Translate

Thursday, February 10, 2022

#Artist Muhe_Abarraa_Walloo

#Muhe_Abarraa Walloo kamisee Aanaa dawaa caffaatti seensa bara 1950 keessatti dhalate. Muhee abarraa sagalee kiloolee isaa saniin xiqqummaa isaa irraa hanga dullumaatti, taphoota kanneen biyya tana keessatti beekamoo ta'an akka Bati major,Ambassal,Anchi hoyye,tizitaa taphachuudhan namni isa qixxaatu hin jiru ture. Artist muhee abarra walaleessaaf taphataa salphaa hin turre nama mana dhugaatii keessa deemee alkoolii dhuguuf maallaqa guurratu hin turre,nama safuuf aadaa ummata isaa eeggatee kiraarif,maasinqoon sagaleen taphatuudha. Muhee abarraa hiree ta'eeti iddoo hin beekamneti dhalateef malee artistoota biyyi tun sadarkaa guddaa kenniteefi ol nama sadarkaan kennamuufii qabuudha ture.muheen kennaa uumaatin, sagaleessaaf,kiraara taphachuun nami isa gitu inuma hin jirre ture.otoo akka warra ammayoomee kanatti sagaleen isaa studio galee waraabamee editor godhamee namni isa gitu hin jiru sadarkaa tokkoffaa irratti taa,aa ture. Artist muhe abarra nama Aadaa,afaan,gootummaa saba isaatii beeksisuudhaan nama kutatee ka,ee ummata isaa ittiin bohaarsaaf beeksisaa tureedha.artist muhe abarra kan beekamuu dhabaate naannoo biraatti waan hin beekaneef qofa dandeettiin isaa dhokatee hafe.waraabbiin sagalee isaatis teephi kaassetatti waan tureef baayyina yeroo keessa badaa dhufe. Akka hireetti ta,ee muheen dandeettii isaa san ka kiraariif,maasinqoo sagaleen taphachuu dandayu san osoon waraabamin hafe. Tapha isaa keessaa, kaaruwwaan tapha baayyee namatti tolu ture. / Balambaras Qimant irraa/ miky sultan..

Thursday, February 3, 2022

#Omotic,#Nilotic የምባሉ ሁሉ የኩሽ ቅርጫፍ ናቸው"

ኦሞቲክ ናይሎቲክ የሚባሉ ሕዝቦች 100% በመረጃ የተረጋገጠ የኩሽ ልጆች ናቸው ።ከ ኩሽ ያልተፈጠረ አንድም የ አፍሪካ ሕዝብ የለም። ሁሉም የ አፍሪካ ልጆች፣ Hortee kush ናቸው። መረጃው የደቡብ ሕዝቦች የጋምቤላና የቤንሻንጉል ሥምችና በግዛታቸው ውስጥ የሚገኙ የቦታ የቀበሌ የተራራ የወንዝ ሥሞች አብዛኞቹ ከኩሽ(Kement)ቃል የመጡ ናቸው። በሙሉ ከነትርጉሙ የኬሜንት ቃል ነው። ካምባታ ፤ ወልሃይታ፤ዋላሞ (ከሁለት አንዱ) ፤ኩሎ መኳኳል ፤ጥምባሮ ቀባጣሪ፤ አላባ ቆሊቶ የባንዲራ ተቀባይ ፤ቡርጂ የተደበረ ፤ዳራሳ ልብሱ፤ ማጂ ታህሣሥ፣ አዋሳ ማህበረሰብ ፤ኮንሶ ንቦች፤ አዲያ ነጫማ፤ ገለብ ግፈፈው ፤ዳዋሮ መዳወሪያ፤ ዳሌ ግራጨ፤ ጌድኦ/ጋዲኦ ማሠሪያ፤ ጋሞ ማሰቃያ ፤ጎፋ ማለት ነው። ገሙ ጎፋ የሚባለው ጎፋ የገሙ አባት በመሆኑ ነው። አዋሳ የጡሙጋ ፤ ጡሙጋ የባሬንቱ ኦሮሞ ልጅ ነው። የአዋሳ ከተማ ሥም ከዚህ ታሪካዊ ሥም የመጣ ነው። ጉራጌ ከጉራ የመጣ ሥም ነው። ጉራ የቦረና ኦሮሞ ልጅ ነው። ጉራ ሲጠብቅ ጥቋቁር ሲላላ ጆሮ ማለት ነው። የጉራጌ ጎሳ ጨቦ ማለት መሰበር፤ ማራቆ መረቃማ፤ምስቃና ጥቃቅን ፍጡር ፤ዋላኔ ቀለበ፤ ማለት ነው። ደቡቦች ብቻ ሳይሆኑ የጋምቤላና ቤንሻንጉል ሕዝቦች የ ኩሽ ጎሳ ናቸው። የቤንሻንጉል ጥንታዊ ሥም ሻንገላ ነበር። ትርጉሙ አምስት ጊዜ የሚገባ ማለት ነው።ሲዳሞ የቦራና ኦሮሞ ልጅ ነው። ቦረና ዋላጋ፣ ጨላባ ፣ጎሬ፣ ጎፋ ፣ሲዳሞ ፣አኒያ፣ ጋሪ፣ ጉራ፣ ጌራና ዳጬን ወለደ። ከወለጋ ጌራና አኒያ ዝርያ በስተቀር የቀሩት ደቡብ ሕዝቦች ናቸው። ኦሮሞ የደቡብ ሕዝቦች ዘር ማህጸን ለመሆኑ ተጨማሪ መረጃ የሚከተሉት ናቸው። ከላይ የተገለጹ ሥሞች በሙሉ ከኦሮሞ በስተቀር በሌላ ሕዝብ ቋንቋ ውስጥ አይገኙም ልተረጎሙ አይችሉም። የብሔረሰቦቹ ሥም ብቻ ሳይሆን በግዛታቸው ውስጥ የሚገኙ የቦታ የቀበሌ የተራራ የወንዝ መጠሪያ ሥሞች አብዛኞቹ ከአሮሞ ቃል የወጡ ናቸው። Website:-https://mikysultan.blogspot.com/ Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU Telegram:- t.me/Oromo_ geography

Wednesday, February 2, 2022

#ቅድስት፣ ሀገር፣ ኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?

"ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ" ÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷ ደብተራ ሲያደነዝዝህ "ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ" ይልህና "የስሟ ትርጓሜ ምንድነው?" ስትለው አይጥ የዋጠች ድመት መስሎ ዝም ጭጭ ይላል። አንዳንዴም "በልሳነ ... ግዕዝ... " ይልህና ተወጃብሮ ተወጃብሮ አንተን አወዛግቦህ ላሽ ይላል። ጠበቅ አድርገህ ከያዝከው "ዘወር በል መናፍቅ" ብሎ ይሰድብህና ሊያሸማቅቅህ ይሞክራል። ÷ ቅድስት ሀገር ማለት የለማኝ መፈልፈያ መሆን ነው እንዴ? ልመና የቅድስና መገለጫ ነው እንዴ? ቅድስና ጉስቁልና ነው እንዴ? ቅድስት ሀገር ውስጥ ወንድሙን ወንድሙ ይገድለዋል እንዴ? ምግባር የለሽ ሃይማኖተኛነት የቅድስት ሀገር መገለጫ ይሆናል ወይ? ነው በገድልና በተዓምር ተራራ ያሳከልካቸውን ፖለቲከኞች 6 ክንፍ ተክለህላቸው ታቦት መቅረጽ ነው ቅድስና? ÷ አሁን ያሉት መለካዊያን ለአብይ አህመድ ታቦት መቅረጻቸው ይቀራል ብላችሁ ነው? እነ ቅዱስ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በቅርቡ ታቦት ይቀረጽላቸዋል የሚል ተስፋ አለኝ። ምንያቱም የቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መሪዋ ነው እና! ይደልዎ በከመ ይሠየም ቅዱስ ወይትወሀብ ስድስቱ አክናፍ ለዳንኤል ክብረት እስመ መራሂሃ ውእቱ ለኢትዮጵያ! ሃሃሃሃ! ÷ እነዚህ ደብተራዎች እንዲህ እየፃፉ ነው "ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ" እያሉ ጆሯችን ያበሸቀጡት። በውኑ ኢትዮጵያ ከሌላው ዓለም በተለየ ቅድስት ናት? አሜሪካስ? የሚገርመው የቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሠባኪዎች አብዛኛዎቹ የአሜሪካ ፓስፖርት ያላቸው ናቸው። እናባ ዘነዘና ሁሉ እዛ ማዶ ነው የሚሞሩት። ÷ የቅድስቷ ሀገር ልጆች በአረብ አገራት ተቀጥረው እየማቀቁ ይገኛሉ። ይሄም የቅድስና መገለጫው ሆኖ ይሆን? መሪዎቿ በደብተራዎችና በጠንቋዮች ተከበው በሰው ልጆች ላይ የፈለጉትን እያደረጉ ሕዝባቸውን የሚያዋርዱባት ሀገር ቅድስት ከተባለች እርሷ ነክሳ ያሳደደቻቸውን ልጆቿን ተቀብለው በሠላም የሚያኖሩት ሀገራት ምን ይባሉ? ልጆቿን የምትበላው ደም መጣጯ ሀገር ኢትዮጵያ ቅድስት ከተባለች ኢትዮጵያዊያንን በስደት ተቀብላ የምትንከባከበው ሱዳን ቅድስተ ቅዱሳት መሆን ሲያንሳት አይደል ÷ ለመሆኑ ኢትዮጵያ የምትባለው በደብተራ ተንኮል የጎበጠች ሀገር ቅድስት ናትን? ከአለም ሀገራት የረከሱት ሀገራት እነማን ናቸው? የጅምላ ፅድቅ አለ ወይ? የቅድስና መገለጫወቿ ምን ምን ናቸው? ÷ ደብተራ ያገነናት አገር ለዛም ሰው ሳይሆን ጋራውና ሸንተረሩ ቅዱስ ከሆነ ሰዎችን የሚያከብሩና በመከባበር የሚኖሩባቸው ሀገራት እንዴት የበለጡ ቅዱሳን አይሆኑም? ÷ ደብተራ ጠላውን ተጎንጭቶ በስካር ጆሮው ሲግል፡ አይኑ ሲፈጥ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጥና በግሳቱ አቧራ ተከልሎ ማንበብ ይጀምራል። በረሃ የሚለውን ኢትዮጵያ እያለ ያነበዋል። ትንሽ ቆይቶም ኢትዮጵያ 44 ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሳለች እያለ ያላዝንብሃል። ታዲያ በዚህ ጊዜ ጌታቸው ረዳ በሚዲያ ብቅ ይልና "በመጽሐፍ ቅዱስ በመጠቀስ ቅድስና ካለ ሦሪያ ከ380 በላይ ተጠቅሳለች፡ ግብጽም ከዚያ በላይ" ብሎ ያሳርፍልኛል። ÷ እነዚህ የምላስ እንጂ የተግባር ክርስትናን የማያውቁ ደብተራዎች ኢትዮጵያን ቅድስት ብለው መጥራት የጀመሩት ከነ ይኩኖአምላክና ተክለሃይማኖት በኋላ መሆኑ ታውቋል። ነገሥታቱ በምድር በሚሠሯቸው ተግባራት እንዳይመዘኑ መለኮታዉ ሆነው ያርፋሉ። ደብተራዎችም ይሄን ይለፍፋሉ። ንጉሳቸውንም "ሥዩመ እግዚአብሔር" ይሉትና ማንም እንዳይቀናቀነው ያደርጉታል። "ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ!" በሚል ድንቁርናችን ተቀብለን እንድንገዛ ይሰብኩናል። አንዳንዴም ቅዱስ ዘርዓያዕቆብ፡ ቅዱስ እከሌ ወዘተ እያሉ እንድንሰግድላቸው ይስልሰብኩናል። "ኢይንሰግድ ለአምላከ ነኪር" ስንላቸው ደግሞ ይገድሉናል። ÷ ለመሆኑ ደብተራው ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት ነው እንዲበዛላቸው ሲጥሩ የኖሩት? ይሄን ለማየት ኪንግ ጄምስ ቨርሽን የሚባለውን እንግሊዝና መዝሐፍ ቅዱስ ከእኛው ጋር ለማነፃፀር ሞክሬ ነበር። ብዙውን እነርሱ እንዲመቻቸው እያደረጉ አስተካክለዋል። ለምሳሌ #1ኛ መዝ. 73፥14 በአማርኛ እንዲህ ይላል፡ "አንተ የዘንዶውን እራስ ቀጠቀጥክ፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።" እንግሊዝኛው ደግሞ "Thou breakest the heads of leviathan in pieces, [and] gavest him [to be] meat to the people inhabiting the wilderness." ታዲያ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ከየት አመጡት። እንግሊዝኛው የሚለው "...በበረሃ ለሚሞሩ ሰዎች ሥጋ እንዲሆናቸው ሰጠሃቸው" ነውና። ÷ #2ኛ መዝ. 71፥9 እንዲህ ይላል፡ "በፊቱ ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፡፡ ጠላቶቹም አፈርን ይልሳሉ።" እንግሊዝኛው ደግሞ እንዲህ ይላል፡ "They that dwell in the wilderness shall bow before him; and his enemies shall lick the dust." ታዲያ ኢትዮጵያ የምትለውን ቃል ከየት አመጧት? "...በበረሃ የሚኖሩት..." የሚለውን ኢትዮጵያ ብሎ መተርጎም ምን ማለት ነው? ኢትዮጵያ በረሃ ነበረች እንዴ? ÷÷ እንግዲህ "ቅድስት ሀገር" የሚሉት ደብተራዎች እንጂ መጽሐፍ አይደለም። ሲጀመር ኢትዮጵያ የሚለውን ሥያሜ ትርጉም ጭራሽ አያውቁትም። በማያውቁት ሀገር ስለሚኖሩ ዝም ብለው ነው የሚቀባዥሩት። ማስረጃ የላቸውም። የተደረተ የተሰረዘ ወግ ነው የሚጠርቁት። እንኳን "ኢትዮጵያ" የሚለውን የመንደራቸውን ስም እንኳ መተርጎም አይችሉም። ÷ ለመሆኑ ነብሰገዳይ እንዴት ብሎ ነው የሀገርን ቅድስና ሊሰብከን የሞክረው? ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ባንዴራው ከሰማይ የወረደ ነው ብሎን ያርፋል። Website:-https://mikysultan.blogspot.com/ Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU Telegram:- t.me/Oromo_ geography

