተፈሪ በቆንስሎቹ ድጋፍ እያሱ የሚገለበጥበትን የሀሰት ክስ ቀምመው ሲያቀርቡለት ህዝቡም እንደ መኳንንቱ “ድሮስ ከሙሐመድ ዓሊ ልጅ” አለና አረፈው። በመሆኑም ሰፊው ህዝበ ክርስቲያን ለዱለታው ድጋፉን ሰጥቷል። የእያሱ እጣ አሳዛኝ የሚሆነው ድሮ የሚገብሩለት ሁሉ በዚህ ቀውጢ ጊዜ ሲከዱት ነው። በተለይ በስልጣን ዘመኑ መጀመሪያ ላይ በወሰዳቸው ተራማጅ እርምጃዎች ተደስተው በርሱ ዙሪያ የተሰለፉት ለውጥ ናፋቂ ምሁራን በዚህ የፈተና ወቅት የገቡበት ሳይታወቅ ከጎኑ ጠፍተዋል። አንዳንዶቹ ጭራሽ ከርሱ ጎራ ተነጥለው እርሱን ወደ መንቀፍ ገብተዋል። ለዚህም ምሳሌ የሚሆነው የነጋድራስ አፈወርቅ ገብረኢየሱስ ነገር ነው። ነጋድራስ አፈወርቅ ልጅ እያሱን በስልጣን ዘመኑ መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ተስፋና የለውጥ ሀዋሪያ አድርገው እንዳላንቆለጳጰሱት ሁሉ በዚህ የመከራ ወቅት እንዲህ የሚል ስንኝ መቋጠራቸውን ታሪክ አዋቂዎች በትውስታቸው መዝግበዋል።

ሙሐመድ እያሱ
ለገመ በራሱ
እያሱ ሙሐመድ
አልጋ ሲሉት አመድ።
(ብርሃኑ ድንቄ፣ ቄሳርና አብዮት፣ 1986፣ ገጽ 30)

እንግዲህ የልጅ እያሱ ውድቀት እውን ሆነ። ለሶስት ዓመታት የነገሠበትን አልጋ ከውጪና ከውስጥ በተሸረበበት ሴራ አጣ። መስከረም 17/1909 ዓ.ል. ዘውዲቱ ምኒልክ ንግሥተ ነገሥታት ተብላ ዙፋኑ ላይ ስትቀመጥ ደጃች ተፈሪ መኮንን “ራስ” ተብሎ የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽና ባለሙሉ ስልጣን እንደራሴ ሆነ። ይህ ሁሉ ሲከናወን ኢላማ የሌለው ተኩስ አልፎ አልፎ ከመሰማቱ በስተቀር አዲስ አበባ ሰላም ነበረች (አንዳንዶች 17 ሰዎች ሞተዋል በማለት ጽፈዋል)። 
***** ***** *****
የልጅ እያሱ ከስልጣን መውረድ ዜና የተሰማው እያሱ ጅጅጋ እያለ ነው። የዜናውን መሰማት ተከትሎ የእያሱ ደጋፊዎች በሚበዙባቸው ሀረርና ድሬ ዳዋ ታላቅ ረብሻ ተነሳ። የደጃች ተፈሪ መኮንን ደጋፊዎች የተባሉት እየተሳደዱ ተፈጁ። እያሱ በከተሞቹ ደርሶ ሁኔታውን ካረጋጋ በኋላ በአሻጥር የተወሰደበትን ዙፋን ለማስመለስ ከከተሞቹ ነዋሪዎች ጋር ተማከረ። በዚህም የህዝቡን ድጋፍ ካገኝ በኋላ በሸዋ ላይ ለመዝመት መዘጋጀት ጀመረ። ይሁንና ዝግጅቱን ሳያጠናቅቅ እነ ራስ ተፈሪ የላኩት 15,000 ጦር ወደ ሀረርጌ እየመጣ መሆኑ ታወቀ። ልጅ እያሱም የሸዋውን ጦር ለመግጠም ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ገሠገሠ። ሁለቱ ሀይሎች ሚኤሶ አጠገብ ተገናኙ። ትልቅ ውጊያም አደረጉ። በጦርነቱ የሸዋው ሀይል ድል ስለቀናው ልጅ እያሱ ወደ አፋር በረሃ ሸሸ። የልጅ እያሱ አባት (ራስ ሚካኤል) የልጁን ስልጣን ለማስመለስ 100,00 ጦር አስከትቶ ወደ ሸዋ ዘመተ። ነገር ግን እርሱም እንደ ልጁ ሰገሌ ላይ ተሸነፈ።
***** ***** *****
ልጅ እያሱ የሰገሌውን መርዶ ከሰማ በኋላ በሽሽት ነው የኖረው ለማለት ይቻላል። በመቅደላና በደሴ አነስተኛ ውጊያዎችን ቢያደርግም በለስ ሊቀናው አልቻለም። ከዚያም ወደ አውሳ በረሃ ሄዶ ከወዳጁ ከሱልጣን አቡበከር ጋር ለጥቂት ዓመታት ኖረ። ነገር ግን ጠላቶቹ እዚያም እንዲቆይ አልፈቀዱለትም። ከሀረርጌና ከወሎ ትልቅ ጦር ቢያዘምቱበት ወደ ትግራይ ሸሸ። በትግራይ ውስጥ ለጥቂት ወራት ከቆየ በኋላ በ1915 ተያዘና ፍቼ ታሰረ። እዚያ እያለ የጎጃሙ ራስ ሀይሉ ተክለሀይማኖት እስር ቤቱን ሰብሮ ሊያስወስደው መሆኑ ስለተወራ ሌላ ቦታ እንዲዛወር ተወሰነ። በመሆኑም ወደ ሀረርጌ ተወስዶ ጋራ ሙለታ አምባ ላይ በተሰራለት እስር ቤት እንዲታሰር ተደረገ። በዚህ አምባ ላይም ለአስር ዓመታት ያህል በእስር ከቆየ በኋላ ጥቅምት 1928 መሞቱ ይፋ ሆነ። 
***** ***** *****
ልጅ እያሱ ሚካኤል የስልጣን ዘመኑ በእንቆቅልሽ የተመላ ነው። መንግሥቱን ያስተዳደረበት ዘይቤ፣ ከስልጣን የወረደበት ሁኔታ፣ በእስር ላይ ያሳለፈው ህይወትና የሞተበትም ሁኔታ እንቆቅልሽ ነው። ሌላው ይቅርና የተቀበረት ቦታ እንኳ እስከ አሁን ድረስ በትክክል አይታወቅም። እንቆቅልሽ በእንቆቅልሽ! 