#ቡና የ እርኩስ መጠጥ ነው ይላል።

ነብሰ ገዳይነትን ባርኮ ቡናን የሚያወግዝ ግራ ገብ ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ደብተራ ዘኮልኮሌ ወዘዝባዝንኬ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሌለን ኮተት ደርቶ ደርቶ ይፅፍና እራሱ የፃፈውን ድሪቶ ተመልሶ የሃይማኖት ማጣቀሻ መጽሐፍ አድርጎ ያቀርበዋል? ግርም ይለኛል! "ቡና አትጠጡ" ይልህና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አምጣ ስትለው "ዜና ሥላሴና ድርሳነ ማርያም ፅዮን" ይልሃል። ለመሆኑ እነዚህን መጽሐፍት ማን ፃፋቸው? እንደ ማጣቀሻ መጽሐፍ መጠቀምስ ምን ይረባል? ይሄን ስታነሳና ስትወጥረው "ተሃድሶ!" ብሎ ስም አውጥቶልህ በድንጋይ ያስወግርሃል! ~~~ እኔ በግሌ ቡና፡ ጫት፡ ጥምባሆ፡ ወዘተ አልጠቀምም። የማልጠቀመው ግን ሃይማኖቴ ከልክሎኝ ሳይሆን ሐዋርያው "ሁሉ ተሰጠኝ፡ ነገር ግን ሁሉ አይጠቅመኝም" ያለውን የህይወት መመሪያ ተከትየ ነው። ሱስ የሚያስይዙ ነገሮችን ከመጠቀም አለመጠቀም ይሻላልና ነው። ማለትም "ቡና፡ ጫት፡ ጥንባሆ፡ ሀሸሽ፡ ወዘተን ከሌሎች የዕለተ ማክሰኞ ፍጥረቶች ለይቼ ርኩሳን ናቸው" አልልም። "አምላክ የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ መልካም እንደሆነ አየ" ብሎ መጽሐፉ እየመሠከረ እነዚህን እፅዋት ለይቼ "ርኩሳን ናቸው" አልልም። አምላክ ያለ ዓላማ አልፈጠራቸውም። እኛ ከዛ ዓላማ ውጭ ስለምንጠቀማቸው እንጂ። ሰው መቼም አስቼጋሪ ነውና ዛሬ በሳይንሱ ዓለም መድኃኒት ብለን ከምንጠቀማቸው መድኃኒቶ መካከል በውስጣቸ የእባብ መርዝ የሌላቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው። ግን እየገዛን እንውጣለን። ግን አናወግዝም! ~~~ አቅም ቢስ ዘኮልኮሌ ደብተራዊች ወንጌልን ሰብከው ማስተማር ሲያቅታቸው የሽብርና የማስፈራሪያ መጽሐፍትን እየፃፉ ሕዝብ ያሸብራሉ። እንዲህ ዓይነት ድርንቁርና ያሳዝናል። በጥቃቅን ነገሮች ላይ ትልልቅ አጀንዳ እየፈጠሩ ሕዝቡን አደነቆሩት። ከወንጌል አራቁት፣ በእውቀትና ጥበብ ሆኖ የፈጣሪን መንገድ ከመከተል አራቁት። ሰው የሚገድለውን ምዕመን እየባረከና እየቀደሰ ቡና የሚጠጥውን ምስኪን ሲያወግዝ ይውላል! ይሄ ነው ወንጌል? በየመሸታ ቤቱ አልኮል ሲያንቃርር ውሎ እያደረ "ቡና የሚጠጣ የሥላሴ ልጅነት የለውም" ይልሃል። እስኪቱን ቀስሮ እህቶቹን በቡድን እየደፈረ "ቡና የጠጣ 10 ዓመት ደረቅ እንጀራ እየበላ ይፁም" ይልሃል! ይሄን ነው ደብተራ ዘኮልኮሌ የምንለው። አልተገናኝቶም! ~~~ "ቡና በአፈጣጠሩ ርኩስ ነው" ካልክ "ቡናን የፈጠረው ርኩሱ ዲያብሎስ ነው" እያልክ መሆንክን ዕወቅ! የለም "ቡናን ዲያብሎስ ነው የሚጠቀመው" ካልክም አንተ ውስጥ ስንት የሰይጣን መንፈሶች አብረውህ ተወልደው አብረውህ አድገው አንተን እየተጠቀሙህ አይደል እንኳን እፅዋቱን። ሲጀመር የዶቅማ ተቀጥላ እበጠበጥክ ስትጠጣ የኖርክ ጀግና ምነው ቡናን አወገዝጋት? ምናለ መጀመሪያ በሰው ልጆች ላይ በድግምት፡ በሟርትና በመተት ሰይጣን መጫንን አላወገዝክምሳ? ነው ይሄ ጥበብ ነው? ፍስንክቶች! ኤጭ! እንዴት ሰለቻችሁኝ!? ~~~ ቡናን ጠንቋዩ ነው የሚጠቀመው ካልከኝም "ምነው ጠንቋይ እንጀራ ይበላ፡ ውሃስ ይጠጣ የለም? ለምን እነዚህንም አልተውካቸውምሳ?" እልሃለሁ። ያልሆነ ዝብረቃ ውስጥ ገብተህ ከምትዘባርቅ 10ቱን ትዕዛዛትና 5ቱን ቃላተ ወንጌል በደንብ አስተምር! ሰዎች የአምላክ ፍቅር ሱያድርባቸው በውስጣቸው በሚያድረው የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ክፉውንና ደጉን መለየት ይችላሉ። ከዝብረቃ መንገድ ውጡ። ~~~~ አሁን ለኮልኮሌ ደብተራዎች ትልክ መከራ የሆነባቸው ሰው ባልነቃበት በጨለማው ዘመን የደረቷቸው መጽሐፍትን ዛሬም ለማስቀጠል መደናበራቸው ነው። ስህተታቸውን ላለማመንና ይቅርታ ላለማለት ያለፈ ስህተታቸውን የማስቀጠል ትግል ውስጥ ገብተው ይዳክራሉ። ውሸታሞች! ~~~ ደብተራ ዘኮልኮሌ የፃፈውን መፅሃፍ አንብበህ በማይከፈት የድንቁርና ቁልፍ ልብህን ከምትቆልፈው ሳታነብ ብትኖር ይሻላል። የደብተራ ዘኮልኮሌ መጽሐፍትን ከማንነብህ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ተማር፡ ጥሩ ክርስቲያን ሁን! ከክርስቲያናዊ አረመኔነት ውጣ! ያኔ የደብተራው ኮልኮሌ በደንብ ይገባሃል። አምላክህ ከደብተራው ለይተህ ለማየት ሞክር!