ተሸዋረጋ የሚወለድ ልጅ
እምብዛም አይከፋ እምብዛም አይበጅ
ትንሽ ወደኋላ ይቀረዋል እንጅ።
ባሽከሮቹ ክፋት ደግሞም ባጋፋሪ
ዘውዱ ሲዞር አየን ወደ ልጅ ተፈሪ።
እያሱ የሚባል አንድ ልጅ ተወልዶ
የአባቶቹን መሬት አደረገው ባዶ።
መች ባንተ ይሆናል ምኒልክ ንጉሡ
አንተ አስበህ ነበር ልትሰጠው ለእያሱ
እንኳን ሊነግሥና ይያዛል ለነፍሱ
በራስ መኮንን ልጅ ትጠፋለች ነፍሱ
ተጌታ ተፈርዷል ዘውዲቱ ሊነግሱ።
የልጅ እያሱ ሰው የአባሻንቆ ሎሌ
ተለቀለቀለት መወቂያው ሰገሌ።
ሰገሌ ሜዳ ላይ የመጣብን መርዶ
በቀኝ እጁ ካራ በግራው ብርንዶ።
(የወሎው ሼኽ ሑሴን ጂብሪል ስለልጅ እያሱ ተናግረውታል ከተባለው ትንቢት: ምንጭ፣ ቦጋለ ተፈሪ በዙ፡ “ትንቢተ ሼኽ ሑሴን ጅብሪል”፣ አዲስ አበባ፣ 1985)
***** ***** *****
አፈንዲ ሙተቂ
ሰኔ 15/2005 
በሀረር ከተማ ተጻፈ።

Tuesday, January 3, 2023

#Adama vs #Nathret

አፄ ኃይለስላሴ አዳማ ከተማ በ1937 ዓ/ም ናዝሬት ተብላ እንድትጠራ ያደረጉበትና በግድግዳ ላይ ስለ ናዝሬት ከተማ መስፋፋትና እድገት ያደረጉት አስተዋጽኦ በሚል በሃውልት ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ቀዳሚ መረጃ ነው። ይህንን ጽሁፍ በጥሩ ጥራት ባለው ካሜራ መነሳትና እንደ ቅርስም በደንብ መጠበቅ ይኖርበታል የአፄው ቡችሎች እንዳያፈራርሱት። አንድ ቀን ደግሞ ፊንፊኔን አዲስ አበባ ብለው የሰየሙበት መረጃ በራሳቸው እጅ እንዲህ የተፃፈ ይገኛል ታሪክ ተቀብሮ አይቀርም ባሻዩ ። 

#Abbaa _#jiffaar

𝐀𝐛𝐛𝐚𝐚 𝐉𝐢𝐟𝐚𝐚𝐫 𝐈𝐈

➊. Maqaan Isaanii Muhammad bin Daawud Jedhama.

➋. Nama Gaafa Ummanni Oromoo Dukkana Keessa Ture Mootummoota Addunyaatiin Wal Barsiise.

➌. Dhiira Dachii Biyya Isaa Bira Dabree Dachii Arabootaa Irratti Mana Rabbii Ijaarsise.

➍. Goota Itoophiyaa Keessatti Oromoon Mootummaa Ta’uu Akka Danda’u Barsiise.

➎. Nama Seenaa Oromoo Fi Islaamaa Keessatti Faana Dhiifatee Deeme.

➏. Mootii Qaroominaan Beekkamu. Gaafa Mootonni Habashaa Miila Qullaa Yaatu, Nama Silipperii Hojjachiise.

➐. Mootii Gaafa Ummanni Oromoo Lafarraa Duguugama Turetti, Haadha Manaa Hedduu Fuudhuun Karaa Ittiin Revive Godhan Barsiise.

➑. Mootii Jireenya Ummata Isaatii Fi Biyya Isaa Jijjiire.

#Dirre_#dhawaa

Dirree dhawaa. 
             ----------
Jecha Daha ykn dhawa ( dhawaa ) jedhu kana galmeen jechootaa  ( English- borana world list ) ykn vencent G. Stegmen kitaaba isaa keessatti jecha dubbachuu ykn waa himuu jedhuun hiikee jira. Bifa wal fakkaatuun fakkeenyaaf:- oromoon booranaa Haasawa isaanii  keessatti " Abaluu maal dhahata ? Jedhu,  oromoo booranaa qofaa mitti , naannoo harargetti yeroo hedduu  " gurbaan maal dhawachaa deema ? ykn qaallichi maal dhawata ?
Jedhu, kana jechuun maal dubbachaa deema 
Ykn maal jedha jechuu barbaadaniitii.
               Magaalaa dirree dhawaa keessatti,
Dirreen dhaha' ykn dhawaa  iddoo Amma dachaatuu irraa kaassee hamma ganda gaaraa jiru kana gubbaa  hoggaa tahu  oromoonni afran Qalloo iddoo kana maaliif lafa dhawaatiif filatan kan jedhuuf yaada bal'aa kaasuun ni dandahama. Haa tahu malee  qulqullina samiitiifi  Ripha lafaa ( Altitude) qofa laaluun iddoon kun hojii dhahatiif mijaa'a akka tahe salphatti hubbachuun ni dandahama. Kana qofaa mitii,
Dirreen tan gubbaa dhaabbachuun  wal qaxxaamura urjilee daawwachuun  hedduu mijaa'aadha.
              Irra caalaa dirree tana lafa dhawaatiif mijooytuu kan godhe dhaloota ji'aa handaara fugug keessatti ( moon under Horizon) arguudhaaf salphaadha.
        Magaalaa dirree dhawaa keessatti,waqtii afran jechuun birraa; bonna, ganna fi badheessa  keessa  Aduun sadarkaa ykn digrii adda addaatiin baati. Kanaan wal qabatee 
tulluu fi gaarreen adda addaa moggaasa 
Gara garaa qaban.
    Fakkeenyaaf guyyaa Arr'aa, galgala  kana, magaalaa dirree dhawaa bakka magaalaa ykn dachaatuu jedhamtu keessa dhaabbachuun  kallattii bahaa  digrii  67°  irratti         
Ji'a  Adeessaa  dhibba irraa harka 87.7 %  arguu ni dandeessa.  Noonnoo kanatti  Amajjii 7 irraa kaassee hamma 14tii guutuu guutuutti 
Ji'ini kan Goobanu taha. bara 2023, Ji'a Bittoteessaa ,
Guyyaa 21 irraa kaassee naannoo kanatti  badheessi kan eegalu hoggaa tahu harargee keessatti  iddoon hedduuun dur irraa kaassee Rooba badheessaa yeroo kana argachuun beekaman.... galgala kana keessa,  akka lakkooysa itiyoophiyaatti sa'aa 12: 20 irratti 
Plaaneeiii venus ,Saturn galgala sa'aa 2: 53 irratti samii magaalaa dirree dhawaa irratti arguu ni dandeenya .

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...