#አባዬ" የሚለው ቃል የአማርኛነት መሠረት የለውም

"አባዬ" የሚለው ቃል የአማርኛነት መሠረት የለውም ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ይህን ጽሑፍ ለመጻድ ያነሳሳኝ የ3000 ዓመት የድንጋይ ሐውልት ላይ "አባዬ" የሚል የአማርኛ ቃል ተገኘ ተብሎ የተለቀቀው ቪዲዮ ነው። ፎቶውን እንደምትመለከቱት ሀውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍ [አባዬ] የሚል ይመስላል እንጂ [1አበየo] የሚል ነው። ስለዚህ ይመስላል በሚል ካልሆነ በስተቀር ቃል በቃል [አባዬ] አይለም። ስለሆነም ከዚህ ቀጥሎ የማቀርበው ጽሑፍ ሐውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍ [አባዬ] እንደሚል ታስቦ የተፃፈ ነው። ~~~ "አባዬ" አማርኛ ነው ብለህ መደምደም አትችልም። ግእዝ ከመካከለኛው ምስራቅ እንደመጣ ይታወቃል። እናም ከሆን ግእዝ ሊሆን ይችላል ብለህ መገመት ይቻላል። ግእዝም ቢሆን ግን ከየት አገኘው የሚል ጥያቄ ይነሳበታል። ምክንያቱም ግእዝም ቢሆን በአለም ከአሉ ቋንቋዎች መካከል በእድሜ ትንሽ ነው። ተጨፍነህ የመልአክ ቋንቋ ነው ብለህ ካልተቀበልከው በስተቀር ማለቴ ነው። ~~~ በግእዝ [እም] "እናት" ብለን [እምየ] "እናቴ" እንላለን፡ [አባ] "አባት" ብለን [አባየ] "አባቴ" እንላለን። እናም ቃሉ ግእዝ ሊሆን ይችላል ብለን ማሰብ ትክክል ነው። ማረጋገጫ ጥናት ቢያስፈልፈውም። ~~~ [አባዬ] የሚለው ቃል አማርኛ ሊሆን አይችልም። ትላንት የተፈጠረው አማርኛ በምን ተዓምር ነው የ3000 ዓመት የድንጋይ ሐውልት ላይ ሊፃፍ የሚችለው? አማርኛ ከቅማንትኛ ወጥቶ የተወሰኑትን ቃላትና አገብብ ከግእዝ ጋር በማዳቀል የተፈጠረ አዲስ ቋንቋ እንጂ ጥንታዊ ቋንቋ አይደለም። ~~~ ሲጀመር አማርኛ የጽሑፍ ቋንቋ የሆነው በ19ኛው ክ/ዘ ሁለተኛ አጋማሽ በአፄ ቴወድሮስ ነበር። ለዛም በመከራ። ፊደሎቹ ከግእዝ የተዋሱ ነበሩ። እንዲሁም አማርኛ የቋንቋ ውጥንቅጦችን ቀላቅሎ ስለሚጠቀም የሚጠቀማቸው ቃላት ስርዎ ማንነታቸውን ማግኘት በጣም ከባድ ነው። ~~~ አማርኛ [አባት] ብሎ እንዴት ነው [አባዬ] የሚለው? በምን ሒሳብ? ልክ [እናት] ብሎ "እናቴ" ወይም "እናትዬ" እንጂ "እናዬ" እንደማይለው ማለት ነው። እናም አማርኛው ማለት የነበረበት [አባት] ብሎ [አባትዬ] ወይም [አባቴ] እንጂ [አባዬ] አይደለም። ምክንያቱም የቋንቋው ሕግ ስለማይፈቅድለት። አማርኛ እንዲህ ዓይነት ውዥንብርን የሚያስተናግደው ዋናው ምክንያት የብድር ብቻ ቋንቋ ስለሆነ ነው። ~~~ ይሄን ክርክሬን የበለጠ ለማጉላት አንድ ሌላ አማርኛዊ ውዥንብር ላሳያችሁ። አማርኛ ጥሬ ዘር ስሞችን ከዛው ከሚጠቀመው ግስ ነው የሚፈጥረው። ለምሳሌ [ሞተ] ብለን "ሞት"፡ [አፈቀረ] ብለን "ፍቅር"፡ [ዋለ] ብለን "ውሎ"፡ [በላ] ብለን "መብል"፡ [ጻፈ] ብለን "ጽሑፍ" እንላለን። ታዲያ የቋንቋው ሕግ እንዲህ ከሆነ አማርኛ [ገመና] የሚለውን ስም ከየት አመጣው? ከየትኛው የግስ ስርዎ ቃሉ አወጣው? ከየትም አላወጣውም። አማርኛ ]ገመና]ን በቀጥታ ከቅማትኛ ወስዶ ነው ራቁቱን የሚጠቀመው። [ገመና] መሠረቱ ቅማንትኛው ነው። በቅማንትኛ [ገም-] "ወረደ" ከሚለው ግስ [ገምና] "መውረድ"፡ [ገምንታ] "አወራረድ"፡ [ገመና] "ውርደት"፣ ወዘተ የሚሉ ስሞች ይፈጠራሉ። አዎ [ገመና] ማለት "ውርደት" ማለት ነው። አማርኛ እንዲህ አይነት ቃላትን አብዝቶ ያለ ስርዎ ቃል ይጠቀማል። ምክንያቱም አማርኛ የትላንት ፈጠራ ስለሆነ ነው። [አባዬ] የሚለው ቃልም ልክ እንደ [ገመና] አማርኛዊ መሠረት የለውም። በመሆኑም የድንጋይ ላዩ [አባዬ] ከታሪካዊ ዳራና ታሪካዊ መቼት ባሻገር በቋንቋው ኀልወተ ታሪክና ባህርይ አንጻርም አማርኛ ይሆናል ብሎ ማሰብ የሞኝነቶች ሁሉ ሞኝነት ነው። ~~~ ሌላው ንግሥት ማክዳ ወይም የሳባ ግሥት የቅማንት ንግሥት እንደነበረች ታሪክ ይመሰክራል። ስለዚህ ቋንቋው ቅማንትኛ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። ለምን ቢባል በቅማንትኛ [አባ] ማለት "አባት" ማለት ሲሆን [አዬ] ማለት ደግሞ "የኔ"፡ "ሆይ" ማለት ነው። እናም [አባዬ] ማለት "አባቴ"፡ "አባት ሆይ" ማለት ነው። እዚህ ላይ ይህን መረጃ ቅማንት ውስጥ ከሚነገር አንድ የቃል መረጃ ጋር ማገናኘት ይቻላል። "ቅማንቱ መጽሐፉን ጥሎ በልቤ ነው ማድረው ብሎ መጽሐፉን ስለጣለ ነው የጽሑፍ መረጃ የሌለው" የሚል የትውፊት መረጅ አለ። እናም እኒህ የቅማንትን ታሪክ እየዘረፉ ለራሳቸው ሲያድድርጉ የኖሩ ሌቦች "ቅማንት በልቡ ብቻ ነው የሚያድረው" የምትለዋን የፈጠራ ታሪክ ፈጥረዋታል የሚል መደምደሚ ሊያመጣ ይችላል። "ቅማንት ከግብጽ መጣ" የሚለው መሠረተ ቢስ የፈጠራ ድስኩራዊ ወግና "ቅማንት ሕንፃ ሊሰራ የመጣ ባርያ ነው" የሚሉት ሁሉ አሻጥር ናቸው። የቅማንትን ጥንታዊነትና የታሪክ ባለቤትነት ለማጥፋት የሚፈለሰፉ የፈጠራ ታሪኮች ናቸው። ይሄም ታሪክን ዘርፎ የራስ ከማድፈግ ጋር አብሮ የሚሄድ አሻጥር ነው። ያገው ቋንቋ የጋኔን ቋንቋ ነው የሚለውም ከዚሁ ጋር አብሮ የሚሄድ አሻጥር ነው። ~~~ እውነቱን ለመናገር አሁን የግእዝ ፊደል ተብሎ የተዘረፈው ሃብት የቅማንት እንደነበር የበለጠ ጥርጣሬየን አጉልቶታል። እናም "ግእዝ ፊደሉን የወሰደው ከቅማንትኛ ነው" የሚል ንድፈ ሃሳብ (hypothesis) መሥርቶ ቀጣይ ጥናቶችን ማድረግ ግድ ይላል። ብዙ ሰፋፊ ምርምሮችን ማድረግ እንዳለብምን ያሳያል። ቅማንቱ ቅዱስ ያረን ዜማውን ዝም ብሎ ከምድር የፈጠረው አልነበረም። ታሪክ አጥፊዎች እንደሚሉትም ከሰማይ አልወረደም። ቀደም ብሎ አባቶቹ ቅማንት ከመዘናዎች ሲያዜሙት የነበረ ነው። በቅማንት የሕገልቡና አስተምህሮ ውስጥ የነበረውን ዜማ ነው ቋንቋ ቀይሮ የጻፈው። እናም የተሰረቁ የጥንት የቅማንት መጽሐፍት የሆነ ቦታ ሊገኙ እንደሚችሉ ይህ ጥሩ ማስረጃዊ ፍንጭ ይሰጣል። ~~~ በእርግጥም ሀውልቱ 3000 ዓመታት እድሜ ካለው ከቅማንት ቋንቋ አይወጣም። ምክንያቱም አክሱም ላይ ተገኙ የተባሉት የድንጋይ ላይ ጽሑፎች በመጀመሪያ በመጀመሪያ ድምፅ ብቻ የተጻፉ ነበሩ። "አክሱም" ለማለት [አከሰመ] ብለው የተጻፉ ናቸው። ይሄን ከ[አባዬ] ጋር ስታነጻጽረው አይገናኝም። ~~~ ሌላው ደቡብ አረቢያ በአፄ ካሌብ ዘመን በኢትዮጵያ ግዛት ስር ነበር። ታዲያ በዚያ ጊዜ ወደ ቦታው የሄደ ኢትዮጵያዊ ገዢ የድንጋይ ሐውልቱ ላይ አጽፎት ላለመሆኑ አሳማኝ ማስደጃ ማቅረብም ከባድ ነው። ብቻ ብዙ ጥናት ይጠይቃል። እርግጠኛ የምንሆነውን ግን ጽሑፉ ጭራሽ አማርኛ አለመሆኑን ነው። አማርኛ የ750 ዓመት ሙጫቅላ ቋንቋ ነው። አይደለም በድንጋይ ላይ በብራና ላይ የተጻፈ የአማርኛ ቃል ከ19ኛ ክ/ዘ በፊት ማምጣት አይቻልም። Website:-https://mikysultan.blogspot.com/ Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU Telegram:- t.me/Oromo_ geography

#ግሼ አባይ ፣ ምነኛ ነው?

ግሼ አባይ፣ ምንኛ ነው? ግሴ አባይ ማለት በቅማንትኛ ግልገል አባይ ወይም ድንክ አባይ ማለት ነው። ደብተራው ግን ሊያጥፋፋ ይዳክራል። እውነት የትኛውንም ያክል በገድል ልትሸፍነው ብትሞክር አይሸፈንም። ~~~~ ግሼ ዓባይ፡ ምንኛ ነው? ~~~~~~~~~~~~ መቼም የእኛ አገር ውስጥ ብዙ ነገሮች ትክክለኛ ማንነታቸውና የስማቸው ትርጉም በውል አይታወቅም። ምክንያቱም ሀገሪቱ ላለፉት አያሌ ምእት ዓመታት የሆነ የታሪክ ነቀዝ አፍርታ ትክክለኛውን የታሪካችን ፍሬ በልቶ እንክርዳዱንና ግርዱም ጥሎልን በመሄዱ ነው። ከሰዎች የስም ስያሜዎች እንኳ ብንነሳ አያሌ ትርጉም የለሽ ስሞች ሞልተዋል። ለምሳሌ ጋሼ፡ ፈንቴ፡ ፈንቲ፡ ወሰንጌ፡ ጀጃው፡ ገልሞ፡ ኮልቫ፡ ጉርባ፡ አስሜ፡ ሰጤ፡ ወዘተ የሚሉትን ስሞች ብንመለከታቸው በአማርኛ፡ በትግርኛ፡ በግዕዝ ወይም በሌላ ማንኛውም ቋንቋ ትርጉም የላቸውም። ይሄ ለምን ሆነ? የሚል ጥያቄ ስናነሳ መልሳችን የሚሆነው "የታሪክ ቀበኞች የሆነን ታሪካዊ ሕዝብ ደዝባ ለማጥፋት ስለሠሩ ነው" የሚል ይሆናል። ~~~ ይሄ ትርጉም አልባነት በሰዎች ስታሜዎች ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን በተለያዩ መልክዓ ምድራዊ ስያሜዎችም ላይ ጎልቶ ይታያል። ለምሳሌ ከመካከለኛው ኢትዮጵያ እስከ ግብፅ ድንበር ያሉ የተለያዩ መልክዓ ምድራዊ ሥያሜዎችን ስንመለከት ከላይ በጠቀስኳቸው ቋንቋዎች ምንም ዓይነት ትርጉም የላቸውም። ሸዋና ሸዋ ውስጥ ያሉ ቦታዎች፡ ጎጃምና ጎጃም ውስጥ ያሉ ቦታዎች፡ ጎንደርና ጎንደር ውስጥ ያሉ ቦታዎች (ካና ሰጌ)ን ጨምሮ፡ ወሎና ወሎ ውስጥ ያሉ ቦታዎች፡ ትግራይና ትግራይ ውስጥ ያሉ ቦታዎች፡ ኤርትራና ኤርትራ ውስጥ ያሉ ቦታዎች፡ ወዘተ አብዛኛዎቹ ብዙዎቻችን በምናውቃቸው ቋንቋዎች ትርጉም የላቸውም። ለምን? እውን ትርጉም የሌላቸው ናቸውን? ~~~ በእርግጥ ትርጉም አላቸው። ትርጉማቸውም አንዳንዶች ራሳቸውን አጥፍተው ሌላውን ለማጥፋት ታሪክ የሚደልዙና የሚደርቱ የታሪክ ድሪቶ ጸሓፍት እንደሚሉት በአረብኛና በኢብራይስጥ ሳይሆን በጥንታዊው የሰው ልጆች አባት ቋንቋ በቅማንትኛ( ኬሜንት) ኩሽ የሚፈታ ነው። ይሄን እውነታ ስጽፍ ብዙ የውሸት ታሪክ ተስፈኞች የተለመደ የስድብና የፉከራ መርዛማ ምላሳቸውን መቀሰራቸው የተለመደ ነው። በእርግጥ እነሱ ስለተሳደቡና ስለሚዝቱ ፈርቼ እውነትን ከመናገር አልገታም። እውነት ያሸንፋልና ለኢትዮጵያ የኋላቀርነትና የድንቁርና መሠረት የሆነውን የታሪክ ድሪቶ ማፈራረስና እውነታን የማውጣት ኅሊናዊ ኃላፊነት ስላለብኝ በህይወት እስካለሁ ድረስ እውነታውን ከማውጣት የሚያግደኝ ፉከራም ሽለላም፡ መተትም ድግምትም አይኖርም። እውነት ከኮልኮሌያም ጠንቋዮችና ደብተራዎች በላይ ናትና አልፈራም። ~~~ በርእሰ ጉዳዩ ላይ ወደ አነሳሁት "ግሼ ዓባይ" ልመለስ። ዓባይ የሚለው ቃል በኋላ የተሰየመ ከግዕዙ "ዓበየ" ተለቀ ከሚለው ግስ ወጥቶ የተሰጠ ስያሜ እንደሆነ ደብተራው ጽፏል። በመሆኑም ዓባይ ትልቅ እንደማለት ነው። ትግርኛውም "ዓባይ ገረብ፡ ዓባይ ገለመሌ" ሲል ይሰማል። የዓባት ጥንታዊ ስሙ ግን "ጊዮን" ነው። ለዚህ ማስረጃ በታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 2 ቁጥር 13ን ተመልከትልቹ። እንዲህ ይላል። "ወስሙ ለካልእ ፈለገ ጊዮን ውእቱ ዘየዐውድ ኩሎ ምድረ ኢትዮጵያ" ይላል። ትርጉሙም "የሁለተኛው ስሙ የጊዮን ወንዝ ይባላል፡ እርሱም የኢትዮን ምድር የሚከበው ነው" ማለት ነው። ~~~ ለመሆኑ "ጊዮን" ማለት ምን ማለት ነው? "ጊዮን" ከ"ሌጊዮን" ጋር የሚያያዝ ትርጉም አለው። "ሌጊዮን" ማለት የአጋንንት መንጋ ማለት እንደሆነ ቅዱስ ወንጌላችን ይነግረናል። ነገር ግን በምን ቋንቋ መሆኑን አናውቅም። ያም ይሁን ይህ ግን "ሌግዮን ማለት በቅማንትኛ "መቶ አጋንንት" ማለት ነው። (ሊጝ + ጊዮን = መቶ + አጋንንት)። ይህ የሚያሳየን "ሌጊዮን" ማለት የ100 ጋኔኖች መንጋ በአንድ ብርጌድ ማለት መሆኑን ነው። ~~~ ይሄ "ሌጊዮን" የሚባለው ርኩር መንፈስ በጣናው ዘጌ ለብዙ ዘመናት ሰዎችን ነጭ በሬ እና ጥቁር ዶሮ እያሳረደ ሲመለክ የኖረ የዲያብሎስ መንፈስ ነው። ዛሬም ድረስ ጣና ሰው ሲበላ የአካባቢው ሰው የዋጠውን ሰው አስከሬን ከጣና የሚረከበው ጥቁር ዶሮ አርዶ ወደ ሐይቁ በመወርወር ነው። ይሄን በተመለከተ ከዚህ በፊት "ካና ሰጌ" በሚል ርእስ የፃፍኩትን ጽሑፍ ማንበብ ጥሩ ነው። የቀደሙ ቅማንቶች ለምን ይህን ወንዝ "ጊዮን" ወይም "አጋንንት አሉት?" ብለን ስናስብ ብዙ ታሪካዊና ስነልሳናዊ ምርምሮችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን መረዳት ግድ ይላል። እንዲያው ኅሊናየ የሚጠረጥረውን ለመናገር ያክል ግን ከላይ ካነሳሁት በአድ አምልኮት ጋር መያያዙን እምብዛም አልጠራጠርም። ዙሮ ዙሮ ግን ትርጉሙ ምንም ይሁን ምን "ጊዮን" አሁን "ዓባይ" ብለን የምንጠራው የአንድ ትልቅና ረዥም ወንዝ ሥያሜ ነው። ~~~ ዓባይ ከሚለው ወንዝ ላይ በመጨመር የምንጠቀምበው "ግሼ" የሚለው ስም አጎላማሽ ወይም አኮሳሽ ቅጽል ምን ማለት እንደሆነ ድግሞ ከዚህ ቀጥለን እንመልከት። "ግሼ" የሚለው ቃል ብዙዎቻችን ደጋግመን እንሰማዋለም። "ግሼ ዓባይ፡ ግሼን ደብረ ከርቤ፣ ወዘተ" እየተባለ ሲጠራ እንሰማለን። በነገራችን ላይ "ግሼን" ማለት የ"ግሼ" ብዙ ቁጥሩ መሆኑን ማሳሰብ እፈልጋለሁ። ~~~ በቅማንትኛ "ግሼ/ግሴ" ማለት "አጭር፡ ድንክ፡ በአካል ትንሽ የሆነ" ማለት ነው። ቅማንቶች "ድንክ ሰው" ሲያዩ "ግሴ ይር" ይሉታል። "ድንክ አልጋ" ለማለትም ደግሞ "ግሴ አርግ" ይላሉ። ቃሉ የስም ገላጭ ወይም ቅጽል ነው። ከስም ጋር እየገባ ስምን ይገልፃል። ለዚህም ነው "ግሼ ዓባይ" የሚባለው። የሆነን የዓባይ ክፍል ከሌላው የዓባይ ግፍል ለመለየት ይረዳ ዘንድ አባቶቻችን ዓባይ በሚለው ስም ላይ "ግሴ" የሚል ቅጽል ቀጽለውበታል። ~~~ "ግሴ ዓባይ" ወይም "ግሼ ዓባይ" የሚለውን ቃል በቃል ስንተረጉመው "ድንክ ዓባይ፡ ትንሹ አባይ፡ አጭሩ አባይ" ማለት ነው። ይሄ የዓባይ ስያሜ የሚያገለግለው ከዓባይ ምንጭ ከሰከላ (ሰቀላ) እስከ ጣና ዘጌ (ካና ሰጌ) ላለው የዓባይ ወንዝ ክፍል ብቻ ነው። ይሄን የዓባይ ክፍል የአካባቢው ሰው በተለምዶ "ግልገል ዓባይ" እያለ ይጠራዋል። ቢኮሎ (መሬት ሰብሮ) ዓባይ የምትባለው ትንሽዬ ከተማ ደርሳችሁ " ይህ ወንዝ ማን ይባላል?" ብላችሁ ማንኛውንም ሰው ብትጠይቁ ያለምንም ጥርጥር "ግልገል ዓባይ ይባላል!" ይሏችኋል። ይሄ ትክክለኛው የ"ግሴ/ሼ ዓባይ" ትርጉም ነው። "ግልገል ዓባይ" ማለትና "ትንሹ ዓባይ" ወይም "ድንኩ ዓባይ" ማለት አንድ ናቸው። ግልገል ከእናቱ ወይም ከአባቱ አንፃር ሲታይ ድንክ ወይም በጣም ትንሽ ነው። ስለዚህ ይሄ የአማርኛው "ግልገል ዓባይ" እና የቅማንትኛው "ግሴ ዓባይ" ምንም ዓይነት የትርጉም ልዩነት የላቸውም። እናም "ግሴ/ግሼ ዓባይ" የሚለው ስያሜ ለ"ግልገል ዓባይ" የተሰጠ ስያሜ መሆኑን ልብ ይሏል። ~~~ የ"ግሼ/ግሴ ዓባይ" ትክክለኛው ትርጉም ይሄ ሆኖ እያላ የታሪክ ላጲስ ደብተራዎች ያልሆነ ድሪቶ ታሪክ ፈጥረው ሲንደፋደፉና ሲያደነቁሩን ይስተዋላሉ። እነርሱ እንዲህ ይላሉ፡ "አንድ የበቁ መነኩሴ ዳዊታቸውን ሰከላ ለሚገኘው የዓባይ ምንጭ አደራ ሰጥተውት ወደ ሌላ አገር ሄዱ። ከብዙ ዓመታት በኋላ ወደ ሰከላ ተመልሰው የዓባይን ምንጭ 'በአደራ የሰጠሁሽን ዳዊቴን ግሺ'! ቢሏት ምንጯ ዳዊታቸውን አውጥታ ሰጠቻቸው። ከዚህም የተነሳ ቦታው 'ግሼ ዓባይ' ተባለ" ይሉናል። ሲጀመር ይሄ አባባል በብዙ መንገዶች ስህተት ነው። 4ቱን ስህተቶች አንስቼ ላብራራ። ~~~ አንደኛው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የበቃ መነኩሴ ዳዊት አንጠልትሎ አይሄድም። የበቃ መነኩሴ ማለት ሁሉም የተገለጠለት ሁሉን ጸሎቶች በልቡ የተጻፉለት ቅዱስ ሰው ማለት ነው። ስለዚህ የዚህ ትፈታሪክ ዋና የክርክር ነጥብ ተቀባይነት የሌለው የክርክር መነሻን የያዘ በመሆኑ ታሪኩ የተፈለሰፈ ኢ-አመክንዮአዊ ነው። ~~~ ሁለተኛው ምንጯ አማርኛውን አጣማ ነው የተረዳችው። ምክንያቱም መነኩሴው "ግሽልኝ!" እንጂ "ትፊልኝ ወይም አስመልሽልኝ ወይንም አቀርሽልኝ!" አላላትም። እሱ ያላት "ግሽልኝ!" ነው። "ማግሳት" ማለት የሆነ ምግብ በልተን ወይም መጠጥ ጠጥተን ስናበቃ ከምግቡ ወይም ከመጠጡ ጋር ወደ ጨጓራችን ውስጥ የገባው አየር ተመልሶ በአፋችን ሲወጣ የሚፈጠር የድምጽ ክስተት ነው። የበላነውን ካስታወክነው ወይም ካቀረሸነው ግን ወደ ጨጓራችን ያስገባነውን ምግብ ወይም መጠጥ መልሰን ባፋችን ማውጣታችን የሚያሳይ ነው። እናም መነኩሴው ማለት የነበረበት "ግሺ" ሳይሆን "አስታውኪልኝ!" ወይም "አቀርሽልኝ!" ነበር። እርሱ በተበላሸ አማርኛ "ዳዊቴን ግሺ" ሲላት ምንጯ ከዳዊቱ ጋር ወደ ሆዷ የገባውን አየር ብቻ ቡልቅ ማድረግ ነበረባት። ነገር ግን ምንጯም እንደ አለቆቿ ቀጣፊ ነች ማለት ነው። "ግሽልኝ!" ስትባል የምታስታውክ ወይም የምታቀረሽ "ሳይጠሯት አቤት ሳይልኳት ወዴት!" የምትል ቅላጥቤ የሆነች ምንጭ መሆኗ አያስገርማችሁም!? መነኩሴውም ቢሆኑ "የሰጠሁሽ ዳዊት መልሽ!" ብሎ በቀጥታ ከማዘዝ ይልቅ ለምን "ግሽልኝ፣ ፍሽልኝ!" ማለት አስፈለጋቸው? ይሄ ሁሉ ዝባዝንኬ የሚወራው የፈጠራ ድሪቶ ታሪክ እንጂ እውነት አለመሆኑን በዚህ እንረዳለን። ~~~ ሦስተኛው "ግሼ" የሚለው ስያሜ የሚገኘው በዚህ በሰከላው የዓባይ ምንጭ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላው የሃገሪቱ ክፍሎች ይገኛል። ለምሳሌ የግሼን ደብረ ከርቤ ማርያምን ስያመ መመልከት እንችላለን። በነገራችን ላይ ቀደም ሲል እንደጠቆምኩት "ግሴ/ግሼ" (ድንክ/በጣም አጭር) ብለን "ግሴን/ግሼን" ስንል "ድንኮች" ማለታችን መሆኑን አይተናል። ለማንኛውም ግን ደብተራው ለምን "ግሼን ደብረ ከርቤ" እንደተባለ የደረተው ታሪክ ይኑር አይኑር አላነበብኩም። ሳስበው ግን ሳይደርቱ አይቀሩም። ሳገኘው አጋራችኋለሁ። በዚህ በሁለተኛው ምክንያት አንፃርም ስናየው የግሼ ዓባይ ተረት ተረት ከድሪቶነት ታሪክ አያልፍም። ~~~ አራተኛው ደብተራው ይሄን የፈጠራ ድሪቶ ታሪክ ሲደርት ምንጯ ከመነኩሴውና ከእርሷ ግንኙነት በፊት ማን ተብላ ትጠራ እንደነበር የነገረም ምንም ፍንጭ የለም። ልክ "አፄፋሲለደስ አሁን ፋሲል ግንብ የተሠራበት ቦታ ሲደርስ የበቁ መነኮሳትን በዛው ሲፀልዩ አገኝቶ የሚሆነውን ነገሩት" ብለው እንደደሰኮሩት ድሪቶ ታሪክ ማለት ነው። ምክንያቱም አሁን ፋሲል ግን የተሰራበት ቦታ "ምዝገኒ" በመባል የሚታወቅ የቅማንት የህገልኑና የጸሎትና የመስዋእት ማቅረቢያ ድግና የነበረ እንጂ የክርስቲያን መነኮሳት መኖሪያ ገዳም አለነበረው። "የበቁ የቅማንት ባቲዋዎችን አግኝቶ እንዲህ አሉት" ላለማለት ዝም ብለው ወደ ራሳቸው መደረታቸው ልማድ ነውና እንዲህ ሲያደርጉ ኖሩ። የግሼውም ተረት ተረት "ግሴ/ግሼ" ቅማንትኛ ነው ላለማለት ያለፈውን እውነተኛ ስያሜ አይናገሩም። ዓላማቸውም የቀደመውን እውነተኛ ታሪክ ማጥፋት ስለሆነ ፈጠራቸውን እንጂ የቀደመውን አይነግሩንም። ለመንገርም ወኔና ሞራል የላቸውም። ~~~ ይሄ የግሼው ተረት ተረት እነዚህ ደብተራ ዘኮልኮሌና ዘዝባዝንኬዎች በምን ያክል ደረጃ የኢትዮጵያን ታሪክ ገድለው በትልቅ የድሪቶ ታሪካዊ ጉድጓድ እንደቀበሩት የሚያሳይ ጥሩ አብነት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ ሕዝቦችና ታሪኮቻቸው እንዲህ ተደርጎ በመቀበሩ ምክንያት በድንቁርና አዙሪት ውስጥ ወድቀን ተቸግረናል። ታሪካዊ፡ ባህላዊ፡ ማህበራዊ፡ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ሕይወታችን ሁሉ እንደተጎለጎለ ልቅ ዐይኑ ጠፍቶብን እንደራገማለን። በዚች ሃገር እርስ በርስ መገዳደል የተጀመረው በእነዚህ የታሪክ ድሪቶ ጎታቾች መፈጠር ምክንያት ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። እነዚህ ናቸው በህዝቦች መካከል ክፍፍልን የፈጠሩት። ያልሆኑትን ሰልሙነው ቅጥቅጥ ሰሎሞናዊያን ሆነው ሌላውን በግደል ጀመሩ። መድሃኒቱ አሁኑኑ ነቅተን ወደ ትክክለኛ ታሪካችን መመለስ ነው። ደብተራው በራሱብቁመቱና ወርዱ ልክ ሰፍቶ ያለበሰንን የታሪክ ድሪቶ አውልቀን መጣል ይኖርብናል። ከደብተራ ታሪክ ካልወጣን መፍትሔ የለውም። Website:-https://mikysultan.blogspot.com/ Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU Telegram:- t.me/Oromo_ geography

#አማራነትና ሰሎሞናዊነት ሲመዘኑ

አማራነትና ሰሎሞናዊነት ሲመዘኑ ~~~~~~~~~~~~~~~~~ አሁን ሀገራችን የተፈጠረው ምስቅልቅል ታሪካዊ ዳራው ከ13ኛው ክ/ዘ የሰሎሞናዊነት የፈጠራ አፈ-ታሪክና ተያይዞ ከተፈጠረው ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው። በወቅቱ ከአክሱም ዘመን ጀምሮ ክርስትናን ወደ ቤተ መንግሥት አስጠግቶ ያላመነውን ሕዝብ መረሸን፡ መመዝበር፡ ማፈናቀልና ልዩ ልዩ የስም ማጥፊያ ስሞችን መለጠፍ በጣም የተለመደ ነበር። በተለይም በኦሪትና ሕገልቡና ተከታይ ቅማንቶች ላይ የተፈጸመው ግፍ በቃል የሚገለፅ አለነበረም። በዚህ ግፍ የተመረሩት የኦሪት እምነት ተከታይ ቅማንቶች ዮዲት ጌዲዮንን አንግሠው የመልሶ ማጥቃት ርምጃ ወስደው አክሱም ላይ ተቀምጦ ሲበጠብጥ የነበረውን ሥርዎ መንግሥት ገርስሳውታል። በዚህም ምክንያት እስከ 13ኛው መቶ ክ/ዘመን ሠላማቸውን አግኝተው ሀገሪቱንም ሠላም አድርገዋታል። ዋና ጠባቸውም በክርስትና ሰበብ ሲገድላቸው ከነበረው ከአክሱሙ የቅማንት ገዢ መድብ ጋር እንጂ ከክርስትና ጋር እንዳልነበር ግልጽ ነው። ከክርስትና ጋር ጠብ ቢኖራቸው ኖሮ ከዛግዊ ሥርዎ መንግሥት ጋር ሲዋጉና ሲገዳደሉ እንደነበር እናይና እንሰማ ነበር። ~~~ የአክሱም ስርዎ መንግሥት ሲገረሰስ ቤተመንግሥቱን ከበው ሲደሰኩሩና ሲተነኩሉ የነበሩ መለካዊያን ካህናት ፈርጥጠው ወደ ሸዋ ቅማንት በመሔድ በጥገኝነት ተቀመጡ። በዚህ ቦታ በነበራቸው ረጅም ቆይታም የሸዋን ቅማንት በእነሱ እሳቤና አመለካከት ሥር እንዲሆንላቸው ትልቅ ሥራ ሰርተው ከጎናቸው አሰለፉት። ለረጅም ዘመናት ሥልጣንን እንዴት አድገው ወደ እጃቸው ማስገባት እንደሚችሉ መንገድ ሲፈልሁ ኖረዋል። በመጨረሻም የግብፅ ኮፕት ቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ቅኝ ገዢዎቻችን ጋር በመገናኘት አንድ ተንኮል ወጠኑ። በወቅቱ የዛግዌ ሥርዎ መንግሥት ነገሥታት "እኛ በራሳችን ጳጳስ ነው መመራትና መባረክ ያለብን፡ ከግብፅ ለሚመጡ ጳጳሳት ግብርና ሥጦታ አንከፍልም። ግብፆች ይሄን የማያደርጉ ከሆነ ደግሞ አባይን እንገድበዋለን" እያሉ ይከራከሩና ተግባራዊ ርምጃዎችን ይወስዱ ስለ ነበር፣ የግብፅ ሃይማኖታዊ ቅኝ ገዢ ደብተራዎች የዛግዌ ሥርዎ መንግሥትን ገልብጠው ለሌላ ተላላኪ ቡድን ማስረከብ ፈለጉ። በዚህ ጊዜ ከሸዋው ደብተራ ተክለሃይማኖት ጋር ይገናኛሉ። የዛግዌን ሥርዎ መንግሥት ገርስሰው መንግሥትን ወደ ሸዋው የደብተራ ቡድን በሚያሸጋግሩበት ሁናቴ ተወያይተው ተስማሙ። ~~~ የግብፅ ሃይማኖታዊ ቅኝ ገዢዎች ክብረ ነገሥት የሚባል የድራማና ተውኔት መፅሃፍ እንዲያዘጋጁ እነ ተክለሃይማኖትና ሞአ እየሱስ ይህን አፈታሪክ በሃይማኖት ስብከት አሥመስለው በህዝቡ ዘንድ ለማስረጽ ተስማሙ። የአፈ ታሪኩ ዋናው ጭብጥ "በኢትዮጵያ መንገሥ ያለበት ትክክለኛው ዘር የሸዋው ዘር ነው። ምንያቱም በፈጣሪ ከተቀባው ከእስራኤላዊው ንጉሥ ሰሎሞን ዘር የሚመዘዘው ይህ የሸዋው የንግሥት ማክዳ ልጅ የቀዳማዊ ምኒልክ ዘር ስለሆነ ነው። የዛግዌ ሥርዎ መንግሥት ከንግሥት ማክዳ ገረድ የተውለዱት አገዎች የመሠረቱት ስለሆነ እግዚአብሔር አልተቀበለውም።" የሚል ነበር። መጽሐፉን ግብፃዊያን በአረብኛ ጽፈው ለነተክለሃይማኖት ሰጧቸው እነ ተክለሃይማኖትም ወደ ግዕዝ አስመልሰው ይህን የፖለቲካ ድስኩር ሃይማኖት አስመስለው በመላው ሃገሪቱ ሰበኩት። እንዲያውም "ጋኔን መሀሮሙ ልሣኖሙ ለሰብአ አገው እስም ሰብአ አገው እኩያን እሙንቱ።" እያሉ አገዎችን ከዲቃላነት ፕሮፓጋንዳ በተጨማሪ "ጋኔኖች ናቸው፡ ቋንቋቸውም የጋኔን ነው" እያሉ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳና መርዝ ረጩ። ለምንድነው የአገው ቋንቋን ጋኔን አስተማረው ያሉት? ምክንያቱም በዛ ጊዜ አዲሱ የወታደሩና የወዲላው ቡድን ቋንቋ አማርኛ ገና ዳዴ እያለ የነበረ ስለሆነና ሕዝቡም ይህን የወዲላ ቋንቋ መናገር ስለማይፈልግ አሸማቀው አማርኛ እንዲናገር ለማድረግ ነው። ቋንቋውን ሲጥልላቸው በቀላሉ የአገውና ቅማንት ማንነቱን አስጥለው "ሰሎሞናዊ ነህ" ይሉታል ማለት ነው። ሕዝቡም ከጋኔንነት ወደ "ጋኔን አሳሪው" ሰሎሞንነት በቀላሉ ይመለሳል ማለት ነው። በዛ ጊዜ የወሎ ህዝብ ቅማንትኛና አገውኛ ተናጋሪ ሕዝብ ነበር። የሸዋው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ቅማንትኛ ተናጋሪ ነበር። የጎንደር ሕዝብ ቅማንትኛ ተናጋሪ ነበር። ጎጃም የዳሞት ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝብ ነበር። ዳሞትኛ ከአሁኑ የአዊኛ ቋንቋ ጋር ተመሳሳይ ነበር። እናም ለአዲሱ ሥርዎ መንግሥት ምሥረታ ያገለግላል ተብሎ የታሰበው ከዛግዌ ወታደሮች መካከል የተገኘው አማርኛ ቋንቋ ነበር። ይሄን በደንብ ለመረዳት የንቡረ እድ ኤርሚያስ ከበደን መጽሐፍ ማንበብ ይጠቅማል። ስለዚህ አማርኛ ለማስፋፋትና አገውኛና ቅማንትኛን በማጥፋት ሕዝቡን ሰሎሞናዊ ለማድረግ "አገው ጋኔን ነው፡ ቋንቋውም የጋኔን ነው" ማለት ነበረባቸው። ~~~ በዚህም ተክለሃይማኖትና ተከታዮቹ ውጤታማ ሆኑ። በ1262 ዓ ም ዋድላ ደላንታ ላይ ንጉሥ ይትባረክን ገድለው የሸዋውን ሰሎሞናዊ ይኩኖ አምላክን አነገሡ። ይሄን የበለጠ ለመገንዘን ገድለ ተክለሃይማኖትን አንብቡት። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሰሎሞናዊነትን በሃይማኖት ሰበብ በህዝቡ ላይ በግድ መጫን ጀመሩ። እምቢ ያለውን ዛሬ ላይ እንደሚያደርጉት በጭካኔና አረመኔነት ይገድሉታል፡ መንደሩና አገሩን በሙሉ ያቃጥሉታል። ፈርቶ እሺ ያለውን ቋንቋውን ያስጥሉታል። አስገድደው ያጠምቁትና "አማራ ሆንክ" ይሉታል። በነገራችን ላይ ያኔ አማራነት የጥሙቃን ሰለሞናዊነት ማንነት ነበር እንጅ ብሔር አልነበረም። የተጠመቀ ሁሉ "አማራ" ይባላ እንጂ የዘር አንድነት የለውም። ከመነሻውም አማራ የሚባል ዘር አልነበረም። አማራ ብሔር ሆኖ መታየት የጀመረው ከ1977ቱ የደርግ የቤትና ሕዝብ ቆጠራ በኋላ ነው። ይልቁንም አማራን ብሔር አድርጎ የራሱ ክልል እንዲኖረው ያደረገው ኢህአዴግ ነው። ሂደቱ ረጅም ጊዜ ቢወስድም አማራነት ብሔር የሆነው በሚገርም መንገድ ነው። ዛሬም ድረስ ኦሮሞዎች የተጠመቀውን ኦሮሞ "አማራ" ነው የሚሉት። እስኪ አስቡት ሙስሊም ብሔር ሲሆን! እንደዛ ነው የሆነው። አማራነትን ወይም ክርስቲያን መሆንን ብሔር እንዲሆን ያገዘው የአማርኛ መፈጠርና ከክርስትናው ጋር አብሮ መስፋፋቱ ነበር። ተጠምቆ አማራ ሲሆን አማርኛን እንዲናገር ግድ ሆነ። ~~~ በዚህ ክስተት ውስጥ የምንረዳው ነገር ሰሎሞናዊነትን በቤት ምልክናው፡ በቤተ መንግስቱና በቤተ ሕዝቡ ዘንድ ለማስረጽና ትክክለኛ አድርጎ ለማሳየት ዋናውን ሚና የተጫዎቹት ክርስትናና አማርኛ ናቸው። ሁለቱም የነባር ዝዝቦችን የቀደመ ትክክለኛ ማንነታቸውን ማስጣያ ናቸው። የአንድን ሕዝብ ማንነት ለመቀየር ባህሉን፡ ሃይማኖቱንና ቋንቋውን መቀየር መሠረታዊ ነው። እናም እነዚህን በሚገባ ተግባር ላይ በማዋል ብዙውን ነባር ሕዝብ ማንነቱን አስጥለው አማራ አደረጉት። ነባር ባህሉን አጥፍተው አዲስ የአማራነት ሰሎሞናዊነት ባህል ፈጠሩለት፡ የቀደመ ሃይማኖቱን አጥፍተው አማራ የሚባል ሃይማኖት ሰጡት፡ ቅማንትኛ፡ አገውኛና ዳሞትኛ ቋንቋውን አጥፍተው አማርኛን ሰጡት። ታዲያ እንዴት አይጠፋ? በትክክለም ቀስ በቀስ ሙልጭ ብሎ ጠፋ። ይሄን የሌሎችን ነባር ባህልና ቋንቋ እያጠፉ አማራ የማድረግ ሂደት በዋናነት የመንግሥትና የቤተክህነት ሰዎች በሚገባ መርተውታል። በየጊዜው ልዩ ልዩ የማፈኛ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ አስኪደውታል። ~~~ ሰሎሞናዊነትም በሉት ማስፈጸሚያዎቹ አማራነት (ክርስትና) እና አማርኛ በራሳቸው የዚህ ቡድን የመጨረሻ ዓላማዎች አይደሉም። እነዚህ ነገሮች ዋና ዓላማውን ለማሳካት የተጠቀሟቸው መንገዶች ናቸው። ዋና ዓላማቸው የሥልጣን የበላይነትን ተቆጣጥሮ ለዘለዓለም በህዝቦች ላይ ነግሦ መኖር ነው። ለዚህ ነው "ንጉሠ ነገሥት እከሌ ሥዩመ እግዚአብሔር ሞአ አንበሳ ዘእም ነገድ ይሁዳ" እያሉ ሲነግሩን የኖሩት። ለዚህ ነው "አማራ ከሌለ ኢትዮጵያ አትኖርም" የሚሉን። ክርስትናው የመንግሥትን ሥርዓት ለመጠበቅ ዋና አፈቃላጤና ወታደር ሆኖ ሲያገለግል ነው የኖረው። አማርኛውም እንዲሁ በዘፈኑ፡ በሽለላው፡ በፉከራ፡ ወዘተ የመንግሥት ወታደው ነው። ሰሎሞንነቱ ደግሞ "ንጉሡ ከዘሎሞን ዘር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በፈጣሪ ቅዱስ ቅባት የተቀባ ነው" ብለን እንድናምን የአእምሮ አጠባ ሥራ ከክርስትናው ጋር ተቀናጅቶ ሰርቷል። ~~~ በዚህ ሂደት የዚህ ቡድን ታሪክ ፀሐፊዎችም ይሄን የተወላገደውን ጠፍቶ የማጥፋት የሰሎሞንነት ታሪክ እውነት ለማስመሰል ያልፃፉልን ኮተት የለም። "ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ" እያሉ ሲተርቱልን ኖሩ። አንድም ቀን ደፍረው ስለ ጥንቱ ትክክለኛ ታሪክ ጽፈውልን አያውቁም። ይልቁንም የቀድሞው እውነተኛ ታሪክ እንዳይወጣ የማዳፈን ሥራ ሲሰሩ ነው የኖሩት። ~~~ ከፍ ሲል እንደገለጽኩት እነዚህ የሥልጣን ጥመኞችና ሥልጣን አመለኮች የኖሩት ለክርስትናው ሳይሆን ለሥልጣናችው ብቻ ነው። ክርስትናን ከአፍ በዘለለ ኑረውበት አያውቁም። ስለቅድስናቸውና ንጹህነታቸው ሲያወሩን እንሰማቸዋለን እንጂ በተግባር የሚታይ ቅድስና የላቸውም። ምክንያቱ ክርስትናን የኖሩት ለምድራዊ ንጉሣዊ ሥልጣን ማስጠበቂያ እንጂ ለሠማያዊው መንግሥት መግቢያ አልነበረም እና ነው። ክርስትና ሥልጣንህን የምታስጠብቅበት አንዱ መንገድ (means) እንጂ መድረሻ (goal) አልነበረም። ሰሎሞንነት ወይም አማራነትም እንዲሁ ነው። አማራነት በራሱ መድረሻ አልነበረም። ሥልጣንን በህዝቦች ላይ ጭነህ በንጉሥነት ዙፋን ላይ ተፈናጠህ ለዘለዓለም ለመኖር የተጠቀሙበት አንዱ መንገድ ነበር። የዛሬውን "አማራን ለማዳን ነው" የሚሉትን ፕሮፓጋንዳ ተውት። አማራን ለማዳን ቅማንትን መግደል ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው። ይሄ የአሁኑ ድርጊታቸው የዓላማና የመንገድ መቀያየር (goal displacement) ነው። ድሮ አማራነት የፖለቲካና የሥልጣን የበላይነትን ለማስጠበቅ ይጠቅም ነበር። ዛሬ ደግሞ አማራነትን ለማስጠበቅ የፖለቲካ፡ የሚዲያና የሥልጣን የበላይነትን እንደ መሳሪያ ወይም መንገድ ይጠቀሙታል። ለዚህ ነው የዓላማ መቀየር ያልኩት። አሁን ላይ ግራ ገብቷቸዋል የምንለውም ለዚህ ነው። ~~~ እነዚህ ሰዎች ለክርስትናው ምንም ግድ አይሰጣቸውም። ጉዳያቸውም አይደለም። በመሠረቱ ራሳችውን ከሰቃልያነ ክርስቶስ አይሁዶች ዘር ጋር ሲያገናኙ አይሁድነታቸውን እንጂ ክርስቲያንነታችውን በፍጹም አያሳይም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ነው የሚለው "ወደ ወገኖቹ መጣ፣ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ሥልጣንን ሰጣቸው። እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከሥጋና ከደማዊ ግብር ወይም ከወንድና ከሴት ፈቃድ አልተወለዱም።" (ዮሐ 1፡ 11-13)። ይሄን የወንጌል ቃል በጭራሽ አያስቡትም። ምክንያቱም ክርስትና ዓላማቸው አይደለምና ነው። ክርስትና አይገዳቸውም የምለውም ለዚህ ነው። ክርስትና ለነሱ እንደ ማጭድ፡ አካፋ፡ መጥረቢያ፡ መኪና፡ ወዘተ መሳሪያ ነው። ሰው ለማምረት ማረሻ እንደሚጠቀመው ሁሉ እነዚህ ሰዎችም በስልጣን ለመኖር ክርስትናን መሳሪያ አድርገው ተጠቀሙበት እንጂ ክርስትናን አያውቁትም። ለዚህ እኮ ነው ንጉሦቻቸው 30 እና 40 ሚስቶችንና እቁባቶችን ሲያገቡ የኖሩት። አይሁዳዊ ናቸዋ። ኦሪታዊ ናቸዋ! እነርሱ ከአይሁዳዊያን ነገሥታቶች ከሥጋና ከደም ግብር ወይም ከወንድና ከሴት (ከሰሎሞንና ማክዳ) ፈቃድ ለመወለድ የፈለጉና እንደተወለዱ አድርገው የተቀበሉ ናቸው። እነርሱ "የአግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ክርስቶስ ስልጣን አልሰጣቸውም። የተወለዱት በመንፈስ ሳይሆን በሥጋ ነውና። በሥጋ ከአይሁድ መወለድ ለክርስቶስም አልጠቀመው። ራሳቸው ወገኖቹ የተባሉት በጭካኔ ሰቀሉት። እነዚህም አይሁድነትን በመንፈስ ተቀብለዋልና የአይሁድ ንጹሃንን የሚገድለው የነብሰ ገዳይነት መንፈስ ተዋርሰዋልና ይሄው በክርስትና ስም ይገድላሉ። ያርዳሉ። ይዘርፋሉ። ይዘፍናሉ። ይፎክራሉ። Website:-https://mikysultan.blogspot.com/ Youtube:-https://youtu.be/CdY1umekwpU Telegram:- t.me/Oromo_ geography

mootittii saba'a Queen of sheba

"Mootittii Saba'a""Queen sheba" ----------------------------------------------------------------- ★Miky Sultan Bar...